Get Mystery Box with random crypto!

NEW PHARMACY and NURSING

የቴሌግራም ቻናል አርማ newepharmacy — NEW PHARMACY and NURSING N
የቴሌግራም ቻናል አርማ newepharmacy — NEW PHARMACY and NURSING
የሰርጥ አድራሻ: @newepharmacy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.70K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ግሩፕ :- 👉 ጤና ነክ ትምህርቶች
👉 coc ጥያቄ ከነ መልሶቻቸው
👉 update information
👉 አዳዲስ የስራ ማስታወቂያ
ለማንኛውም አስተያየት @EBROGC

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 18:01:18 ጠያቂ

"የሸረሪት በሽታ "Shingles ምንድን ነው

እስኪ እንወያይበት
250 views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:30:12

571 views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:18:16 ፎቢያዎች (Phobias)
===============
ፎቢያ ለአንድ ነገር ወይም ሁኔታ ምክኒያታዊ ያልሆነ ከፍተኛ ፍርሀት ማለት ሲሆን የአንዳንድ ሰዎችን ህይወት ከባድ ሊያደርገው ይችላል።

።።። ።።። የተወሰኑ ፎቢያዎች እነሆ፦
•አኩሎፎቢያ (Achulophobia)- የጨለማ ፍርሀት
•አክሮፎቢያ (Acrophobia)- የከፍታ ፍርሀት
•አውቶፎቢያ (Autophobia)- የብቸኝነት ፍርሀት
•ክላስትሮፎቢያ (Claustrophobia)- ትፍግፍግ ያለ ቦታ ፍርሀት
•ሳይኖፎቢያ (Cynophonia)- የውሻ ፍርሀት
•ኢሉሮፎቢያ (Elurophobia)- የድመት ፍርሀት
•ጋሞፎቢያ (Gamophobia)- የትዳር ፍርሀት
•ሄሞፎቢያ (Hemophobia)-የደም ፍርሀት
•አያትሮፎቢያ (Iatrophobia)-የዶክተር ፍርሀት
•ሎኪኦፎቢያ (Lockiophobia)- የምጥና የመውለድ ፍርሀት
•ሙሶፎቢያ (Musophobia)- የአይጥ ፍርሀት
•ኔክሮፎቢያ (Necrophobia)- የሞተ ነገር ፍርሀት
•ኦፊዲኦፎቢያ (Ophidiophobia)- የእባብ ፍርሀት
•ፓቶፎቢያ (Pathophobia)- መታመምን መፍራት
•ፊሎፎቢያ (Philophobia)- የፍቅር ፍርሀት
•ፎቦፎቢያ (Phobophobia)- የፍርሀት ፍርሀት
•ፖለቲኮፎቢያ (Politicophobia)- የፓለቲከኞች ወይም የፓለቲካ ሂደት ፍርሀት
•ስኮሊኦኖፎቢያ (Scolionophobia)- የትምህርት ቤት ፍርሀት
•ትሪፓኖፎቢያ (Trypanophobia)- መርፌ የመወጋት ፍርሀት
•ታናቶፎቢያ (Thanatophobia)- የሞት ፍርሀት
•ዜኖፎቢያ (Xenophobia)- መጤ የሆነ ሰው ፍርሀት

ፎቢያዎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ብቻዎን እንዳልሆኑ ያስታውሱ፡፡ ከመቶ ሰዎች አስሩ የሆነ አይነት ፎቢያ እንደሚኖራቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ያለ መድሀኒት በንግግር ህክምና (Psychotherapy, specifically behavioral therapy) ሊታከሙ ይችላሉ፡፡

@NEWEPHARMACY
@NEWEPHARMACY
@NEWEPHARMACY
624 views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 09:17:48 'የሚጥል ህመም’ ላለበት የክብሪት ጭስ ማሸተት ይጠቅማል?

የሚጥል ህመም /EPILEPSY/

የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች ያለጊዜ የመሞት እድላቸው ከጠቅላላ ሕዝብ በ 3 እጥፍ ይበልጣል ፣ ነገር ግን ለሞት መንስኤ የሚሆኑትን ነገሮች (እንደ ከከፍታ መውደቅ ፣ መስመጥ ፣ በጋለ ነገር መቃጠል ፣ የመኪና አደጋ ፣ስብራት፣ የአየር ቧንቧ መዘጋት ፣ መደፈር እና የመሳሰሉትን) መከላከል ይቻላል።

እንዴት?

የሚጥል ህመም /EPILEPSY/ የአንጎል ነርቭ ጊዜያዊ ኤሌክትሪካል ንዝረት እንጂ የክፉ መንፈስ ውጤት አይደለም ! ከሰው ወደ ሰው ተላላፊም አይደለም። ስለዚህ የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች እራሳቸውን ስተው ባዩ ጊዜ ችላ አይበሏቸው።

መደረግ ያለባቸው የመጀመሪያ እርዳታዎች

- ከጭንቅላት ስር ለስላሳ ትራስ ነገር ማድረግ
- ሲንፈራገጥ ራሱን እንዳይጎዳ በዙሪያው ያሉ ሊጎዱት የሚችሉ ነገሮችን (እሳት፣ ኤሌክትሪክ፣ ስለታማ ነገሮችን) ማስወገድ

- እንዳይንፈራገጥ በኃይል ለመያዝ አለመሞከር (የአጥንት ወይም የጡንቻ ጉዳት ሊያስከትል ይችላልና)
- አንገት አካባቢ ያሉ የልብስ ቁልፎችን ማላላት ፤ መነፅሩን ማዉለቅ

- መንቀጥቀጡ ከቆመ በኃላ እስኪነቃ ድረስ በጎኑ ማስተኛት( የአየር ቧንቧ እንዳይዘጋ ለማድረግ)

- ክብሪት አለማሽተት (የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው ወድቆ ሲንፈራገጥ የመተንፈሻ አካሉ በምራቅ አረፋና በምላስ ሊዘጋ ይችላል ፤ የክብሪት ጪስ ሲጨመርበት ይባሱን ይዘጋል ፤ ጪሱ በራሱም አንጎልን የሚጎዱ ኬሚካሎች አሉት)

- ህመምተኛው እስኪነቃ ድረስ አብሮ መቆየት
-ህመምተኛው ከነቃ በኋላ ማረጋጋት

- መንቀጥቀጡ ከ 5 ደቂቃ በላይ የሚረዝም ከሆነ ወይንም የታማሚዉ የቆዳ ቀለም ወደ ሰማያዊነት ከተለወጠ በአስቸኳይ አምቡላንስ መጥራት

ከ care epilepsy, ethiopia ፅሁፍ የተወሰደ.

By EBRO


t.me/NEWEPHARMACY
1.6K views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 18:21:22 የሚጥል ህመም " ላለበት የክብሪት
ጭስ ማሸተት ይጠቅማል ወይስ ጠቃሚ አይደለም ?? ለምን

Comment ላይ እንወያይበት
808 views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 16:01:09
Share
Share

Join
Join
@NEWEPHARMACY
1.3K viewsedited  13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 16:00:31 ለምፅ | Vitiligo

ለምፅ ከተወለድን በኋላ የሚከሰት (acquired) የቆዳ ቀለም ባለመመረቱ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው

ለምፅ በንክኪ አይተላለፍም

ለምፅ ከህጻናት ጀምሮ በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ሊታይ ይችላል

ለምፅ በምን ምክንያት ይከሰታል?

ምክንያቱ ይሄ ነው ተብሎ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ፤ የተለያዩ መላምቶች እንደምክንያት ይጠቀሳሉ፤ከነዚህም መካከል "የሰውነታችን በሽታ የመከላከያ ስርአት (immunity system) የራሳችንን የቆዳ ቀለም አምራች ህዋሳትን(melanocytes) በሚያጠቃበት ጊዜ የሚከሰት የቆዳ ህመም ነው" የሚለው መላምት በይበልጥ ተቀባይነት አለው።

በዚህም ምክንያት ለምጽ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚከሰቱ ሌሎች ህመሞች (autoimmune diseases) ጋር ተያያዥነት አለው ተብሎ ይታሰባል ፤ ለምሳሌ ከየስኳር ህመም፣ የእንቅርት ህመም (autoimmune type)፣ ላሽ (alopecia areata)....

ለምፅ ከጭንቀት (emotional stress)፣ ከእርግዝና፣ ከአደጋ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል

የለምፅ ምልክቶች

ለምጽ ያለበት ቦታ ወደ ነጭነት የሚያደላ ቀለም ሲኖረው ከዚህ ውጪ ማሳከክ ወይም ቦታው ላይ ቅርፍቶች መኖር የለምጽ ባህሪ አደለም

በማንኛውም የቆዳችን ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል

ለምፅ አንድ ቦታ ላይ ብቻ (focal)፣ በግራ ወይም በቀኝ የሰውነት ክፍል ብቻ (segmental) ወይም አብዛኛው የቆዳችኝ ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል

የለምፅ ህክምና

የህክምናውን አይነት የሚወስኑ ሁኔታዎች ፦
የህመሙ ጥንካሬ (severity)
እየተስፋፋ መሆኑ ወይም ባለበት መቆሙ
የህክምናው በቀላሉ መገኘት እና የህመምተኛው የመክፈል አቅም...

የህክምና አይነቶች
የሚዋጥ
የሚቀባ
Phototherapy (ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ ብርሀንን በመጠቀም የሚሰጥ ህክምና)
Excimer laser
የቀዶ-ጥገና (surgery) ህክምና

የማንጣት ህክምና (depigmentation)
አብዛኛው የሰውነት ክፍል በለምፅ ከተጠቃ እና ለማከም አስቸጋሪ ከሆነ ጤነኛውን የቆዳ ክፍል በማንጣት የማመሳሰል ሂደት ነው (Michael Jackson ይህ ህክምና ተደርጎለታል)

ስለህክምናው ሂደት ማወቅ ያለብን

ህክምናውን ከጀመርን በኋላ የህክምናውን ውጤት ለማየት ከ 2-3 ወር ሊፈጅ ይችላል

ጠቅላላ ህክምናው ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ያለማቋረጥ መከታተል ያስፈልጋል

ህክምናው ከተጠናቀቀ በኋላ ለምፁ እንደገና ሊመለስ ይችላል

ከንፈር ላይ፣ጣት ላይ እንዲሁም ከቆዳው በተጨማሪ ፀጉርም አብሮ ነጭ ከሆነ የመዳን እድሉ ዝቅተኛ ነው

ለምፅን ባንታከምስ?

ለምፅ ከፍተኛ የሆነ የስነ-ልቦና ጫና ያሳድራል
እየሰፋ ሊሄድ ይችላል
ቆዳችን በፀሐይ ጨረር እንዲጠቃ ሊያረግ ይችላል (ፀሐይ መከላከያ/sunscreen መጠቀም ያስፈልጋል)

በመጨረሻም

ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል
for #comment @EBROGc


t.me/NEWEPHARMACY

፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
1.1K viewsedited  13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:30:49
1. prescription paper
2.
929 views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:12:40
1.2K views06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:08:26 ድንገተኛ የፊት መጣመም (bells palsy) ምንድን ነው?

- አንዳነዴ ሰምተን ከሆነ መጋኛ መታው፣መጋኛ ፊቱን አጣመመው ሲባል ሰምተን ሊሆን ይችላል። የዚህን ነገር ሳይንሳዊ ትንታኔ በጥቂቱ ይዤላቹ ቀርቢያለሁ።

-ፊታችን ከጭንቅላታችን በሚነሱ ነርቮች አማካኝነት የእለት ተእለት ተግባራትን ይከውናል። ከጭንቅላታችን የሚነሱ 12 የጭንቅላት ነርቮች (cranial nerves) አሉ። ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ነርቮች የፊታችንን እንቅስቃሴ ያዛሉ፣ ይቆጣጠራሉ። ፊታችን ቀስ በቀስ ወይም በድንገት ሊጣመም ይችላል።

-ድንገተኛ የሆነ የፊት መጣመም (bell's palsy) የምንለው በአንድ በኩል የሚገኘውን የፊት ጡንቻዎች መድከም ፣ መስነፍ ወይም መዛል ሲሆን የፊታችንን ቅረፅ የሚቀይር ከአንጎል ከሚነሱት 12 ነረቮች አንዱ የሆነው ሰባተኛው ነርቭ (facial nerve) ብግነት ወይም እብጠት ምክንያት የሚመጣ የነርቭ ህመም ነው።

ይህ ችግር በማንኛውም የእድሜ ክልል ሊከሰት የሚችል ፣ ግማሽ ፊታችን ወይ በቀኝ ወይም በግራ ፊት እነዳይታዘዝ የሚያደርግ ህመም ነው ፣ ይህም ፊታችንን የሚመግቡ ነርቮች (nerve supplies) ከጭንቅላታችን ሲወጡ በሚከሰት ጫና ወይም ጉዳት ሊከሰት ይችላል።

ምክንያቶቹስ ምንድን ናቸው?

-ይህ ነው የሚባል ምክንያት ባይቀመጥም አንዳንድ ኤክስፐርቶች በአንድ በኩል የሚገኘውን የፊታችንን ጡንቻ የሚቆጣጠረው ነርቭ ሲቆጣ ፣ ወይም እብጠት ሲኖረው ነው ብለው አሰቀምጠዋል። ይህም በተለይ በቫይረስ ኢንፌክሽን አማካኝነት ነው ተብሎ ይታሰባል።

እእነዚህ ቫይረሶች ለምሳሌ Herpes simplex virus,herpes zosther, episten barr virus, CMV virus, mumps virus, adeno virus ይጠቀሳሉ።

ተጋላጭ ሰዎችስ እነማን ናቸው?

-ነፍሰጡር እናቶች ፣ የላይኛው የመተነፈሻ አካል ኢንፌክሽን ፣ ስኳር ፣ ደም ግፊት እና ከመጠን በላይ ውፍረት ያለባቸው ሰዎች ፣ ተጋላጭ ናቸው ተብሎ ይታሰባል።

ምልክቶቹስ?

-በአብዛኛው ጊዜ ምልክቶቹ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በተወሰነ መልኩ ይመለሳል ተብሎ ይታሰባል። ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበረበት ለመመለስ ሳምምነታት ወይም ወራት ይፈጃል ተብሎ ይታሰባል። የተወሰኑ ሰዎች ላይ ደግሞ እስከ ሂወት ዘመን ሊቆይ ይችላል።

-ድንገተኛ የሆነ በአንድ በኩል ብቻ የፊት መድከም ፣ መስነፍ ፣ የፊት መውደቅ ፣ ጉነጭ በአየር መሙላት መቸገር ፣ መሳቅ ፣ ፈገግ ማለት ፣ እና ሌሎች የፊት እንቅስቃሴዎች ለማድረግ መቸገር ፣ የፊት መደንዘዝ ፣ የአንድ አይን መክደን አለመቻል ፣ የምራቅ መዝረክረክ ፣ ማፏጨት አለመቻል ፣ የአፍ በአንድ በኩል መውረድ ፣ በግነባር መኮሳተር አለመቻል ፣ ከጆሮ ጀርባ አና መንጋጭላ አካባቢ የህመም ስሜት ፣ እራስ ምታት፣ ጣእም ለማጣጣም መቸገር ፣ የእንባ እና የምራቅ መጥን መለወጥ ፣ ሊኖሩ ይችላሉ።

የሚያመጠውስ መዘዝ?

-የፊት ነርቭ በቋሚነት መጎዳት
-የነርቭ ዘንጎች በትክክል አለማደግ
-የአይን መድረቅ ፣ የአይን ኢነፌክሽን ፣ መታወር ድረስ ሊደርስ ይችላል።

ምርመራዎቹስ?

-የጤና ባለሙያው ከታካሚው ታረክ በመውሰድ እና አካላዊ ምርመራ ከተደረገ በዃላ እንደ አስፈላጊነቱ ምን አልባት አጋላጭ ምክንያቶችን ለማወቅ የደም ናሙና ምርመራ (ለምሳሌ የስኳር ፣ የHIV ፣ የኮሌስትሮል ምርመራ) እንዲሁም የጭንቅላት MRI ወይም CT scan ፣ Electromyography ሊያስፈልግ ይችላል።

ህክምናውስ?

-ይህ አይነት ችግር ሲያዩ ሰዎች ወዲያውኑ የጤና ተቋም መታየት ይጠበቅባቸዋል። ይህም ቶሎ ለመዳን በቶሎ መታከም አስፈላጊ ስለሆነ ነው። መድሀኒቶች ለምሳሌ የህመም እና ፀረ ብግነት መድሀኒቶች ለምሳሌ Corticosteroids, ፀረ ቫይረስ (antiviral) መድሀኒቶች ፣ አካላዊ ህክምና (physical theraphy) ፣ የፊት ማሳጅ ፣ ቀዶ ህከምና ተጠቃሽ ናቸው።

-በተለይ የፊዚዮቴራፒ ህክምና እጅግ ጠቃሚ የሆነ የህክምናው አካል ነው። ይህም የተለያዩ የፊት ላይ እንቅሰቃሴዎች ፣ የፊት ጡነቻ ሰፖርቶች የደነዘዙ የፊት ጡንቻዎችን ወደ ነበሩበት ለመመለሰ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ያሳያሉ።

ጤና ይብዛላችሁ

Ebro

t.me/NEWEPHARMACY
1.2K views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ