Get Mystery Box with random crypto!

ልጁም ፈጣሪውን 'በነጋታው ወደ ምድር ልትልከኝ እንደሆነ ነገሩኝ። ነገር ግን ኮሳሳ እና ረዳት አል | ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

ልጁም ፈጣሪውን "በነጋታው ወደ ምድር ልትልከኝ እንደሆነ ነገሩኝ። ነገር ግን ኮሳሳ እና ረዳት አልባ ሆኜ እዛ እንዴት ልኖር ነው?" ሲል ጠየቀው።

አምላክ "መላዕኩም ይጠብቃሃል"

ልጁ "እዚህ ገነት ምንም ማድረግ አይጠበቅብኝም ነገር ግን ለመደሰት ማዜም እና መሳቅ ይበቃኛል።"

አምላክ "በምድር መላዕኩም ያዜምልሃል፣ ፈገግም ይልላሃል። እናም ፍቅሩን ታየለህ፤ ደስም ይልሃል"

ልጁ "ቋንቋቸውን ሳላውቅ ሰዎች ሲያነጋግሩኝ እንዴት መረዳት እችላለሁ?"

ፈጣሪ "መላዕኩ ምንግዜም በጣም ውብ እና ጣፋጫ ቃላቶችን ይነግርሃል። በትዕግስት እና እንክብካቤ እንዴት መናገር እንዳለብህም ያስተምርሃል"

ልጁ "አንተን ማናገር ባስፈለገኝ ጊዜ ምን ላድርግ?"

ፈጣሪ "መላዕኩም እጆችህን አንስተህ እንዴት መፀለይ እንዳለብህ ያስተምርሃል"

ልጁ "እሺ…ማን ይጠብቀኛል?"

ፈጣሪ "ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሎም ቢሆን መላዕኩ ይጠብቅሃል"

ልጁ "ነገር ግን ከዚህ በኋላ አንተን ስለማላይህ ሁሌም ይከፋኛል!"

ፈጣሪ "መላዕኩም ሰርክ ስለኔ ይነግርሃል፤ ወደኔ እንዴት እንደምትመለስም ያስረዳሃል። ቢሆንም እኔ ሁሌም ቅርብህ ነኝ!"

በዛ ኹኔታ ገነት ፍፁም ሠላም ነበር። ነገር ግን ከምድር የመጣ ድምፅ ተሰማ። ሕጻኑም በፍጥነት "ጌታዬ አሁን መሄድ ከሆነ እባክህን የመላዕኩን ሥም ንገረኝ?"

ፈጣሪ "እንዲህ ብለህ ብቻ ጥራት፣ እማ!"

@Inspirational Quotes Page's

•••

መልካም የእናቶች ቀን!

@Noahtoaels_idea