Get Mystery Box with random crypto!

🛎🛎ጅማ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ🛎🛎

የቴሌግራም ቻናል አርማ juwanagebi — 🛎🛎ጅማ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ🛎🛎 ጅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ juwanagebi — 🛎🛎ጅማ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ🛎🛎
የሰርጥ አድራሻ: @juwanagebi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.03K
የሰርጥ መግለጫ

"የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር። "(ኢሳ1:9)
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ(ማቴ 3:2)
"እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።"(1ኛ ቆሮ13:13)
ለማንኛውም አስተያየት @Jugebigubae
#0966152762

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-08 20:20:15 በጥቂቱ መታመን

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ!.." ማቴ 25፥21፡፡ ይህም ማለት በምድራዊ ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ በሰማያዊ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ማለት ነው፡፡ በዚኛው ዓለም ታማኝ ሆነ ከቆየህ በዘለዓለማዊነት ውስጥ እሾምሃለው ማለት ነው፡፡ ይህ መመሪያ በብዙ መስኮች ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል... ዘመዶችህን በመውደድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ጠላቶችህንም በመውደድ ላይ ይሾምሃል፡፡ ጠላትህን የምትወድበት ጸጋ ያድልሃል ማለት ነው፡፡

በትርፍ ጊዜዎችህ እግዚአብሔርን የምታገለግል ከሆንህ በሕይወትህ ጊዜ ሙሉ በእርሱ ላይ ትኩረት የምታደርግበትን ፍቅር ያድልሃል፡፡ የፈቃድ ኃጢአቶችን ከአንተ በማስወገድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ያለ ፈቃድ ከሚመጡ ኃጢአቶች ነጻ ያወጣሃል፡፡

ንቁ ኅሊናህን ከክፉ አሳቦች የምትጠብቅ ከሆንህ እግዚአብሔር ንቁ ያልሆነው ኅሊናህን ንጽሕና ያድልሃል፤ ከዚህ በተጨማሪ የህልሞችህን ንጽሕናም ያድልሃል፡፡ ልጅ እያለህ ታማኝ ከሆንህ እግዚአብሔር ውጊያዎች በሚበዙበት በወጣትነትህ ዘመን ውስጥም ታማኝነትን ያድልሃል ሌሎች ሰዎች ላይ በቃላት ብቻ የማትፈርድባቸው ሆነህ በመገኘትህ ታማኝ ከሆንህ ይበልጥ አስቸጋሪ በሆነው በአሳብ እንዳትፈርድባቸው ያስችልሃል፡፡ ልክ እንደዚሁ ራስህን ከውጫዊ ንዴት በመጠበቅ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አውስጣዊ ቁጣ፣ንዴትና ቅናት ነጻ ያወጣሃል፡፡

በተለመዱ መንፈሳዊነቶች (በመንፈስ ፍሬዎች) ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የመንፈስ ስጦታዎችን ያድልሃል፤ በመጀመሪያው ላይ ታማኝ ሆነህ ካልተገኘህ ሁለተኛውን ፈጽመህ ልታገኘው አትችልምና፡፡

እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሚፈትሽህ በጥቂት ነገር ነው፡፡ በዚህች በጥቂቷ ነገር ላይ ታማኝ መሆንህ ካረጋገጥህ እርሱ በሚበልጠው ነገር ላይ ይሾምሃል፡፡ ውድቀትህንና አለመታመንህን በጥቂቷ ነገር ላይ ከገለጽህ ግን እግዚአብሔር በሚበልጠው ነገር ላይ አይሾምህም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና፦ "ከእረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱህ ቢደክሙህ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ?" ኤር 12፥5 ብዙ ሰዎች ዝቅተኛውን ኃላፊነት መወጣት ሳይችሉ ከፍተኛውን ኃላፊነት ለመቀበል ማሰባቸው እጅግ አስደናቂ ነገር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ ሳይጠቀሙ ተጨማሪ ጸጋ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ይህን ሲያደርጉም "በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ" የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመዘንጋት ነው፡፡

("መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅማቸው" ከሚለው #አያሌው_ዘኢየሱስ ከተረጎመው #የብጹዕ_አቡነ_ሽኖዳ መጽሐፍ የተወሰደ!!!)
78 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 23:25:13 ፦፦፦፦ እንኳን አደረሳችሁ ፦፦፦፦፦፦
[በሊቀሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ]

ይህ ወር የእመቤታችን ወር ነው። መጀመሪያ የተፀነሰችበት በኋላም ያረገችበት ወር ስለሆነ።
ሰው ሆና በማኅፀነ ሐና በተቀረጸችበት ወራት ለሰው የተዘጋጀውን ታላቁን ክብር ተቀበለችበት። ይህም ክብር ነቢረ የማን - በቀኝ መቆም ነው።
ጥንቱንም የሱባኤ አበው ቀደምት ምክንያቱ ድንግል ማርያም ነበረች። አሁንም በነቢያት ቦታ የተተኩ የሐዋርያት የሱባኤ ምክንያት የሆነቻቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።
ነቢያት የልዑል እግዚአብሔር ማደሪያ ሆና እስከሚያገኟት ድረስ ሱባኤ ገቡ።
ሐዋርያት ደግሞ በሰማይ በልጇ ዘንድ የተሰጣትን ማደሪያ ለማየት ሱባኤ ያዙ።

የተወደዳችሁ የአምላካችን የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች የእመቤታችን ልጆች ሆይ!
እግዚአብሔር እንደ እመቤታችን ያከበረው ምን ፍጥረት አለ?
እንደ እመቤታችን የሚገርም ምሥጢረ መለኮት የተገለጠበት ስፍራስ ከወዴት አለ?
ከሁሉ ይልቅ የከበረችውን የእግዚአብሔር ከተማ ለማየት አባቶቻችን ቀኖና ሠሩ። ሊናገሩት የማይቻለው የመለኮት ሥራ የተገለጠባትን ድንቅ የሲና ተራራ ለመቀበል ሱባኤ ያዙ።
በሱባኤው መጨረሻም እመቤታችንን አገኙ።
የልባቸው ምኞት የሱባኤያቸው ምክንያት ይህ ነበርና ደስታቸው ፍጹም ሆነ።
በኢየሩሳሌም ከሐዋርያት ጋር የነበሩ ምዕመናን እንዴት የታደሉ ናቸው? እመቤታችንን ለማየት ከሚፋጠኑ ከሐዋርያት ጋር ነበሩና።
እነዚህ ምዕመናን በሐዋርያት ሱባኤ ተሳትፈዋል ለሐዋርያት የተገለጠውንም በረከተ ትንሣኤዋን አይተዋል።
ዛሬም በየገዳማቱና አድባራቱ ከአባቶቻችን ጋር ሱባኤ የገባችሁ ጾም የጀመራችሁ ምዕመናን ሆይ! እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ጋር መከራቸውን ለመሳተፍ አብረን ስንሰለፍ በረከታቸውንም አብሮ ያሳትፈናልና አይዟችሁ በተስፋ ሱባኤ ያዙ። እናንተ ባላችሁባቸው አድባራትና ገዳማት
እመቤታችን ዘወትር እየተገለጠች የምታነጋግራቸው ብዙ ቅዱሳን ስለመኖራቸው አትጠራጠሩ።
እመቤታችን ሠውራ ያኖረቻቸው እየተገለጠችም የምታረጋጋቸው በየቀኑ ሰአሊ ለነ ቅድስት የሚሏት ብዙ ወዳጆች አሏት።
እመኑ! ከእነሱ አጠገብ ነው ያላችሁት።
እመኑ! ከእነሱ ጋር ነው ውዳሴ ማርያም ለመድገም የቆማችሁት።
እመኑ! ከእነሱ ጋር ነው ውዳሴ ማርያም ሲተረጎም እየሰማችሁ ያላችሁት።
ከእነዚህ ቅዱሳን ጋር በአንድ ደብር ማስቀደስ፤ በአንድ ገዳም ማደር ምን ያኽል የከበረ ዕድል እንደሆነ ልብ በሉ።
እነሱን ሊባርክ የወረደ መንፈስ ቅዱስ ይባርከናል።
እነሱን የሚጠብቅ መልአክ ይጠብቀናል።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
የሐዋርያትን መሻት የፈጸመች ድንግል እመቤታችን የኛንም መሻት ትፈጽምልን።
153 views20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 23:22:41 እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላም አደረሰን። ጾሙን የረድኤት የበረከት ያድርግልን። ስለ ራሳችሁ ስለ እኅትወንድሞቻችሁ ስለ ግቢ ጉባኤያችሁ ስለ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ስለ አገር ሰላም ሳትታክቱ ጸልዩ።
142 views20:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 15:04:35 ​​#ቅዱስ_ገብርኤል

እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!

በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡

በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡

ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡

መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡

መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡

በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡

እናት ሆይ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡

ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡

አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው።

እኒኽም ቅዱሳን ይኽንን በሚነጋገሩበት ጊዜ በውስጡ አንገትን የሚቆለምም ልብንም የሚያቀልጥ ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርን የሚበጣጥስ መሳሪያ ካለበት የብረት ጋን ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና የብረቱን ጋን እሳት አጠፋው፡፡ ከቅዱሳኑም አንዳቸውንም ሳያቃጥላቸው የብረቱ ጋር ማቃጠሉና መፍላቱ ጸጥ አለ፡፡

ወንድሞቻችን ሆይ እንግዲህ በጭንቃቸው ጊዜ ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ይህ መልአክ ከሰማእታትና ከጻድቃን ጐን እንደማይለይ እወቁ ለኃጥአንም ኃጢአታቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላቸዋል፡፡ እኛም የዚህ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓሉን እያከበርን አማላጅና ወዳጅ እናድርገው። በዚህም በሚመጣውም ዓለም ሊረዳን ይችላልና፡፡

ዳግመኛም መስፍኑ ሐሳቡ ሳይሳካለት ስለቀረ 14 የሾሉና የጋሉ የብረት ችንካሮች አምጥተው ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል ሰባቱን በራሱ በቂርቆስ አካል ማለት ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዐይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይቸነክራቸው ዘንድ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ዳግመኛም የህፃኑን የእራስ ቆዳ ገፈው እሳት ውስጥ ይጨምሩ ዘንድ አዘዘ፡፡

አሁንም መልአኩ መጥቶ ይህንን መከራ ከእርሱ አራቀለት፡፡ ቀጥሎም በመቃን ውስጥ ጨምረው በገመድ እንዲጎትቱት አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ አዳነው፡፡ ሕዝቡም ይህንን ሁሉ ተአምር ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑት ቅዱስ ገብርኤልንም አከበሩት፡፡ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15 በሰይፍ ተመትተው ስማትነትን ተቀብለዋል።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን
የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት አይለየን፤ በቅዱስ ቂርቆስና በቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን
489 views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 11:17:30
"አኅለፍከነ ማእከለ እሳት ወማይ:
ወአውፃእከነ ውስተ እረፍት።" መዝ ፷፭÷፲፪

እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!!!

ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት።

የታች ቤት ጽዋችን ፲፩ እንደሚጀምር ልብ ይሏል።

ክቡራን ቀደምቶቻችን ጽዋ ቅመሱ ብለናል!!
346 views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 10:02:13 አዲስ የበገና ዝማሬ
474 views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 17:28:43
ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል
443 viewsedited  14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 17:28:39 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ሐምሌ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን)
2.ታላቁ አባ ብስንዳ ጻድቅ
3.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ጳጳሳት

ወርኀዊ በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

ቅዱስ ናትናኤል - በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው። ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው። ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕፃን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕፃናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል። እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር። ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ) አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር:: ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው። ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ?" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልጶስ አማካኝነት ጠርቶታል:: ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል:: ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ: ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል::
የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም ሁለተኛ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በመቶ ሃምሳ ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል::

አባ ብስንዳ - ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ አባ ብስንዳ ይታሠባል:: አባ ብስንዳ በዘመነ ጻድቃን ምድረ ግብጽ ውስጥ ከነበሩ ታላላቅ አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱን ከገድሉ ጽናት የተነሳ መላእክት በእጅጉ ይወዱት ነበር:: "እኔ ልሸከምህ - እኔ ልሸከምህ" እያሉ ይሻሙበት: በተራ በተራም ተሸክመውት ይውሉ ነበር:: እርሱም ለበርካታ ዓመታት ውኃ የሞላበት ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ይጸልይ ነበር:: እንደ እሳት በሚባላው በረዶ ውስጥ ገብቶ መጸለዩ የፈጣሪውን ሕማማት ለመሳተፍ እና ለኃጥአን ምሕረትን ይለምን ዘንድ ነው:: ሁሌም በዘጠኝ ሰዓት መላእክት ተሠብስበው ይመጡና በብርሃን ሠረገላ ይሸከሙታል:: ከመሬትም ዘጠኝ ክንድ ከፍ ያደርጉት ነበር:: ከብዙ ዓመታት ተጋድሎ በኋላም በዚህች ቀን ዐርፎ ወደ ፈጣሪው ሒዷል። እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ከሐዋርያው እና ከጻድቁ አባ ብስንዳ በረከትም አይለየን::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
403 views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ