Get Mystery Box with random crypto!

ሰዎች ስለአንተ የሚኖራቸው ግምት አንተ ስለራስህ ከሚኖርህ የራስ ግምት የሚነሳ ነው፡፡ ሰዎች ስለአ | መልካም አስተሳሰብ ™

ሰዎች ስለአንተ የሚኖራቸው ግምት አንተ ስለራስህ ከሚኖርህ የራስ ግምት የሚነሳ ነው፡፡ ሰዎች ስለአንተ የሚፈጥሩት ግምት በሀዘኔታ፣ በፍቅር ወይም በተመሳሳይ ስሜት የተነሳ እንዳይመስልህ፡፡ ሰዎች ላይ የአስፈላጊነት ስሜት መፍጠር የምትችለው ለራስህ ባለህ የአስፈላጊነት ስሜት ደረጃ ነው፡፡ የአንተ ዋጋ መተመኛ ራስህ ነህ። የራስህን ዋጋ አራክሰህ ከተገኘህ በውድ የሚገዛህ የለም፡፡ ሌሎች ዋጋ እንዲሰጡህ ከፈለግህ አንተ ጋር ያለውን አታርክስ፡፡ አንተ ያረከስከውን አንተን ሌላው በውድ የመግዛት ግዴታ የለበትም፡፡ ለአንተ ከአንተ በላይ አስፈላጊ ሰው የለም። አሁን አጠገብህ ካሉት ሰዎች መካከል ለአንተ በጣም አስፈላጊ ሊሆን የሚችለው የመጀመሪያው ሰው አንተ ነህ፡፡