Get Mystery Box with random crypto!

ማዕደ ሰማይ

የቴሌግራም ቻናል አርማ elgraceministry — ማዕደ ሰማይ
የቴሌግራም ቻናል አርማ elgraceministry — ማዕደ ሰማይ
የሰርጥ አድራሻ: @elgraceministry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 882
የሰርጥ መግለጫ

#በፀጋ ነው
#ፀጋው ብቻ
#የታደገን ከዓለም ጡጫ።
#በፀጋ የዳነ
#ያለፀጋ አይፅፍም
#ያዳነው እያለ
#የዳነው አይነግስም፤
#ባለፀጋው #ባይኖር
#እኔም ችዬ አልኖርም።
እንዳለው እንድኖር
ጸጋ አለ የሚያኖር።
http://t.me/ElgraceBot
ለአስተያየቶ በዚህ 👇 ይላኩልኝ።
@Surtsega
@Surafeltsegamets

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 22:00:14 የማሸነፊያ ምስጥር

አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጎበዞች ሆይ፥ ክፉውን #አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ #አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።

1ኛ ዮሐንስ 2 ፥ 13 - 14
¯¯¯¯¯¯¯¯
ወዳጆቼ ሆይ ጉብዝናችሁ እንዴት ነው? የት ውሎ ፤ የት ያድራል? በበረታችሁበት ጊዜ መሮጥ መታገል መማርና መለወጥ በምትችሉበት ዘመን ምን አደረጋችሁበት?
ክፉውን አሸንፋችሁበታል?

ጎበዞች በብርታታችሁ ላይ የጉልበታችሁን ነዳጅ ሆነ ፍሬን ሊሆን የተገባውን የማሸነፊያ ምስጥር ልንገራችሁ? -------- የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። ቃለ እግዚአብሔርን መርህና መልህቅ ያላደረገ ጉብዝና ፍሬን እንደበጠሰ ከፍተኛ ተሽከርካሪ ነው።

አስባችሁታል? የአቅም እና የመንገድ ማጣት ሳይሆን የሚያስቆመንን ኃይል #አለመገናኘት መኪናውንም ተሳፋሪውን ብሎም ተራማጅ መንገደኛም ይፈጃል።

ከሰሪህ እንደተበጀልህ ስሪት በጉብዝና ወራት ይሰምርልህ ዘንድ የሰሪህ እስትንፋስ የተሸከመውን ቃሉን በልብህ ጽላት ላይ ጻፈው። ቃሉን ቀን እና ሌሊት አስበው አሰላስለው። በውንህም በህልምህም ተቆራኘው።

#ስኬት የአሰብከው ነገር ጋር መድረስ ሳይሆን ቃሉ ያወራህን መኖር፤ በቃሉም ያሰበልህን አውቀህ እርሱንም መሆን ነው።

#ልብ_በል ድልህን ሳይሆን የድሉን ባለቤት (ቃሉን በልብ ጽላት ላይ ከትቦ፥ በሙላቱ በመመላለስ) የሙጥኝ ማለት #እያሸነፉ ዘላለምን መዝለቅ ነው።

@elgraceministry
@elgraceministry
346 viewsሱራፌል ወርቁ ጸጋ, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 16:09:53 #ስለ_መጽሐፍ_ቅዱስ

❖ የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
• 66 መጽሐፍት
• 1,189 ምዕራፎች
• 31,173 አንቀፆች
• 810,697 ቃላት
• 3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ።

❖ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን
• በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ
• በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119
• አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው።

❖ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው።

❖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው።

❖ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው።
ይኸውም፦
• መጽሐፍ ቅዱስ #66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ #66 ምዕራፎች አሉት።
• የመጀመሪያው #39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ #39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው።
• የመጨረሻው #27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ #27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21)

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" #30 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ "ድመት" ብቻ ናት።
ውሻ #14 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ
እነርሱም፦
1. አቤሜሌክ
2. ሳምሶን
3. ሳዖል
4. የሳዖል ወታደር
5. አኪጦፌል
6. ዚምራ
7. ይሁዳ ናቸው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ
ስለ ፀሎት 400 ጊዜ
ስለ እምነት 500 ጊዜ
ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው።

ምንጭ፦ ቅዱሳን መፅሐፍት

@elgraceministry
@elgraceministry
550 viewsሱራፌል ወርቁ ጸጋ, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 09:38:33 #እግዚአብሔር_ታላቅ

እግዚአብሔር የአብርሃም ማርጀትም ሆነ የሳራ የሴትን ወግ ማየት ማቆም አያስደነግጠውም። እርሱ በየትኛውም ጊዜ የሚሰራ በማንም አቅም የማይመረኮዝ ደግሞም ዘገየሁ ብሎ በሰው ጊዜ የማይደናበር የሰማይ አባታችን ነው።

ለስራው በራሱ እንጂ በማንም የማይምል እመጣለው በአለበት ጊዜ በባዶ እጁ የማይመጣ በዘመናት መሃል ዘመን ወርዋሪ ምጡቅ ነው።

ከዘመን ውጪ እየኖረ በዘመን መሃል የሚሰራ የሰማይ ልዑል እግዚአብሔር ዘመም ያለውን ዘመናችሁን ቀና ቀና ያድርግላችሁ።

@elgraceministry
@elgraceministry
770 viewsሱራፌል ወርቁ ጸጋ, 06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 09:48:59
ታዘብንሽ

ታዘብንሽ ግን አለም፥
አሁንም አልሞላሽም፤
አለው ደላው ያልነውም፥
አላረፈብሽም።

ዘወትር ከርታታ ላፍታም ዕረፍት የለሽ
መሽቶ እየነጋም አለሽ ተቅበዝብዘሽ።

መላ ያልሽው ፈጥሮ ቁስል
ያኖርሽውን ሲያመሳቅል

ጠቢባንሽ ደም ሲያቃቡ
ጎዳኖችሽ ሰላም ጤና እንደተራቡ
ሳቅሽ ራሱ ሀዘንሽን እያሳበቀ
ሀሴት ከአንቺ እንደራቀ።

በቅብ ምስል በሽውሽው
ያጀበሽን እያሳወርሽው
እያታለልሽው
በአቦ ሰጠኝ እየመራሽው

ዛሬም ወናፍ ከንቱ ለፊ
በሞት መንገድ ህይወት ሽቶ ተሰላፊ
እውነት አልባ ወሸት ሰፊ
በሺ ዘመን ለሺ ዘመን ነሽ ቀጣፊ

ታዘብንሽ አለም ታዘብንሸ

ይብላኝ እንጂ
አንቺን
ዛሬም ድረስ በልቡናው ላደመቀ
የተናቅሽውን ላገዘፈ
ውጥን ስርሽን ላላወቀ።

እኛስ ለይተናል ሰፊውን ከጠባብ
መንገድ አንስትም ተወጥረን በሀሳብ።

በህይወት ጎዳና በጠበበው ገብተን
የታረደውን በግ
ክርስቶስ ኢየሱስን እንጠብቃለን።


━━━━⊱✿⊰━━━━━
@elgraceministry
@elgraceministry
805 viewsሱራፌል ወርቁ ጸጋ, 06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 22:19:29


በአዳም ዕንቅልፍ
ሔዋን ተሰራች
በኢየሱስ መሞት
ነፍሴ ነፍስ ዘራች።

በአዳም መሳሳት
ፍጥረት ወደቀ፥
በኢየሱስ ስራ
አማኝ ጸደቀ።

በአዳም አለመታዘዝ
የአብ ፊት ጠቆረ
ኢየሱስ ግን ለአብ ደስታ
እስከሞት ታዘዘ።

በአዳም ድኩምነት
ኃጢአት የሚገዛውን
ዘር ቁጥር ጨመረ
በኢየሱስ ድል መንሳት
ወንጌል ተበሰረ።

በኢየሱስ መሞት
በክርስቶስ ዝምታ
አብ #ተማለደ፥
በመስቀል ላይ ጣሩ
በፈጸመው ግብሩ
አምኖ የመሰከረ ዳግም #ተወለደ።

በአዳም ፍሬ ውስጥ
የዕባብ ተንኮል እንዳለ
በኢየሱስ ድል መንሳት
መንፈስ ቅዱስ አለ።

ሔዋን ከእባብ ገጥማ
ከኤደን ገነት እንደ ተሰረዘች፥
በኢየሱስ ዝምታ፤
ነፍሴ በአብ ቀኝ ተቀመጠች።

እባብ በተንኮሉ ሔዋንን ሲያስታት
ኢየሱስ በጸጋው
አለምንን ሊያስክዳት
#የኔን_ነፍስ_ተቤዣት።

አዳም ዕርቃን ሆኖ ከአብ ዕቅፍ እንደራቀ
ኢየሱስ
ስለእኛ ዕርቃኑን መስቀል ላይ ማቀቀ።

ኢየሱስ
#ሲራቆት ለእኛ ልብስ ሆነ
#ሲቆስል የእኛ ደዌ ዳነ

#በመገረፉ ግርፋታችንን ሻረ
#ጽድቃችን_በመሆን በአብ ዘንድ ከበረ።

አዳም በስራው
እኛን ሞት ሲግተን
ኢየሱስ በሞቱ
ክርስቶስ በስራው
ህይወትን ሸለመን
ሊያውም ያልተገባን ሳለን።
ከማንኛው አለን?
ከየትኛው ተዛመድን?

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@elgraceministry
@elgraceministry
1.1K viewsሱራፌል ወርቁ ጸጋ, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 21:15:19
#የበጉ_ሙሽሪት

አንቺ የሙሽራሽ ሙሽሪት፤
የምድር ጨው
የዓለም ብርሃን ሰማያዊት፤

ሰማይን ማያ በምድር ያለሽ
አብም በልጁ ርዕስት የሆነሽ

መልክሽን ሊያነጣ መልኩን ያጠቆረ፤
ሞትሽን ሊሽር ከመስቀል የዋለ፤

ሙሽራ አለሽና ደም የከፈለልሽ፤
ነፍሱን ሰውቶ ነፍስን የዘራብሽ፤

በጌቴሴማኒ የደም ላብ ያላበው፤
በቀራንዮ በጎልጎታው
የአንቺን ቁስል የቆሰለው፤

ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ
እርሱ እያነባ አንቺ ስትድኚ

የተተወ
የተጠላ
የተናቀ
ደም ግባቱን ያጣ
የውበት ዳርቻ

መሪር የሞት ጽዋን
ያለኃጢአቱ የጨለጠ
ላመኑበት ልጅ መሆንን
ሰርቶ የሰጠ

በዋኖስ ደም ደጀ ሰላም እንዳትጠኚ
በአንድ ምልጃው ለዘላለም እንድትድኚ

ቁጣ አብርዶ የአብን ፊት ሊመልሰው
ራሱን ለአንቺ የቆረሰው

ሞገስ የሆነልሽ
የማያረጅ ዝርግፍ ጌጥሽ

በክብር በደመና በኃይል ታጀቦ
ይመጣል ሙሽራሽ
ይመጣል ክርስቶስ ጊዜውን አስቦ
በታላቅ ብርሃን እጅጉን ተውቦ።

እናልሽ

ደሙን ማክፋፋቱን
ለወንጌል መክፋቱን
ደጀ ሰላም መዝጋቱን
ለክብር ለድል መኳተኑን

እንዳይበጅሽ
እንዳይረባሽ
አውቀሽ ንቂ
ጊዜ የለሽም ተጠንቀቂ።

ተማልደሽ በትኩስ ደሙ፤
ተደምጠሽ በጻድቅ ስሙ፤

አንጽተሽ መፈለግ መኳተኛሽን
ጓጉተሽው ጽዮን ቤትሽን

በማነፅ ድንኳን ዓለምን ንቀሽ
በትኩራትሽ በጉን ተሳልመሽ

በመጓጓት ጠብቂው፣
ግድየለም፣
አይቀርም፤
እንዳለሽ ይመጣል፣
ላይመጣ፣
አይቀጥርም።

ሁሉም አይቀጥልም
ሰርክ አዲስ ይሆናል
ሙሽራሽ ሊያከብርሽ
ሊወስድሽ ይመጣል።

በትግስት በንቃት ጠብቂ
እርሱን ብቻ ናፍቂ

ጽዮንን ናፍቀሽ በድንኳን ኑሪ
በምድር ምጻተኛ ነሻ ሰማያዊ

@elgraceministry
@elgraceministry
@elgraceministry
668 viewsሱራፌል ወርቁ ጸጋ, 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 14:13:13 #እግዚአብሔር_እኮ

እግዚአብሔር የምኞታችን መፈጸምያ በትር ሳይሆን የሰማይ ፍቃዱን ለማድረግ እኛን በማክበር የሚጠቀምብን
በስራው ቀን ገንዘብ አድርጎ ለስራው የሚሾመን እጅ ታማኝ እና ታላቅ አምላክ ነው።

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@elgraceministry
@elgraceministry
1.5K viewsሱራፍኤል ወርቁ ፀጋ, 11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 22:47:26 የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ

አንቀጽ ፩
እኔ ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ፡፡¹

አንቀጽ ፪፦
ደግሞም በአንድ ልጁ² ፣ በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰ፣ ከድንግል ማርያም በተወለደ³ ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበለ⁴ ፣ በተሰቀለ⁵ ፣ በሞተ እና በተቀበረ፤ ወደ ሲዖልም በወረደ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን በተነሣ፡፡⁶ ወደ ሰማይም በወጣ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በተቀመጠ⁷ ፣ ከዚያም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በሚመለስ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፡፡⁸

አንቀጽ ፫፦
ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ⁹ ፣ በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ፣ በቅዱሳን አንድነት¹⁰ ፣ በኀጢአት ስርየት¹¹ ፣ በሥጋ ትንሣኤ¹²፣ በዘላለም ሕይወት አምናለሁ፡፡¹³ አሜን!

የመጽሐፍ ቅዱስ ማጣቀሻዎች
¹ ራዕ ፬÷፲
² ፩ ዮሐ ፬÷፱ ፤ ዮሐ ፩÷፲፰
³ ማቴ ፩÷፲፰፣፳፤፪÷፲፩ ፤ ሉቃ ፩÷፳፯፣፴፬
⁴ ሐዋ ፬÷፳፯-፳፰ ፤ ማቴ ፳፯÷፪
⁵ ማቴ ፳፰÷፭ ፤ ፩ ቆሮ ፩÷፳፫
⁶ ዮሐ ፲፱÷፴፫ ፤ ፪ ቆሮ ፭÷፲፬-፲፭ ፤ ፩ ቆሮ ፲፭÷፫ ፤ ሐዋ ፪÷፳፯ ፤ ፩ ተሰ ፬÷፲፬ ፤ ሮሜ ፰÷፴፬
⁷ ዮሐ ፫÷፲፫ ፤ ኤፌ ፬÷፲ ፤ ማር ፲፮÷፲፱ ፤ ሉቃ ፳፬÷፶፩ ፤ ሮሜ ፰÷፴፬ ፤ ቆላ ፫÷፩ ፤ ዕብ ፩÷፫፣፰÷፩፣፲÷፲፪፣፲፪÷፩-፪ ፤ ፩ ጴጥ ፫÷፳፪
⁸ ፪ ጢሞ ፬÷፩ ፤ ሐዋ ፲÷፵፪
⁹ ሐዋ ፲÷፴፰፣፩÷፭፣፪÷፴፫፣፲፫÷፪ ፤ ዮሐ ፲፬÷፳፮ ፤ ቲቶ ፫÷፭
¹⁰ ሮሜ ፲፪÷፭ ፤ ቆላ ፩÷፲፰ ፤ ኤፌ ፭÷፳፯፣፬÷፲፪-፲፫፣፪÷፳ ፤ ፩ ቆሮ ፲፪÷፳፰ ፤ ዮሐ ፲፯÷፲፩-፳፫
¹¹ ማቴ ፳፮÷፳፰ ፤ ሐዋ ፲÷፵፫፣፲፫÷፴፰-፴፱ ፤ ኤፌ ፩÷፯ ፤ ቆላ ፩÷፲፫-፲፬
¹² ፩ ቆሮ ፲፭÷፲፪-፶፰
¹³ ዮሐ ፲፯÷፪-፫፣፫÷፴፮፣፭÷፳፬፣፮÷፵


━━━━⊱✿⊰━━━━
@elgraceministry
@elgraceministry
768 viewsሱራፌል ወርቁ ጸጋ, 19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 23:51:28 #አልፋና_ኦሜጋዬ

ጆሮዬ ከዝናህ
አይኔ ከዝናርህ እንደተሰፋፉ፤
ሰማይና ምድር
ተጠቅልለው ይለፉ።

━━━━⊱✿⊰━━━━━
@elgraceministry
@elgraceministry
1.8K viewsሱራፌል ወርቁ ጸጋ, 20:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:51:48
Graphic by @FOR_EVER67
@GOSPEL_PICTURES
@GOSPEL_PICTURES
479 viewsሱራፌል ወርቁ ጸጋ, 17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ