Get Mystery Box with random crypto!

​ መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ ' #እግዚአብሔር በደስታ የ | አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝

​ መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ " #እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና ።" /2ቆሮ 9*7 / እንዲል ። #እግዚአብሔር የምትሰጠውን ገንዘብ ሳይሆን የመጀመሪያውን ፍሬ እና #ቃል_ኪዳን የሆነውን ከማዕረጎች ሁሉ የሚልቀውንና ያለ ነቀፋ በነፃነት የሚሰጠውን #ፍቅር_ከአንተ_ይጠብቃል ።

ፍቅር #የመንፈስ_ቅዱስ የመጀመርያ ፍሬ ነው ። ስለዚህ ጌታ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን በነቀፋ ንሥሓም እንዲገባ በጠራው ጊዜ ነቀፋውን የተወሰነ ኃጢአትን በመግለጽ ሳይሆን በአንድ ሐረግ አጠቃልሎ " ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና ። " / ራዕ 2*4 / በማለት ነው ።
እግዚአብሔር ይህንን ፍቅር ይፈልጋል ስለዚህ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ ።" / ምሳ 23*26 / አለ ። #ትእዛዙን_መፈጸም_የፍቅር_ተፈጥሮአዊ_ፍሬ_ነው ።

ውጪያዊ የንሥሓ ሕይወት ብቻ የሚኖሩ ነገር ግን ውስጣዊ ፍቅር የሌላቸው ይወድቃሉ ። ምክንያቱም ሥራዎቻቸውና #ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ፍቅር የጎደለው ነውና ።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት ? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ " ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ፣ ታላቂቱና ፊተኛይቱ #ትእዛዝ_ይህች_ናት ። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርሷም ባልጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትል ናት ። ኦሪትና ነቢያት በነዚህ በሁለቱም ትእዛዛት ጸኑ ። " / ማቴ 22*36-40/ የሚል ነበር ።

በዚያን ቀን ብዙዎቹ " ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም በስምህ አጋንንት አላወጣንም ...? " /ማቴ7*22/ ይሉታል ። ነገር ግን እርሱ ይህን ሁሉ ትቶ በውስጣቸው ስላለው ፍቅር ይጠይቃቸዋል ።
ይህ የተአምራት እና የስጦታዎች ችግር አይደለም ፣ ባሏቸው በተሰጡአቸው ስጦታዎች የተነሳ የሚጠፉ ብዙዎች ናቸውና ። ለዚያ ነው ሐዋርያት ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ባወሩ ጊዜ ሁሉ ይህንን ከሁሉ ይልቅ በተሻለ መንገድ አብራርተውታል ።

#አብነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ