2022-07-04 11:08:34
ነዋይ ቻሌንጅ አካዳሚ
ቀን፡ 28/10/2014 ዓ.ም
የተከበራችሁ ወላጆች
ት/ቤታችን ለ2ዐ15 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምንም አይነት የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ አለማድረጉን በደስታ ይገልፃል፡፡
እባክዎ የ2ዐ15 ዓ.ም ምዝገባን በተመለከተ ቀጣዮቹን ማስታወሻ እና ማሳሰቢያዎች አንብበው ተግባራዊ ያድርጉ፡፡
-
ከሐምሌ ዐ6-26/2ዐ14 ዓ.ም የነባር ተማሪዎች ምዝገባ
-
ከሐምሌ ዐ6-ዐ7/2ዐ14 ዓ.ም የነባር ተማሪዎች ቤተሰብ የሆኑ የጀማሪ አፀደ ህፃናት አመልካች ተማሪዎች ምዝገባ
-
ከሐምሌ ዐ8-ዐ9/2ዐ14 ዓ.ም የአዲስ የጀማሪ አፀደ ህፃናት ተማሪዎች ምዝገባ በሚኖረው ክፍት ቦታ
ከእነዚህ ቀናት ውጪ ምዝገባ የማናካሄድ መሆናችንን እየገለፅን ከጀማሪ አፀደ ህፃናት ውጪ አዲስ ተማሪዎችን ዘወትር ቅዳሜ ከሐምሌ ዐ9/2ዐ14 ዓ.ም ጀምሮ የመግቢያ ፈተና በመፈተን ሊኖሩ በሚችሉ ክፍት ቦታዎች የምንመዘግብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ሆኖም ቦታ በሌላቸው የክፍል ደረጃዎች ወይም በሞላባቸው ክፍሎች የማንመዘግብ መሆኑን ከወዲሁ እናሣውቃለን፡፡
ሌሎች መረጃዎችን በት/ቤቱ ትክክለኛ የቴሌግራም እና ፌስቡክ አድራሻዎች እንዲሁም ከማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ እንድታነቡ እናሣስባለን፡፡
Neway Challenge Academy-Official Account
ት/ቤቱ!
5.6K viewsedited 08:08