Get Mystery Box with random crypto!

አይ አንቺዬ ስንቱ ሲያወራ ቀጥሎም ሲያዜም እወድሻለው ብሎ እንዲው ሲያልጎመጉም እናቴ | ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

አይ አንቺዬ

ስንቱ ሲያወራ ቀጥሎም ሲያዜም
እወድሻለው ብሎ እንዲው ሲያልጎመጉም
እናቴ ሲሉሽ ከልባቸው መስሎሽ
ስቃይሽ የገባቸው ያመማቸው ህመምሽ
አይ አንቺዬ
አንቺን የወደደሽ ራስሽን ሲገልሽ
በጣሙን ሚወድሽ ለሌላ ሲሸጥሽ
ገዳይሽ ሲፎክር ገሎ አምጡልኝ እያለ
ሟች አፈር ለብሶ ሀዘን እያየለ
አይ አንቺዬ
ደሞ ይዜምልሻል
የዜግነት ክብር በአንቺ ፀንቶ
ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከ ዳር በርቶ
እያሉ ቀጠሉ...
ስለየቱ ክብር ባንቺ ስለፀናው
ስለየቱ ህዝባዊነት ባንቺ ስለበራው
ባይገባኝም ቅሉ መዝሙር ስለተባለ
ሁሉም በእኩል አፍ ማዜሙን ቀጠለ
ግና ገዳይና ሟች
በዳይና ተበዳይ
ባለበት ሁኔታ የዜግነት ክብር
የመቻቻል ሀገር የቀለማት ህብር
እያሉ መደስኮር
ፍፁም አይገባኝም
እንዲገባኝ አልሻም
አይ አንቺዬ
ሁሉም ሲያወራ ከልቡ መስሎሽ
ስንት ግዜ ተሸወድሽ
ስንቴ አፈር ለበሽ
አይ አንቺዬ ሀገሬ
ባንቺ ነው ማማሬ
እያሉ ሲያወሩ ስንቴ እውነት መሰለሽ
ግን ሳስበው የምርም ሞኝ ነሽ
የሰራልሽ ሞቶ የሸጠሽ ሲከብር
አንቺ እያጨበጨብሽ የምትሰጪ ክብር
በጣሙን ሞኝ ነሽ
'ወድሻለው ያለሽ አንቺን ከገደለ
ጠላሻለውም ያለው ይህንኑ ካስቀጠለ
እኔ ምንም አልልም
የቱም ጋር አልሆንም
የቱንም አልወግንም
ግን አንቺን ነፃ የሚያደርገውን
ያንቺን ሞት ሚሞተውን
ያንቺን ክርስቶስን
ማየትን እሻለው።



በዮቶራዊት