Get Mystery Box with random crypto!

ንዋየ ቅድሳት

የቴሌግራም ቻናል አርማ newayekidisat — ንዋየ ቅድሳት
የቴሌግራም ቻናል አርማ newayekidisat — ንዋየ ቅድሳት
የሰርጥ አድራሻ: @newayekidisat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.07K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ጹሑፎች፣አበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል.በተጨማሪም ከኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤ/ክ ገድላት ላይ የተገኙ የቅዱሳን አባቶቻችን እና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድላቸው በየቀኑ ይቀርብበታል
ለሀሳብ
አስተያየት(ለ #paid_promotion)
@Newayebot ን ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-01 10:01:33 እመቤቴ ማሪያም ሆይ

እነደ ጥቅምት ውሀ ለጠሩ እንደ አጥቢያ ኮከብ ለሚያበሩ ዓይኖችሽ ሰላምታ ይገባል። ደሀ አደጉንና ችግረኛውን ይመለከታሉና።

መልካም እለተ ሰንበት።
901 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 10:00:19 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሁለተኛ ጊዜ
ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
#አምላካችን_በሠላም_በጤና_ጠብቆ_የዓመትሰዉይበለን
#መልካም_በዓል
@newayekidisat
853 viewsedited  07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 12:57:15 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን
አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና
ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
@newayekidisat
@newayekidisat
870 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 10:30:39 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ
ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ
ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
@newayekidisat
@newayekidisat
804 views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 08:27:57 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና
የተገባለት ቃልኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡
@newayekidisat
@newayekidisat
762 views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 09:30:04 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ
አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ
የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ በትንሣኤ፡ ድል ያደረገ ንጉሥ
መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
@newayekidisat
@newayekidisat
708 views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 08:39:27 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታንን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና
አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
@newayekidisat
@newayekidisat
685 views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 08:50:46 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ
ዕለት በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣
ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን
እናስባለን፡፡
@newayekidisat
@newayekidisat
668 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 07:13:31 @newayekidisat
@newayekidisat

#በሰሙነ_ሕማማት_የሚገኙ_ዕለታትና_ስያሜአቸው

ቀዳሚት ሥዑር

ዕለተ ቅዳሜ እግዚአብሔር አምላካችን
የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር
የሚሔዱትን፣ በክንፍ የሚበሩትን እና በባሕር
የሚዋኙትን እንስሳትን፣ በመጨረሻም ሰውን
በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈባት ዕለት
ነች፡፡ የመጀመሪያዋ ቅዳሜ ለእግዚአብሔር
የዕረፍት ዕለት ናት፡፡ @newayekidisat እግዚአብሔርን
ፍጥረታትን ፈጥሮ ከፈጸመ በኋላ ስላረፈባት
‹ሰንበት ዐባይ› (ታላቋ ሰንበት) ትባላለች፡፡
ይህቺን ዕለት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት
ታዟል፡፡ ዕለተ ቀዳሚት (ሰንበት ዐባይ)
በዘመነ ሐዲስም የተለየ የደኅነት ሥራ
ተከናውኖባታል፡፡ እግዚአብሔር ጥንት ሥነ
ፈጥረትን በመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት
ዅሉ፣ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን
ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው
አምላካችን ክርስቶስ በመቃብር አርፎባታል
(ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡
ቀዳሚት ሰንበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በከርሠ መቃብር አርፎ የዋለባት ዕለት
በመኾኗ ‹ቀዳሚት ሥዑር› ትሰኛለች፡፡
‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት
አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ)
ነው፡፡ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል
ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን
ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ
ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እኽል ውኃ
በአፋቸው አልዞረም፡፡ @newayekidisat ይመኩበትና ተስፋ
ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር
ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን
በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡
እመቤታችንና ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን፣
በመጾምና በመጸለይ ዕለቷን እንዳከበሯት
ዅሉ የተዋሕዶ ልጆችም የተቻላቸው ከዓርብ
ጀምረው በማክፈል (በመጾም) እኽል ውኃ
ሳይቀምሱ ለሁለት ቀናት ያድራሉ፡፡
ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው
ቅዳሜን በመጾም ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡
በዚህ ዕለት ከሰኞ ከሆሣዕና ማግሥት
ጀምረው እስከ ስቅለተ ዓርብ ድረስ በስግደት
እና በጾም ያሳለፉ ምእመናን በዕለተ ቅዳሜ
በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡ የጠዋቱ
ጸሎት ሲፈጸምም ካህናቱ ‹‹ገብረ ሰላመ
በመስቀሉ፤ በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ»
እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡ ምእመናን
የምሥራች ቄጠማ ያድላሉ፡፡
ቄጠማው የምሥራች ምልክት ነው፡፡ @newayekidisat
ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ
የተወሰደው በኖኅ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ
ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ
እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ
ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ኾነው
እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር
ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ
ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት
መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት
ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ
ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ
ትመልሳለች፡፡ @newayekidisat ኖኅም በዚህ ቄጠማ
የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል (ዘፍ.
፱፥፩-፳፱)፡፡
ቄጠማ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች
መንገሪያ እንደ ኾነ ዅሉ፣ አሁንም
‹‹በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች
ተወገደ፤›› ስትል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም
የምሥራች ተምሳሌት የኾነውን ቄጠማ
በግንባራቸው ያስሩታል፡፡ የክርስቶስ
ተከታዮች ዅሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን፤
ከዋዕየ ሲኦል (የሲኦል ቃጠሎ) ወደ ጥንተ
ማኅደራቸው ገነት መመለሳቸውን በዚህ
አኳኋን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት
ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር።

(ማ/ቅ)
#forward በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ
@newayekidisat
@newayekidisat
688 views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 07:58:18 @Newayekidisat
@Newayekidisat
13ቱ ሕማማተ መስቀል
7ቱ የመስቀሉ ቃላት
7ቱ ተዐምራት
5ቱ ችንካሮች


#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል

1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ
መውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ
መረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር
መላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)

#ሰባቱ_የመስቀሉ_ቃላት
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡
46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር
በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት
እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ
(ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡
30)

#ሰባቱ_ተዐምራት
ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ
የተፈጸሙ ተዐምራት
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ
+ + + + +
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ
ችንካሮች
1. #ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. #አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን
ቸነከሩት
3. #ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን
ቸነከሩት
4. #አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን
ቸነከሩት
5. #ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት

@newayekidisat
@newayekidisat
1.1K views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ