2022-05-31 22:18:11
ተማሪዎች እንደምታውቁት ከፊታችን ያለው የአንድ ወር ጊዜ የአጋማሽ ፈተና፣ የፕሮጀክት ስራዎችና የማጠቃለያ ፈተና በተከታታይ የሚሠጡበት ጊዜ ነው። ስለሆነም ሁኔታውን በመረዳት ራሳችሁን ከፊታችሁ ለሚጠብቋችሁ ስራዎች አጣጥማችሁ ለተሻለ ውጤትና ስኬት ለመትጋት ይረዳችሁ ዘንድ አንዳንድ ጫናችሁን ሊያቃልሉላችሁ የሚችሉ መንገዶችን እንጠቁማችሁ!
1.ዕቅድ ማቀድ፥ ለአመቱ ያቀድነውን እቅድ አሁን ካለው የጊዜ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣም አድርጎ ማስተካከል
2.ዕቅዳችንን ለመፈፀም የሚያስፈልጉንን አጠቃላይ ግብአቶችን ማዘጋጀት። ለምሳሌ የአመቱ የትምህርት ማስታወሻ፣ አጋዥ መፅሀፍትና ሌሎች ነገሮችን ማካተት።
3.መስራትና ማከወን የሚገባንን ተግባራት አንድም ሳያስቀሩ ለመፈፀም በአይነትና በጊዜ በመከፋፈል መፈፀም
4.አቅማችንንና ብቃታችንን ያማከለ ጥረት ማድረግ
5.ጫና ስለሚፈጥርብን በአንድ ጊዜ ብዙ ተግባራትን በጭንቀት ከመከወን መቆጠብ
6.ፍፁምነትን አብዝቶ አለመጠበቅ፤ የአቅምን ያህል ግን መስራት
7.ቶሎ ወደ ተግባር መግባት፤ በጨዋታ፣ በቴሌቪዥን እና በመሣሠሉት ጊዜን አለማባከን።
እነዚህን እና ሌሎችንም መንገዶች በመጨመር ያሉንን ጊዜያት ከፋፍለን በመጠቀም አመቱን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ ጥረት እናድርግ!
ከሰላምታ ጋር
ነዋይ ቻሌንጅ አካዳሚ
6.0K views19:18