Get Mystery Box with random crypto!

SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት )

የቴሌግራም ቻናል አርማ sabbathschool — SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት ) S
የቴሌግራም ቻናል አርማ sabbathschool — SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት )
የሰርጥ አድራሻ: @sabbathschool
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.62K
የሰርጥ መግለጫ

@TekalignSorato
251913070430

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 00:01:48 አርብ
ነሐሴ 27
September 2


ተጨማሪ ሀሳብ

Read Ellen G. White, “The Importance of Seek- ing True Knowledge,” pp. 453, 454, in The Ministry of Healing; “The Sermon on the Mount,” pp. 298-314, in The Desire of Ages; “The Worker and His Qualifications, p. 630, in Evangelism. “ልንጋፈጣቸው የተገቡን አስቸጋሪ ነገሮች በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ በሚሸሸግ ትህትና በጣም ሊቀሉን ይችላሉ። የመሪያችንን ትህትና ብንላበስ፣ በየዕለቱ በፊታችን ከተደቀኑብን ከሚረብሹን፣ ነገሮች ከፍ እንላለን በእርሱም በመንፈሳችን ላይ የሚያንዣብበው ዳመና ይጠፋል። የክርስትያን ህይወት ትልቁ የትክክለኛ ጽኑ ባህሪይ መገለጫ የሚሆነው ራስን መቆጣጠር ነው። ጭካኔ እና አግባብነት የጎደለው ነገር ሲደረግበት፣ የሚታመን እና የተረጋጋ መንፈስ የማያሳይ ሰው እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የባህሪ ፍጽምና እንዳይሰራ የእግዚአብሔርን መብት እየነጠቀ ነው። ለክርስቶስ ተከታዮች ድልን የሚሰጠው ጥንካሬ የልብ ፈቃደኝነት ነው። ይህም ከሰማይ ጋር ላላቸው ግንኙነት ምልክት ሆኖ ይቀመጣል።
የመወያያ ጥያቄዎች


1.ራስን ማዋረድ ከሚረብሹንና ከሚጎዱን ነገሮች እኛን ከፍ ሊያደርገን የሚችለው እንዴት ነው? ይህንን እንድናደርግ የሚረዳን ራስን የማዋረድ ባህሪ ነውን? 2. በትዕግስት መጠበቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በክፈል ወስጥ ያሉትን ሰዎች ይጠይቁ። ፍርሃቶቻቸው፣ የሚያስደስታቸውስ ምን ነበር ? እንዴት አለፉት? ምን ተማሩበት? በየትኛው ተስፋ ላይ ነበር የበለጠ የተደገፉት? 3. እንደ ቤተክርስቲያንና ወይም እንደ ክፍል በፈተና ውስጥ ሆነው የእግዚአብሄርን ጊዜ የሚጠብቁትን ለመርዳት ምን ያደርጋሉ? 4. በትዕግስት መጠበቅን ለመለማመድ ጸሎት ምን ያህል ይጠቅማል? መንፈስ ቅዱስ ትዕግስትን እንዲያለማምዳቸው የሚፈልጉ ሌሎች አሉ?

@SabbathSchool @TekalignSorato
210 views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 00:00:14 ሐሙስ
ነሐሴ 26
September 1

መጠጊያችንና ዓለታችን

በጣም ኩሩ የሆኑ ሰዎች ብዙውን ጊዜ፣ በራስ መተማመን ከሌላቸው ይልቅ ቁጡና ነገሮችን በደፈናው የሚጋፉ ናቸው። የእነርሱ ማን አለብኝነትና ኩራት፣ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ትህትናን ማጣት፣ ወይም ለሽፋን ያህል የሚታየው ዝቅ ዝቅ ማለት፤ ምናልባትም ሳያውቁት የሚሆን፣ ከውስጥ የሌለ ነው። እነርሱ የሚፈልጓቸው ነገሮች ለምሳሌ እንደ ከለላ የማግኘት፣ ከአደጋ ነጻ መሆን፣ ጠቃሚ ሆኖ መገኘት፣ ተቀባይነት ማግኘት የመሳሳሉት በቀጥታ እኛ የምንፈልጋቸው ነገሮች ናቸው። ይህን ደግሞ ማግኘት የምንችለው በክርስቶስ ብቻ ነው። በአጭሩ ትህትናና ራስን ዝቅ ዝቅ ማድረግ የደካማነት መገለጫዎች ሳይሆኑ ይልቁንም መሰረቷ በድንጋይ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እና ኃይለኛ የሆነች ብርቱ ነፍስ መገለጫ ናቸው። መዝ 62:1-8ን ያንብቡ። የዚህ መዝሙር አውድ ምን ይመስላል? ደዊት ምን እያለ ነው? እርሱ ከሚናገረው ምን መንፈሳዊ መርህ ማግኘት እንችላለን? ከሁሉም በላይ፣ እነዚህን መመርያዎች በህይወትዎ ለመተግበር የሚችሉት እንዴት ነው?



“ያለ ምንም ምክንያት ሰዎች ጠላቶቻችን ይሆናሉ። የእግዚአብሔር ህዝቦች አንድን ነገር የሚያደርጉበት መነሻ ሀሳባቸው በስህተት ይተረጎማል ፣ ይኸውም በአለማውያን ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያን በሚገኙ ወንድሞቻቸው ጭምር ነው። የእግዚአብሔር አገልጋዮች አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች ያስቀምጧቸዋል። ሰዎች ቅድስና የሌለውን፣ራስ ወዳድነት ያለበትን ነገር ለማድረግ ሲሉ ተራሮችን በተራ ጭቃ ክምር የተሰሩ ነገሮች አድርገው ለማሳመኛነት ያቀርባሉ። እነዚህ ሰዎች የራሳቸው ያልሆነ ስብዕና ወይም ለተግባሮቻቸው የተሳሰተ ትርጓሜ ስለሚሰጣቸው ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ይሆኑባቸውና በጨለማ ውስጥ እንዲቀመጡ እና ነገሮቻቸው በሙሉ ግራ የተጋባ እንዲሆኑ ይደረጋል ። እነርሱ እንደማይታመኑ ሰዎች ይጠቋቋሙበቸዋል። ይህ ደግሞ የሚደረገው በቤተክርስቲያን ሰዎች አማካይነት ነው። የእግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳቸውን በክርስቶስ አስተሳሰብ ሊያስታጥቁ ይገባቸዋል። እነርሱ ስድብንና የፍርድን መጓደል ሊሸሹ አይገባቸውም። እነርሱ አክራሪዎችና ከልክ በላይ ሞቅታን የሚወዱ ተብለው ይጠራሉ። ነገር ግን እነርሱ ተስፋ ሊቆርጡ አይገባም። የእግዚአብሔር እጆች ሥራውን ወደራሱ ክብር ለማድረስ በእርሱ መልካምነት እና ደጋፊነት እሽክርክርት ላይ ነው። —Ellen G. White, The Upward Look, p. 177. ለተግሳጽና ሰዎች በእናንተ ላይ ለሚሰነዝሩት ትችቶች ምን ያህል የመቋቋም አቅም አላችሁ? ምናልባት ይህን ያህል አቅም ላይኖራችሁ ይችላል። የመቋቋም አቅም ብዙም አይመስልም አይደል? ። ከኃጢአት እርስዎን ለማዳን ከመውደዱ የተነሳ በመስቀል ላይ ራሱን በሰጠው ክርስቶስ ላይ ለመጣበቅ የራስን ብቃት የመቁጠር አባዜን ሊተው የሚችሉት እንዴት ነው?

@SabbathSchool @TekalignSorato
453 views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 00:01:54 ረቡዕ
ነሐሴ 25
August 31

ዝም ያለ አፍ

በጣም ትልቁ ለየዋህነት ምሳሌ የሚሆነው የሚገኘው በክርስቶስ መስቀል ላይ ነው። ‹‹ ከእኔ ተማሩ፣ እኔ የዋህና በልቤም ትሁት ነኝ›› (ማቴ 11፡29) ሲል እየተናገረ ያለው እኛ ልንገምተው እንኳ በማንችልበት መንገድ (ሁኔታ) ነው። 1ኛ ጴጥ 2:18-25ንያንብቡ። ጴጥሮስ ለባሮች አንድ የሚያስደንቅ ሥጦታ እየሰጣቸው ነው። እርሱ በኃጢአተኞች ለተደረገበት ታላቅ ህመምን ለሚያስከትል ድርጊት ምን ዓይነት መልስ እንደሰጠ ይገልጽና፣ ይህን ምሳሌ ይሆናቸው ዘንድ ለእነርሱ እንደተወላቸው ይነግራቸዋል። ‹‹ እርሱም ምሳሌውን ትከተሉ ዘንድ›› (1ጴጥ 2፡21)። እዚህ በጴጥሮስ በተገለጠው መሰረት፣ በፈተና ውስጥ ሆነን ስለ የዋህነትና ራስን ዝቅ ስለ ማድረግ ምን ዓይነት መርሆዎችን መማር እንችላለን? አንድ ሰው ሌላውን ፍትሃዊ ባልሆነ መልኩ ሲጎዳው ማየት በጣም አስጨናቂ ነው። እናም ይህንን ዓይነት መስተንግዶ የሚደረግብን እኛ ስንሆን ደግሞ የከፋ ይሆናል። ለፍትሃዊነት ጠንከር ያለ አመለካከት ስላለን፣ ኢ-ፍትሃዊነትን የማይቀበለውን ‹‹ነገሮችን በትክክል አስቀምጣቸው›› የሚለውን የውስጥ ተፈጥሮአዊ ማንነታችንን ሲነካብን፣ እኛ የምናምነው ለፍትሃዊነት መጮህ ጽድቅና ቅዱስ ቁጣ ነው ብለን ነው። እንደዚህ መኖር ቀላል ነገር አይደለም። በሁሉም ቅንነት እና ፍትህ በጎደለባቸው ነገሮች ሁሉ የሰማዩ አባታችን የሁሉም ተቆጣጣሪ ነው፣እንደ እርሱ ፈቃድ በሆኑ ነገሮች በእኛ ፈንታ እርሱ ይቆማል የሚለውን እውነት ለራሳችን አድርገን ካልወሰድን በስተቀር ከባድ ነው። ይህ ማለት ደግሞ ፣ እንደ ክርስቶስ እኛም ለኢ-ፍትሃዊነት የተጋለጥንና በጭካኔ የምንስተናገድ ስለመሆናችን ማስተዋል አለብን ማለት ነው። ነገር ግን ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእኛ ጋር መሆኑንና እርሱ ኃላፊነታችንን የሚወስድ ስለ መሆኑ ነው። ጴጥሮስ ከክርስቶስ ህይወት ተሞክሮ የወሰደው ምሳሌነት በጣም የሚያስገርም ነው፣ ምክንያቱም፣ ሰዎችን ወደ ትክክለኛ (ሁኔታ)ነገር እንዲመጡ ከመርዳት በላይ፣ ፍትሃዊ ባልሆነ መከራ ውስጥ ሆኖ ዝም ማለት ለእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ምስክርነት ነው። ክርስቶስ በቀያፋ እና በጲላጦስ ፊት በተጠየቀ ጊዜ ንጽህናውን ለማስረዳት እና ሁኔታውን ለመቀየር ብዙ ነገር አልተናገረም። የእርሱ ዝምታ የየዋህነቱ ምስክር ነበር። አግባብ ባልሆነ መንገድ ሰዎች ቢያስተናግዷችሁ እንዴት ይሰማችኋል? እዚህ የታየውን መርህ በግል ህይወትዎ የሚተገብሩት እንዴት ነው?

@SabbathSchool @TekalignSorato
270 views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 00:01:39 ማክሰኞ
ነሐሴ 24
August 30

የሚጎዱንን መውደድ

አንድ ሰው እንዲህ አለ፡ ‹‹ ጠለቶቻችንን መውደድ ማለት፣ ዕንቁው የተደበቀበትን ቆሸሻ መውደድ ማለት አይደለም፣ ይልቅ፣ በቆሻሻው ውስጥ የተደበቀውን እንቁ መውደድ ማለት ነው…እግዚአብሔር እኛን የወደደን እኛ በተፈጥሮ የምንወደድ ስለሆንን አይደለም። ነገር ግን እኛ የምንወደድ የሆንነው እርሱ ስለወደደን ነው። ጠላቶችህን በምታይበት ጊዜ ምን ይታይሃል-በዙሪያው ያለው ቆሻሻ ወይስ በውስጡ ያለው ዕንቁ?



ማቴ 5፡43-48 ያለውን ያንብቡ። የሱስ ጠላቶቻችንን እንድንወዳቸውና እንድንጸልይላቸው ጥሪ እያደረገልን ነው። ክርስቶስ ጠላቶቻችንን መውደድ እንዳለብን ከተፈጥሮ እየሰጠን ያለው ምሳሌ ምንድነው? እርሱ እያስተማረን ያለው ምሳሌ ለምንድነው?



በማቴዎስ 5፡45፣ ክርስቶስ ጠላቶቻችንን እንዴት መቅረብ እንዳለብን ሲነግረን ምናልባትም ትልቅ ችግር ውስጥ ሊከቱን ስለሚችሉ ሰዎች በሰማያት ያለውን አባቱን ምሳሌ ይጠቀማል። የሱስ እንዲህ ይላል፡ - የእርሱ አባት ዝናብንና ፀሐይን ለክፉዎችም ለጻድቃንም እኩል ይልካል፤ እግዚአብሔር ለኃጢአተኞች ዝናብን የሚሰጣቸው ከሆነ፣ እኛ ይልቁንስ እንዴት ልንንከባከባቸው ይገባናል? መሆን እንኳ የሚቻል ቢሆን፣ የሱስ ሁልጊዜ በህይወታችን ችግር ለሚፈጥሩብን ሰዎች ሁሉ ሞቅ ያልን (ፍልቅልቅ) እንድንሆን አይደለም ሊነግረን የፈለገው። በመሰረቱ ጠላቶቻችንን መውደድ ማለት፣ ስለ እነርሱ የሚሰማን ስሜት ሳይሆን ለእነርሱ ጥንቃቄ ለማድረግ በምንፈጽመው የተለየ ድርጊት የሚገለጽ ነው። ክርስቶስ ይህን ንባብ የሚጨርሰው ብዙ ጊዜ ክርክር በሚያስነሳ ሃሳብ ነው ይህም ‹‹ የሰማዩ አባታችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ››(ማቴ 5፡48) በማለት ነው። ነገር ግን ትርጉሙ በንባቡ አውድ ግልጽ ነው። እነዚያ እንደ እግዚአብሔር ፍጹም መሆን የሚፈልጉ ሁሉ፣ እርሱ ለጠላቶቹና ለወዳጆቹ ፍቅሩን እኩል ለሁሉም እንዳሳየ እነርሱም ጠላቶቻቸውን በመውደድ ያሳዩ። በእግዚአብሔር እይታ ፍጹም መሆን ማለት ጠላትን መውደድ እና እግዚአብሄር ብቻ ሊሰጠው የሚችለው የልብ የዋህነት ነው። <<በጉዳት ውስጥ በትዕግስት መጽናት ›› የሚለውን ለየዋህነት የተሰጠውን ትርጉም በሀሳባችን እንደያዝን፤ እግዚአቤሔር ትክክለኛውን የልብ የዋህነት እንዲሰጥህና ጠላቶችህን ለመውደድ ማድረግ ያለብህን ነገሮች ዝርዝር ጻፍ።

@SabbathSchool @TekalignSorato
450 views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 00:01:41 ሰኞ
ነሐሴ 23
August 29

ለጸጋ መማለድ

ዘዳግም 32 ፡ 1-14 ያንብቡ። ሙሴ በዚህ ስፍራ እየተጫወተ ያለው ሚና ምንድነው?



ሰዎች የወርቅ ጥጃን ማምለክ ከጀመሩ በኋላ እግዚአብሔር የሰው ልጆች ከእርሱ ርቀው ስለሄዱ እነርሱን እንደሚያጠፋና ሙሴን የነገዶች አባትና ብዙ ህዝብ እንደሚያደርገው ወሰነ። ነገር ግን ሙሴ እግዚአብዚሔር የሰጠውን ሥጦታ በመቀበል ፋንታ ይቅር እንዲላቸው ለመነ እርሱም ተለመነው። ዘጸአት 32 ፡ 1-14 ሁለት አስፈላጊ ነጥቦችን ያነሳል። የመጀመሪው፣ አመጸኞችን የማጥፋትና ሙሴን መባረክ ይህም ለሙሴ ታላቅ ፈተና ነበር። እግዚአብሔር ለዚህ በተለየ ሁኔታ ዓመጸኛ ለሆነው ህዝብ ምን ያህል ፍቅር እንደሚያሳይ ማወቅ ፈለገ። እናም ሙሴ ፈተናውን አለፈ። እርሱም እንደ ኢየሱስ ለህዝቡ ኃጢአት ይቅርታን ተማጸነ። ይህ አንድ በጣም ደስ የሚል ነገርን ያሳየናል። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ተቃውሞን እንድንጋፈጥ ይፈቅዳል፤ በፈተና ውስጥ እንድናልፍ ልፈቅድ ይችላል፣ ይህንም የሚያደርገው ከእግዚአብሔር ርቀው ለሄዱት በሚያየን ሰማይ ፊት ምን ያህል እንደምንራራላቸው ለማየት ነው። ሙሴ እግዚአብሔር እስራኤልን እንዳያጠፋ የሰጠው ምክንያት ምንድነው?



ሁለተኛ፣ ይህ ምንባብ እንደሚያሳየው ተቃርኖውና አለመታዘዙ የእግዚአብሔርን ጸጋ ለመግለጥ የቀረበ ጥሪ ነው። ጸጋ የሚያስፈልገው ሰዎች በጣም ያልተገባችው በሆኑበት ጊዜ ነው። ነገር ግን በፍጹም ያልተገባቸው ሲሆኑ ያ ጊዜ ጸጋን ለመስጠት ትክክለኛው ጊዜ ነው ማለት ነው። ነገር ግን የሙሴ እህት እርሱን በናቀችው ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከለምጽ እንዲያድናት ጸለየ። እግዚአብሔር በቆሬና ተከታዮቹ ላይ ሲቆጣ እና ሊያጠፋቸው በፈለገ ጊዜ ሙሴ ህይወታቸውን ለማትረፍ በግንባሩ ወድቆ ይለምን ነበር። በሁለተኛው ቀን፣ እስራኤል ስለሞቱት አመጸኞች ሰዎች ሙሴ ላይ ቁማር ሲጫወት እንደገና እንደሚያጠፋቸው በተናገረ ጊዜ ሙሴ በግንባሩ በመደፋት አሮን የሚቃጠል መስዋዕት እንዲያቀርብና ህዝቡ ይቅርታ እንዲያገኝ ይለምን ነበር። ሙሴ በራሱ የዋህነት እና ራስ ወዳድነት በሌለው ሁኔታ በዚህ ትልቅ ፈተና መካከል፣ ላልተገባው ህዝብ ጸጋን ሲለምን እንመለከታለን። በዙሪያዎ ስለሚገኙ ጸጋ በፍጹም አይገባቸውም የስለሚሏቸው ሰዎች ያስቡ። እርስዎ ራስ ወዳድነት በሌለበት በየዋህነት እነዚህን ሰዎች የእግዚአብሔርን ጸጋ እንዲያገኙ የሚረዷቸው እንዴት ነው?

@SabbathSchool @TekalignSorato
531 views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 00:00:46 እሁድ
ነሐሴ 22
August 28

የተቆረሰው ዳቦ እና የፈሰሰው ወይን

ኦስዋልድ ቻምበርስ እንዲህ ብሏል እኛ ለሌሎች ‹‹ የተቆረሰ ዳቦና የፈሰሰ ወይን ልንሆን ይገባናል››። በዚህ አባባሉ ምን ማለት የፈለገ ይመስሎታል?



በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ በሙሉ ስናነብ ሌሎችን ለማገልግል ሲሉ ‹‹የተሰበሩ›› ሰዎች ምሳሌዎችን እናገኛለን። ሙሴ ህዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲመራ ሲጠራ የወሬና የስድብ ማዕበል እንዲቋቋም ነበር። ዮሴፍ ወደ ግብጽ ትልቅ ስልጣን ከመድረሱ በፊት በተጠራ ጊዜ በወንድሞቹ መካድንና እስራትን በጉዞው እንዲያልፍ ሆነ። በእንዳንዱ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሁኔታዎችን ሲፈቅድ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም መልካም ይሆን ዘንድ የእርሱ ጸጋና ጥንቃቄ ማሳያዎች እንዲሆኑ፣ በመፈለግ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ እግዚአብሔር እኛንም ሊጠቀመን ይችላል። በዚህ ዓይነት ጊዜ መቆጣት፣ መጎዳትና ማጉረምረም ቀላል ነው። ነገር ግን ትናንት እንደተመለከትነው የዋህነት‹‹በትዕግስትና ያለማጉረምረም›› እንደዚህ ዓይነት ጊዜያትን እንድናልፍ እግዚአብሔር የሰጠን ስጦታ ነው። ህዝ 24:15-27ን ያንብቡ። በዚህ ስፍራ እየሆነ ያለው ምንድነው? ህዝቅኤል በዚህ ፈተና እንዲያልፍ የተደረገው ለምንድነው?



በህዝቅኤል 24፡24 እግዚአብሔር አንዲህ ይላል፡-‹‹ህዝቅኤል ምልክት ይሆናችኋል፤ እናንተ እርሱ እንዳደረገ ታደርጋላችሁ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ እናንተም እኔ ታላቅ ሁሉን ቻይ አምላክ መሆኔን ታውቃላችሁ።›› በህዝቅኤል ምሳሌነት መሰረት፣ የእስራኤል ህዝቦች ስለ እግዚአብሔር መኖር እውነትነት እንዲረዱ፣ በህዝቅኤል ህይወት በሚፈጸመው ትንቢትና በህይወቱ በሚታየውና በሚያጋጥመው መከራ ምሳሌ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ማየት ይችላሉ። ማን ያውቃል እኛ በተሰበርንበት ጎን ‹‹ ታላቁን አምላክ›› እግዚአብሔርን ምን ያህል ሰዎች ማየት ይችሉ ይሁን? ፈጠነም ዘገየ ህይወት ራሷ ሁላችንንም መስበሯ አይቀሬ ነው። ስለ መሰበር የእርስዎ ልምምድ ምን ድነው? ምን ትምህርት ተማሩ? የርስዎን የተሰበረችውን ነፍስ ራሷን ሌሎችን ለመርዳት እግዚአብሔር የተጠቀመባት እንዴት ነበር?

@SabbathSchool @TekalignSorato
275 views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 00:00:34 ከነሐሴ 21- 27
10ኛ ትምህርት
Aug 27 - Sep 2




የዋህነት በፈተና ውስጥ


ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ህዝ 24:15-27 ዘጸ 32:1-14 ማቴ 5:43-48 1 ጴጥ 2:18-25 መዝ 62:1-8ን ያንብቡ።

የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “የዋሆች ብጹአን ናቸው ምድርን ይወርሳሉና።” (ማቴ 5:5).
የ ዋህ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል አይታይም፤ ምናልባትም ፣ የምናገኘው በተራራው ስብከት ውስጥ ወይም ስለ ሙሴ በሚነግሩን ንባቦች ውስጥ ብቻ ሊሆን ይችላል። የዋህነት ‹‹ ጉዳትን በትዕግስት ባለማጉረምረም መቋቋም(መቀበል ) ማለት ነው።›› ስለዚህ ብዙ አለመስማታችን ብዙ አያስገርምም፤ በባህላችን በአሁን ጊዜ በጣም ዝቅተኛ ቦታ የተሰጠው ባህሪይ ነው ። አንዳንድ ጊዜ ይህ ቃል በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ትሁት በሚል ተተርጉሟል። በድጋሚ ፣ራስን ዝቅ ማድረግ በብዙ ማህበረሰባችን ዘንድ ተቀባይነት ያለው ባህሪይ ነው። ነገር ግን ፣ የዋህነት፣ መከራን በትዕግስትና ያለማጉረምረም ተቋቁሞ ማለፍ፣ የክርስቶስና የተከታዮቹ እጅግ ኃይለኛ የሆነው ባህሪያቸው ነበር። ሆኖም ለብቻው የነገሮች ሁሉ ፍጻሜ ግን አይደለም። በመንፈስ የዋህ መሆን በመከራ ውስጥ በህመምና ስቃይ ለሚኖሩ በእጃቸው የሚገኝ እጅጉን ኃይለኛ መሳሪያ ነው። በእርግጥ፣ በልባችን የዋህነትን ለመማር የሚያስችል ዋንኛ መሳሪያ ፈተና ነው። በየዋህነታችንና በተሰበረ ነገራችን ምክንያት ለእግዚአብሄር ኃይለኛ ምስክሩ ልንሆንለት እንችላለን። ሳምንቱን በኣጭር እይታ: በየዋህነትና በመከራ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድነው? እና በተሰበረው ነገራችንና በየዋህነታችን ለሌሎች ምስክር ልንሆን የምንችለው እንዴት ነው? በእርግጠኝነት የዋህነት ለክርስትያን ጥንካሬ እንጂ ድካም ሊሆን የማይችለው እንዴት ነው? *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሐሴ 28 አጥንተው ይዘጋ

@SabbathSchool @TekalignSorato
546 views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 00:00:59 አርብ
ነሐሴ 20
August 26


ተጨማሪ ሀሳብ

አበውና ነብያት በሚለው የኤለን ዋይት መጸሐፍ ፣ ‹‹ ኢዮሳፍጥ›› የሚለውንና ‹‹የኢያርኮ አወዳደቅ›› የሚለውን ክፍል ያንብቡ። “ወደር ለማይገኝለት ፍቅሩ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን ልባችንንና አፋችንን እናለማምደው። ከመስቀሉ ላይ በሚፈነጥቀው ብርሃኑ ነፍሳችን እንድትጸናና ተስፋ እንድታደርግ ልናስተምራት ይገባናል። እኛ የሰማዩ ንጉስ ልጆች የሰራዊት አለቃ ወንዶችና ሴቶች መሆናችንን በፍጹም ልንዘነጋ አይገባንም። በእግዚአብሔር የተረጋጋ ምላሽ ላይ መጽናት ለእኛ ትልቅ እድል ነው። The Ministry of Healing, p. 253. “እርሱን ሳከብረውና ከፍ ሳደርገው፣ አንተ ከእኔ ጋር እንድታከብረው እፈልጋለሁ። በጨለማ ውስጥ ብትሆን እንኳ እግዚአብሔርን አመስግነው። በፈተና ውስጥም ስሙን ከፍ አድርገው። ‹‹ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ›› ‹‹ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ›› ። ለእርስዎና ለቤተሰብዎ ይህ ጨለማንና ጭጋግን ያመጣ ይሆን? አይደለም፣ የጸሐይን ጨረር ይፈነጥቃል እንጅ። ስለዚህም፣ ከክብር ዙፋኑ ዘላላማዊ የሆነውን ብርሃን በዙሪያዎ ይሰበስባል። ይህን ብርሓን በራስዎ ህይወትና መንገድ ብቻ ሳይሆን አብረዎት ባሉ ወገኖች ሁሉ ዙርያ እንዲያደርጉና በዚህ ሥራ ተካፋይ እንዲሆኑ ልጋብዝዎት እፈልጋለሁ። በዙሪያዎ የሚገኙ ሰዎችን ህይወት ምድራዊ ከሆነው ነገር ሁሉ በላይ ጠፊ ከሆነው ርስት እና ምድራዊ ሀብት ይልቅ ወደ ሰማይና ወደ ክብሩ ወደ ከፍታ ማድረስ ዓላማዎ ይሁን።›› Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 593, 594.
የመወያያ ጥያቄዎች


1. የማህበረሰቡ የምስጋና ህይወት በክርስትና ላይ ምን ተጽዕኖ አለው? ምስጋናን በሰንበት አምልኮ ውስጥ እንዴት ይገልጹታል? ወደ ጌታ ከፍ የሚያደርግ ነው? አባላትን በችግሮች ውስጥ ታማኝነታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የሚያበረታታ ነው? ይህ ካልሆነ መደረግ ያለበት ምንድነው? 2. “በጨለማ ውስጥ ብትሆን እንኳ እግዚአብሔርን አመስግን” ወይም “በፈተና ውስጥም ቢሆን አመስግነው ማለት ምን ማለት ነው”? በእነዚህ ነገሮች ውስጥ ምስጋና የሚጠቅመን እንዴት ነው? 3. አባላት ምስጋና በህይወታቸው ላይ ያመጣውን ተጽዕኖ ምስክርነት ይስጡ። አንዱ ከሌላው የህይወት ልምምድ ምን መማር ይችላል? 4. እንደ ሰንበት ትምህርት ክፍል፣ አንድ የምስጋና መዝሙር ለማንበብ ጊዜ ውሰዱ። ስለ ምስጋና ምን ያስተምራችኋል? ምስጋና በእምነትዎ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምንድነው?

@SabbathSchool @TekalignSorato
711 views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 00:00:51 ሐሙስ
ነሐሴ 19
August 25

አሸናፊ መሳርያ

2ዜና 20 1- 30 ያለውን ያንብቡ። ኢዮሳፍጥ ምስጋና ታላቅ አሸናፊ መሳርያ መሆኑን ተረድቷል።‹‹ታላቅ ሰራዊት›› ወደ እርሱ እየመጣ እንደሆነ መልዕክት እንደደረሰው ኢዮሰፍጥ፣ ወደ ወታደራዊ እርምጃ አልሔደም፣ ነገር ግን ‹‹ የእግዚአብሔርን ፊት ፈለገ›› ( 2 ዜና 20:3):: የይሁዳ ሰዎች ለጻሎትና ለጾም ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ፣ ኢዮሳፍጥም ሁኔታውን እንዲህ በማለት ገለጸው ‹‹ ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፣የምናደርገውንም አናውቅም፤ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው›› (2 ዜና 20፡12)። እርስዎ ታላቅ ሰራዊት በሚያዩበት ጊዜ ቶሎ ብለው የሚወስዱት ኤርምጃ ምንድነው? በ2 ዜና 20 2-12 ታላቅ ግድድሮሽን አስመልክቶ ኢዮሳፍጥ ከሰጠው ምላሽ ምን ትምህርት ወሰዱ?



የእግዚአብሔር መንፈስ በየሕዝቅኤል ላይ እንደመጣ ‹‹ በዚህ ሰልፍ እናንተ የምትዋጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ ተሰለፉ ዝም ብላችሁ ቁሙ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፤ ነገም ውጡባቸው››(2 ዜና 20:17) ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን አመለኩ‹‹ በታላቅ ድምጽም›› ምስጋናንም ሰጡት ። (2 ዜና 20:19):: እግዚአብሔር የሚዋጋላቸወ እንኳ ቢሆንም፣ እነርሱ በጠላት ፊት መቆም አለባቸው። ነገር ግን ይህ ወደ ጦርነት የሚደረግ ተራ ሰልፍ አይደለም። ኢዮሳፍጥ ወደ ጦርነቱ ጉዞ ሲያደርጉ ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር የሚያዜሙ መዘምራንን ሰየመ። “ዝማሬውንና ምስጋናውን በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡት በአሞንና በሞአብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ድብቅ ጦር አመጣባቸው፤ እነርሱም ተመቱ” (2ዜና 20:22)። እንደ መጸሐፉ ጸሐፊ፣ እነርሱ እንደ ተስፋ ቃሉ እግዚአብሔርን ስለምህረቱና ቅድስናው ማመስገን ሲጀምሩና እምነታቸውን ሲለማመዱ እርሱ ጣልቃ ገባ። እርስዎ ከእግዚአብሔር ጋር በሚያደርጉት ጉዞ በተለየ ሁኔታ በችግርና በመከራ ጊዜ የሚጠቅም ምን መንፈሳዊ መርህ አገኙ?

@SabbathSchool @TekalignSorato
787 views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 00:01:50 ረቡዕ
ነሐሴ 18
August 24

የሚያሳምን ምስክር

በሐዋርያት ስራ መጸሐፍ ውስጥ፣ ምስጋና በሰሚዎቹ ዘንድ በጣም አስገራሚ ተጽዕኖ አድርጎ እናያለን። የሐዋ ሥራ 16 ፡ 16-34 ያለውን ያንብቡ። በከባድ ሁኔታ ከተደበደቡና ከተገረፉ በኋላ ጳውሎስና ሲላስ ወደ እስር ቤት ተጣሉ። ክፉኛ በተደበደቡበት ቁስላቸው ላይ ዘይት የሚያፈስላቸው ማንም አልነበረም። በትልቅ ህመምና እግራቸው በግንድ ተጠርቆ፣ በውስጠኛው ክፍል ተጥለው ነበር። ነገር ግን ሌሎቹ እስረኞች እያዳመጡ ሳለ፣ ጳውሎስና ሲላስ ይዘምሩና ይጸልዩ ነበር። የመሬት መንቀጥቀጡ ከሆነ በኋላ፣ ጳውሎስ እና ሲላስን ጨምሮ ከእስር ቤቱ ማንም አስረኛ አለማምለጡን የእስር ቤቱ ሐላፊ ሲያውቅ፣ ‹‹ በጳውሎስና በሲላስ ፊት እየተንቀጠቀጠ፣ ከእስር ቤቱ ወደ ውጪ አውጥቶአቸው፣ ወዳጆቼ እድን ዘንድ ምን ላድርግ? አላቸው” (ሐዋ 16:29, 30) :: ይህ ሁኔታ የእስር ቤቱን አለቃ በራሱ መዳን ላይ ብቻ እንዲያተኩር ያደረገበት ምክንያት ምንድነው? በሌሎች እስረኞች ለማምለጥ ባለመፈለግ እና በዚህ ሰው እና ቤተሰቡ መለወጥ ላይ የጰውሎስና ስላስ መዝሙርና ጸሎት ያደረገው ተጽዕኖ ምንድነው?



ምስጋና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች የህይወት ፍጻሜን በመለወጥ ረገድ ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ማወቅ በጣም አስገራሚ ነው። ጳውሎስና ሲላስ እንደተለመደው በእስር ቤቱ ጨለማ ውስጥ ሆነው አጉረምርመው ቢሆን ኖሮ፣ በዚያ ምሽት አንድም ሰው ይድናል ብለው ያምናሉ? በስተመጨረሻ የእስር ቤቱ አለቃ ምን እንደሆነ አናውቅም፣ ነገር ግን ጳውሎስ በሌለው አስር ቤት ሆኖ በፊል 1፡ 29፣30 ላይ ‹‹ ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኃልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ እንድትቀበሉ እንጅ በእርስ ልታምኑ ብቻ አይደለም። በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ የምትሰሙት ያው መጋደል ደርሶባችኃል›› በማለት የጻፋቸውን ቃላት ያስቧቸው። እነርሱ ይህንን መልዕክት በማንበብ የእርሱን ህይወት ካንጸባረቁ በህይወታቸው ደስታን አምጥቶላቸዋል፣ በእርግጠኝነት ለልባቸው ደስታን በማምጣት እንዲዘምሩ አድርጓቸዋል፣ እናም ግድድሮሾች ምንም ያህል ዋጋ የሚያስከፍሉ እንኳ ቢሆን ታማኝ ሆነው እንዲቆሙ አድርጓቸዋል ማለት ነው። ከእርስዎ አንደበት ስንት ሰው ለእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር በሚሰጡት በትክክል ይታወቅ፣ ከዚያ እንደሚያሰድር ያያሉ። በሚወጣው የምስጋና ዝማሬ የተነሳ ተማርኳል? በሌሎች ዘንድ እርስዎ ምስጋና ልዩ ትኩረት እንዳለዎት በኋላ ምን ያህል አዎንታዊ ተጽዕኖ

@SabbathSchool @TekalignSorato
880 views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ