2022-07-05 01:04:17
ለቅዱስ ዮሴፍ አዳማ ተማሪዎች በሙሉ
ለመላው የቅዱስ ዮሴፍ አዳማ ተማሪዎችም እና የተማሪ ወላጆች እንደሚታውቀው የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በስኬት መጠናቀቁ የሚታወቅ ነው
እናም በክረምቱ ወራት ስለሚደረጉ ክንዋኔዎች ከታች እንደሚከተለው በዝርዝር የምናስቀምጠው ይሆናል
በመጀመሪያም የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ የአመቱ የማጠቃለያ ካርድ በትምህርት ቤቱ ካላንደር ላይ እንደተጠቀሰው ሀምሌ 3 ነው የሚያሳየው ነገር ግን የቀን ቅያሬ በመደረግ ወደ ቅዳሜ ማለትም ወደ ሀምሌ 2 መጠጋቱን ለማሳወቅ እንወዳለን
በመቀጠልም የሚሆነው የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሲሆን ምዝገባውም የሚከናወነው ከKG-12ኛ ክፍል ከሰኞ ሀምሌ 4 - አርብ ሀምሌ 8 ድረስ የሚቆይም ይሆናል
የምዝገባው ቅድመ ሁኔታዎችም የሚሆኑት ለምዝገባ ከመምጣታቹ በፊት በብርሀን ባንክ በኩል የመመዝገቢያ ብር 630 እና መስከረም ወር የወር ክፍያን ጨምሮ በባንክ በማዝገባት የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ትምህርት ቤት ይዛቹ በመምጣት ምዝገባችሁን የምታከናውኑ ይሆናል
እንዲሁም ለክረምት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ ደግሞ በነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት በተገለፁበት ቀናት ብር 400 በመክፈል የክረምት ትምህርታችሁን ትምህርት ቤቱ በሚያስቀምጥላቹ ቀን መሰረት ትምህርታችሁን የምትጀምሩ ይሆናል
በተጨማሪም የወላጆች ቀን ሁላችሁም ብትገኙ መልካም ነው ትምህርት ቤት ስለ ቀጣይ የትምህርት ዘመን ክንውኖቾ ይፋ የሚያደርጋቸው በርካታ ነገሮች ስላሉ ወላጆች መገኘት ብትችሉ መልካም ነው
ስለ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ አዲስ መረጃ ሲኖር የምናደርሳቹ ይሆናል እስከዛ በትዕግስት ጠብቁ
መልካም ውጤት
[ት/ቤቱ]
#Share
@senjonews
2.1K views22:04