Get Mystery Box with random crypto!

የንፁሃን ሞት እና ግድያ ይብቃን በምዕራብ ወለጋ ከሁለት ሳምንታት በፊት የተፈፀመው እጅግ ዘግናኝ | Shemsu Jemal-Official 🇪🇹

የንፁሃን ሞት እና ግድያ ይብቃን

በምዕራብ ወለጋ ከሁለት ሳምንታት በፊት የተፈፀመው እጅግ ዘግናኝ የንፁሃን ጭፍጨፋ እና የሽብር ተግባር ልባችንን አቁስሎን ፍትህ ይገኝ ዘንድ ድምፃችንን እያሰማን ባለንበት ወቅት ዛሬም የወገኖቻችንን እልቂት ዳግም እየሰማን ነው::

በቄለም ወለጋ ዞን ሀዋ ገለን ወረዳ ፤ ለምለም ቀበሌ ዉስጥ መንደር 20 ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በድጋሚ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ ጭፍጨፋ ፈፅመዋል::

የክልሉ እና የፌደራሉ የፀጥታ ሃይሎች ንፁሃን በዚህ መልኩ በጅምላ እየተጨፈጨፉ የነዚህን ሽብር ፈፃሚ ሃይሎች መቆጣጠር አለመቻል እንደ ሀገር ትልቅ አደጋ ውስጥ እንዳለን ይሰማኛል::

ንፁሃንን ኢላማ አድርጎ ብሄር እና እምነትን እየተለየ የሚፈፀመው እልቂት ከጊዜያዊ ሀዘን መግለጫ በዘለለ በዘላቂነት መፍትሄ ሲሰጠው እያየን አይደለንም::

መንግስት በሀገሪቱ ላይ እያለ ሰው በሀገሩ በሰላም ወጥቶ ካልገባ፣ በሚኖርበት አካባቢ ደህንነት ካልተሰማው፣ በእምነቱ እና ብሄሩ እየተለየ የሚጨፈጨፍ ከሆነ በመንግስት ላይ የሚኖራቸው አመኔታ መሸርሸሩ እና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ማስገባቱ አይቀርም::

ህዝብ ከምንም ነገር በፊት ሰላም እና ደህንነቱን ይሻል:: በሃገሩ በሰላም መኖር ካልቻለ የሀገር ትርጉሙን ያጣል::

የኦሮሚያ ክልል እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት ከልክ በላይ አልፎ የንፁሃን ደም እንደ ጅረት እየፈሰሰ እያዩ ይህን ለማስቆም ከምንም ጉዳይ በፊት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል::

በክልሉ ያሉ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣የክልሉ ህዝብ በአጠቃላይ የሰው ልጆች የግፍ ግድያ የሚሰማው ሁሉ ከማንም በፊት በክልሉ የተንሰራፋውን የንፁሃን ጭፍጨፋ እና ግድያ እንዲቆም በቃ ብለው ከሌላው የሀገሪቱ ህዝብ ጋር በጋራ ሊንቀሳቀሱ ይገባል::

የንፁሃን ሞት እና ግድያ ይብቃን!
||
ይህ የቴሌግራም ቻነሌ ነው፤ በቀላሉ የምለቃቸው መረጃዎች እንዲደርሷችሁ ከፈለጋችሁ ተቀላቀሉት።
Join:

t.me/shemsu_jemal
https://twitter.com/shemsujemmal
Join ያድርጉ