Get Mystery Box with random crypto!

#እግዚአብሔርን_ተስፋ_አድርግ ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ #እግዚአብሔርም | አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝

#እግዚአብሔርን_ተስፋ_አድርግ

ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ #እግዚአብሔርም በፍጥረታቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር በዝምታ ይሠራል። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው #የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሰራ አድርገው ያስባሉ። እነርሱ #እግዚአብሔር አይሰራም በሚያስቡበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ በጥልቅ እየሰራ ነው። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ #የእግዚአብሔርን ሥራና የስራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይነቻቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል።" #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፡፡" መዝ 26 ፥ 14።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ