Get Mystery Box with random crypto!

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝

የቴሌግራም ቻናል አርማ popeshenoudaa — አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝
የቴሌግራም ቻናል አርማ popeshenoudaa — አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝
የሰርጥ አድራሻ: @popeshenoudaa
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 19.70K
የሰርጥ መግለጫ

"ትክክለኛው ቻናላችን ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኛ አይደሉም"
የአባታችን ብጽዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ትምርት የሚቀርቡበት መንፈሳዊ ገፅ ነው፡፡
"የንስሀ አባት ማለት እርሱን ስትመለከት እግዚአብሔርን እና ትዕዛዛቱን የምታስታውስበት
ሰው ማለት ነው።"
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
ለማንኛውም ሓሳብ እና አስተያየት
@RomareBot ይላኩልን፡፡

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2020-09-10 14:28:42 የተስፋ ቃላት

እኛ ዛሬ ወደፊት የምንኖርባት #የእግዚአብሔር ሀገር በተስፋ ዓይኖቻችን ልንመለከት እንጂ ይሁን ሁካታና ግርግር የበዛበት ዓለም ልንመለከት አይገባም።

ለእኛ በጣም አስቸጋሪ መስሎ የሚታየን ችግር #በእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ አሉትም። ማንኛውም የተዘጋ በር ለመክፈት በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ቁልፍ አንድ ብቻ ሳሆን ብዙ ቁልፎች ናቸው። በእንደዚህ ዓይነት መንገድ የተከፈተውን ማንም ሊዘጋው አይችልም ፡፡ ራዕ 3፥7።

ተስፋ ፍርሀትን ጭንቀትን ግራ መጋባትን በመከላከል ዕረፍትን ይሰጣል።ተስፋ ዕረፍትን ከመጠቱ በላይ በተስፋ ደስ እንዲለን ተነግሮናል። ሮሜ 12፡2

መጥፎውን ወደ በጎ መቀየር የሚቻለውን #የእግዚአብሔር አሠራር ሳትይዝ ወደ ችግሮችህ ብቻ አትመልከት።

#እግዚአብሔር ሁሉም አጋጣሚዎች እርሱ በወደድው መንገድ ማስኬድ ይቻለዋል።

በሰዎች ድካም ሊደረግ የማይቻለው ሁሉ #በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይቻላል። የሰዎች ጥበብ ሊወጣው ያልቻለውንም #የእግዚአብሔር ጥበብ ያመጣዋል።

ምንጊዜም በመለከታዊ ዕርዳታ የተከበብክ ስለሆንህ ብቻህን ላለመሆንህ እርግጠኛ ሁን፡፡
የሰማያት ወዳጆቻችንና ቅዱሳን ሁሉ በአንተ ዙርያ ሁነው ስለ አንተ እንደሚማልዱም እወቅ።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
የተስፋ ሕይወት ከሚለው መጽሐፋቸው
16.8K viewsአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ, 11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-05 10:02:02 አባቶቻችን እንዲህ አሉ +
በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት እኩል ናቸው - #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
በሃይማኖት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ከጠየቃችሁኝ አንደኛው ትሕትና ሲሆን ሁለተኛውም ትሕትና ነው:: ሦስተኛው ደግሞ ትሕትና ነው - #ቅዱስ_አውግስጢኖስ
ሕይወታችን ለሌሎች የሚያበራ ቢሆን ኖሮ ስብከት ባላስፈለገ ነበር:: በምግባራችን መመስከር የምንችል ብንሆን ኖሮ ቃላት ባላስፈለጉ ነበር:: እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ኖሮ አረማውያን ባልበዙ ነበር - #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ሰዎች ወደ ተራሮች ከፍታ ይወጣሉ ወደ ኃይለኛው የባሕር ሞገድና ወደ ውቅያኖስ ስፍሐት ይቀዝፋሉ : የከዋክብትን ክበባዊ ዑደት ያደንቃሉ [ግሩምና ድንቅ የሆኖ የተፈጠረ] ሰውነታቸውን ግን ሳያደንቁ ያልፉታል:: -
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ
"ጌታ ሆይ ክርስቲያን አድርገኝ ክርስቲያን ሆኜ ልኑር ክርስቲያን ሆኜ ልሙት ዳግም ልትፈርድ ስትመጣም ክርስቲያን ሆኜ ልገኝ" #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
Deacon Henok Haile
22.9K viewsአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ, 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ