Get Mystery Box with random crypto!

​​ በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ #እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !! #እግዚአብሔርን ከወ | አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝

​​ በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ #እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !!

#እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ ። አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል ። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና ። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው ።

በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ ። ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው ።

በጸሎት ውስጥ በመትጋት በጸሎታችሁ ውስጥ ወደ ምትናገሩት ወደ እያንዳንዱ ቃል ጥልቀት ልትደርሱ ትችላላችሁ ። ከዚህ በተጨማሪ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ወደ #እግዚአብሔር እየተጠጋችሁ ትመጣላችሁ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም ትናፍቃላችሁ ። ስለሆነም ጸሎት እንዴት #እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለባችሁ ያስተምራችሗል ።
እንዲህ ባለ ጠባይ በጸሎታችሁ ውስጥ #ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ አንደበታችሁ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ እየለመደ ይመጣል ። ይህ ደግሞ አዲስ ቋንቋ መማር የሚፈልግ ሰው ይመስላል ። ይህ ሰው ይህን ቋንቋ በሚገባ ባያውቅና መጀመርያ ላይ ቢሳሳትም እንኳ ይህን ቋንቋ መናገር አለበት ። ብዙ ጊዜ በመደጋገም ግን አንደበቱ ቋንቋውን ይለማመደዋል በሚገባ እስከሚጠቀምበት ድረስም ቀላል እየሆነለት ይመጣል ።

በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ #ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል ። ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ ።

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ