Get Mystery Box with random crypto!

​ ​መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ 'እግዚአብሔር በደስታ የሚ | አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝

​ ​መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ "እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና።" /2ቆሮ 9፥7/ እንዲል። #እግዚአብሔር የምትሰጠውን ገንዘብ ሳይሆን የመጀመሪያውን ፍሬ እና ቃል ኪዳን የሆነውን ከማዕረጎች ሁሉ የሚልቀውንና ያለ ነቀፋ በነፃነት የሚሰጠውን ፍቅር ከአንተ ይጠብቃል።

ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ የመጀመርያ ፍሬ ነው። ስለዚህ ጌታ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን በነቀፋ ንሥሓም እንዲገባ በጠራው ጊዜ ነቀፋውን የተወሰነ ኃጢአትን በመግለጽ ሳይሆን በአንድ ሐረግ አጠቃልሎ "ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።" /ራዕ 2፥4/ በማለት ነው።

#እግዚአብሔር ይህንን ፍቅር ይፈልጋል ስለዚህ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።" /ምሳ 23፥26/ አለ። ትእዛዙን መፈጸም የፍቅር ተፈጥሮአዊ ፍሬ ነው።

ውጪያዊ የንሥሓ ሕይወት ብቻ የሚኖሩ ነገር ግን ውስጣዊ ፍቅር የሌላቸው ይወድቃሉ። ምክንያቱም ሥራዎቻቸውና #ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ፍቅር የጎደለው ነውና።
#መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ "ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፣ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርሷም ባልጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትል ናት። ኦሪትና ነቢያት በነዚህ በሁለቱም ትእዛዛት ጸኑ።" /ማቴ 22፥36-40/ የሚል ነበር።

በዚያን ቀን ብዙዎቹ "ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም በስምህ አጋንንት አላወጣንም?" /ማቴ7፥22/ ይሉታል። ነገር ግን እርሱ ይህን ሁሉ ትቶ በውስጣቸው ስላለው ፍቅር ይጠይቃቸዋል።

ይህ የተአምራት እና የስጦታዎች ችግር አይደለም፣ ባሏቸው በተሰጡአቸው ስጦታዎች የተነሳ የሚጠፉ ብዙዎች ናቸውና። ለዚያ ነው ሐዋርያት ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ባወሩ ጊዜ ሁሉ ይህንን ከሁሉ ይልቅ በተሻለ መንገድ አብራርተውታል።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ