Get Mystery Box with random crypto!

የርኩሳን መናፍስት ስብስብ በሰይጣን የሚመሩት ርኩሳን መናፍስት ንስሓ በገቡትና በአማኞች ላይ ስለ | አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝

የርኩሳን መናፍስት ስብስብ

በሰይጣን የሚመሩት ርኩሳን መናፍስት ንስሓ በገቡትና በአማኞች ላይ ስለሚከፍቱት ውጊያ ዕቅድ ለማውጣት ይወያዩ ዘንድ ጉባኤ ተቀመጡ ። በዚህ ጊዜ ሊቀ መንበሩ አማኞችን ሊያጠፋ የሚያስችል እጅግ አዲስ ዕቅድ እንዲያቀርቡ አባላቱን ጠየቀ ።

አንደኛው ርኩስ መንፈስ እንዲህ አለ : " #የእግዚአብሔርን ሕልውና እንዲጠራጠሩ እናድርጋቸው ። "

ሁለተኛው " መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጠራጠሩ እናድርጋለው ። " አለ ።

ሌላኛው ደግሞ " ዘላለማዊነትን እንዲጠራጠሩ እናድርጋቸው ። " አለ ።

አራተኛው " በምኞትና በፈተናዎች እናታላቸው ። " ብሎ ተናገረ ።
እነዚህን የሚሙስሉ አሳቦች ከየአቅጣጫው መወርወራቸው ይቀጥል እንጅ ሊቀ መንበሩን አንዱንም አሳብ ሊያጸድቅ አልፈለገም ፤ ሁሉም የቆዩና ከዚህ በፊት #የተጠቀሙባቸው_ዕቅዶች_ነበሩና ። ሁሉም እርግጠኛ የሆኑ ውጤቶች ሊያቀርቡ ስላልቻሉ ብዙ ሰዎች ከእነርሱ እያመለጡ ወደ እምነት ጎራ መግባት ቻሉ ።

አንድ የሚሻል ልምድ ያለው ርኩስ መንፈስ የሰው ልጆችን ሊያጠፋ የሚችል አንድ አዲስ እና ስኬታማ ዕቅድ ለማዘጋጀት ኃላፊነቱን ከወሰደ በኋላ እንዲህ በማለት ተናገረ ፦ " ስለ #እግዚአብሔር ሕልውና ፤ ስለ መጨረሻው ፍርድ እውነትነት ፤ ስለ ዘላለማዊው ቅጣት ፤ ስለ ገነትና ስለ ሲዖል መኖር መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር ሁሉ ትክክለኛ እና እውነት መሆኑን አጉልተን እናሳያቸው ። ከዚህ በተጨማሪ ንስሓ አስፈላጊና መቅረት የማይገባው ጉዳይ መሆኑንም እናሳያቸው ..." በዚህ ጊዜ እያንዳንዱ ርኩስ መንፈስ እጅግ በቁጣ ተሞልቶ ንግግሩን ከመጨረሱ በፊት አቋረጡትና ዕቅዱን በውግዘት ውድቅ አደረጉበት ። ተቃውሞአቸው እጅግ መራር ነበር ።
በዚህ ጊዜ ሊቀ መንበሩ ርኩስ መንፈሱ እቅዱን ገልጾ እስኪጨርስ ድረስ እንዲረጋጉ ምልክት ሰጣቸው ።

ይህን ተንኮል አዘል አሳብ ያቀደው ርኩስ መንፍስ ንግግሩን እንዲህ በማለት ቀጠለ ፦ " እነዚህን ነገሮች በሙሉ ለሰው ልጆች እጅግ አጉልተን ስናሳያቸው ከእኛ ጋር ተደላድለው መኖር ይጀምራሉ ፤ በምክራችንም ይታመናሉ ። በዚህ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ንስሓ የሚያደርሷቸውን ቀና እርምጃዎች መራመድ ሲጀምሩ ንስሐቸውን ለጥቂት ጊዜ ምናልባትም እስከ ነገ ድረስ እንዲያቆዩት እናድርጋቸው ። ይህን የምናደርገውም ኃጢአትን እስከሚሰናበቱትና ፍላጎታቸውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያረኩ ነው ። በዚህ መንገድ ንስሓ ለመግባት ከተዘጋጁ በኋላ እስከ ነገ ድረስ እናቆየው እያሉ ይቆያሉ ። በመጨረሻም ቀናቶቻቸው ስለሚጠናቀቁ ንስሓ የመግባት ዕድሉን ከነጭራሹ ያጡታል ። "

እያንዳንዳቸው ብድግ ብለው ርኩሱ ጥበቡን በማድነቅ አጨበጨቡለት ። ታውቃላችሁ? ! ከዚያን ጊዜ በኋላ ሰዎች በቡድንም ሆነ በነጠላ በኃጢአት መውደቅ ስለ ጀመሩ መጨረሻ ወደሌለው ጥልቅ ጉድጓድ ይወድቁ ጀመር ። ይህ ሊደርስባቸው የቻለውም #በእግዚአብሔርና በመጽሐፍ ቅዱስ ወይም በዘላለማዊነት ስላላመኑ አይደለም #ንስሓ_የመግባት_ዕድሉን_ካገኙት_በኋላ_ለነገ_በማለት_ስላዘገዩት_እንጂ ።

ወንድሜ ሆይ ፦ እንዲህ ያለውን አጭበርባሪ ወጥመድና አረመኔያዊ ብልጠት ተጠንቀቀው!! " ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ. .." [ዕብ 4*7 ] የሚለውን የመጽመፍ ቅዱስ ቃል በውስጥህ ሸሽግ ።
አንተ ዛሬ ልትሞት ስለምትችል ንስሓህን እስከ ነገ ድረስ አታዘግየው ።
ወይም ደግሞ ነገ ሊመጣ ቢችልም ባተሌ ልትሆንና ብዛት ባላቸው ነገሮች ልትወጠር ትችላለህ ። ወይም ደግሞ ነገ ልብህ ሊደነድንና የመንፈስን አነሳሽነት ልታጣው ትችላለህ ።
ለንስሓ እጅግ ተመራጩ ጊዜ አሁን ነው ፦ " በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳን ቀን ረዳሁህ ይላልና ፤ እነሆ ፦ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው እነሆ ፦ የመዳን ቀን አሁን ነው ። " [ 2ኛ ቆሮ 6*2]

ንስሓ ትገባ ዘንድ #እግዚአብሔር አምላክ ጸጋውን ያድልህ ።
አባት ዘካርያስ ቡትሮስ እንደጻፉት

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ