Get Mystery Box with random crypto!

👉 ᴘʀᴏᴍɪsᴇ 👑

የቴሌግራም ቻናል አርማ pick_model — 👉 ᴘʀᴏᴍɪsᴇ 👑
የቴሌግራም ቻናል አርማ pick_model — 👉 ᴘʀᴏᴍɪsᴇ 👑
የሰርጥ አድራሻ: @pick_model
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.04K
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
▬▬ ▬▬ஜ۩۞۩ஜ▬▬ ▬▬
𝐈𝐍 ᴛʜɪs 𝐆𝐑𝐎𝐔𝐏 ᴜ 𝐂𝐀𝐍 ɢᴇᴛ
❆𝐌𝐄𝐌𝐄 ☻
❆𝐏𝐎𝐌𝐄༊
❆𝐌𝐔𝐒𝐈𝐂♬
❆𝐕𝐈𝐃𝐄𝐎▷
❆𝐃𝐀𝐍𝐂𝐄✦
♥ MOTIVATION ♠
𝐂𝐑𝐎𝐒𝐒&𝐀𝐃𝐌𝐈𝐍
۝ @KING_ERMI_AB ۝

GROUP @PROMISE_GROUP

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-17 06:53:32 #MoE

በቻይና ሀገር ትምህርታቸው ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ያቋረጡትን ትምህርት እንዲከታተሉ መፈቀዱ ይታወቃል።

ትላንትና ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠው አድራሻ እንደማይሰራ በርካታ የቤተሰባችን አባላት ገልፃችኃል።

የሚሞላው ፎርም ከላይ የተያያዘው ሲሆን በዚህ Email daddiketema@gmail.com, educationattache@ethiopianembassy.org.cn ነው የሚላከው።

መላክ የሚቻለው እጅግ ቢዘገይ እ.ኤ.አ. እስከ June 20/2022 ብቻ ነው።

ይህ የሚመለከተው የኢትዮጵያ መንግስት የላካቸውን ብቻ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
189 viewsØžåñ, 03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 17:23:36 ቤት ብርጭቆ ሰብረህ ወተህ ስትመለስ FATHER ሶፋ ላይ ፊት ለፊት ተኮሳትሮ ተቀምጦ ስታይ


እግዚአብሄር ሆይ በ አላህ እርዳኝ
@pick_model
207 viewsØžåñ, 14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 09:02:04 Piz follow me
196 viewsØžåñ, 06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 09:02:04 tiktok.com/@ermi_ab2
191 viewsØžåñ, 06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 06:57:25
#ጥንቃቄ ፦ ለቲክቫህ ቤተስብ አባላት ፦

" የተለያዩ ገንዘብ የማግኛ / ሀብት ማፍሪያ መንገዶች " እየተባለ በዲጅታል ሚዲያው በኩል ከቀርብ ጊዜ ወዲህ በርካቶች እጅግ በስፋት እየተከሰቱ ነው።

እነዚህ አካላት ፍቃድ ይኑራቸው አይኑራቸው ፤ የመስሪያ አድራሻቸው ይታወቅ አይታወቅ ፣ የሚመራቸው / የሚያስተባብራቸው ግለሰብ ይኑር አይኑር የሚለውን በግልፅ ለማወቅ አዳጋች ነው።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከዚህ በፊትም እንዳልናችሁ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችል እንቅስቃሴ ውስጥ ስትገቡ / ኢንቨስት ስታደርጉ እነዚህ ጥያቄዎች እንድትጠይቁ አደራ እንላለን ፦

1. ድርጅቱ / ተቋሙ እውቅና ያለው ፣ ፍቃድ ያለው ነው ? የሚሰራበትን ፍቃድ በይፋ አሳውቋል ?

2. በትክክል የሚታወቅ አድራሻቸው የት ነው ? ቢሯቸው ?

3. ለሚደርስብኝ ማኛውም አይነት ነገር ማንን ተጠያቂ ማድረግ እችላለው ?

4. የሚሰራው ስራ ምን ያህል ቀጣይነት አለው ? ነገ እንደማይቆም ምን ማስተማመኛ አለ ? ይህንን ማንስተማመኛ ማን ይሰጠኛል ? የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ ያስፈልጋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የማጭበርበር እና የማታለል ድርጊቶች እየሰፉ በመሆናቸው ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

ብዙሃንን ሊጠቅም ያሚችል ማንኛውም ህጋዊ ስራ በሚስጥር፣ በድብቅ ፈፅሞ ሊሰራ አይችልም እና ውድ ቤተሰቦቻችን ማኛውም እንቅስቃሴ ስትጀምሩ ከላይ የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች በቅድሚያ መልስ እንዳያገኙ አድርጉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
201 viewsØžåñ, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 10:16:14 #የምፈልገውን_እስካገኝ_ድረስ_ነው
:
:
:
ቀን ቀንን ተክቶ ጊዜ ጊዜን ሽሮ፤
ሀዘንም በደስታ ዞሮ ተቀይሮ፤
ያለቀሰ ሲስቅ የከፋው ሲፅናና፤
የተንገዳገደው ሦር ሰዶ ሲፀና፤
የታጩት ሲያገቡ አፍቃሪው ሲፈቀር፤
የኔ ህልም ብቻ ቅዠት ሆኖ ሲቀር፤
ዛሬስ የውነት ከፋኝ፤
ቅጡ ዳሩ ጠፋኝ።
:
:
የማላውቀው ስሜት ውስጤ ተለኩሷል፤
ከትናንቱ ዛሬ ነበልባሉ ብሷል፤
ያላየውሽ እንደው ይንራል ግለቱ፤
አንቺን አለማየት ጭድ ነው ለእሳቱ፤
የሚገርመው ነገር ያ ትግታግ ነበልባል፤
ያወጋን ለት ደርሶ ህመሙም ይረግባል።
እያልኩኝ ስነግርሽ የልቤን ውስጥ ስሜት፤
«የምትፈልገውን እስከምታገኝ ነው» ትያለሽ አንቺ ሴት።
:
:
ሆድ ብሶኝ ተክዤ ቀኑን ሙሉ ከፍቶኝ፤
ከቀኔ ጋር አብሮ ጥርሴም ጭምር ከድቶኝ፤
ሚያስቅ ሳያስቀኝ ተጭኖኝ ድባቴ፤
ገና ከሩቅ ሳይሽ እንደኮረኮሩት ፈግጌያለው ስንቴ።
የደስታዬ አልፋ የሳቄም ሆሜጋ፤
መሀልት ሆነ ሌሊት ሲመሽም ሲነጋ፤
አንቺው ነሽ እያልኩኝ ዘውትር ብመላለስ፤
«የምትፈልገውን እስከምታገኝ ነው» የሚል ነው ያንቺ መልስ።
:
:
መልክሽ ላይ ቅርፅሽ ላይ ወይም ስብህናሽ ላይ ያልተመረኮዘ፥
ሳይታሰብ በድንገት ውስጤ የተረገዘ፤
እራሴን ለራሴ ያረገኝ ሌላ ሰው፤
ነቅዬ ማልነቅለው ጥሼ ማልበጥሰው፤
በኔ ላይ ተሹሞ እንዳሻው ሚያሮጠኝ፤
ዱካ ና ዳናሽን ሰርክ የሚያስረግጠኝ፤
አንድ ታምር አለ ብዬ ባወራሽም፤
«የምትፈልገውን እስከምታገኝ ነው» ማለቱን አልተውሽም።
:
:
ሳይበግረኝ ከቶ ወበቅ እና አመዳይ፤
ላለማደር ብዬ ዓይኖችሽን ሳላይ፤
ንፁ ፍቅር ይዞኝ ፅናት የተቸረ፤
እያንገዳገደ እያንደረደረ፤
ወዳንቺ ሲያመጣኝ አይተሻል ታውቂያለሽ፤
«የምትፈልገውን እስከምታገኝ ነው» መልሰሽ ትያለሽ።
:
:
እውነት ነው አንቺ ሴት ብልሀትሽ ይደንቃል፤
የኔን ስሜት ጠልቆ እንዳንቺ ማን ያውቃል።
ከቶ አልተሸወድሽም አንቺ ጥበብ ሙዳይ፤
ተገንዝበሺዋል ያንድ ልቤን ጉዳይ።
:
:
ምንም አልተሳሳትሽ ቅንጣት የለው እንከን፤
አዎ ትክክል ነሽ! እንዲያ ምማስነው እንዲያ ምብከነከን፤
ይሄን ሁሉ ጊዜ የተመላለስኩት እግሬ እስከሚነቃ፤
ለምን እንወሻሽ «የምፈልገውን እስካገኝ ነው በቃ»።
:
:
አዎ!! ከነቃሽ ምን ቀረኝ በይ ስሚው እውነቱን፤
እንዲያ ያረገኝን የኔን ፍላጎቱን።
:
:
እኔ ምፈልገው
:
:
:
እኔ ምፈልገው
:
:

የዘውትር መሻቴ
:
:
:
እንድትሆኚልኝ ነው ውዷ ባለቤቴ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@pick_model
@pick_model
197 viewsØžåñ, 07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 09:05:20 አጥፍቻለው ማረኝ!

ለሌላ ምዕራፍ ላ'ዲስ ቀን መጓጓት
ማሰብ ያስተማርከኝ ስለነገው ንጋት
አንተ በመሆንህ የተስፋዬ ሙላት...
ባንተውም ነውና ያለፍኩት ያን ትናንት
ያላንተ ምንም ነው አይጥምም መኖሬ
ትርጉምም አይሰጠኝ መዋሌ ማደሬ..
ስወድህ አታኩርፍ አታጣላኝ ከንቅልፍ
በዝቷል መናፈቄም ጠቡ ይብቃ ፍቅሬ..
አጥፍቻለሁ ማረኝ ስቄ ልደር ዛሬ

ቻናላችንን join& ሼር በማረግ አግዙን
@pick_model
@pick_model
180 viewsØžåñ, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 06:51:22 ሶስቱ “ማንነቶቼ”
(“የማንነትህ መለኪያ” ከተሰኘው የደ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

ከስነ-ልቦና እይታ አንጻር ሶስት አይነት ማንነት እንዳሉን ማሰብ እንችላለን፡-

1. ራሴ “እንዲህ ነኝ” ብዬ የማስበው

እኔ በራሴ ላይ ያለኝ ተጽእኖ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ይህ ከሆነበት ምክንያቶች ዋነኛው ብዙውን ጊዜ ከራሴ ጋር ስለማሳልፍና ብዙ ነገሮችን ለራሴ የመናገር እድሉ ስላለኝ ነው፡፡ ይህ ልቀይረውና ሌላ አማራጭ ልፈልግለት የማልችለው እውነታ በመሆኑ በሚገባ ላስብበት ይገባኛል፡፡ በራሴ ላይ ያለኝ አመለካከት ራሴው በእኔው ላይ ከለጠፍኩበት ዋጋ አልፎ በመዝለቅ ወደ ትክክለኛው መስመር እስከሚገባ ድረስ ትክክለኛ መለኪያን እንዳላዳበርኩ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የሰውነቴ ዋጋ የማይለዋወጥ እንደሆነና እኔው በፈቃዴ ግን የተለያዩ የዋጋ ተመኖች እንዲለጠፉብኝ መፍቀድ እንደምችል ማስታወስ የግድ ነው፡፡

2. ሰዎችና ሁኔታዎች “እንዲህ ነህ” ብለው የሚነግሩኝ

ሰዎች ካለማቋረጥ መልእክትን ወደ እኛ ይልካሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቃል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በሁኔታ፡፡ በተለይም የመደብ ልዩነት ከባህሉ ጋር ተገምዶ በሚገኝበት እንደኛው አይነት ማሕበረሰብ ውስጥ ጀርባችንን፣ የወቅቱ ሁኔታችንን፣ ያለንና የሌለንን በመደመርና በመቀነስ ካለማቋረጥ ማንነታችን ላይ ተመን ይለጥፋሉ፡፡ ይህ ዋጋ ደግሞ አንዴ ከፍ ይላል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝቅ ይላል፡፡ ይህንን ሁኔታ በተገቢው ሚዛናዊነት የማስተናገዱ ግዴታ እኔው ላይ ነው ያለው፡፡ ሰዎች በእኔ ላይ የሚለጣጥፉት የዋጋ ውጣ ውረድ በማንነቴ ላይ ተጽእኖ የሚያመጣው እኔው ራሴ ስፈቅድለት ብቻ እንደሆነ ማስታወስ የግድ ነው፡፡

3. እውነተኛውና ትክክለኛው ማንነቴ

እውነተኛው ማንነቴ ማለት እኔው በራሴ ላይ ወይም ደግሞ ሌሎች ሰዎች የለጠፉብኝ ተመን (Price) ሳይሆን ሰው በመሆኔ ከፈጣሪ የተሰጠኝ ዋጋ (Value) ነው፡፡ ይህ የመጨረሻ ስልጣን ያለውና ሁሉንም ትቼ ላምነው፣ ላሰላስለውና ልለማመደው የሚገባኝ እውነት ነው፡፡ ይህ የማንነቴ ዋጋ በምንም ሁኔታ ሊቀንስም ሆነ ሊጨምር አይችልም፡፡ ይህንን ዋጋ በጥረቴ ልጨምረውም ሆነ ላሳድገው አልችልም፡፡ ለዚያ ሊቀነስም ሆነ ሊጨመር ለማይችለው ከፈጣሪዬ ለተቀበልኩት የከበረ ዋጋ ላለው ማንነቴ የሚመጥን አመለካከትና የኑሮ ዘይቤ የመከተሌ ሁኔታ ግን የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡

እንግዲህ አንድ ሰው በራሱ ማንነት ላይ ያለው ዋጋ የተዛባ መሆኑን ለማወቅ ካሉን መመዘኛዎች መካከል አንዱ በችግሮቹ ላይ ያለውን አመለካከት በማጤን ነው፡፡ የተቃኘና ትክክለኛ ራስ-በራስ ምልከታ ያለው ሰው እለት በእለት በሚገጥመው ችግሩ ላይ ያለውም ምልከታ ሚዛናዊና አዎንታዊ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ችግር ሲገጥመው የወደቀ አመለካከት ያለው ሰው በቅድሚያ በራሱ ላይ ያለው አመለካከት አለመስተካከሉን አመልካች ነው፡፡

የኑሯችሁ ሁኔታ በተለዋወጠ ቁጥር በማንነታችሁ ላይ ያለችሁን አመለካከትና ለራሳችሁ የምትሰጡትን ግምት አትለዋውጡ፡፡ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብታልፉም የማንነታችሁ ዋጋ ያው ነው!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@pick_model
@pick_model
195 viewsØžåñ, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 05:48:29 በርግጥ ናፍቀኸኛል
......................
ግን ግን አንተን ማግኘት ማለት
በጠራራ ጸሐይ እሳት እንደማንደድ
ከ ሙሽሮች መሃል ሙሾ አንደ መውረድ

እየሄድኩ በመታኝ እንቅፋት መደገም
ከ መስኪድ ደጃፍ ላይ አማትቦ መሳለም


የኔ መንገድ ካንተ አንዲህ ነዉ ተቃርኖ
በ ናፍቆት መዳፍ ላይ መኖር ንፋስ ዘግኖ ::

@kmemuwaaa
@kmemuwaaa
229 viewsØžåñ, 02:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 07:00:02 Amen
242 viewsØžåñ, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ