Get Mystery Box with random crypto!

ዲን ምክክር ነው

የቴሌግራም ቻናል አርማ nesihaa — ዲን ምክክር ነው
የቴሌግራም ቻናል አርማ nesihaa — ዲን ምክክር ነው
የሰርጥ አድራሻ: @nesihaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 996
የሰርጥ መግለጫ

//طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ//
‘ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ
ነው።’
(("الدين النصيحة"، قلنا: لمن يا رسول الله؟ قال:" لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم")).
joinand share via link
t.me//nesihaa
ለአስተያየት @nesihaabot

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-26 07:47:07 እስልምና= ውበትና ንጽህና

ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ልብሱ የቆሸሸን ሰው ባዩ ጊዜ "ይህ ሰው ልብሱን የሚያጥብበት ውኋ አጥቶ ነው እንዴ?!" በማለት ሁኔታውን አውግዘዋል።
ጸጉሩ የተንጨባረረ ሰው ባዩ ጊዜም
"ይህ ሰው ጸጉሩን የሚያስተካክልበት (ቅባትና ማበጠሪያ) አጥቶ ነው እንዴ?!" ብለዋል። አቡ ዳውድ 4062።

ኢስላም ውስጥን በዒባዳና በተውበት፣ ውጭን በውሃና በልብስ እንድናሳምር ያዛል።
#ጁሙዓህ ቀን ላይ ደግሞ ገላን መታጠብ፣ ንጹህ ልብስ መልበስና ለወንዶች ሽቶ መቀባት ይበልጥ ይወደዳል፤ ትልቅ ምንዳም ያስገኛል።
ይህም በትክክለኛ ሐዲሥ ከነቢዩ ተነግሯል።
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
ዛዱል-መዓድ
https://telegram.me/nesihaa
133 views04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:57:31 ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ

የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል).
____
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
T.me/nesihaa
257 views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 08:46:12 የዘንድሮ የዓሹራ ጾም

የዘንድሮ 1443 ዓ.ሂ (2014 ዓ.ል) የዓሹራ ጾም ከነገ ወዲያ ሰኞ ቀን ላይ ሲሆን ከፊቱ ያለውን 9ኛውን ቀን አብሮ መጾም ተወዳጅ ስለሆነ ነገ እሁድና ከነገ ወዲያ ሰኞን እንጹም።
ነገ መጾም የማይችል ሰው ሰኞና ማክሰኞን መጾም ይችላል።
ከፊትም ይሁን ከኋላ አንድ ቀን ጨምሮ መጾም የማይችል ሰው አስረኛውን ቀን (ሰኞን) ብቻ በመጾም በዓሹራ ጾም የሚገኘውን የአንድ ዓመት ወንጀል የመማር ትሩፋት ማግኘት ይችላል።

ዛዱል-መዓድ
https://nesihaa
871 views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 16:06:21 ከዙል–ሒጃ ወር 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– "አያሙ አት‐ተሽሪቅ (ከዙል‐ሒጃ ወር 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት) የመብላት፣ የመጠጣት እና አላህን የማውሳት ቀናት ናቸው።" (ሙስሊም ዘግበውታል)

መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በዚህ ሐዲስ በነዚህ ቀናት የምንፈፅማቸውን ዋነኛ ነገሮች ጠቁመውናል። ትኩረት ልናድረግበት እና ልንተዋወስበት የሚገባው ትልቁ ነገር አላህን ማውሳት (ዚክር ማድረግ) እንዲሁም እርሱ በእኛ ላይ የዋለውን ውለታ በማስታወስ ማመስገን ነው። ይህን የሚታደሉ ጥቂቶች ናቸው።

አላህ እርሱን ለማስታውስ፣ ለማመስገን እና አሳምሮ ለማመለክ ይርዳን!

ጣሀ አህመድ

https://t.me/nesihaa
545 views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 07:06:42 T.me/nesihaa
376 views04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 23:20:24 ውድ የኢስላም ወንድም እህቶቼ፤ እንኳን ለኢድ አልአድሓ በአል በሰላም አደረሳችሁ

መጪው ዘመን ለሁላችንም የኢማን የእድገትና የስኬት እንዲሆንልን አላህን እንለምነዋለሁ

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال وأعاده الله علينا ونحن في عز وكرامة وسعادة

أخوكم في الله
أبو جنيد صالح أحمد

T.me/nesiha
360 views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 18:24:26 ዲን ምክክር ነው pinned an audio file
15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 18:24:08 የውሙ ዐረፋ ዒባዳ

የውሙ ዐረፋን (9ኛውን ቀን ) መፆም የ2 ዓመት ወንጀል እንደሚያሰርዝ ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተናግረዋል።

የዐረፋን ቀን ፆም ሙሉ አጅር ለማግነት፣
1/ ስምንተኛው ቀን ምሽት ላይ ጾምን ነይቶ ማደር፣
2/ በዕለቱ ከዐረፋ ፆም ውጪ ሌላ (የቀዳና ወዘተ) ፆም አዳብሎ አለመነየት ይገባናል።

ማስታወሻዎች፥
ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።
ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።
ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።
ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።
በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት
ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።

ነገን (ጁሙዓ ሰኔ 30/2014) በልባችን የዐረፋን ፆም በማሰብ(በመነየት) እንጾም!
ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ
ለራሳችን፣ለቤተሰባችን፣ ለሀገርና ለኡመታችን ዱዓእም እናብዛ

ሀሙስ / ዙል-ሒጃህ 8)1443 ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ

t.me/nesihaa
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
81 views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 18:22:50 #share
T.me/nesihaa
52 views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 08:18:49 የዐረፋ ቀንን መፆም
°
ከአቢቀታዳ ተይዞ እንደተወራው ነብዩ - ﷺ - ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ እና እንዲህ አሉ ፦ [ ያለፈውን እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያብሳል ] (ሙስሊም ዘግቦታል)
_
የዘንድሮው ቀን ጁሙዓ ዙልሒጃ 9/1443ሂ. ወይም ሐምሌ 1/2014 ላይ ይውላል።
T.me/nesihaa
104 views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ