Get Mystery Box with random crypto!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ noahtoaels_idea — ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚
የቴሌግራም ቻናል አርማ noahtoaels_idea — ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚
የሰርጥ አድራሻ: @noahtoaels_idea
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.79K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኖህቶኤል ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት ቻናል ነው። የምትስማሙባቸውን ለወዳጆ ሼር ያድርጉላቸው።🙏
@Noahtoael
በማንበብ ብቁ እና ጤናማ እውቀት ያላቸውን ትውልድ እናፍራ!
በዚህም ቻናል.!
፦አጫጭር አዝናኝ እና አስተማሪ ታሪኮች
፦ተከታታይ ታሪኮች
፦ትረካዎች
፦ግጥም እና ስነፅሁፎች
.......ያገኛሉ!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-10 15:45:27 ጓደኛዬ ብርሃኑ
ከአመጿ ጀርባ
#ኤደንሀብታሙ
#ኮኬትአዲሱ


join us and share
@Noahtoaels_idea
2.9K viewsedited  12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 21:41:37 ፪ ፡፡ እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!! ።
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!
እንዴትስ፡ብወድህ፡ነው ?!
ከሰማይ፡ደመና፡ከየብሱ፡ከፍ፡ብሎ፣
የልቤ፡ለመምቴ፡ከጠፈሩ፡ታሎ፤
ህይወትህን፡ናፍቆ፡ሳለ፣
በእቅፍህ፡ስር፡ታለለ፤



እምምምምምምህህህህህ
ማግሁት፡ጠረንህን፡ነፍሴ፡እስኪነደል፣
ለአይኔ፡ለንባ፡ስለሆንኸኝ፡ቀንዲል፤
ለመንገዴ፡ንጋት፣
ለእንቅፋቴ፡ስቀት፤



በወደድኩህ፡መጠን፣
በአፈቀርኩህ፡መጠን፤
ልቤ፡ሸጣሸጡ፣
ልቤ፡ሰርጣሰርጡ፤
ሊጀምር፡መታመን፣
በቃልህ፡ለመዳን፤
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
እኮ
እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!!
እንዴትስ፡ብወድህ፡ነው ?!!
ሚወለፍነኝ፡ትርተቴ፡እስኪቆም፣
አቅሌ፡እስኪስት፡አቋሜ፡እስኪዘም፤





የኔ፡ሽልማት፡የልቤ፡አቴርሳታ፣
የሰውነቴ፡ቅጥ፡የውስጠቴ፡ቃታ፤
መሬት፡ሆነህ፡እርፎ፣
ማይ፡ሆነህ፡እርፎ፤



ተጠበለ፡ነፍሴ፡እረካ፡መንፈሴ፣
ተጠለሰ፡ሂወቴ፡ሆንክልኝ፡ምናሴ፤
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
ለ-ዘላለም፡እስክኖር፣
እስክጠልቅ፡ጀምበር፤
እስክቶነኝ፡ምርኩዝ፣
የህማማቴ፡ጣዝ፤
እስክጠለል፡ካካልህ፣
እስክሸሸግ፡ከልብህ፤
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
እኮ
እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!!
እንዴትስ፡ብወድህ፡ነው ?!!
እንዳይጸልም፡ቀኔ ፡እንዳይነጋ፡ምሽቴ፣
በሰመመን፡ህልም፡እንዳይዳክር፡ሰውነቴ፣
በአንተ፡ውስጥ፡እስክጠፋ፡የተረታ፡ጉልበቴ፤
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
እኮ
እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!!
እንዴት፡ብወድህ፡ነው ?!!

፡ ገጣሚ--ሀሴት በአምላክ
2.9K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 20:01:41 ስዕል-አብስትራክት ብቻ የፈለጋችሁትን ለማሳል ለምትፈልጉ ይሄንንንን የምታዪትን channel join በማድረግ ከታች በምታገኙት አካውንት ገብታችሁ እዘዙ።

channel link - @yotodforethiopia


Acc- @Unkown44Y44
2.1K views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 20:31:46
ኖህቶኤል በምን ቢመጣ ደስ ይላችዋል
Anonymous Poll
35%
በ ቲክቶክ
41%
በ you tube
11%
በፌስቡክ
8%
በinstagram
5%
በቲውተር
327 voters1.9K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 20:30:08 ብዙ እያየው ያለሁት እየተራመድኩኝ ስለሆነ ነው
ገና አያለው ይህ ማለት ደግሞ......


#ኖህቶኤል

@Noahtoaels_idea
1.7K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 14:29:48 ኤልሮኢሽ መቼ ይሆን??

ከላይ ከላይ ካለው ሰማይ
አንገቱን ዝቅ አድርጎ አይኑ አንቺን የሚያይ
እላይ ያለውን የፈጠረሽን ጌታ
ከማንም ከምንም እጅግ የበረታ
ያ የላይኛውን በስስት 'ሚያይሽን
እጆችሽን ዘርጊ ልያዝሽ ያለሽን
አንቺም 'ምታዪው ተክለሽበት አይንሽን
ኤልሮኢሽ መቼ ይሆን??



በ ዮቶራዊት «Dedicated to our country whos passing through a lot right now»
1.7K viewsedited  11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 19:29:51 አይ አንቺዬ

ስንቱ ሲያወራ ቀጥሎም ሲያዜም
እወድሻለው ብሎ እንዲው ሲያልጎመጉም
እናቴ ሲሉሽ ከልባቸው መስሎሽ
ስቃይሽ የገባቸው ያመማቸው ህመምሽ
አይ አንቺዬ
አንቺን የወደደሽ ራስሽን ሲገልሽ
በጣሙን ሚወድሽ ለሌላ ሲሸጥሽ
ገዳይሽ ሲፎክር ገሎ አምጡልኝ እያለ
ሟች አፈር ለብሶ ሀዘን እያየለ
አይ አንቺዬ
ደሞ ይዜምልሻል
የዜግነት ክብር በአንቺ ፀንቶ
ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከ ዳር በርቶ
እያሉ ቀጠሉ...
ስለየቱ ክብር ባንቺ ስለፀናው
ስለየቱ ህዝባዊነት ባንቺ ስለበራው
ባይገባኝም ቅሉ መዝሙር ስለተባለ
ሁሉም በእኩል አፍ ማዜሙን ቀጠለ
ግና ገዳይና ሟች
በዳይና ተበዳይ
ባለበት ሁኔታ የዜግነት ክብር
የመቻቻል ሀገር የቀለማት ህብር
እያሉ መደስኮር
ፍፁም አይገባኝም
እንዲገባኝ አልሻም
አይ አንቺዬ
ሁሉም ሲያወራ ከልቡ መስሎሽ
ስንት ግዜ ተሸወድሽ
ስንቴ አፈር ለበሽ
አይ አንቺዬ ሀገሬ
ባንቺ ነው ማማሬ
እያሉ ሲያወሩ ስንቴ እውነት መሰለሽ
ግን ሳስበው የምርም ሞኝ ነሽ
የሰራልሽ ሞቶ የሸጠሽ ሲከብር
አንቺ እያጨበጨብሽ የምትሰጪ ክብር
በጣሙን ሞኝ ነሽ
'ወድሻለው ያለሽ አንቺን ከገደለ
ጠላሻለውም ያለው ይህንኑ ካስቀጠለ
እኔ ምንም አልልም
የቱም ጋር አልሆንም
የቱንም አልወግንም
ግን አንቺን ነፃ የሚያደርገውን
ያንቺን ሞት ሚሞተውን
ያንቺን ክርስቶስን
ማየትን እሻለው።



በዮቶራዊት
1.9K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 07:41:59
#choice

Small choice become actions.
Actions become habit.
And habits become our way of life.
So.what will you choose?

Choose Good think!

@Noahtoaels_idea

Share to ur friend!!!
1.6K viewsedited  04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 06:05:57 ፍቅር የእግዚአብሔር ሕግ ነው፤

ምንጭ ፦ መፅሀፈ ሚርዳድ
ፀሀፊ ፦ ሚካኤል ኔይሚ
ትርጉም ፦ ግሩም ተበጀ

ሚርዳድ - ፍቅር የእግዚአብሔር ሕግ ነው። የምትኖሩት ፍቅርን ትማሩ ዘንድ ነው። የምታፈቅሩትም መኖርን ትችሉ ዘንድ! ለሰው ልጅም ከዚህ ውጪ ሌላ ትምህርት አያሻውም።

ማፍቀር ማለትስ ምንድነው፣ አፍቃሪ ተፈቃሪውን ለዘለዓለሙ ወደ ራሱ ስቦ ሁለቱ አንድ እንዲሆኑ እንጂ?

ደግሞስ ... ማንን ወይም ምንን ይሆን ማፍቀር የሚገባ? እውን ከሕይወት ዛፍ ቅጠሎች አንዷን መርጦ ልብ ያጋተውን መላውን ፍቅር ማዝነብ ይገባ ይሆን?

ግና፣ቅጠሉን ያፈራው ቅርንጫፍ፣ ቅርንጫፉን የያዘው ግንድ፣ ግንዱን ያቀፈው ቅርፊትስ ? ቅርፊት፣ ግንዱን፣ ቅጠላ ቅጠል፣ ቅርንጫፎቹን የመገቡት ስሮችስ? ስሮቹንስ ያቀፈው አፈር? አፈሩንስ ያለማው ፀሐይ? ውቅያኖስ ... አየሩስ?

ዛፍ ላይ ያለች ትንሸ ቅጠል፣ ለፍቅራችሁ ከተገባች፤ መላ ዛፉን ምን ያህል እጥፍ ትወዱት!? ከእጠቃላዩ ነጥሎ አንዱን ክፋይ የሚወድ ፍቅር፣ ራሱን ለሐዘን አጭቷል ቀድሞ ነገር!

እናንተ ግን፣ “ከአንድ ዛፍ ቅርንጫፍ እንኳ፣ እልፍ አእላፍ ቅጠሎች አሉ...

አንዳንዱ ጤነኛ፣ አንዳንዱ ታማሚ፤ ገሚሱ ቆንጆ ሌላው አስቀያሚ።

ከፊሉ ግዙፍ ከፊሉ ድውይ፣ አማርጦ መውደድ አይገባም ወይ?”

ስትሉ ሰማሁ...

እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ፣

ከታማሚው መጠውለግ ነው የጤነኛው ትኩስነት የሚመነጭ። እናም እንዲህ እላችኋለሁ፣ አስቀያሚነት የውበት መኳያዋ፣ ቀለም እና ብሩሿ ነው። ኧረ ለመሆኑ፣ ድውዩ ቁመቱን ለለግላጋው ባይሰጥ ለግላጋው መለሎ የሚሆን ይመስላችኋል?

እናንተ የሕይወት ዛፍ ናችሁ። ራሳችሁን ላለመከፋፈል ተጠንቀቁ። ፍሬን በፍሬ ላይ፣ ቅጠልን በቅጠል ላይ፣ ቅርንጫፍን በቅርንጫፍ ላይ አታስነሱ፤ ግንዱንም በሥሮች ላይ፣ ዛፉንም ከእናት አፈሩ አታጣሉ፣ አታናክሱ። ይህ ደግሞ ... በእርግጥም ... አንዱን ከሌላው አስበልጣችሁ ወይም ከተቀረው ሁሉ ለይታችሁ ስትወዱ የምታደርጉት ነው።

አዎን ... እናንት ሁላችሁም ... የሕይወት ዛፍ ናችሁ። ሥራችሁም የትም ነው። ቅርንጫፍና ቅጠሎቻችሁም በሁሉም ሥፍራ፣ ፍሬዎቻችሁም በሁሉም አፍ ውስጥ! በዚያ ዛፍ ላይ ያሉት የትኞቹም ፍሬዎች፣ የትኞቹም ቅርንጫፍ እና ቅጠሎች፣ የትኞቹም ሥሮች፤ የእናንተው ፍሬ፣ የእናንተው ቅጠልና ቅርንጫፍ፣ የእናንተው ሥሮች ናቸው።

ዛፉ፣ ጣፋጭና ባለማራኪ መዓዛ ፍሬ ቢቸር፣ ሁሌ ጠንካራ እና ፍፁም አረንጓዴ ሆኖ ቢታይ ... ሥሮቹን ወደመገባችሁበት የሕይወት ወለላ እዩ...

ፍቅር የሕይወት ወለላ ነው። ጥላቻ ደግሞ የሞት መግል። ፍቅር ግን ልክ እንደ ደም፣ ሳይታጎልና ሳይገደብ በሕይወት ሥሮች ውስጥ ሊፈስስ ይገባዋል። የደም ፍሰት ሲገደብ በሽታ እና ወረርሽኝ ይሆናል። ጥላቻስ ምንድነው? ለጠይውም ለተጠይም፣ ለመጋቢውም ለተመጋቢውም ገዳይ መርዝ የሆነ የታፈነ፣ የተገደበ ፍቅር እንጂ

በሕይወት ዛፋችሁ ላይ ያለች ቢጫ ቅጠል፣ ሌላም ሳትሆን ፍቅር-ያስጣሏት ቅጠል ነች።

ቢጫዋን ቅጠል አትውቀሷት። ደርቆ የተንጨፈረረው ቅርንጫፍም ሌላም ሳይሆን ፍቅር የተራበ ቅርንጫፍ ነው። የደረቀውን ቅርንጫፍ አትውቀሱት። የበሰበሰው ፍሬም ቢሆን ሌላም ሳይሆን ጥላቻ የመረዘው ፍሬ ነው። የበሰበሰውን ፍሬ አትኮንኑት።

ይልቁንም የሕይወትን ወለላ፣ ለጥቂቶች ብቻ ቸሮ ለብዙዎች የሚነፍገውን፣ በዚህም ራሱን ጭምር የነፈገውን፣ ዕውር እና ንፉግ ልባችሁን ውቀሱ።

የፍቅር መጸነሻው፣ የመውደድ አብራኩ ራሥን ማፍቀር ነው።

የራስ ፍቅር ቢኖር እንጂ ፍቅር የሚባል ጨርሶ የለም፤ የሚቻልም አይደለም።

ከሁሉን አቃፊው እኔነት በቀር የቱም እኔነት እውን አይደለም። ስለዚህም፣ እግዚአብሔር መላ ፍቅር ነው፤ ምክንያቱም ራሱን ይወዳልና።

ፍቅር ካሳመመህ ... መውደድ ስቃይ ከሆነብህ ... እውነት እልሃለሁ ... እስካሁን ድረስ እውነተኛው ማንነትህ፣ የፍቅር ወርቃማ ቁልፍ ገና እጅህ አልገባም ማለት ነው። አላፊ ጠፊእኔነትን ስላፈቀርክ፣ ፍቅርህም እንዲሁ አላፊ ጠፊ ነው።

የወንድ ሴትን ማፍቀር ፍቅር አይደለም። ይልቁንም የሩቅ ተምሳሌቱ ነው። ወላጅ ለልጁ ያለው ፍቅርም፣ ሌላም ሳይሆን የፍቅር ቤተመቅደስ ደጀ ሰላሙ ነው። የትኛውም ወንድ የሁሏም ሴት አፍቃሪ፣ የትኛዋም ሴት የሁሉም ወንድ አፍቃሪ እስክትሆን ድረስ፤ የትኛውም ልጅ የሁሉም ወላጅ ልጅ፣ የትኛውም ወላጅ የሁሉም ልጅ ወላጅ እስኪሆን ድረስ ... ወንዶችና ሴቶች ... ሥጋና አጥንት ከሥጋና አጥንት ጋር ስለመተቃቀፍ ይለፍፉ እንጂ ... ፈፅሞ በተቀደሰው የፍቅር ሥም ሰይመው አያርክሱት። ይህ የፍቅርን ሥም ማጠልሸት ነውና። አንድ እንኳ ጠላት ካለህ ምንም ጓደኛ እንደሌለህ እወቀው። ጠላትነት ያሸመቀ ልብ ለወዳጅ ማደሪያ ይሆናል እንዴ?

በልቦቻችሁ የጥላቻ ዘር እስካለ ድረስ የፍቅርን ሐሴት አታውቋትም። የሕይወትን ወለላን ለሁሉም መግባችሁ ለአንዲት ቅንጣት ነፍሳት ብትነፍጉ ያቺ የተነፈገችዋ ሕይወታችሁን ታመርረዋለች። የቱንም ነገር ሆነ ማንንም ስትወዱ፣ እንደ እውነቱ ከሆነ የምትወዱት ራሳችሁን ነው። ስትጠሉም እንዲሁ ነው ... የቱንም ነገር ሆነ ማንንም ስትጠሉ እንደ እውነቱ የምትጠሉት ራሳችሁን ነው። የምትወዱትና የምትጠሉት ልክ እንደ አንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ላይነጣጠሉ ተጣምረዋልና። ለራሳችሁ ታማኝ ብትሆኑ ኖሮ፣ የምትወዱትንና የሚወድዳችሁን ከመውደዳችሁ በፊት የምትጠሉትንና የሚጠላችሁን ትወድዱ ነበር።

ፍቅር መልካም ምግባር አይደለም። ፍቅር መሰረታዊ ፍላጎት ነው። ከዳቦና ከውኃ፣ ከአየርና ከብርሃን የበለጠ ፍቅር ያሻችኋል። ማንም በማፍቀሩ አይኩራራ፣ ይልቁንም ነጻ ሆናችሁ እንዲሁ በዘፈቀደ አየሩን ወደ ውስጥ እንደምትስቡትና እንደምታስወጡት ሁሉ ፍቅርንም እንዲሁ በነጻነት ልብም ሳትሉ ተንፍሱት። ፍቅር፣ ማንም እንዲያወድሰው አይሻም። ይልቁንም ለፍቅር የተገባ ልብ ሲያገኝ ያን ልብ ያወድስ ይቀድሰዋል እንጂ። ከፍቅርህ ወሮታ አትጠብቅ። ፍቅር በራሱ ለፍቅር በቂ ሽልማቱ ነው፤ ልክ ጥላቻ ለጥላቻ በቂ ቅጣቱ እንደሆነው ሁሉ። ከፍቅር ጋር ሒሳብ አትተሳሰቡ። ፍቅር ሒሳብ የሚያወራርደው ከራሱ ጋር ብቻ ነውና፣ ተጠያቂነቱም ለማንም ሳይሆን ለራሱ ብቻ!

ፍቅር አያበድርም፣ አያውስምም። ፍቅር አይገዛም፣ አይሸጥምም። ሲሰጥ ግን ሁለመናውን ይሰጣል። ሲወስድም ሁለመናውን ይወስዳል። መቀበሉ በራሱ መስጠት ነው። መስጠቱም በራሱ መቀበል! እናም፣ ለዛሬም፣ ነገም ለከነገወዲያም እንዲሁ ነው።

ራሱን ሳይሰስት ለባሕሩ የሚለግስ የትኛውም ወንዝ፣ ዘወትር በባሕሩ ደግሞ እንደሚሞላ ሁሉ እናንተም እንዲሁ ፍቅር መልሶ ይሞላችሁ ዘንድ ራሳችሁን አንጠፍጥፋችሁ ለፍቅር ስጡ።

አዎን .... የባሕሩን ሥጦታ ከባሕሩ የሚነፍግ ኩሬ መጨረሻው መበስበስም አይደል!? በፍቅር ... ትንሽ ወይም ትልቅ የሚሉት ነገር የለም። ፍቅርን መለካት፣ መመተር ... ለፍቅር ደረጃ ማውጣት ስትሞክር፣ ፍቅር መራር ትዝታዎቹን አስታቅፎህ እብስ ይላል...

በፍቅር ዘንድ ..ትናንት ወይም ዛሬ፣ ዛሬ ወይም ነገ እዚህ ወይም እዚያ ብሎ ነገር የለም። ሁሉም ወቅቶች የፍቅር ወቅቶች ናቸው። የትኛውም ቦታ ቢሆን ለፍቅር ማረፊያነት የተገባ! ፍቅርን ... ወሰንም ሆነ ዳር ድንበር፣ ካቴናም ሆነ የተዘጋ በር አይገድበውም። የትኛውም መሰናክል ጉዞውን ያሰናከለው ፍቅርም በተቀደሰው የፍቅር ሥም ለመጠራት ባልተገባው።


ይቀጥላል

@Noahtoaels_idea
2.9K views03:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 18:16:49 ልጁም ፈጣሪውን "በነጋታው ወደ ምድር ልትልከኝ እንደሆነ ነገሩኝ። ነገር ግን ኮሳሳ እና ረዳት አልባ ሆኜ እዛ እንዴት ልኖር ነው?" ሲል ጠየቀው።

አምላክ "መላዕኩም ይጠብቃሃል"

ልጁ "እዚህ ገነት ምንም ማድረግ አይጠበቅብኝም ነገር ግን ለመደሰት ማዜም እና መሳቅ ይበቃኛል።"

አምላክ "በምድር መላዕኩም ያዜምልሃል፣ ፈገግም ይልላሃል። እናም ፍቅሩን ታየለህ፤ ደስም ይልሃል"

ልጁ "ቋንቋቸውን ሳላውቅ ሰዎች ሲያነጋግሩኝ እንዴት መረዳት እችላለሁ?"

ፈጣሪ "መላዕኩ ምንግዜም በጣም ውብ እና ጣፋጫ ቃላቶችን ይነግርሃል። በትዕግስት እና እንክብካቤ እንዴት መናገር እንዳለብህም ያስተምርሃል"

ልጁ "አንተን ማናገር ባስፈለገኝ ጊዜ ምን ላድርግ?"

ፈጣሪ "መላዕኩም እጆችህን አንስተህ እንዴት መፀለይ እንዳለብህ ያስተምርሃል"

ልጁ "እሺ…ማን ይጠብቀኛል?"

ፈጣሪ "ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሎም ቢሆን መላዕኩ ይጠብቅሃል"

ልጁ "ነገር ግን ከዚህ በኋላ አንተን ስለማላይህ ሁሌም ይከፋኛል!"

ፈጣሪ "መላዕኩም ሰርክ ስለኔ ይነግርሃል፤ ወደኔ እንዴት እንደምትመለስም ያስረዳሃል። ቢሆንም እኔ ሁሌም ቅርብህ ነኝ!"

በዛ ኹኔታ ገነት ፍፁም ሠላም ነበር። ነገር ግን ከምድር የመጣ ድምፅ ተሰማ። ሕጻኑም በፍጥነት "ጌታዬ አሁን መሄድ ከሆነ እባክህን የመላዕኩን ሥም ንገረኝ?"

ፈጣሪ "እንዲህ ብለህ ብቻ ጥራት፣ እማ!"

@Inspirational Quotes Page's

•••

መልካም የእናቶች ቀን!

@Noahtoaels_idea
1.9K views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ