Get Mystery Box with random crypto!

፪ ፡፡ እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!! ። ፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤ | ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

፪ ፡፡ እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!! ።
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!
እንዴትስ፡ብወድህ፡ነው ?!
ከሰማይ፡ደመና፡ከየብሱ፡ከፍ፡ብሎ፣
የልቤ፡ለመምቴ፡ከጠፈሩ፡ታሎ፤
ህይወትህን፡ናፍቆ፡ሳለ፣
በእቅፍህ፡ስር፡ታለለ፤



እምምምምምምህህህህህ
ማግሁት፡ጠረንህን፡ነፍሴ፡እስኪነደል፣
ለአይኔ፡ለንባ፡ስለሆንኸኝ፡ቀንዲል፤
ለመንገዴ፡ንጋት፣
ለእንቅፋቴ፡ስቀት፤



በወደድኩህ፡መጠን፣
በአፈቀርኩህ፡መጠን፤
ልቤ፡ሸጣሸጡ፣
ልቤ፡ሰርጣሰርጡ፤
ሊጀምር፡መታመን፣
በቃልህ፡ለመዳን፤
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
እኮ
እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!!
እንዴትስ፡ብወድህ፡ነው ?!!
ሚወለፍነኝ፡ትርተቴ፡እስኪቆም፣
አቅሌ፡እስኪስት፡አቋሜ፡እስኪዘም፤





የኔ፡ሽልማት፡የልቤ፡አቴርሳታ፣
የሰውነቴ፡ቅጥ፡የውስጠቴ፡ቃታ፤
መሬት፡ሆነህ፡እርፎ፣
ማይ፡ሆነህ፡እርፎ፤



ተጠበለ፡ነፍሴ፡እረካ፡መንፈሴ፣
ተጠለሰ፡ሂወቴ፡ሆንክልኝ፡ምናሴ፤
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
ለ-ዘላለም፡እስክኖር፣
እስክጠልቅ፡ጀምበር፤
እስክቶነኝ፡ምርኩዝ፣
የህማማቴ፡ጣዝ፤
እስክጠለል፡ካካልህ፣
እስክሸሸግ፡ከልብህ፤
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
እኮ
እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!!
እንዴትስ፡ብወድህ፡ነው ?!!
እንዳይጸልም፡ቀኔ ፡እንዳይነጋ፡ምሽቴ፣
በሰመመን፡ህልም፡እንዳይዳክር፡ሰውነቴ፣
በአንተ፡ውስጥ፡እስክጠፋ፡የተረታ፡ጉልበቴ፤
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
እኮ
እንዴት፡ባፈቅርህ፡ነው ?!!
እንዴት፡ብወድህ፡ነው ?!!

፡ ገጣሚ--ሀሴት በአምላክ