Get Mystery Box with random crypto!

መልካም አስተሳሰብ ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ positivethinkingquoteset — መልካም አስተሳሰብ ™
የቴሌግራም ቻናል አርማ positivethinkingquoteset — መልካም አስተሳሰብ ™
የሰርጥ አድራሻ: @positivethinkingquoteset
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 372
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን በደህና መጡ ቀኖን በጥሩ #መንፈስ ማሳለፍ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ትክክለኛ ቦታ መተዋል🙌 በኛ ቻናል
>#ድብርትን_የሚያጠፉ_ጥቅሶች ☺
> የተሻለ_አስተሳሰብን_የሚሰጡ_ንግግሮች😇
> ልቦለድ መፃህፍት 📚
> እንዲሁም #አስተማሪ_መልክቶችን በአማርኛ እና English ቋንቋዎች ያገኛሉ ይቀላቀሉን t.me/positivethinkingquoteset ለሎችም_ሼር_ያርጉ_እናመሰግናለን😘

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-25 08:55:26 ጣዝማ እጅግ ብልሕ ናት። መሬት ቀዳ ገብታ እንደዚያ ያለ መድኃኒት የሚሆን ማር ትሠራለች። ምነው እናንተ ሰዎች ወይ ከፈጣሪ ወይም ከሰው ብልሐትን አትፈልጉምን?
ማር ሁለት ጊዜ ያገለግላል አንድ ጊዜ መጠጥ አንድ ጊዜ መብራት ሆኖ። ምነው ቢሉ፥ የብልሕ ሥራ ነውና አሰርም የለው።
ቅቤ ለመጽሐፍ ዘመዱ አይደለም።መጽሐፍ ግን ለሰው ቅቤ ነው።
ነገስታት እና መምህራን እንደ ውሃ ቢሆኑ ወንጌል በዓለም ሁሉ በተሰበከ ነበር።የውሃም መልካምነቱ እንደዚህ ነው።ከምድር ላይ በፈሰሰ ጊዜ ሁሉን አብቅሎ ምግብና ልብስ ይሆናል፤ዱቄቱን አርሶ እንጀራ ያደርገዋል፤የደረቀውን እርሾ ለስላሳ ያደርገዋል፤ያደፈውን አጥቦ ንጹሕ ያደርገዋል፤መምህራንም እንዲህ ቢሆኑ ዓለም ሁሉ አንድ አካል አንድ አምሳል በሆነ ነበር።
የረሀብ ጌትነቱ መቼ ነው እህል በታጣ ጊዜ ነው ምነው ቢሉ የሌለውን አምጡ ይላልና። የማጣትስ ጌትነቱ መቼ ነው የፈለጉት ነገር በታጣ ጊዜ ነው። የጥጋብስ ጌትነቱ መቼ ነው መብልና መጠጥ በተገኘ ጊዜ ነው። የመብላትስ ትርፉ ምንድር ነው ጥጋብ ነው።
ሰው ፍሪዳን አብልቶ አብልቶ ያሰባዋል በመጨረሻውም ይበላዋል።ምነው ቢሉ አብልቶ መብላት ገበያ ነው። (capitalism )
ማርና እሬትን ቢመዝኑ ማን ይደፋል እሬት ምነው ቢሉ ክፉ መራራ ነውና።ከብዙ ቀን ደስታ ያንድ ቀን መከራ ይበልጣል።
ሕዝብና ሕዝብ ደጋና ቆላ ናቸው ንጉሡ ግን ገበያ ነው ሁሉን ያገናኛልና።ሸክላ ከተሰበረ በኋላ ገል ነው መኳንንትም ከተሻሩ በኋላ ሕዝብ ናቸው።
ሸክላ እጅግ ክፉ ነው ውሀ አርሶ አሠርቶት መከታ እየሆነ እሳትን ያስወጋዋል።ክፉም ሰው እንደዚያ ነው። ወንፊት ዱቄትን እንዲነፋ ዘርዛራም ሸማ ጠጅን እንዲያወርድ ባለቤቱም ያልቻለውን ምሥጢር ሌላው ሰው አይችለውም።
ቅቤ ካይብና ካጓት እንዲለይ በላይም እንዲሆን ጻድቅም ሰው እንደዚያ ነው።
ማሽላን ወፎች ራስ ራሱን ሲሉት አይቶ ባቄላ ፍሬውን በጎኑ አዝሎ ክንፉን አልብሶ ይኖራል።ውሃ ወርዶ ወርዶ ባይመቸው ኩሬ ይሆናል።ብልህም በጨነቀው ጊዜ ሞኝ ይሆናል።
መሳል መልካም ነው፤ብረትን ይስለዋልና።መጽሐፍም መልካም ነው፤ልብን ያበራዋልና።
ፀሐይ ለኢያሱ ለምን ቆመችለት መድሐኒቱን ኢየሱስ መስሏት ይሆን?ኢየሱስ መድሐኒቱ ሰውም አይገድል፤ያድናል እንጂ
አይሁድ ጾማቸውን አጥርጠው ይጾማሉ፤ክርስቲያኖች ግን ጦማቸው የጠራ አይደለም፤አርብ የታረደውን የበግ ስጋ ይበላሉና።አይሁድ ከእንስሳት እንኳን ለይተው ነው የሚበሉት፤ክርስቲያኖች ግን ወንድማቸውን ይበላሉ።
106 views05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 09:10:57 ሰዎች ስለአንተ የሚኖራቸው ግምት አንተ ስለራስህ ከሚኖርህ የራስ ግምት የሚነሳ ነው፡፡ ሰዎች ስለአንተ የሚፈጥሩት ግምት በሀዘኔታ፣ በፍቅር ወይም በተመሳሳይ ስሜት የተነሳ እንዳይመስልህ፡፡ ሰዎች ላይ የአስፈላጊነት ስሜት መፍጠር የምትችለው ለራስህ ባለህ የአስፈላጊነት ስሜት ደረጃ ነው፡፡ የአንተ ዋጋ መተመኛ ራስህ ነህ። የራስህን ዋጋ አራክሰህ ከተገኘህ በውድ የሚገዛህ የለም፡፡ ሌሎች ዋጋ እንዲሰጡህ ከፈለግህ አንተ ጋር ያለውን አታርክስ፡፡ አንተ ያረከስከውን አንተን ሌላው በውድ የመግዛት ግዴታ የለበትም፡፡ ለአንተ ከአንተ በላይ አስፈላጊ ሰው የለም። አሁን አጠገብህ ካሉት ሰዎች መካከል ለአንተ በጣም አስፈላጊ ሊሆን የሚችለው የመጀመሪያው ሰው አንተ ነህ፡፡
153 views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 16:42:48 ህይወት አዙሪት ናት

ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህ የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው።
ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ጥርሱን በረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ።

ዘመንም ተምኔታዊ ነው መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም በሉ ይመጣብሀል ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ።

ህይወት አዙሪት ናት፡ መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው የጀመርክበትን አትናቀው ትጨርስበታለህና ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር ነገ ህዝብ ብትበታትን ተሹመህ በህዝብ ላይ ብትሰለጥን ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው።

ባለማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሔድም በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅት ትጨርሳለህ በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ
ህይወት መጀመሪያዋ እና መጨረሻዋ አንድ ነው ርቀህ የሔድክ ቢመስልህም ትልቅ ክብ ሰርተህ ትመለሳለህ።

@positivethinkingquoteset
170 views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 08:23:00 በህይወታችን የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት ጥረት ስናደርግ ችግሮችን ሊገጥመን ይችላል።

ሆኖም ፈተናዎችን መጥላት ሳይሆን ፊት ለፊት መጋፈጥ ጀግንነት ነው።

ፈተናዎች ተመጣጣኝ የሆኑ ብሎም የተሻሉ መልካም እድሎችን ይዘው እንደሚመጡ ስናምን ተስፋ መቁረጥ የሚባል ነገር ድራሹ ይጠፋል።


መልካሙን ሁሉ ተመኘን!
206 views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 11:01:21 የምትናገረውን ነገር አስተውል...???
አልችልም አትበል ⇄የሚያስችልህ ጌታ እያለ!!!
ከብዶኛል አትበል ⇄ በተሸነፈ አለም ላይ እየኖርክ!!!
ደክሞኛል አትበል ⇄እንደዛ ለሚሉ ህይወት ታደክማለችና!!!
ዛሬ ቀኑ ያስጠላል አትበል ⇄ ይልቅስ ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው ብለህ ቀንህን አሳምረው!!
ተስፋ አትቁረጥ ⇄ተስፋን የሰጠህ የታመነ ነውና!!
ስለዚህ እንደዚህ በል
በእኔ ዘመን መልካሙን አያለው
ፈጣሪ አብሮኝ እያለ አንገቴን አልደፋም ፤ አልፈራም ፤ አልደነግጥም ፤
ሀይልን በሚሰጠኝ በፈጣሪ አንዳንዱን አይደለም ሁሉን አዎ ሁሉን እችላለው በል!!!!!

መልካም ቀን
300 views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 07:51:19 #ምርጡን_ዘር_ዝራ

ውብ መናፈሻ ለመስራት ያገኘኸውን ዘር ሁሉ አትዘራም፡፡ አዎ! መጀመሪያ የምትፈልገውን የአበባ አይነት ትለያለህ፡፡ ቀጥሎ ዘሩን ትመርጣለህ፡፡ አበባው እንዲያብብ ትክክለኛውን መመሪያ በመከተል ትንከባከበዋለህ፡፡

ዘር ዘርተህ ለተወሰኑ ጊዜያት ምን እንደሚሆን ምንም መረጃ አይኖርህም፡፡ ነገር ግን ከተንከባከብከው እንደሚያፈራ ታውቃለህ፡፡

የዚህን ተመሳሳይ አመለካከት ለአእምሮህ አስተዋውቀው፡፡

አሉታዊ ልምዶች ካንተ ጋር ከርመዋል፡፡ አዎንታዊ አስተሳሰብ መስራት ይጀምራል፡፡ ግን ልክ እንደ ዘሩ ለመጽደቅ የተወሰነ ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ ውጤታማና አዎንታዊ አስተሳሰብ ይዘህ ተጓዝ፡፡ ቀስ በቀስ የአዲሱን አስተሳሰብ መስመር ማንጸባረቅ ትጀምራለህ፡፡

ሁልጊዜም ያለማቋረጥ ምርጡን ዘር መዝራትህን ቀጥል።



መልካም ቀን
265 views04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 09:08:15 የምትወደውን ሰዉ ስታይ ፈገግ በል #እንደምትወደው ይረዳል
ጠላትህንም ስታገኝ ፈገግ በል #ጥንካሬህን ይመለከታል ፡፡
ጥሎህ የሄደን ሰዉ ስታገኝም ፈገግ በል #ፀፀት ይሰማዋል ፡፡
የማታቀዉንም ሰዉ ስታገኝ ፈገግ በል #ሰላም ያስገኝሀል ፡፡
አዚ ገፅ ላይ የተለጠፉትን ነገሮችም ስታይ ፈገግ በል #አይቆጥርብህም እኮ ፡፡

#ሁል_ግዜ_ፈገግ_በሉ



ውብ ቀን
244 views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 08:35:58 ራእያችሁን ሁሉም ሰው ይገነዘበኛል ብላችሁ አትጠብቁ!

በእናንተ ውስጥ ያለውን ራእይ (Vision)፣ ዓላማ (Purpose) እና የውስጥ ጥማት (Passion) ሌሎች ሰዎች ከተገነዘቧችሁ ጥሩ ነው፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው ይገነዘበኛል ብላችሁ አትጠብቁ፡፡

አንዳንድ ጊዜ ከልጅነት ጀምሮ የሚያውቋችሁ ወላጆቻችሁ፣ አብሯችሁ ውሎ የሚያድር የትዳር አጋራችሁና ሁሉ ነገሬን ነግሬያቸዋለሁ የምትሏቸው የቅርብ ጓደኞቻችሁ እንኳን ውስጣችሁ የሚያየውን ነገር በእናንተ መልኩ አያዩትም፡፡

ሰዎች እናንተን አለመገንዘባቸው፣ አለመደገፋቸውና አንድ አንድ ጊዜም መቃወማቸው ተስፋ እንዳያስቆርጣችሁ ከፈለጋችሁ ይህንን እውነት መገንዘብና መቀበል የግድ ነው፡፡

ማንም ሰው ከሚያውቃችሁ ይልቅ ራሳችሁን ታውቃላችሁ፡፡ ከማንም ሰው ጋር ከምታሳልፉት ጊዜ ይልቅ ከራሳችሁ ጋር ታሳልፋላችሁ፡፡ ከማንም ሰው ጋር ከምትነጋገሩት በበለጠ ሁኔታ ከራሳችሁ ጋር ትነጋገራላችሁ፡፡ የትኛውም ሃሳባችሁ፣ ራእያችሁም ሆነ ዓላማችሁ የተጀመረው እናንተው ውስጥ ነው፡፡

በሉ እንግዲህ ከሁሉም በፊት ከራሳችሁ ጋር ተስማሙ! ራሳችሁን እወቁ! ራሳችሁን ተገንዘቡ! የምትፈልጉትን እወቁ! የሌላውን ሰው ድጋፍ ካገኛችሁ ደግሞ ጥሩ ምርቃት ነው፡፡

ይህ እውነት ሲገባችሁ የሰዎችን ድጋፍ እንደ መብት ሳይሆን እንደ እድል በመቁጠር አመስጋኞች ትሆናላችሁ፡፡ ሰዎች እናንተን ያለመገንዘባቸው ሁኔታ ደግሞ እንደመብታቸው በመቁጠር እናንተ ግን ወደታያችሁ እውነት ትገሰግሳላችሁ፡፡
302 views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 09:50:13 ፍራቻ!

"በአጽንኦት የምታስበው ማንኛውም ሀሳብ፣ ብታምነውም ብትፈራውም፣ ወደ ውጤት መቀየሩ አይቀርም!"

ምን የምትፈራው ነገር አለ? ሕልምህን እንዳታሳካ ምን የሚያስፈራህ ነገር አለ? ራስህን ለመቀየር ስታስብ ምን ያስፈራሀል? በሕይወታችሁ ምን የሚያስፈራችሁ ነገር አለ?

ፍራቻን በትክክል ካልተረዳኸው፣ ሕልምህን ሊገድለው ይችላል። ፈጣሪ ትልቅ ሕልም ለማለም ብቻ ሳይሆን፣ ለማሳካትም ጭምር የሚያስችልህን በቂ አቅምና ችሎታ ሰጥቶሀል። ነገር ግን ብዙ ሰው ትልቅ ሕልሙን ስለማሳካት ሲያስብ፣ አቅምና ችሎታ እንዳያንሰው ይፈራል። አብዛኛው ሰው በአዕምሮው ስለ ትልቅ ሕልሙ ሲያስብ፣ በልቡ እምነት ሳይሆን ፍራቻ ነው የሚፈጠረው። ብዙ ሰዎች "ሕልሜን ለማሳካት መሥዋዕትነት ከከፈልኩ በኋላ፣ ሕልሜ ባይሳካስ? ከአቅሜ በላይ ቢሆንስ? ወዳጆቼ ባይረዱኝስ? ገንዘቡ ቢጎድለኝስ? ዕውቀትና ልምድ ቢያንሰኝስ? ጊዜ ባጣስ? ብከስርስ?.....ብለው አቅማቸውን በመጠራጠር ፍርሀት ውስጥ ይገባሉ። እንደዚህ አይነት ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ በመጠየቅ በውስጣቸው ፍራቻ ሲነግስ፣ ሕልማቸውን በእምነት ማሳካቱን ትተው፣ በፍራቻ መሸሽ ይጀምራሉ።
ትልቅ ሕልም ስታምነው የሚጠጋህ፣ ስትፈራው ደግሞ የሚሸሽህ ነው። ስለዚህ ትልቁን ሕልምህን ከፍራቻህ የተነሳ እያባረርክ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብህ።

357 views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 09:48:20 ያንሱብናል

ሰው መሆን እየበለጠ~ ዘርና ሀረግ የሚመዙ
አንድ ጫማ ሲቀይሩ ~እወቁልኝ የሚነዙ
አንድ ብርሌ ሲጠጡ ~አንድ ሺ ቃል ሚወጣቸው
የጭንቅላታቸው ማነስ~ በልብስ ያልደመቀላቸው
ያንሱብናል ከሰውነት
ያንሱብናል ከሰው ሚዛን....
ያንሱብናል ከሰው ልኬት
በኪሳቸው ረብጣ ልክ~ የገዘፉ የሚመስላቸው
በቃል ማቁሰል የሚወዱ ~የድሀ እንባ ሚያኖራቸው
ለሰላምታ የተዘረጋን ~እጅ ቆርጠው የሚጥሉ
በጋለሞታ ፈገግታ- ሰይፎቻቸውን የሳሉ
በሌሎች መንገድ ላይ ቆመው ~
እንቅፋት ሆነው ሚጥሉ
ሀገር ስንል መንደር ጠርተው ~
በቤት ቁጥር የሚያፋጁ
በይቅርታ ስንመለስ ~አዲስ ጠብ የሚያበጃጁ
ዛሬን አልፈን ስለነገ አሀዱማለት ስንጀምር
ባለፈ የዘመን ተረክ~በጥላቻ መስተፋቅር
መንገዱን በእሾህ ተብትበው አናሳልፍ ያሉን ሁሉ
እንዲያ ባይሆንም ሀቁ~ ኢትዮጵያዊ የመሆን ውሉ
ያንሱብናል ከሀገሬ አፈር~
ያንሱብናል ከሰው ፍቅር
ያንሱብናል ከሰው ክብር
ያንሱብናል!

@positivethinkingquoteset
251 views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ