Get Mystery Box with random crypto!

Reyan Records

የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records R
የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_records — Reyan Records
የሰርጥ አድራሻ: @reyan_records
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 346

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 24

2022-08-22 17:04:11 (ነሱሀ አወል)

ፃፊልኝ!
አትበለኝ ግጥም፣
መውደድ ይዤ የማይገጥም።

ይልቅ ልንገርህና...!
ግጥም አልገጥምልህም
ለቃል አትገራምና።

እስቲ ምን ብየ ልግጠም?
መፈቀር ተረት ሆኖ
ፌዝ በሆነበት ዛሬ፣
ምን ልፈይድ? ምን ላመጣ?
መአት ፊደላት ዘርዝሬ።

እናም እንዳትገረም!
ቃላት ለኔ ባይገሩ፣
ዞሮም ለካ ፃፍኩልህ
ምን ያስከፋሀል? ነገሩ።
90 viewsGlamor, 14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 09:38:12 ውርሰ ውበት

ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን..

በፈረሶች ፀጉር
ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር
ውበት ይሁናቸው

ብዙ ኩል ቀላቅለው
አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው
አይንሽን ይትከሉ

ለቁንጅና ድጋፍ
አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው
ውብ ጌጥ ነው በራሱ

ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ
አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው
ወስደው ያስተክሉት

ሁሉንም አካልሽን
ከአፈር መበስበስ
መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም
ሞተሽ ውበት ሁኚ

ፀባይሽ ግን ውዴ...

እኔ ያልቻልኩትን
አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ
ትርፉ መቃጠል ነው

ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...

ውበትን ለሚሹ
ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ

እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል
እነሱን ላግባቸዉ
90 viewsGlamor, 06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:04:58 ፍትህ ከመስፈኑ የተነሳ ተኩላዎች ፍየሎችን መብላት ያቆሙበት ዘመን ይሉታል የታሪክ ሊቃውንታት። ዘራፊና ቀማኛ የጠፋበት ደጃፎች ተከፍተው የሚታደሩበት ይሉታል ሙጨሪኾች። አዎ በእርግጥም ነፍሱን ለአላህ ባሳደረ ፍፁም ፍትሀዊ መሪ አለም ትተዳደር ነበርና ነው። ሚስቱ የቀድሞው ኸሊፋ የዐብደላህ ኢብኑ መርዋን ልጅ ነበረች። አባቷ በተለያዩ ውድ ጌጣጌጦች አስውቧት። በወርቅ በተለበጡ ሸዋሊያዎች፣ በሚያብረቀርቁ የንገት ጌጣጌጦች፣ ውበትን በሚያጎናፅፉ የእግር አልቦዎች ተሽቀርቅራ አምራለች። ታዲያ እኚህ ሰው መንበረ ስልጣኑን ከአባቷ ሲረከቡ ለአስቸኳይ ጉዳይ እንደሚፈልጓት ነግረው ወደ ክፍላቸው አቀኑ። እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ጀመሩ:-

"አባትሽ በስልጣን ዘመናቸው የሰጡሽ ጌጣጌጦች የበዙ ናቸው። ይህ ከሙስሊሞች ግምጃ ቤት የወጣ ንብረት ነውና እንድትመልሺ እጠይቅሻለሁ። ካልሆነ ግን የሙስሊሞችን ሐቅ ይዘሽ አብረን መኖር አንችልም። ጌጥሽን ወይም እኔን ምረጪ" አሏት።

አንገቷን ወደመሬት አቀርቅራ ንግግራቸውን ስታዳምጥ የነበረችው ፋጡማ
"አንተ የወደድከውን ጀነት እኔ የምጠላ ይመስልሀልን አኼራንና ድህነትን መርጬ ካንተ ጋር እኖራለሁ" አለች እጇን ወደ ጌጧ መክፈቻ እያስጠጋች። አውርታም አልቀረች ጌጧን ሁሉ አውልቃ አስረከበች። ስልጣን ከመያዛቸው በፊት የነበረውን ውብ መኖርያ ቤታቸው ሳይቀር ወደ ሙስሊሞች ግምጃ ቤት አስገቡት። ግና ማረፊያ ይሆናቸው ዘንድ አንገት ማስገቢያ ቤታቸውን ሲቀይሩ ኻዲም ስላልነበራቸው ባለቤታቸው ፋጡማ ጭቃ ታቦካለች እሳቸው ተቀብለው ይለጥፋሉ። እኚያ ሰው ዑመር ኢብኑ ዐብዱል አዚዝ ይሰኛሉ። እንዲህ አይነት ፍትህ ነው ተኩላ ፍየልን እንዳይበላ ያደረገው።

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch
90 viewsGlamor, 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 16:44:39 አሰላሙአለይኩም ያ አህባብ



ከዚ በፊት ሹሩቅን ማስነበባችን ይታወቃል አሁን ደሞ በድምፅ ለናንተ ለማቅረብ ዝግጅታችንን ጨርሰን መጥተናል ቻናላችንን እየተቀላቀላቹ ለሌሎችም እያጋራቹ ተዝናኑበት




@TEWBEET
85 viewsGlamor, 13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 22:00:45 ቀፈፈኝ ጅስሜ፣ ጠላኋት ሩሄን
ካንተ የራቀች ደካማ ነፍሴን፣
ወደድኩኝ አንተን፣ ከሱጁድ ቀረሁ
በምባ ታጥቤ ምህረትን ለመንኩ፣
.
.
ወደድከኝ መሰል፣ ፀፀቴን ሰምተህ
መኖር ጀመርኩኝ አንተን ሳገኝህ፤

rehima hussen
97 viewsGlamor, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 08:59:12 #እያሰብን 25
:
<< መናገር ያለብንን ለማን እና እንዴት መንገር እንዳለብን በትክክል ማወቅ አስተዋይነት እንጂ ድብቅነት አይደለም። ሰዎች የምስጢር ቀብድ ጀምረዋል። <<የሆነ ቀን ለሊት በተኛሁበት አንድ ቀጫጫ ቁንጫ ጀርባዬን የበላኝ ቦታ አሁንም ጠባሳው አለ። ደግሞ ይሄን የነገርኩህ/ሽ አንተን/ቺን ስለማምንህ/ሽ እንጂ ለማንመ ተናግሬው አላውቅም።>> እንግዲህ አንዳንዱ ለማንም ያልተነገረ ነገር ለኔ ተነገረኝ ብሎ የባጥ የቆጡን ይዘረግፋል። ግዴላችሁም ረጋ በሉ። ወገን ኧረ እያሰብን! ለማንኛውም ይህን ጥያቄ አስባችሁ መልሱ።
#ክብራችሁን_በስንት_ትውውቅ_ውስጥ_ሸጣችሁ?
#ምስጢራችሁን_ስንቴ_አይዟችሁ_ስትባሉ_ዘረገፋችሁ? >>
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
130 viewsGlamor, 05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 23:59:30 ፍቅር ማስተጋባት ነው ከአንድ ወገን የሆነ ማስተጋባት ..ከአንድ በኩል ወደሌላ አቅጣጫ የሚወረወር። አንተም እኔም የምናውቀው ብቻችንን የተሸከምነው ፍቅር። ፍቅርን ማፍቀር ከመቻላችን በፊት እናውቀዋለን።ግና መውደድ ከመቻላችን በፊት ተወደን ነበር። ከመስጠታችን በፊት ተሰጥቶናል። ምን መስጠት እንዳለብን ሳንረዳ በፊት ተለግሰናል። ያ ፍቅር ልባችን የተፈጠረለት ፍቅር ነው ።ሁሉንም ፍቅሮች የሚፈጥር እና የሚያስቀጥል ፍቅር እሱ ነው ከሁሉ በፊት የነበረ፣ ከሁሉ በኋላ የሚቀር ፍቅር ነው።

ከሁሉ በፊት የነበረ፣ ጩኸቶች ሁሉ ካለፉም፣ከሁሉ በኋላ የሚቀር ፍቅር ነው።


የአምላካችን የአላህ ፍቅር ።


(ምንጭ ፦ ልብህን አስመልስ )
19 viewsGlamor, edited  20:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:08:18 ግራ እጁን ለሚጠቀም ግራኝ ካልን
ቀኝ እጁን ለሚጠቀምስ ......

መልስ Commnent ላይ
33 viewsGlamor, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 12:54:19
ብቸኛ የሆንኩ ያህል ሲሰማኝ ብቸኝነቴ ከሰዎች ጋር ስሆን ብቻ እንደሆነ የገለጥክልኝ ጌታዬ፣
ጣእመቢስ ሆንኩ ስል . . .ለነሱ ስቀርብ ጣእመቢስ ሐያት መምራቴን ያሳኸየኝ ጌታዬ፣
ካንተ ጋር ብቻ ሁኜ አለምን ልሙላ
አንተን ይዤ ለዛ ይቀፈኝ
መውደድህ መሪ ይሁነኝና ከፍቅርህ ወንዝ እንድቀዳ ፍቀድ!

መድ
45 viewsGlamor, 09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 21:16:51 "አፈቅርሻለሁ" የሚለዉ ቃል
ምንም እንኳ አጭርና ቀላል ቢሆንም
ልብን ሰርስሮ የመግባት ጉልበቱ
ግን.... ሐያል ነዉ፡፡
ሐቢቢ ...! ፍቅርህን በገለፅክላት ቁጥር
በርሷ ዉስጥ ያለህ ቦታ ይበልጥ እየጨመረ
ይሄዳል፡፡ ስለዚህ... በዚህ ዉብ ቃል
ሚስትህን አስፈንድቃት!!
(አ ፈ ቅ ር ሻ ለ ሁ)
64 viewsGlamor, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ