Get Mystery Box with random crypto!

Neway Challenge Academy-Official Account

የቴሌግራም ቻናል አርማ newaychallenge — Neway Challenge Academy-Official Account N
የቴሌግራም ቻናል አርማ newaychallenge — Neway Challenge Academy-Official Account
የሰርጥ አድራሻ: @newaychallenge
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.37K

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-29 13:13:09 የተከበራችሁ ወላጆች እና ተማሪዎቻችን
ዛሬ የትምህርት ቢሮ ባስታወቀው መሠረት፤ አርብ መስከረም 20/2015 ዓ.ም ትምህርት የሚኖረው ለግማሽ ቀን ብቻ እንደሆነ ከወዲሁ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።
ከሰላምታ ጋር
ት/ቤቱ
4.0K views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 15:37:55 #ብሔራዊ_ፈተና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኮማንድ ፖስት በፈተናው ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ፦
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣
• የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣
• የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣
• የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
• የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
• የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ሀላፊዎች እና የክ/ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ፦

- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች አቅርበዋል።

#የተፈታኞች_መብቶች_የሆኑት፡- 

➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።

➭ በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።

➭ የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።

#የተፈታኞች_ግዴታ_የሆኑት፡-

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት #ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ  ሲመጣ  አንሶላ፣  ብርድልብስና  የትራስ  ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

➤ #ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት።

#ለተፈታኞች_የተፈቀዱ_ነገሮች ፦

➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ  ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

➣ ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)

➣ ገንዘብ (ብር)

➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ

➣ የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

#ለተፈታኞች_የተከለከሉ_ነገሮች ፦

⮕ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

⮕ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና  ሌሎች  ማንኛቸውም  ፎቶ፣  ምስል  እና  ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ  ዙሪያ  ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት  ወይም  መጠቀም  የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣  ሲጋራ፣  በሓኪም  ማዘዣ  የሌለው  መድኃኒት  (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)

⮕ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ  45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

⮕ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ ሲሆን ፈተናው ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው ይፈተናሉ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ ያገኛሉ።

(የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ)

@tikvahethiopia
5.4K views12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 14:32:26 የተከበራችሁ ወላጆች እና ተማሪዎቻችን
ዛሬ የትምህርት ቢሮ ባስታወቀው መሠረት:-

<<ሰኞ የመስቀልን ዋዜማ በመሆኑ የመንገድ ስለሚዘጋጋ  የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት  ስለማይኖር ለወላጆች አሳውቁ  እሮብ መደበኛ ትምህርት ይቀጥላል  ሲፐርቫይዘሮች ለግል ትምህርት ቤቶች አሳውቁ ሳይሰሙ  የሚመጡ ተማሪዎች እንደመጡ ወደ ቤታቸው ሸኙ>>
ሰኞ፣ መስከረም 16/2015 ዓ.ም ሙሉ ቀን ት/ቤት ዝግ መሆኑን እናሳውቃለን።
ከሰላምታ ጋር
ት/ቤቱ
6.6K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 17:34:01 ለ2014 ዓ.ም. ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎቻችን
ቅዳሜ መስከረም 14, 2015 ዓ.ም. ቁጥር 1 ትምህርት ቤት በመገኘት የመፈተኛ መታወቂያ ካርዳችሁን (Admission card) እንድትወስዱ  እንዲሁም ስለፈተናው አጠቃላይ መረጃ (Orientation) ስለሚሰጥ ትምህርት ቤት ከጠዋቱ 2:00 ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን። በተጠቀሰው እለት ሳይገኝ የቀረ ተማሪ ሀላፊነቱን ትምህርት ቤቱ እንደማይወስድ እናሳውቃለን። ትምህርት ቤት ስትመጡ ልትይዟቸው የሚገቡ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው።
የትምህርት ቤቱን መታወቂያ ካርድ
አንድ በቅርብ ግዜ የተነሳችሁትን ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ እንድትመጡ።
የተሟላ የደንብ ልብስ እንድትለብሱ።
ስርአታማ የጸጉር አቆራረጥ እንዲሁም አሰራር እንድትከተሉ።
ትምህርት ቤቱ
2.3K viewsedited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 15:37:33 ለ2014 ዓ.ም. ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች
የመፈተኛ መታወቂያ ካርዳችሁ (Admission card) ትምህርት ቤት የመጣ ሲሆን ከመውሰዳችሁ በፊት ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ከዚህ በላይ በላክነው ፋይል ላይ ስማችሁን ፤ እድሜያችሁን እንዲሁም የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ መሆናችሁን በመመልከት እንድታረጋግጡ እናሳስባለን። ስህተት ካገኛችሁ እስከ አርብ መስከረም 13 2015 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ቤት በመምጣት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ትምህርት ቤቱ
4.5K viewsedited  12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 09:56:14 ለ2014 ዓ.ም. ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች
አንደሚታወቀው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተናችሁ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ቀጥሎ ደግሞ በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች አንደሚጀምር ይታወቃል። በክረምቱ መርሃ ግብር በምህርት ቤት በመገኘት ትምህርታችሁን ለተከታተላችሁ እንዲሁም በቤተ መጽሀፍት ቤት ስታጠኑ የነበራችሁ አሁንም ፈተናው አስኪሰጥ ድረስ ያሉትን ቀናቶች ግዜያችሁን በአግባቡ ተጠቅማችሁ ዉጤታማ አንድትሆኑ መስራት እንደሚጠበቅባችሁ ከወዲሁ ልናሳስባችሁ እንወዳለን። መፈተኛ ቦታችሁ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲሆን በቅርቡ አጠቃላይ ሙሉ መረጃውን ከትምህርት ሚኒስቴር እንደደረሰን የምናሳውቃችሁ ይሆናል። የመፈተኛ መታወቂያ ካርዳችሁ (Admission card) ትምህርት ቤት የመጣ ሲሆን መች መውሰድ እንዳለባችሁ ወደፊት የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ወላጆችም ለልጆቻችሁ መልካም ውጤት በቤት ዉስጥ አስፈላጊውን እገዛ አንድታደርጉላቸው እና አንድታበረታቷቸው አደራ ለማለት አንፈልጋለን።
ትምህርት ቤቱ
4.6K views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 13:26:40 ለተከበራችሁ የአጸደ ህጻናት ተማሪዎች ወላጆች በሙሉ
የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መስከረም 09/2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በዕለቱም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡ በሚጠቀሙባቸው ምሳ እቃዎች እንዲሁም ቦርሳዎቻቸው ላይ ስማቸውን እንዲሁም የሚማሩበትን ክፍል ፅፋችሁ እንድትልኩልን እናሣስባለን፡፡
የጀማሪ አፀደ ህፃናት (Nursery) ተማሪዎች ብቻ ለመጀመሪያዎቹ ሦስት ቀናት ማለትም ከሰኞ መስከረም 09/2015 - ረቡዕ መስከረም 11/2015 ዓ.ም ትምህርት የሚሠጠው ለግማሽ ቀን እስከ 6፡00 ሰአት ብቻ ስለሆነ
በእነዚህ ቀናት ወላጆች ልጆቻችሁን በሰዓቱ ተገኝታችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡ 
ትምህርት ቤቱ
5.3K views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 12:13:08
5.0K views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 15:26:32 የተከበራችሁ ተማሪዎቻችን
ትምህርት የሚጀምረው ሰኞ መስከረም 9, 2015 ዓ.ም. እንደሆነ ይታወቃል። ስለሆነም ትምህርት ቤት ከመምጣታችሁ በፊት የተመደባችሁበትን ክፍል አስቀድማችሁ እንድታውቁ ሲባል ከዚህ በታች የተማሪዎች ምደባ ስም ዝርዝር አያይዘን የላክን መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።
ትምሀርት ቤቱ!
5.4K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ