2020-09-25 10:08:23
"አኃት አብያተ ክርስቲያናት" እና "አሐቲ ቤተክርስቲያን"
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
▬▬▬▬▬▬▬
ይህንን ጽሑፍ በተለያየ ምክንያት ለአቅመ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ያልደረሳችሁ ሰዎች እንድታነቡት አይመከርም!! ፅሑፉ ከተፃፈበት ዓላማ (intention) ውጪ እንደ ፍላጎትህ አድርገህ ማንበብ ነውር ነው!!
~
"አኃት አብተ ክርስቲያናት" ትርጉሙ ምን ማለት ነው!?
~
ምናልባት የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት የተማርን ሰዎች ይህንን ጥያቄ ሲጠየቅ በጣም ቀለል አድርገን "እንዴ! አኃት አብያተ ክርስቲያናት እማ ግብፅ፣ ሶርያ፣ አርመን፣ ሕንድ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ ናቸው፤ ይህንን ምን ጥያቄ ያስፈልገዋል!?" ልንል እንችላለን። ነገር ግን ከምር የእህትማማችነት ትርጉም ገብቶናል ወይ!?
~
አኃት የሚል ቃል በራሱ የግእዝ ቃል ሆኖ ትርጉሙም እህትማማቾች ማለት ነው። እንደሚታወቀው እህትማማቾች ሲባል መንትዮች ሊሆኑም ላይሆኑም የሚችሉ፣ በዕድሜ ሊበላለጡም ላይበላለጡም የሚችሉ፣ እኩል የሆነ መልክና ቁመና ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም የሚችል ነገር ግን የአንድ ደም ዘር ያላቸው፣ ከሌላው በፊት ቀድመው የሚተዋወቁ፣ ደግና ክፉውን አብረው በኖሩበት ጊዜ ያሳለፉ፣ የአንዷን እህት ደስታ ደስታቸው የሚያደርጉና ሕመምዋም ተጋርተው የሚታመሙ ማለት ነው። እውነተኞች እህትማማቾች አንዷ እህታቸው ሲቸግራት ችግርዋን ባላየ ባልሰማ የሚያልፉ ሲመቻት ደግሞ ልታይ ልታይ የሚሉና በደስታዋ ቀን የሚያኮርፉ አይደሉም።
~
የሆነ ሆኖ ሁልጊዜ ሸምድደንና አቀላጥፈን እንደምንናገረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እህቶች የሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግብፅ፣ ሶርያ፣ አርመን፣ ሕንድና በኋላም ኤርትራ ናቸው። እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ልደታቸው የተለያየ፣ አመጣጣቸው ለየቅል፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስትና ያልተቀበሉ ሲሆኑ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ከተቀበሉ በኋላ ግን # አንድ ዓይነት ዶግማ (Doctrine) ያላቸው ናቸው። ይህ ማለት ግን የቀኖና እና የሥርዓት ልዩነት የላቸውም ማለት አይደለም። እንደ አንዳንዶቹ አተረጓገም አኃት ማለት መንትዮች ብቻ ሳይሆን እንደተሰጣቸው ጸጋ መጠን ያላቸውን መክሊትና አቅም የሚጠቀሙ ናቸው።
~
በእህትማማችነት ኑሮ ውስጥ ብዙ ጸጋና መክሊት የሌላት እህት ብዙ ጸጋና መክሊት ላላት (ለተሰጣት) እህት ለምን ይህንን ነገር ተሰጠሽ?፣ ለምን ይሄንን ንዋይ ቅዱስ ትጠቀሚያለሽ?፣ በእኔ ዘንድ የሌለ ባንቺ ቤት እንዴት ሊኖር ይችላል? ልትላት አትችልም፤ ምክንያቱም ይህንን # ምቀኝነት_ነው ! የእውነተኛ እህትነት ጠባይም አይደለም። በተመሳሳይ መልኩም ብዙ ጸጋና መክሊት ያላት (የተሰጣት) እህት ብዙ ጸጋና መክሊት ለሌላት እህት ለምንድነው ይህንን ነገር የማታደርጊው?፣ ለምን ይሄንን ንዋይ ቅዱስ አትጠቀሚም?፣ በእኔ ዘንድ ያለ ጉዳይ ባንቺ ቤት እንዴት አይኖርም? ልትላት አትችልም። ምክንያቱም ይህንን # ትዕቢት_ነው! የእውነተኛ እህትነት ጠባይም አይደለም። ስለዚህ ሁሉም ተከባብረው አንዷ የአንዷን ጸጋ አክብራ ትኖራለች። ከዚህ በተጨማሪም አንዷ እህት ከቸገራት ሌሎች እህቶቿ ይረዷታል! በአከባቢዋ ካሉ ጎረቤቶቿ ይልቅ በሩቅ ያለች እህቷ ልትደርስላት ያስፈልጋል። የእህትማማቾቹ ልጆችም በደምብ ተዋውቀው ዝምድናቸውን አጠናክረው ሊያስቀጥሉና ሊተባበሩ ይገባል።
~
በዘመናችን እየታየ ያለው ሁኔታ ግን በጣም ያሳፍራል። አባቶቻችን በዓላማ ያደረጉት ቁምነገር እንደ ምናምንቴ ቆጥረን ለዓላማቸው "አኃት" ብለን ከመናገር የዘለለ ምንም ፋይዳ እንደሌለው እየተመለከትነው ነው። አብዛኞቻችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እናትነት ሥር ተጠልለን የምንገኝ ልጆች እንኳንስ የእናታችንን እህቶች አውቀን ለልጆቻቸው ራርተን እንደ ወንድሞቻችን ልናያቸው ይቅርና የአንዲት እናት ልጆች ሆነንም ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን መራራት አቅቶናል፤ ችግራቸው ችግራችን አድርገን መቀበል አልቻልንም፤ እየተገፉ፣ እየተጨነቁ፣ እየተሰቃዩና እየተገደሉ ያሉ ወንድምና እህቶቻችን የእናታችንን መለያ ሰንደቅ ስለያዙ መሆናቸው ገና አልገባንም፤ ያሳዝናል!
~
እንዴ! እየተገፋና እየተገደለ ያለው ወገንህ እኮ አንተ የምታመልከው አምላክ ስላመለከ ነው፤ አንተ የምታከብራቸው ቅዱሳን ስላከበረ ነው፤ አንተ በኩራት በአንገትህ ያሰርከው ማዕተብ ስላሰረ ነው። ሁልጊዜ ቅዱሳን አባቶቻችን ባስቀመጡት በዘወትር ጸሎታችን ላይ ከውስጣችን አምነን "ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት፤ ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን" እያልን እየጸለይን በተግባራችን ግን እየካድነው ነው፤ ፈጽመን አናምንም። "አሐቲ (አንዲት)" ማለት ምን ማለት ነው!? በአንድ አከባቢ ብቻ የተወሰነች ማለት ነው እንዴ!? ቤተክርስቲያናችን ዓለም አቀፋዊት (Catholic) ናት! በሁሉም ክፍላተ ዓለም ቁጥር ልክ መርበቦችዋ ዘርግታ የምትገኝ የእግዚአብሔር መርከብ ናት። እንዲህ በዝታ ተባዝታ እያለች አንዲት መባሏ ታድያ ምሥጢሩ ምንድን ነው!? ከተባለ መልሱ በየትም ትኑር የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ # አካል ስለሆነች ነው። እኛም በእናታችን ቤተክርስቲያን በኩል የክርስቶስ አካላት ሆነናል ማለት ነው።
~
ታድያ በዚህ ከተስማማን አንዲትና አካላችን ያልናት ቤተክርስቲያን ስትመታ የማናለቅሰው፣ ስትንቋሸሽ የማንሳቀቀው፣ ስትወረር የማንጮኸው ለምንድነው!?
# ምናልባት_ከኣካሏ_ተቆርጠ
ን_ወድቀን_ተለይተን_ይሆን_እንዴ !? ወይስ በአካላቶቿ እያለን ሽባ (paralysis) ሆነን ነው!? እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ!?
~
እናት ቤተክርስቲያን የኦሪት ታሪክ፣ የዘመነ ሐዋርያት ታሪክ፣ የዘመነ ሰማዕታት ታሪክ፣ የዘመነ መናፍቃን ታሪክ፣ የዘመነ ጻድቃን ታሪክ ብላ ያስተማረችን የታሪክ ተመራማሪዎችና አዋቂዎች ለመሆን ብቻ ነው እንዴ!? በህይወታችን እንድንኖረው አይደለም!? ታድያ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እሩቅ ካለችውና አካላችን ከሆነችው እህታችን ይልቅ በቅርብ ከምናውቃቸውና ከማይመስሉን ጎረቤቶቻችን የወገንነው!? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ይላል፦ "በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ
# አንድ_ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር
# አንድ_አምላክ የሁሉም አባት አለ።" ኤፌ.4፥4-6
~
እስኪ በሞቴ መልሱልኝ ልጠይቃችሁ! ማን ነው አሁን ስለ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ስማቸውና ታሪካቸው በዝርዝር አውቆ # በሶርያ በግፍ እየተጨፈጨፉና በረሃብ እያለቁ ያሉ ወገኖቹ (አካላቱ) የሚጨነቅ!? ማን ነው በግብፅ ስለታረዱት ኦርቶዶክሳውያን የሚገደው!? ማናችን ነን ስለ ኤርትራ፣ ስለ ህንድና ስለ አርመን ቤተክርስቲያን አስበን የምናውቀው!? ይቅርታ አድርጉልኝና ነገሩ አሰፋሁት መሰለኝ! ወደ እህቶቻችን አብያተ ክርስቲያናት ዘልዬ ገባሁ! ለካ በአንድ የቤተክርስቲያን መጠርያ ስም የምንጠራ አካላትም ተጨካክነናል! ለካ በሶማሌ ክልልና
# በሆሳዕና_ከተማ ላለችው የእኛው ቤተክርስቲያንም ማሰብ ትተናል! ለካ ከክልላችን ውጪ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በአፋር... ስላሉት አብያተ ክርስቲያናትም በፖለቲካው ጦስ ምክንያት ተቆራርጠናል! ያሳዝናል! ደግሞ እኮ አናፍርም ሁልጊዜ "ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን..." እያልን ነው የምንጸልየው! አንድ መሆኗ መቼ ነው ያመንነ
ው? "በሌላ ክልል ላይ ካለ
16.9K viewsአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ, 07:08