Get Mystery Box with random crypto!

ህይወት አዙሪት ናት ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህ የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው። ራቁትክን ት | መልካም አስተሳሰብ ™

ህይወት አዙሪት ናት

ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህ የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው።
ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ጥርሱን በረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ።

ዘመንም ተምኔታዊ ነው መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም በሉ ይመጣብሀል ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ።

ህይወት አዙሪት ናት፡ መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው የጀመርክበትን አትናቀው ትጨርስበታለህና ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር ነገ ህዝብ ብትበታትን ተሹመህ በህዝብ ላይ ብትሰለጥን ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው።

ባለማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሔድም በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅት ትጨርሳለህ በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ
ህይወት መጀመሪያዋ እና መጨረሻዋ አንድ ነው ርቀህ የሔድክ ቢመስልህም ትልቅ ክብ ሰርተህ ትመለሳለህ።

@positivethinkingquoteset