Get Mystery Box with random crypto!

SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት )

የቴሌግራም ቻናል አርማ sabbathschool — SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት ) S
የቴሌግራም ቻናል አርማ sabbathschool — SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት )
የሰርጥ አድራሻ: @sabbathschool
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.62K
የሰርጥ መግለጫ

@TekalignSorato
251913070430

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-23 00:00:10 ማክሰኞ
ነሐሴ 17
August 23

የምስጋና ህይወት

በመልካም ነገሮች ውስጥ እንኳ ሆነን ማመስገን ለእኛ የተለመደ አይደለም። ስለዚህ በክፉ (በአስቸጋሪ) ጊዜ ደግሞ እንዴት ይሆን? ሆኖም ግን እንድናደርግ የተጠራነው ይህንን ነው። ምስጋና፣ በተወሰነ ጊዜ ከምናደርገው ድርጊትነት አልፎ የኑሮ ዘይቤያችን እስኪሆን መለማመድ አለብን። ምስጋና የተለየ ድርጊት ሳይሆን አኗኗር ሊሆን ይገባል። መዝ 145ን ያንብቡ። ዳዊት እግዚአብሔርን ስለ ማመስገን የሰጣቸው ምክንቶች ምንድናቸው? የዚህ መዝሙር ቃላት የእርስዎ መሆን የሚችሉት እንዴት ነው?



ቻርለስ ሃደን ስፓርጅን የተባለው ታላቅ የእንግሊዝ ሰባኪ የምስጋና ልምምድ የሚል መጽሓፍ ጽፏል። ይህም የተመሰረተው በዚህ በመዝሙር ቁጥር 7 ላይ ይገኛል። በዚህ አጭር ጥቅስ ስፓርጅን፣ በህይወታችን ውስጥ ምስጋናን እንዴት ማሳደግ እንደምንችል ሐሳባችንን ወደሚመሩ ሶስት አስፈላጊ ነገሮች ይመራናል። 1. ምስጋና የሚለመደው ዙሪያችንን ማየት ስንችል ነው። የእግዚአብሔርን ታላቅነት ለማየት፣ ዙሪያችንን ካላየን እርሱን ለማመስገን ምንም ምክንያት አይኖረንም። በተፈጠረው ዓለም ወስጥ እንደ እግዚአብሔር ፍጥረት ውበት የመሳሰሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ለመስጠት የተገባ እንደሆነ የሚያሳዩ ምን ምን ነገሮችን ታገኛላችሁ? በመንፈሳዊውስ ዓለም ለምስጋና የሚሆኑ ምን ነገሮችን ታገኛላችሁ ለምሳሌ በአዲስ ክርስቲያን እያደገ የሚታይ እምነት የመሳሰሉትን? 2.ምስጋና የሚለመደው የተመለከትናቸውን ነገሮች ስናስታውስ ነው። በምስጋና አየር ውስጥ መቆየት ከፈለግን፣ ለማመስገን ምክንያት የሆነልንን ነገር ማስታወስ ግድ ይለናል። የእግዚአብሔር መልካምነት እና ታላቅነት ከአእምሮአችን እንዳይጠፋ የእርሱን ታላላቅ ነገሮች ማስታወስ የምንችልባቸው የትኞቹ መንገዶች ናቸው (አዲስ የማምለክ መንገዶችን በመከተል ወይም የእርሱን መልካምነት የሚያስተውሱንን ምልክቶችን በማድረግ)? 3. ምስጋና የሚለመደው ስለ እርሱ ስንናገር ነው። ምስጋና እና በአእምሮአችን ውስጥ የምናደርገው ነገር አይደለም። ይህ ማለት ፣ ከአፋችን የሚወጣ ሆኖ በዙሪያችን ላሉ ሌሎች ሰዎች የሚሰማ ነገር ማለት ነው። እግዚአብሔርን በቃላት ለማመስገን የሚሆን ምክንያት ምንድነው? የዚህ ምስጋና ተጽዕኖ ምን ይሆናል፣ እናስ በማን ላይ? በሶስት ነገሮች ላይ ለመስራት እስክርብቶና ትንሽ ወረቀት ውሰድ። በህይወትህ የምስጋና ልምድ ለማዳበር ምን ነገሮችን ማድረግ ትችላለህ?

@SabbathSchool @TekalignSorato
982 views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 00:01:58 ሰኞ
ነሐሴ 16
August 22

ከላይ ወደ ታች መጸለይ

በእንግሊዝኛ አንድ አባባል አለ፡ “በአንድ አራት ማዕዘን ውስጥ በቀለም መከበብ” እስቲ የአንድን ክፍል ግድግዳ ቀለም ስለ መቀባት ያስቡ ፣ ቅቡን የመጨረሻ ያደረጉት አንድ ኮርነር ቢሆንና ከዚያ መውጫው ብቸኛ መንገድ እርጥቡን ቀለም ረግጦ ብቻ ከሆነ ከዚያ ለመውጣት የግድ ቀለሙ እስኪደርቅ መጠበቅ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ እምነታችን በአንድ ማዕዘን በቀለም እንደተከበብን ያደርገናል። በግድግዳ ላይ እንዳለ እርጥብ ቀለም፣ እምነታችን አጣብቆ ይዞናል ወደሚለው ድምዳሜ እንደርሳለን። ሁኔታዎችን በመመልከት፣ እግዚአብሔርን፣ እምነትን፣ እና ያመንነው ሁሉንም ነገር መቃወም፣ ወይም እምነታችን የማይቻል የሚመስለውን ነገር ሁሉ ማሸነፍ እንደሚንችል እንድናምን ያደርገናል። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ወደ ማዕዘን አመጣቸው። ለአርባ አመታት በምድረበዳ ከተቅበዘበዙ በኋላ፣ እግዚአብሔር ህዝቡን ባዶ ወደሆነ ሰላማዊ የሳር መሬት አልመራቸውም። እግዚአብሄር የመራቸው በዙሪያው ካሉ ከተሞች ሁሉ እጅግ አብልጠው ወደተመሸጉ ከተሞች ነው። ስለዚህ በእያሪኮ ዙሪያ ለስድስት ቀናት በዝምታ መጓዝ ነበረባቸው። እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን እንዲጮሁና ጩኃታቸው ከመለከቱ ድምጽ ጋር ድልን እንደሚመጣ ነገራቸው። ኢያሱ 5፤13 – 6፡20 ድረስ ያንብቡ። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ለማስተማር የፈለገው ምንድነው?



ደምጽን ከፍ አድርጎ መጮህ ግምብ እስኪያፈርስ ድረስ መሬትን የማንቀጥቀጥ ኃይል የለውም። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ‹‹እንዲጮሁ›› ሲጠራቸው፣ ዳዊት በመዝሙር 66 ከጻፈው ጋር ተመሳሳይ ጩኃት ነው።‹‹በምድር ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፡ለስሙ ዘምሩ ለምስጋናውም ክብርን ሥጡ።›› (መዝ66፡ 1፣2) ይህ ጩኃት ምስጋና ነው! ለስድስት ቀናት እጅግ ግዙፍ የሆነውን አጥር እየተመለከቱ፤ ይህንን በራሳቸው ኃይል ማፍረስ እንደማይችሉ ድምዳሜ ላይ ደርሰው ይሆናል። ይህ ሀሳብ ዕብ 11፡30ን እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው? እግዚአብሔር በህይወታችን ውስጥ አንድን አዲስ ነገር በመስራት ጉዳይ ላይ በሚሆንበት ጊዜ ፣ ምናልባትም የማሸነፍ ኃይል በራሳችን ኃይልና ዘዴዎች መምጣት እንደማይችል ለማስረዳት ሲፈልግ ወደ ኢያርኮ ሊያመጣን ይችላል። የሚያስፈልገን እያንዳንዱ ነገር የሚመጣው ከእኛ ውጪ ከሆነ ኃይል ነው። ስለዚህ በፊታችን ያለው ነገር ምንም ይሁን ምን ፣ ምንም እንኳ በፍጹም የማይገፋ መስሎ ቢታየንም የእኛ ድርሻ የሚያስፈልግን ነገር ሁሉ ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔርን ማመስገን ብቻ ነው። ይህ ነው እምነት በተግባር የሚባለው!

@SabbathSchool @TekalignSorato
997 views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:45:19 እሁድ
ነሐሴ 15
August 21

የምስጋና መሰረተ ሀሳብ

ታላቁ የሩስያው ጸሐፊ ፌዶር ድስቶቭስክ በመጨረሻው ሰዓት በተናገረው አንድ አረፍተ ነገር ምክንያት ብቻ ሞት ተፈርዶበት ነበር። በዚህ ፋንታ ብዙ ዓመታትን በእስር ቤት እንዲቆይ ተገዷል። እስር ቤት ስለነበረው ቆይታ ልምድ ሲናገር እንዲህ በማለት ጽፏል፡- “ሰዎች ሁሉ ተቅበዝብዘው እግዚአብሔርን ትተው ቢሄዱና አንተ ብቻህን እንኳ ብትቀር ለእግዚአብሔር ስጦታህን ይዘህ በመምጣት በብቸኝነትህ ምስጋናህን አቅርብለት” በዚህ ትምህርት ጳውሎስ ትልቁን ተቃውሞና ስደት እንዴት ችሎ እንዳለፈ ተመልክተናል። አሁን ግን እርሱ በሮማውያን እስር ቤት ቁጭ ብሏል። ቢሆንም እርሱ ተስፋ አልቆረጠም፤ በዚህ ፋንታ የፊልጵስዩስን አማኞች ለማበረታታት በትጋት ይጽፋል! ፊሊ 4:4-7ን ያንብቡ። ጳውሎስ ራሱ በሮም እስር ቤት ውስጥ ተቀምጦ ሳለ ይህንን ዓይነት ደብዳቤ እንዴት ጻፈ? በዚህ ንባብ ፣ ‹‹የእግዚአብሔርን ሰላም›› ለማግኘት ቁልፎቹ ምንድናቸው?



ነገሮች በመልካም ሁኔታ ላይ ሳሉ መደሰት አንድ ነገር ነው። ጰውሎስ እኛን እያሳሰበን ያለው ሁልጊዜ እንድንደሰት ነው። ይህም እንግዳ አነጋገር ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ የጻፈውን በቀጥታ ከወሰድን ሁለት ጠንከር ያሉ ወሳኝ ትርጉሞችን ይሰጠናል። የመጀመሪያው፣ ሁልጊዜ መደሰት ካለብን፣ ነገሮቻችን ለደስታ ምንም ዓይነት ፍንጭ በማይሰጡ ጊዜም ቢሆን መደሰት አለብን ማለት ነው። ሁለተኛ፣ ሁልጊዜ መደሰት ካለብን፣ ውስጣችን ደስታ በማይሰማበት ጊዜም ቢሆን መደሰት አለብን ማለት ነው። ጳውሎስ ነገሮቻችን ተፈጥሮአዊ ሁኔታቸውን ባልጠበቁ ጊዜም ቢሆን እንድናመሰግን ጥሪ እያቀረበልን ነው። እንድናመሰግነውም ምክንያታዊ መስሎ ላይታየን ሁሉ ይችላል። በአጭሩ ስንመለከተው ስናመሰግን ምክንያታፈልገን ብቻ መሆን እንደሌለበት ነው። በሌላ አነጋገር ምስጋና የእምነት ተግባር ነው። እምነት በክስተቶች ላይ ሳይሆን መሰረት ማድረግ ያለበት ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር ባለው እውነት ላይ ነው በመሆኑም እምነት እኛ ጥሩ ስሜት ስለተሰማን ሳይሆን በርግጥ እግዚአብሔር ማን እደሆነ በመረዳትና እርሱ ለእኛ በገባው ቃል ላይ መሰረት ያደርጋል ማለት ነው። በሚያስገርም መልኩ በህይወታችን፣ ሀሳባችንን፣ ስሜታችንን፣ እና ሁኔታዎቻችንን ቅርጽ የሚያስይዝልን፣ ይህ እምነት ነው :፡ ጳውሎስ በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ እግዚአብሔር ሊያብራራልን የፈለገው እውነት ምንድነው ፣በእስር ቤት ሊያስደስተው (ሐሴት) እንዲያደርግ የረዳው እውነት? እስቲ ስለ እግዚአብሔር የሚያውቁትን እውነቶች በዝርዝር በአጭሩ ይጻፉ። ስለ እያንዳንዱ ነገር እግዚአብሔርን ያመስግኑ። ይህ ስለነገሮች ያሎትን ስሜት ልለውጥ የሚችለውና እይታዎን ሊያስተካክል የሚችለው እንዴት ነው?

@SabbathSchool @TekalignSorato
892 views19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:44:17 ከነሐሴ 14 -20
9ኛ ትምህርት
Aug 20 - Aug 26




የምስጋና ህይወት


ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ፊሊ 4:4-7, ኢያሱ 5:13–6:20 መዝ 145, ሐዋ 16:16-34, 2 ቆሮ 20:1-30.

የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ!” (ፊሊጵ 4:4) ።
ደ ስ ሲለን የምስጋና ጩኃት ለአምላካችን ማቅረብ ቀላል ነው። ነገር ግን ነገሮች መጥፎ ስሆኑብን፣እጅግ አስቸጋሪ በሚበሉ ነገሮች ውስጥ ስንገባ እና የፈተናው እሳት በሚያቃጥልበት ጊዜ ማመስገን ቀላል አይሆንም። ሆኖም ግን በዚህን የመከራችን ጊዜ፣ ከቀድሞው ይልቅ ልናመሰግን ይገባናል ምክንያቱም፣ በመከራ ውስጥ በእምነት የሚያቆመን ማመስገን ነውና። በእርግጥ፣ ማመስገን ጨለማ የሆኑብንን ነገሮች እንኳ ቢሆን በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን እና ሁኔታዎችን በመለወጥ ሳይሆን እኛን በመለወጥ እኛን የሚገዳደሩንን ነገሮች መቋቋም እንድንችል ያደርገናል። ምስጋና ማለት እምነት በተግባር ማለት ነው። ለእኛ ምናልባት የተለመደ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን ምስጋናን ከተለማመድነው የህይወታችን ክፍል ሊሆን ይችላል፣ እርሱም የመለወጥና የማሸነፍ ኃይል አለው። ሳምንቱን በአጭር እይታ: ምስጋና ምንድነው? ምስጋና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንደዚህ ኃይለኛ የሆነ መንፈሳዊ መሳሪያ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? ምስጋና እኛንና በዙሪያችን ያሉ ሁኔታዎችን ሊለውጥ የሚችለው እንዴት ነው? *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሐሴ 21 ሰንበት ያጥኑ።
@SabbathSchool @TekalignSorato
933 views19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 06:01:51 አርብ
ነሐሴ 13
August 19


ተጨማሪ ሀሳብ

በኤለን ዋይት ነብያትና ነገስታት በሚለው “በንግስት አስቴር ዘመን,” ገጽ 598–606። “መንፈስ ቅዱስን ለሚፈልጉት እንደሚሰጥ እግዚአብሔር አልተናገረምን? እና ይህ መንፈስ እውነት አይደለምን? ትክክለኛ መሪስ አይደለምን? አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔርን በአእምሮአቸው አስቀድሞ እንዳመኑት በማሰብ እንደ ተስፋ ቃሉ ለመያዝ ያፍራሉ። እነርሱ እግዚአብሔር እንዲያስተምረን ይጸልያሉ ሆኖም ግን ፣ ልመናውን የተሰጠንን የተስፋ ቃል የራስ በማድረግ ሥፍራ ለመስጠት እና ስለ እርሱ የተማርነውን ለማመን ይቸገራሉ። ወደ ሰማያዊ አባታችን ለመማር ፈቃደኛ በሆነ ራስን ዝቅ ባደረገ ፣ መንፈስ የምንመጣ እስከሆነ ድረስ፣ የእግዚአብሔር የራሱ የሆነውን የተስፋ ቃሉን መፈጸም ለምን እንጠራጠራለን? ለጥቂት ጊዜም ቢሆን በመጠራጠር ለምን ክብሩን እናጎድለዋለን። የእርሱን ፈቃድ ለማወቅ በፈለግህ ጊዜ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሰራ ከአንተ የሚጠበቀው በእርሱ ስትመራ፣ ስትከተለው እና ፈቃዱን ስታደርግ እንደምትባረክ ማመን ብቻ ነው። ምናልባትም የእርሱን ትምህርት በስህተት ከተረጎምነው ራሳችንን በስህተት እናምነዋለን ። ይህንን ራሱን የጸሎት ርዕስህ በማድረግ፣ መንፈስ ቅዱስ እንዲመራህና የቃሉን ትክክለኛ ትርጉም እንዲገልጽልህ፣ እቅዱንና በአንተ ላይ ያለውን የእርሱን አሰራር፣ እመነው እናም እስከ መጨረሻው እመነው።”—Ellen G. White, Manuscript Releases, vol. 6, p. 225. “እምነት የሚጠነክርው በሚቃረን ሀሳብና በጥርጥር ላይ ግጭት መፍጠር ስንጀምር ነው። በእነዚህ የፈተና ጊዜያት የምናገኘው ልምድ በጣም ትልቅ ዋጋ ካላቸው ጌጣጌጦች እጅግ የበለጠ ነው። ”—Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 3, p. 555.
የመወያያ ጥያቄዎች


1. እንደ ክፍል፣ ሳናይ ስለምናምናቸው ነገሮች፣ የምናያቸውን ነገሮች ሁሉ ደግሞ ከእይታችን በላይ ናቸው። ስለነዚህ ነገሮች ተወያዩባቸው። ‹‹የማይታየውን ማየት›› የሚለውን ለመረዳት ይህ እንዴት ያግዘናል? 2. በረቡዕ ቀን ትምህርት መጨረሻ ላይ ያለው ጥያቄ ላይ ተወያዩበት። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ራሳችንን የምናገኘው ምን ያህል ጊዜ ነው? እኛ የምንፈልገው ዓይነት እንኳ ባይሆን የእግዚአብሔር መንገድ ከሁሉ የተሸለ እንደሆነ ለመቀበል ምን እናድርግ? 3. “ከሚቃረኑ ሀሳቦችና ከጥርጥር ጋር በመታገል እምነት የሚጠነክር ከሆነ” እና ይህ ደግሞ ትልቅ ዋጋ ካላቸው ጌጣ ጌጦች ዋጋው እጅግ ወደ ከበረ ወደ አንድ‹‹ ትልቅ ዋጋ ወዳለው ነገር›› የሚመራን ከሆነ ይህን ግጭት የምንረዳበትን መንገድ ሊቀይርልን የሚችለው እንዴት ነው? 4. ብዙዎቻችን ክርስቲያን የሆኑ ሰዎች እንኳ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የገቡት ለመውጣት እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ አይተናል። በጸሎትና በጥረት ካልሆነ በስተቀር ነገሮች ከዚህ የከፉ እንደሚሆኑ እናውቃለን። ከተማርናቸው ነገሮች አንጻር እነዚህን ሁኔታዎች እንዴት እናያቸዋለን?

@SabbathSchool @TekalignSorato
1.3K views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 06:01:09 ሐሙስ
ነሐሴ 12
August 18

እግዚአብሔር ባይታይም ታማኝ መሆን

በእኛ ላይ እየደረሰ ስላለው ነገር ማንም ጥንቃቄ የማያደርግልን መሆኑን ማሰብ ደስ የማይል ስሜትን የሚፈጥር ነገር ነው። ነገር ግን እግዚአብሄር እንደማያውቅና እንደማይጠነቀቅ ማሰብ ደግሞ ከሁሉ የከፋ ነገር ነው። በባቢሎን ለነበሩ የይሁዳ ምርኮኞች፣ እግዚአብር ስለ እነርሱ ሁኔታ ግድ የሚለው አይመስልም። እነርሱ አሁንም ምርኮኞች አሁንም በኃጢአታቸው ምክንያት እግዚአብሔር የተዋቸው ይመስላቸዋል ። ነገር ግን ኢሳያስ ለእነርሱ የሚያጽናና ቃል ይናገራል። ኢሳ 40 አጅግ በጣም በተዋቡ ቃላት ኢሳያስ ስለ አምላካቸው የሚናገርበት ክፍል ነው። “መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።” (ኢሳ 40:11)። ነገር ግን ምርኮኞቹ ከረዥም ጊዜ በኃላም እግዚአብሔር አንተ የት ነህ አንተ ስለመኖርህ ወይም ለእኛ የምትጠነቀቅ ስለመሆንህ ምንም አላየንም ይሉ ነበር። ኢሳ 40:27-31ን ያንብቡ። ኢሳያስ እግዚአብሔርን የሚገልጸው እንዴት ነው? ይህ ለእግዚአብሔር የተሰጠው መግለጫ ‹‹ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ለሚሉ መልስ ሊሰጥ የሚችለው እንዴት ነው” (ኢሳ 40:27)?



ሌሎች መንገዳቸው ከእግዚአብሔር የተደበቀ እንደሆነ የሚያስቡ ሰዎች ቡድን የሚገኘው በአስቴር መጽሐፍ ውስጥ ነው። በዚህ መጸሐፍ የእግዚአብሔር ስም አንድም ጊዜ አልተጠቀሰም። ሆኖም ግን ታሪኩ በሞላ እግዚአብሔር ህዝቡን ለማጥፋት የታቀደውን አዋጅ ለመቀልበስና ህዝቡን ለማዳን በሚያደርገው ድራማ የተሞላ ነው። ይህ ታሪክ ባለፈው ዘመን የተደረጉ ነገሮችን የሚገልጽ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ፊት የእግዚአብሔር ህዝቦች እንደገና ሲሰደዱ እነርሱን ለማጥፋት የሚወጣውን አዋጅ ጭምር የሚያሳይ ነው። (ራዕ 13:15)። ታያለችሁ እንደዚህ የሚከብዱ ዓይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን እውነትም እግዚአብሔር ህዝቦቹን ትቷቸዋል ብሎ ለማጠቃለል እንዴት ቀላል እንደሚሆን? ነገር ግን መፍራት የለብንም ። በአስቴር ታሪክ ውስጥ ህዝቦቹን ያዳነው ያው አምላክ በመጨረሻው ፈተናና ችግር ጊዜ ህዝቦቹን ያድናቸዋል። ኢሳያስ እግዚአብሔርን ለምርኮኞቹ የገለጸው እንዴት እንደሆን ተመልክተናል። እርሰዎ እግዚአብሔር እንደተዋቸውና እንደረሳቸው ለሚሰማቸው ሰዎች የሚገልጡት እንዴት ነው? በዙሪያቸው በሚታዩ ነገሮች ብቻ ሳይደገፉ መንፈሳዊ አይኖቻቸውን በመክፈት ተስፋ እንዲደርጉ ሊያስተምሯቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

@SabbathSchool @TekalignSorato
1.2K views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 06:00:44 ረቡዕ
ነሐሴ 11
August 17

ጭንቀታችንን ሁሉ ለመሸከም

አንዳንድ ሰዎች በቤታቸው ውስጥ በእንጨት ወይም በብረት ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ ተሰቅሎ ይታያል።‹‹ መጨነቅ እየተቻለ ለምን ይጸለያል? ›› ይህ አስቂኝ ነገር ነው፣ ምክንያቱም ነገሮቻችንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ስንችል ምን ያህል ጊዜ እንደምንጨነቅ እናውቃለን። አንድ ጊዜ አንድ ሰው እንዲህ አለ፣ ህይወትህ ሙሉ በሙሉ አስጨናቂ ሲሆንብህ ፣ ለእግዚአብሔር ስጠውና እርሱ ነገሮቹን ይፍታ ብሏል። እግዚአብሔር ለእኛ እንደዚህ ለማድረግ ምን ያህል ይጓጓል! ሆኖም በሚደንቅ ሁኔታ፣ እኛ ነገሮች እስኪያስቆሙን ድረስ በችግሮቻችን ላይ እናተኩራለን። ወደ ጌታ ከመሄዳችን በፊት ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ የምንቆየው ለምንድነው? 1 ጴጥ 5:7ን ያንብቡ። ጴጥሮስ እየጠቀሰ ያለው ከመዝ 55:22 ለይ ነው። በዚህ ስፍራ ለእኛ የሚሆን መሰረታዊ መልዕክት ምንድነው? ማቴ6:25-33ን ጨምረው ይመልከቱ።



1 ጴጥ 5:7 በጣም ግልጽ የሆነ ጥቅስ ነው። የተደበቀ ምስጢር የለበትም፣ ማለት የፈለገውም በቀጥታ የተጻፈውን ራሱን ነው። መጣል ማለት ያንኑ ማለት ነው፣ መወርወር፣ ወዲያ ማድረግ፣ ከዚያም ህመምን የሚያስከትለውን እና የትኩረት ነጥብ የሆነውን ነገር ከአንተ ጋር ምንም ግኑኝነት እንደሌለው ማሰብ ማለት ነው። ነገር ግን ሸክሞቻችን የትም አልተጣሉም አልተወረወሩም። ጭንቀታችን ዝምብሎ ቦታ ላይ አልተጣለም። ሊያስተካክለው ቃል ለገባው ሰማያዊ አባታችን ተሰጥቷል። በማትዎስ ወንጌል ክርስቶስ እየነገረን ያለው ይህንን ነው። ይህንን በማድረግ የተፈጠረው ችግር በጣም ትልቅ አይደለም፤ ግን በጣም ቀላል መስሎ መታየት፣ ከዚያም እንደጥሩ ነገር መታየት ይጀምራል። ጭንቀት በተለያዩ ነገሮች ምክንያት ይፈጠራል። የሥራ ጫና ሊሆን ይችላል፣ ሳይጠበቁ የሚፈጠሩ ነገሮች፣ የሚወደን ሰው ባለመኖሩ የማንፈለግ መስሎ ሲታየን፣ የጤና ወይም የገንዘብ እጥረት ፣ ለእግዚአብሔር ያልተገባን መስሎ መታየት፣ ይቅር ያልተባልን እንደሆንን ማመን። ችግሩ ምንም ይሁን ምን፣ ሁላችንም የምንስማማው አንድ ነገር አለ፣ እርሱም ከማንም በተሻለ ሁኔታ ችግሮቻችንን በራሳችን እናስተካክላለን ብለን ማሳባችን ነው። ነገር ግን ጴጥሮስ ይህን አስተሳሰባችንን እንደገና እንድናጤነው ይነግረናል። የማንጨነቅበት ብቸኛ ምክንያት እግዚአብሔር ይጠነቀቅልናል። ነገር ግን እግዚአብሔር ፍቺ በዙሪያችን እያንዣበበ፣ወይም እኛ ምንም የማንጠቅም መሆናችን እየተሰማንም ጥንቃቄ እያደረገልን ነው ማለት ነው? መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እርሱ ሁልጊዜ ነገሮቻችንን ለመለወጥ ይሰራል። አሁን እንድትጨነቅ የሚያደርግህ ነገር ምንድነው? ምንም ህጋዊ ነገሮች ቢሆኑ፣ ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆኑም፣ ለእግዚአብሔር የሚሳነው አለን? ምናልባትም የእኛ ትልቁ ችግር እግዚአብሄር ነገሮቹን የሚያውቃቸው እና ሊያስተካክላቸው የሚችል ቢሆንም እኛ እንዲፈታልን በምንፈልገው መልኩ ይፈታልናል ብለን አናምንም። በመጨረሻው ነጥብ ላይ ተወያዩበትና ይህ ነገር በህይወትዎ ምን ያህል እውነት እንደሆነ ራስዎን ይጠይቁ።

@SabbathSchool @TekalignSorato
1.1K views03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 06:01:25 ማክሰኞ
ነሐሴ 10
August 16

የትንሳኤው ኃይል

ትንሳኤው የሚያመለክተው የሰዎችን የአቅመ-ቢስነት ችግር ነው። ስለ ክርስቶስ ህይወት፤ ሞትና ትንሳኤው ስናስብ፣ እኛን በህጋዊነት ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ያደረገን ክስተት መሆኑን እናስተውላለን። ይህም ደግሞ እውነት ነው። ነገር ግን፣ ትንሳኤው ሌላ የተለየ የማዳንን ተጨማሪ ጎን ያሳየናል። የክርስቶስ ትንሳኤ የሚያሳየን እርሱ ከሞት እንደተነሳ አንድ ቀን እኛም ከሞት የምንነሳ መሆናችንን ብቻ አይደለም። ትንሳኤ ክርስቶስን ስልጣንና ኃይል ባለበት በአባቱ ቀኝ ከፍ አድርጎ አስቀመጠው። የትንሳኤው ኃይል እግዚአብሔር ዛሬም ለእኛ የሚያዘጋጀው ተመሳሳይ ኃይል ነው! በኤፌ 1:18-23 ጳውሎስ ስለ እግዚአብሄር ኃይል ይናገራል። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ትንሳኤው ኃይል ምን ያስተምሩናል? ለራስዎ የሚሆን ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ተስፋና ቃል ኪዳን ያገኛሉ?



በዚህ ስፍራ ጳውሎስ የኤፌሶን ሰዎች በመለኮታዊ መረዳት ብቻ በትክክል የሚስተዋሉ ጥቂት ነገሮችን እንዲያስተውሉ እየጸለየላቸው ነው። (1ኛ) የሱስ ክርስቶስ የጠራን ለውጥና የዘላላም ህይወት ተስፋ ያለን ስለመሆኑና፣ (2ኛ) በእኛ ፈንታ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ኃይል የምናስተውል ስለመሆናችን ይሆናል። ከዚያም ጳውሎስ ይህ ኃይል ምን ዓይነት አስደናቂ መሆኑን ወደ መግለጽ ይመጣል። ዛሬ ለእኛ የተዘጋጀው ኃይል ክርስቶስን ከመቃብር ያነሳውና ወደ ህይወት የመለሰው ብቻ ሳይሆን፣ ኃይል በሚገኝበት በአባቱ ቀኝ ያስቀመጠውም ጭምር ነው። ነገር ግን ጳውሎስ በዚህ አያቆምም። ትንሳኤው ለክርስቶስ ዝም ብሎ የሆነ ዓይነት ኃይል አይደለም የሰጠው፣ ነገር ግን፣ ለመግዛትና ለህዝቦቹ በዘላላም ዘመናት አስፈላጊ የሆነ ነገርን ሁሉ ለማቅረብ የሚያስችለው ኃይል እንደሆነ ይነግረናል።! በህይዎትዎ የክርስቶስ የትንሳኤው ኃይል የሚያስፈልገውን አከባቢ ይለዩ። ሲጨርሱ ፣ ይህ ኃይል በአስፈላጊ ስፍራዎች ሁሉ እንዲሰራ ይጸልዩ። ተመሳሳይ ጊዜ ፣ ይህ ኃይል በተሻለ ሁኔታ በህይወትዎ በነጻነት እንዲሰራ ለማድረግ ምን የተለየ ነገር ማድረግ ይችላሉ?

@SabbathSchool @TekalignSorato
1.1K views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 06:00:36 ሰኞ
ነሐሴ 9
August 15

በኢየሱስ ስም

“ምንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ” (ዮሐ 14:14):: ከዚህ በኃላ ክርስቶስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ብዙ አይቆይም። ድጋፋቸውና መጽናናታቸው የሆነው ወደ ሰማይ ሊሄድ ነው፣ እናም ደቀመዛሙርት ግራ ሊጋቡና አቅመ-ቢስ መሆን ሊጀምሩ ነው። ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ በአካል ማየት ባይችሉም፣ ክርስቶስ የማይረሳ በጣም አስፈላጊ የሆነ ተስፋ ሰጥቷቸዋል። ዮሐ 14፡1-14 ያለውን ያንብቡ። እንደ ቁጥር 13 እና 14፣ ኢየሱስ በስሙ የምንለምነውን ‹‹ማንኛውንም›› ነገር ሊያደርግልን ቃል ገብቶልናል። ከዚህ የተነሳ፣ሁልጊዜ በጻሎታችን መካከል ‹‹ በኢየሱስ ስም አሜን ›› የሚለውን እንጨምራለን። ይህንን በምንልበት ጊዜ፣ ምን ማለት እንደሆነ ነው የምናስበው? እንዲህ ብለን እንድንጸልይ ሲያበረታታን ክርስቶስ ምን እያለን ነው? እርሱ ሊነግረን የፈለገውን ነጥብ ለማስተዋል እነዚህ ጥቅሶች ፍንጭ የሚሰጡን እንዴት ነው?



ጥያቄያችን ‹‹በክርስቶስ ስም›› በሚሆንበት ጊዜ፣ ሰማያዊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ስለ እኛ መስራት እንደሚጀምሩ እርግጠኞች እንሆናለን። መላዕክት በዙሪያችን እየሰሩ ሲንቀሳቀሱ ላናይ እንችላለን።ነገር ግን እነርሱ በኢየሱስ ስም ከሰማያዊ ዙፋን የእኛን ጥያቄ ለማሟላት ይላካሉ። አንዳንድ ጊዜ በክርስቶስ ስም ስንለምን፣አይናችንን ገልጠን እያያን ያኔውኑ ነገሮች ተለውጠው ለማየት እንፈልጋለን ፣ሆኖም ነገሮች እንደነበሩ ይሆናሉ። ነገር ግን፣ ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ እንዲል በተናገረው ጊዜ እንደነበረ ቅጽበታዊ ምላሽ ቢመጣ ወይም፣ ክርስቶስን በጌተሴመኔ በኃይል እንዳጸናው ዓይነት በዝምታና ማንም ሳያውቀው ሊመጣ ይችላል። አንድ ቅጽበታዊ ነገር በድንገት ላይፈጸም ይችላል፣ ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር ለእኛ ምንም እየሰራ አይደለም ለማለት አይቻልም። በድጋሚ ዮሐ 14፡1-14 ያለውን ያንብቡ። እያነበቡ ሳለ ክርስቶስ ፊት ለፊት እየተናገረዎት እንዳለ ያስቡ፣ ከእነዚህ ተስፋዎች ምን ዓይነት መጽናናትና ተስፋ ያገኛሉ? በተመሳሳይ ጊዜ፣ ራስዎን እንዲህ ብለው ይጠይቁ፣ እነዚህ ተስፋዎች በህይወቴ እንዳይፈጸሙ የሚያደርጉ ምን ነገሮች አሉ? በልቤ ምን ዓይነት ለውጥ ለማድረግ ወስኛለሁ?

@SabbathSchool @TekalignSorato
1.2K views03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 06:00:34 እሁድ
ነሐሴ 8
August 14

የአባታችን አባካኝነት

“በትክክል እግዚአብሔር የሚወደን ቢሆን ኖሮ ለእኔ ይህንና ያንን ያደርግልኝ ነበር!” ይህ ዓይነት አስተሳሰብ ምን ያህል ጊዜ ይመላለስ እንደነበር ባውቅ ደስ ይለኛል። ያለንበትን ሁኔታዎች እናይና በእርግጥ እግዚአብሔር እኛን ይወደናል፣ ቢወደን ኖሮ ነገሮች እንዲህ ባልሆኑ ነበር እንላለን። የእግዚአብሔርን መልካምነት እንድንጠራጠር የሚያመሩ ሁለት ማሳመኛ የሚመስሉ ነገሮች አሉ። የመጀመሪያው፣ በአእምሮአችንና በልባችን ጥሩ ነው ብለን ላመንነው ነገር በልባችን ውስጥ የሚቃጠል ፍላጎት ሲኖር፣ እግዚአብሔር ለእኛ የሚፈልገው አንድ የተለየ ነገር ለእኛ አስቸጋሪ ይመስለናል። ሁለተኛ፣ የእኛ ህይወት ተሞክሮና የምናምነው ነገር ስለሚጋጭብን የእግዚአብሔርን መልካምነት እንጠራጠራለን። አንድ ነገር ጥሩ መስሎ ከታየ፣ጥሩ ስሜት ከፈጠረ፣ ጥሩ ጣዕም ካለው፣ አንድ ነገር ጥሩ ነው እንላለን። ስለዚህ ይህ መልም የመሰለንን ነገር ካላገኘን በእግዚአብሔር ላይ እንቆጣለን። በዚህ ሁኔታ ላይ ነው አሁን እምነት ወደ ተግባር የሚመጣው። እምነት በተግባር የሚገለጸው የእግዚአብሔርን መልካምነት ለማጠናከር ልንፈተን በምንጀምርበት ጊዜ ነው። ሮሜ 8:28-39 ላይ ያለው ጥቅስ እግዚአብሔር ለእኛ ስላለው መልካምነት የሚናገር ኃይለኛ ጥቅስ ነው። በጥቅሶቹ ውስጥ ከጥርጥር አእምሮን ሊጠብቅ የሚችል ምን ነገር እናገኛለን



በሮሜ 8:32 ላይ ባጋጠሙን ነገሮች ላይ ተውጠን እንዳንቀር የሚጠቅመን በጣም አስፈላጊ የሆነ ለማሳመን የሚያስችል ሐሳብ እናገኛለን። “እግዚአብሔር ራሱን በሚያዋርድ እጅግ በከፋ ሁኔታ ዝቅ በማለት ልጁን ወደ ምድር በመላክ ሁሉንም ነገር ለእኛ በሚሆን መንገድ ካበጀው ፣ እርሱ ለእኛ ሲል በደስታ እና በነጻ ሊያደርግልን የማይችለው ነገር ይኖራልን?” እግዚአብሔር ልጁን ለእኛ እንዲሞት ወደ ምድር እንደ ላከው ካሰብን በኃላ ተመልሰን እንደ ተራ እና ዋጋ እንደሌለው ነገር ማየት የምንችለው እንዴት ነው? ይህ ማለት እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ርህራሄ እውነታው፣ በክርስቶስ ሞት ከታየ፣ ከጥርጥሮቻችን ሁሉ በላቀ ሁኔታ ፈተና በአስተሳሰባችን እና በውስጣችን ትልቅ ተጽዕኖ ሊያሳድርብን ይገባል። የእግዚአብሔር መልካምነት ከጥርጥራችን በላይ ተጽዕኖ ሊያደርግብን የሚችለው እንዴት ነው በሚለው የተወሰነ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን በእርስዎ ፈንታ እንዲሞት ስለመስጠቱ እና ይህ ከግምት በላይ የሆነው ርህራሄው በተለያዩ ሺህ መንገዶች ዛሬም እንደሚቀጥል ተወያዩ። ይህ ስለ እምነት ምን ይናገራል?

@SabbathSchool @TekalignSorato
1.3K views03:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ