Get Mystery Box with random crypto!

መምህራችን ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው ሁለተኛ መልእክቱ ምዕራፍ 13 ውስጥ የጠቀሰልንን | አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝

መምህራችን ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው ሁለተኛ መልእክቱ ምዕራፍ 13 ውስጥ የጠቀሰልንን ሁልንም የፍቅር ዓይነቶች ተግባራዊ እናድርግ።

"ፍቅር ሁልን ይታገሳል፣" ሰዎችን ሁሉ በትዕግስት ቻል።

"ፍቅር አይቀናም፣" በሌሎች ላይ ላለመቅናት እንለማመድ።

"ፍቅር ራሱን አያስመካም፣" አንድ ሰው ሌሎች ሰዎች ሊያገኙት በሚችሉት ነገር ላይ ሊመካባቸው አይገባም።

"ፍቅር አይታበይም፣" እግዚአብሔር አምላክ ትዕቢተኞችን ስለሚቃውምና ለትሑታን ጸጋን ስለሚሰጥ ትዕቢት አደገኛ ማነቆ ነው።

"ፍቅር ክፉ ነገር አያሳስብም፥" ሰውን የሚወድ ሰው በክፋት አይናገርም በትሕትና እንጂ ልክ ጣፋጭ ውኃ እንደሚያመነጭ ንጽህ ምንጭ።

" ፍቅር ብቻየን ይድላኝ አይሰኝም፣" ሰዎች የሚወድ ሰው ራሱን ወዳድ አይደለም ሌሎችን ይወዳል እንጂ፡እርሱ ለእነርሱ መሥዋዕት ይሆናል ያለውን ሊሰጣቸውም ዝግጁ ነው ራስ ወዳድነት የብዙ ችግሮች ምክንያት ስለሆነ እርሱን ከእናንተ አርቁ።

"ፍቅር አይበሳጭም፣" ብስጭት(ቁጣ) የእግዚአብሔርን ጽድቅ ስለማይሰራ አትበሳጩ።

"ፍቅር ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፣" ሌሎች ሰዎችን የሚጎዳ ውድቀት አይመኝም። ሕሊናቸው ንጹህ ለሆኑ ሰዎች ሁሉም ነገር ንጹህ ነው። ንጹሓን ሰዎች ከራሳቸው ይልቅ ሌሎች ሰዎችን ያስቀዳማሉ።
"ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል ፣"ፍቅር ያለው ሰው ሰዎች ስኬት ወይም ሀብት ወይም ደስታ ወይም ልጆች ወይም በሌሎች እግዚአብሔር በሚሰጣቸው በረከቶች ይደሰታል ።ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ከምያለቅሱም ጋር አልቅሱ።"ሮሜ11፥15

"ፍቅር ሁሉን ይታገሳል ፣" ታጋሽ ሰው ለመሆን ተለማመድ። እጅግ ከባድ የተባሉ ስሕተቶች ላይ ብትወድቅም እንኳን ቁጣህ ፈጥና አትቀጣጠል የሰዎችን ፍቅርና ክብር ታጣለህና። ለመታገስ የሚቻለው ለማፍቀር ሲቻል ነው። ስለዚህ ሁሉንም ነገሮች ሁሉንም ሁኔታዎችና ሁሉንም ሰዎች ያለ ምንም ማማረር ታገሡ።

"ፍቅር ሁሉንም ያምናል፥" ፍቅር ቀላል ነው እንጂ አታላይ አይደለም ፍቅር ጠቢብና አርቆ አሳቢ ነው።ተስፋ የሚያደርገው ለሌሎች ሰዎች መልካምነት ነው ።

" ፍቅር በሁሉ ይጸናል ፣" ከእርሱ ጋር የሕይወት አክሊል ስለሚመጣ ትዕግስትን ተለማመድ። ሌሎች ሰዎችን መቻልም ተለማመድ እነዚህ ሰዎች ችግር ፈጣሪዎች ቢሆንም እንኳ ይህን ስታደርግም ትዕግስትህ መልካም ነገር እንደሚያሰገኝልህ በማወቅ ይሁን።

"ፍቅር ለዘላለም አይወድቅም ፥" የተለያዩ ፈተናዎችና መከራዎች ቢገጥሙም እውነተኛ ፍቅር ፈጽሞ አይወድቅም፡በማንኛውም ፈተና ፊት በጽናት ይቆማል እንጂ: -"ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና ፥........ብዙ ውኃ ፍቅርን ይጠፋት ዘንድ አይችልም ፈሳሾችም አያሰጥሟትም ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይንቁታል።"ምሳ 8፥6-7
#ጸሎት_ንሰሐና _ተምስጦ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
#አቡነ_ሺኖዳ_ሳልሳዊ