2022-04-21 10:52:37
ቀን፡- 11/08/2014 ዓ.ም
የተከበራችሁ ወላጆች፤
በያዝነው የሁለተኛ መንፈቅ አመት ት/ቤታችን ከእናንተ ወላጆች እና ተማሪዎቻችን ጋር የበለጠ ተጣምሮ በመስራት በርካታ አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ ተማሪዎቻችን የመንፈቀ-ዓመቱን የመጀመሪያ ፈተና ያጠናቀቁ ሲሆን በቀጣይ ለሚመጡ ፈተናዎች / ሞዴል ለ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል/ የበለጠ ተጠናክረው እንዲሰሩ የእናንተ ክትትል እና ድጋፍ በእጅጉ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ልጅዎን ከትምህርቱ በተጨማሪ በስነ-ምግባር ብቁ ለማድረግ ከት/ቤቱ ጋር ተቀራርቦ መስራት አስፈለጊ ነው፡፡ ምንም አይነት ጉዳይ ወይም ቅሬታ ካልዎት ከእኛ ጋር ቀርበው እንዲወያዩ ሁሌም ፍላጎታችን ነው፡፡
የሚያዚያ ወር የባህሪ ማረቂያ መርህ
“ማምረት” ሲሆን ይህ መርህ ተማሪዎች አዳዲስ ነገሮችን የማምረት፣የመፈልሰፍ ወይም የመስራት አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ያስተምራል፡፡ ይህን አስፈላጊ የባህሪ ማረቂያ መርህ መሰረት በማድረግ ከልጅዎ ጋር በቤት ውስጥ የበለጠ ይወያዩበት፡፡
እባክዎን የሚከተሉትን ወጪ ክንውኖች አንበብው ለተግባራዊነቱ ከልጅዎ ጋር ይስሩ፡፡
ሀሙስ ሚያዚያ 13/2014 ዓ.ም፡- ትምህርት ለግማሽ ቀን እስከ 6:30 ብቻ ይሆናል፡፡
ከአርብ እስከ ሰኞ፤ ከሚያዚያ 14-17/2014 ዓ.ም፡- የስቅለት በዓል እና የፋሲካ በዓል (ት/ቤት ዝግ ነው)
ስለሆነም ወላጆች ከላይ የተጠቀሱትን ቀናት ክንውኖች ተረድታችሁ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ለልጆቻችሁ እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር!
9.2K viewsedited 07:52