Get Mystery Box with random crypto!

ንባብ ለሕይወት

የቴሌግራም ቻናል አርማ nibab_lehiwot — ንባብ ለሕይወት
የቴሌግራም ቻናል አርማ nibab_lehiwot — ንባብ ለሕይወት
የሰርጥ አድራሻ: @nibab_lehiwot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 104
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም እንኳን ወደ channelላችን በሰላም መጡ በዚህ channel
*ልብወለድ
*ባህል ባህል የሚሸቱ ወግ እና ጥቅሶችን
*ከ ተወደዱ መፅሀፍት የተመረጡ አስተማሪ እና አዝናኝ ፅሁፎችን ያገኛሉ።
ንባብ ካለንበት ወጥተን ዓለምን የምናስተውልበት መነፀር ነው።
ማንበብ የአእምሮን አድማስ ማስፋት፣ እይታን ማርቀቅ አጠቃላይ ሙሉ ሰው የምንሆንበት ብቸኛ መንገድ ነው።ይቀላቀሉን @nibab_lehiwot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-12 13:34:17
በአሁኑ ሰዓትና ጊዜ ከፍቅረኛዎ ጋር ሲጣሉ : በፍቅር ሲወድቁ : ብቸኛ ሲሆኑ : የሚያምኑበትን ነገር ሲያጡ እና ሂወት ሲያስጠላዎ አልያም ሲደሱቱ ፕሮፋይሎዎን ምን ላድርገው ብለዉ ሳይጨነቁ እኛ ጋር ጥቅሶች ና አባባሎች ይዘን መተናል
https://t.me/joinchat/AAAAAFGvZJWv9XX_t42_vA
78 viewsPapa , 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 17:11:39 አሁን Online ላላችሁ ብቻ የካርድ ሽልማት አለ።
ካርዱ ሊለቀቅ ❽ ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው
Join ብላችሁ ጠብቁ
30 viewsPapa , 14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 17:10:08
34 viewsPapa , 14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 16:40:26 ተማሪ ነህ ?
16 viewsPapa , 13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 16:37:51 የፍቅረኛችሁን   ሰው   ስም   የመጀመርያ ፊደል   በመጫን   የምታገኙትን   የፍቅር ቻናል   ተጋበዙልኝ ︎


ዳይ ለሁላችሁም ነው እንዳያመልጥዎ!!
31 viewsPapa , 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 16:27:13
የተወለዱበትን ወር ይምረጡ እና ስለ ፍቅር ህይወቶ በጥልቅ ይወቁ
67 viewsPapa , 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 21:53:23 #ራስህን_ሁን!....ሰዎች.. ምን ይሉኛል የሚል ይሉኝታ ማቆም አለብህ፤ መቼም በዚህ ምድር ላይ ራስን እንደመሆን የሚያስደስት ነገር የለም። እናም ሰዎች ምን ይሉኝ ይሆን? ሰዎች ስለኔ ምን ያስባሉ? የሚለውን ማቆም ያለብህ አሁን ነው።

የእርስዎን መኪና የሚነዳው ማን ነው? ቤተሰብ ነው? ጓደኛ ነው? በዙሪያህ ያለ ሰው ነው? ወዳጄ ልቤ፣ መኪና በሁለት ሰው አይነዳም። መኪና ደግሞ ህይወትህ ነው። እንደ መኪና ሁሉ ህይወት በተለያዩ ሰዎች አይመራም፤ በሌሎች አስተሳሰብ የምትመራ ከሆነ ግን ወደ ገደል ነው የምትገባው!

ስለዚህ በአንተ ህይወት ማንም ማዘዝ የለበትም።
በገንዘብህ፣ በጉልበትህ፣ በአእምሮህ ማንም ሥልጣን ሊኖረው አይገባም። አንተና ፈጣሪ ካላዘዛችሁበት ሰዎች እንደ ጥላ ናቸው። አጥተህ ፀሐይ ስትጠልቅብህ ይበተናሉ፤ ኖሮህ ስትደመቅ ደግሞ ይከተሉሃል፤ ያከብሩሃል!

ስለዚህ በራስህ ላይ ሥልጣን ይኑርህ፤ እራስህን ሁን!

ሰዎች የሚወዱህ ጥንካሬህን መዝነው ነው። ምን ይሉሃል መሰለህ.. "እሱ'ኮ የማነበትን ነው የሚያደርገው" ይሉሃል፤ "ምን አይነት ጎበዝና ደፋር ነው" እያሉ ያከብሩሃል። በጥንካሬህና ራስህን ስትሆን ትከበራለህ፤ ሰዎች ባይወዱህ እንኳን በልባቸው እንዳተ መሆን ይፈልጋሉ።

ስለዚህ ለራስህ ቅድሚያ ስጥ። አግኝተህ ብታጣ፣ ታመህ ብትተኛ፣ ነግደህ ብትከስር፣ ሰዎች "አይዞህ" ሊሉህ ይችሉ ይሆናል ህመምህን ግን ማንም አብሮ ሊታመምልህ አይችልም፤ በገባህበት ገደል ማንም መግባት አይፈልግም።

...አንድ ሰው ወደ ከርሰ መቃብር ሲገባ አብሮ የተቀበረ የለም። እንዲህ ያለ ታሪክ አልሰማንም። የምናውቀው እስከ መቃብር ቦታ ሸኝተው "ወይኔ፥ ወይኔ" ብለው አልቅሰው ቀብረው ሲመለሱ ነው።

ስለዚህ በዚች ዓለም ማንም አብሮህ ስለማይቀበር
ቅድሚያ ለራስህ ቦታ ስጥ፤ የምታደርገውን ነገር እምንበት። አንተ ካላመንክበት፤ ዓላማህን ካላወቅህው ግን ሰዎች እንደ እንዝርት ወደፈለጉበት ያሽከረክሩሃል!

እናም ወዳጄ ልቤ፣ ለራስህ የምትሰጠው ቦታ መቀየር ያለብህ አሁን ነው። በራስህ ላይ ራስህን ሹም!

መልካም አዳር ይሁንላችሁ

@Tesh5050
508 viewsTeshe ......, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 11:07:52 በቅድሚያ ወላጆቻችሁን አግዙ...

አንድ ወጣት ስራ ለመቀጠር ፈለገ በድርጅቱ ውስጥም ትልቅ ቦታ ለማግኘት ወደ አንድ ድርጅት አቀና ።

ወጣቱ ቃለ መጠይቁን በጥሩ ሁኔታ አለፈ ለመጨረሻ ቃለ መጠይቅ ለማድረግም ከዳይሬክተሩ ጋር ተገናኘ። ዳይሬክተሩ የመጨረሻውን መጠይቅ ካረገለት በኋላ ...

የወጣቱን የትምህርት፣ችሎታ የሚያሳየውም ሰነድ (ሲቪ)አገላብጦ ካየ በኋላ በጣም ጥሩ መሆኑን ገለፀ።

ዳይሬክተሩ:- ከአሁን በፊት የተሻለ የትምህርት እድል አግኝተሃል ሲል ጠየቀው ?

ልጁም:- "አይ" ሲል መለሰ

ዳይሬክተሩ:- ትምህርትህን እንድትከታተል እና የትምህርት ቤት ክፍያዎችን ከፍሎ ያስተማረህ አባትህ ነው?

'ወጣቱ :- አዎ.' ብሎ መለሰ።

ዳይሬክተሩ :- አባትህ ምንድነው የሚሰራው?

ወጣቱ:- አባቴ አንጥረኛ ነው"

ዳይሬክተሩ:- ወጣቱ እጆቹን እንዲያሳየው ጠየቀው።

ወጣቱ :- ለስላሳ እና ፍጹም የሆነ እጆቹን አሳየው

ዳይሬክተሩ:- ወላጅ አባትህን በሥራ ረድተሃቸው ታውቃለህ?

ወጣቱ:- በጭራሽ፣ ወላጅ አባቴ መጻሕፍቶችን እንዳነብና እንዳጠና ነበር ፍላጎቱ እና ደግሞ ከኔ በተሻለ ሁኔታ ስራውን መስራት ይችላል።

ዳይሬክተሩ እንዲህ አለ፡- ለዛሬ ወደ ቤትህ ትመለሳለህ እቤት እንደደረስክም የአባትህን እጅ በደንብ አርገህ ታጥብና ነገ ጥዋት ተመልሰህ አግኘኝ ብሎ ቀጠሮ ያዘለት ።

ወጣቱ ስራውን የማግኘት እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ተሰማው ወደ ቤቱ እንደተመለሰም የአባቱን እጅ እንዲያጥብለት አባቱን ፍቃድ ጠየቀው?

አባቱ በልጁ እንግዳ ተግባር ተገረመ ደስም አለው , ነገር ግን የደስታ ስሜቱ የተደባለቀ ነበር ከዚያም እጆቹን ለልጁ አሳየው. ወጣቱ ቀስ እያለየአባቱን እጆች አጠበ።

ይህን ጊዜ የአባቱ እጆች የተሰነጣጠቁ እና በጣም ብዙ ጠባሳ እንዳለባቸው አየ ይህን ያስተዋለው ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር።

በአባቱ እጆች ላይ አንዳንድ ቁስሎቹ ነበሩ እነዚህ ቁስሎች በጣም ያሙት ስለነበር ቆዳውን ሲነካቸው ያመው ነበር ።

ወጣቱ እነዚህ እጆች የእርሱ ትምህርት ገንዘብ ለመክፈል በየቀኑ መሥራት ምን ማለት እንደሆነ ሲያውቅም ይህ የመጀመሪያው ነው።

የአባቱ እጆች ላይ ያሉት እብጠቶች አባቱ ለእርሱ ትምህርት መሰረታዊ፣ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ለወደፊት ህይወቱ የከፈለው ዋጋ ነው!!!

ወጣቱ የአባቱን እጅ ካጸዳ በኋላ ለጠቂት ያክል በዝምታ ቆመ ።ከዚያም የአባቱን የስራ መስሪያ ቁሳቁሶች ማፅዳት ጀመረ። በዚያ ምሽት ላይ አባትና ልጅ ለረጅም ሰዓታት ተነጋገሩ፣ አብዛኛውን የምሽቱን ክፍለ ጊዜ በጨዋታ እና በውግ አሳለፉ ።

በማግስቱ ጠዋት ወጣቱ ወደ ዳይሬክተሩ ቢሮ ሄደ።
ዳይሬክተሩ የወጣቱ አይን እንባ ሲያቀር አስተዋለ ።

ዳይሬክተሩ:- ትናንት ቤትህ ውስጥ ያደረግከውን ሁሉ ልትነግረኝ ትችላለህ?
ልጁም 'የአባቴን እጅ አጥቤ ስጨርስ የአባቴን የስራ መገልገያ( አውደ ጥበቡን )አጸዳሁ' ሲል መለሰ።

ዳይሬክተሩ :- ከዚህ ምን ተማርክ ?
ወጣቱ :- ወላጆቼ ባይኖሩ ኖሮ ዛሬ ላይ እኔ
[እኔ እንደማልሆን] ተረዳሁ ።በዚህም አባቴን በመርዳት አንድ ነገር በራሴ ማድረግ ምን ያህል ከባድ እና ከባድ እንደሆነ አሁን ተገነዘብኩ። ቤተሰቤን የመርዳትን አስፈላጊነት እና ጥቅም ተገነዘብኩ አለ ።

ዳይሬክተሩም "በድርጅቴ የምቀጥረው እና በድርጅቴ ውስጥ እንዲኖር የምፈልገው ይህንን ነው,።እርሱ የሌሎችን እርዳታ የሚያደንቅ፣በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ለእኛ ሲሉ ብቻ የእነሱ ያልሆኑ ሌሎች ነገሮችን ለማከናወን ሲሉ የሚደርስባቸውን ችግር እና ስቃይ የሚያውቅ ሰው መቅጠር እፈልጋለሁ አለ ።

ሁላችንም የራሳችንን ሸክም መሸከም ስንጀምር ለወላጆቻችን ልፋት ዋጋ መስጠት እንጀምራለን
1.4K viewsTeshe ......, 08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 22:48:44 የልጅነት የኳስ ጨዋታ ህጎች!

1 ምንጊዜም ሰፈር ውስጥ ወፍራሙ ልጅ ጎል ጠባቂ ነው።

2 ሁልጊዜ ጨዋታ የሚያልቀው ሁሉም ተጫዋች ከደከመው  ብቻ ነው።

3 አስር ጊዜ ጎል ስታስገባ ብትውልም የሚያሸንፈው መጨረሻ ላይ ጎል ያስገባው ቡድን ነው።

4 ዳኛ ቢኖርም በጩህትና በጭቅጭቅ ያሳመነው ያሸንፋል።

5 ምንጊዜም የኳሱ ባለቤት ካኮረፈና ከተበሳጨ  ጨዋታው ያልቃል።

6 ሁለት ጎበዝ ተጨዋች አንድ ቡድን ውስጥ መጫወት በልጅነት ህግ የተከለከለ ነው።

7 ድንገት ተቃራኒ ቡድኑ ፔናሊቲ ካገኘ የኳሱ ባለቤት ከመቅፅበት ጎል"ጠባቂውን አባርሮ ራሱ ጎል ጠባቂ ይሆናል።

8 ኳሱ ፎሪ ወጥቶ የሰው ግቢ ውስጥ ከገባ ያስገባው ልጅ ሙሉቀንና ሙሉ ለሊት ሸፋፋ እየተባለ ሲሰደብና ሲረገም ይውላል።

9 ምንጊዜም በጣም ጎበዙ ተጫዋች የኳሱ ባለቤት ጋር አንድ ቡድን ናቸው።

10 ጨዋታው አንዱን ቲም ከተቃራኒው ለመለየት አንዱ ቲም ከወገብ በላይ ራቁቱን ይጫወታል።

11 ምንጊዜም ጨዋታ የሚጀመረው ኳሷን ወደ ሰማይ በመጠለዝ ነው።

12 አጥቂ ተከላካይ የሚባል የለም ሁሉም ያጠቃል ሁሉም ይከላከላል የደከመው ወገቡን ይዞ በረኛውን ያወራዋል።

13 ምንጊዜም የኳሱ ባለቤት FIFA በለው።

14 ኦፍ ሳይድ የለም ግር ብለህ ታጠቃለህ ግር ብለህ ትከላከላለህ ግሪሳ ሁላ።

15 ድንገት በጨዋታ መሃል እናትህ ከጠሩህ ሰው ተክተህ ትሄድና ስትመለስ የተካህውን ሰው አባርረህ ጨዋታውን ከቆምክበት መቀጠል ትችላለህ።

ጨምሩበት!
427 viewsTeshe ......, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 07:35:44
ቢኒያም ዶንኪ ቲዩብ ላይ አስሮ እየገረፈን ነው።

"ቀኑን ሙሉ ለሚተኛ ሰው ማጨብጨብ አይከብዳችሁም? ለእኔ ማልቀስ ነው ያለባችሁ።.....ትጋት ከእሸቱ መማር አለብን። ስለራሴ ድክመት ነው ማውራት ያለብኝ። እንደ መቄዶንያ እኛ ዜሮ ነን። ከዜሮ በታች ታውቃላችሁ? የሞት ፍርድ የሚገባው ሰው ማለት እኔ ነኝ።" ይኽን የሚለው ቢኒያም ነው። እሱ ራሱን በስንፍና ከወቀሰ ማን ሊተርፍ ነው? ኧረ ተው ቢኒ ትህትናም ልክ አለው። አስብልን። You are Angel of our clan.

እኛ ስናጎርስ እንኳን ፎቶ የምንነሳ የታይታ ዘመን ሰዎች፣ ይኽን ሁሉ የሰራ ሰው አሳፋሪ ሰው ነኝ ሲል ከፍተኛ ቶርቸር ነው። አናሳዝንህም ወይ? ለምን በሰላም ዋላችሁ ብለው በስልጣናቸው ሕዝብ የሚበድሉስ ምን ይበሉ?

እግዚአብሔር ብድራቱን ይክፈልህ። ስለ አንድ ጻድቅ እግዚአብሔር ይምራል። ስላንተ ይማረን። ስለ ሌላም በድብቅ ስለሚተጋ ይማረን። መቄዶንያ ስላሉ አባቶችና እናቶች ሲል ይማረን። ስለህጻናት እና ስለ አልጋ ቁራኛ ሰዎች ሲል ይማረን።
Via Yohannes Molla
1.6K viewsTeshe ......, 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ