Get Mystery Box with random crypto!

†እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ራሱን በራሱ ያጎሳቁል ለነበረው ወጣት ያደረገችው ተአምርና የሰ | አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝

†እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ራሱን በራሱ ያጎሳቁል ለነበረው ወጣት ያደረገችው ተአምርና የሰጠችው ምክር †

ራስን በራስ ማጎሳቆል የዚህ ዘመን ትልቁ ፈተና ነው፡፡ ብዙ ወጣቶች በዚህ ሱስ ይያዛሉ፡፡ ወደ ትዳር ገብተው ራሱ ከዚህ ሱስ መውጣት አቅቷቸው ከትዳር አጋራቸው ጋር የተገባ ሩካቤን የማይፈጽሙ ቊጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች ንስሓ መግባት ራሱ ያሳፍራቸዋል፡፡

እስኪ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ክሪሶስቶሞስ (አፈ ወርቅ) የተባሉ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ራሱን በራሱ ያጎሳቁል (Masturbate ያደርግ) ስለ ነበረ አንድ በዓሥራዎቹ ዕድሜ ስለሚገኝ ወጣት የጻፉትን ላካፍላችሁ፡-

“አንድ ወጣት አንድ ጊዜ የሚከተለውን ነገረኝ፡፡ በዓሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያለ ለስፖርቶች በተለይም ለትግል ልዩ ፍላጎት ነበረው፡፡ ወደ ዓሥራ አምስት ዓመቱ ገደማም አንድ የቡድን ጓደኛው ራስን ስለ መበደል ኃጢአት አስተዋወቀው፡፡ ከማፈሩ የተነሣም ንስሓ አልገባም ነበር፡፡ አንድ ቀንም ከአንድ ወር በኋላ ከታላቅ ወንድሙ ጋር እየታገሉ እያለ በወንድሙ ደረት ላይ ዘፍ ብሎ ወደቀ፡፡ መተንፈስ አልቻለም፡፡ ሞተ፡፡

“በዚህ ውስጥ ኾኖም የገዛ አስከሬኑን፣ ወንድሙና እናቱ ተደናግጠው እርሱን ለመርዳት ሲሯሯጡ፣ ነፍሱ ደግሞ በጠባቂ መልአኳ ታጅባ ከቤቱ ስትወጣ፣ ከሚኖርበት ከተማም እጅግ ከፍ ብላ በመጨረሻም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ስትኼድ ይመለከት ነበር፡፡ ከዚያም ጥልቅ በኾነ ጨለማ ውስጥ ራሱን አገኘው፡፡ ከዚያ አልፎም መጨረሻ ላይ ብርሃንንና ገነትን ተመለከተ፡፡

“ወደዚህ ብርሃን እንደ ገባም ወላዲተ አምላክን አያትና ጠባቂ መልአኩን ለምን እንደ አመጣው ጠየቀችው፡፡ መልአኩም የልጁን አሟሟት በዝርዝር ነገራት፡፡ በዚህ ጊዜ እመቤታችን ለዚያ ልጅ ‘ትድንላት ዘንድ እናትህ አጥብቃ እየለመነቺኝ ነው፤ ልጄም ጸሎቷን ሰምቷል” አለቺው፡፡ ያ ልጅ ግን በገነት ውበት ስለ ተማረከ በዚህ ይቆይ ዘንድ ለመናት፡፡ ወላዲተ አምላክ ግን ‘አይኾንም' አለቺው፡፡ ‘ለእናትህ ስትል መመለስ አለብህ፡፡ ነገር ግን አድምጠኝ፡- ከአንድ ወር በፊት ስለ ሠራኸው ኃጢአት ልትናዘዝ ይገባል፡፡ ይህ እጅግ አስጸያፊ ኃጢአት ነው፡፡ ይህን ለካህን ካልተናዘዝክ፥ ምን እንደሚያገኝህ ተመልከት፡፡' ከዚህ በኋላ ወላዲተ አምላክ የሲዖል ሥቃይ ምን እንደሚመስል እንዲያሳየው ለቅዱስ ሚካኤል አዘዘችው፡፡ የሚመለከተው ነገር እጅግ የሚያስፈራ ከመኾኑ የተነሣ፥ ልጁ ራሱን እስከ መሳት ደረሰ፡፡

“ከዚያ በኋላም ወደ ጥልቁ ጨለማ፣ ቀጥሎም ወደ ሰማያት፣ ዝቅ ብሎም ይኖርበት ወደ ነበረ ከተማ - ወደ መኖሪያ ቤቱ - ቤተሰቦቹ አስከሬኑን ከብበው ወደሚያለቅሱበት ክፍል ወረደ፡፡ በሰውነቱ ላይ ከፍተኛ የኾነ መጫጫን ከተሰማው በኋላም ነፍሱ ወደ ቦታዋ ተመለሰች፤ ዓይኖቹንም ከፈተ፡፡ ከዚያም የኾነውንና የተመለከተውን ኹሉ ለቤተሰቦቹ ነገራቸው፡፡ በኀዘን ተጎድታ የነበረችው እናቱም ይህን በሰማች ጊዜ እመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ ስላማለደቻት አመሰገነቻት፡፡ እጅግ እያለቀሰችም ልጇን ዕቅፍ አድርጋ ሳመችው፡፡”

ፈጣኗ ደመና ወላዲተ አምላክ በዚህ ሱስ ውስጥ ያሉትን ኹሉ ከዚህ በደል ይወጡ ዘንድ ትድረስላቸው፡፡