Get Mystery Box with random crypto!

ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕

የቴሌግራም ቻናል አርማ negerefej — ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕
የቴሌግራም ቻናል አርማ negerefej — ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕
የሰርጥ አድራሻ: @negerefej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.91K
የሰርጥ መግለጫ

ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2)
Ignorance of the law is no excuse.
civil code article 2035(2)
ነገረ ፈጅ ከፈለጉ አለን @NegereFeji_Bot ወይም negerefej@gmail.com ይላኩልን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

3

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-23 16:11:51
701 views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:56:43 ‘ሁከት ይወገድልኝ’ – የሰበር ችሎት የህግ ትርጉም
የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ይዞታውን ለመንጠቅ ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ለመፍጠር የሚፈፀምን ማንኛውንም ድርጊት እንዲቆም ወይም ንብረቱ እንዲመለስለት የሚያቀርበው የይዞታ ክስ
በፍ/ሕ/ቁ. 1149/1/ መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ መቅረብ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ነገር በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ ሲኖረው ነው፡፡ እንዲሁም የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም ዓይነት መብት በሌለው ሰው ላይ ስለመሆኑም የድንጋጌው መንፈስ ያስረዳል፡፡ የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ አቅራቢ በማስረጃ ማረጋገጥ ያለበት ንብረቱ በይዞታው ስር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጢር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ነው፡፡ ሁከት ተፈጥሯል የሚባለው ባለይዞታ የሆነው ሰው በይዞታው ስር በሚገኘው ንብረት እንዳይገለገልበት ሌላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ሲፈጥርበት ወይም ረብሻ ሲፈጥርበት ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 80241 ቅጽ 15፣[1] ፍ/ህ/ቁ. 1149(1)
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ ከሳሹ ማስረዳት ያለበት ባለቤትነት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዳለው ሳይሆን ክስ ያቀረበበት ንብረት ህጋዊ ባለይዞታ መሆኑ በሌላ አነጋገር ሁከት የተፈጠረበትን ነገር በእጁ አድርጎ በእውነት ሲያዝበት እንደነበር ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 38228 ቅጽ 9[2]
ሁከት እንዲወገድ በቀረበ ክስ ተከሳሽ የሚያነሳው የባለቤትነት ክርክር እራሱን የቻለ ባለቤትነት የመፋለም ክስ /petitory action/ በሚመለከተው ላይ አቅርቦ ከሚታይ በስተቀር ሁከት ተፈጥሯል ወይስ አልተፈጠረም ተብሎ ለሚያዘው ጭብጥ ተገቢነት የለውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 27506 ቅጽ 6[3]
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሲቀርብ በፍርድ ቤት በጭብጥነት ተይዞ መፈታት የሚገባው ጉዳይ ሁከት አለ ወይንስ የለም? የሚለው ነው፡፡
የውሉ ተገቢውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ አለመደረግ ይዞታው በተጨበረበረ መንገድ ስለመያዙ ወይንም በማናቸውም ሕገወጥ ሁኔታ ስለመያዙና ሁከት እንዲወገድለት ክስ ያቀረበው ከሳሽ በይዞታው በእውነት ሊያዝበት እንደማይችል አያረጋግጥም፡፡ በዚህ ረገድ ውሉ ጉድለት አለበት ከተባለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1808(2) ላይ እንደተመለከተው ውሉ ፈራሽ ነው እንዲባል የክስ ምክንያት ከሚሆን በስተቀር ሁከት ይወገድልኝ ተብሎ በቀረበ ክስ ላይ ሊስተናገድ የሚችል አይሆንም፡፡
ሰ/መ/ቁ 36645 ቅጽ 9[4]
በአብላጭ ድምፅ የተሰጠ
[1] አመልካች ጽናት የሆቴል ቱሪዝም ስራዎች ኃ.የተ. የግል ማህበር እና ተጠሪ አቶ ዳመነ ነጋ /5 ሰዎች/ የካቲት 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
[2] አመልካች ሐጂ መሀመድ አወል ረጃ እና ተጠሪ እነ አቶ ዲኖ በሺር /2 ሰዎች/ ታህሣሥ 7 ቀን 2001 ዓ.ም.
[3] አመልካች እነ ሣሙኤል ውብሸት እና ተጠሪ ብዙነህ በላይነህ ሐምሌ 19 ቀን 1999 ዓ.ም.
[4] አመልካች ረዳት ሳጂን አያኖ አንጀል እና ተጠሪ እነ ወ/ሮ ዓለሚቱ ህዳር 11 ቀን 2001
1.1K views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 16:46:58 ህግን ለማወቅ እንዲሁም ህግ ነክ መረጃዎችን ለመከታተል አዳዲስ ህጎችን፣ አዋጆች፣ መመሪያዎች እና ደንቦችን የሚያገኙባቸው ጠቃሚ የቴሌግራም ቻናሎች ናቸው።

የህግ መምህር፣ ጠበቃ፣ ህግ ባለሙያ፣ ነገረ ፈጅ፣ ህግ አዋቂዎች ከፈለጉም በእነዚህ ቻናሎች ያገኛሉ።
ከዚህ በታች እንደምርጫ ከቀረቡት ውስጥ መርጠው ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑ፣ ህግና ስርዓት ይወቁ ምክር ያግኙ።
3.7K views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 08:44:38
ፒያሳ አካባቢ ከሚገኝ አንድ ወርቅ ቤት በግሩኘ ሆነው ገዢ መስለው በመግባት ከአንድ ምስኪን የሽያጭ ሰራተኛ ላይ ወርቅ ዘርፈው የተሰወሩ ናቸው የምታውቋቸው ወይም ያያቹኋቸው ካላችሁ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ጠቁሙን እያሉዋችሁ ነው ተበዳዬች ሼርም እያደረግንም እንተባበራቸው
0961497770
701 views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:01:02 Share 'DRAFT-Value-Added-Tax-Proclamation-2022.pdf'
265 views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:09:14 አዲሱ ጀርመን የስደተኞችሕግ

ሕጉ በተለይ ጉዳያቸው በእንጥልል ለነበረ ኢትዮጵያውያንና አፍሪቃውያን እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ ለDW ተናግረዋል።
የጀርመን ጥምር መንግስት በአገሪቱ ላለፉት 5 ዓመታት የቆዩት ስደተኞች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያገኙበትን ሕግ አጸደቀ።
ሕጉ በተለይ ጉዳያቸው በእንጥልል ለነበረ ኢትዮጵያውያንና አፍሪቃውያን እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ ለDW ተናግረዋል።
Via DW Amharic
https://p.dw.com/p/4DsNU?maca=amh-Facebook-dw
326 views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 12:46:20 #MERSA Media Institute# For Fresh Graduate

Req No - 8
Position - Project Associates
Qualification: Bachelor’s degree on Information technology, Economics, Law, Medicine, Social Studies or related field of study
Experience - 0 year
Find More Details here

https://bit.ly/3ccjiB5

Deadline - July 23/2022
295 views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:01:32 አዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ተ.እ.ታ)
ረቂቅ አዋጅ፣ 2015

።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የ(ረቂቅ) አዋጁ መዘጋጀት በዋናነት
ቁጠባንና ኢንቨስትመንትን የማበረታት ሚና ያለው ፥ የካፒታል ዕቃዎችን ሳይጨምር በእቃ እና አገልግሎት ፍጆታ ላይ የሚጣል የተጨማሪ እሴት ታክስ ከ1994 ጀምሮ ሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ፣
መሠረታዊ የሆኑ የተ.እ.ታ ድንጋጌዎችን በአዋጁ ውስጥ በማካተትና ዝርዝር ድንጋጌዎችን ለደንብና መመሪያ በመተው አዋጁ በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችል አወቃቀር እንዲኖረው እንዲሁም ለአፈፃፀም ግልጽና ምቹ እንዲሆን መቅረጽ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በአገራችን ተግባራዊ እየሆነ በሚገኘው የኤሌክትሮኒክ የግብይት ሥርዓት ከሚከናወኑ ግብይቶች ታክሱን በሚገባ መሰብሰብ የሚያስችል አሠራር መዘርጋት በማስፈለጉ፣
ከታክሱ ነፃ የመሆን መብት አተገባበር የመብቱ ተጠቃሚ እንዲሆን የታሰበውን የህብረተሰብ ክፍል ማዕከል ያደረገና በግብዓት ታክስና በውጤት ታክስ መካከል ያለውን ሰንሰለት የጠበቀ እንዲሆን በማድረግ ፍትሃዊነትንና የዜጎችንም ሆነ የንግድ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በማስፈለጉ፣

በሕገ - መንግሥቱ አንቀጽ 55(1) እና (11) መሠረት አዋጁ እንደሚፀድቅ የሚጠበቅ ሲሆን በዚህ አዋጅ ሊሻሩ ይችላሉ ተብለው የሚጠበቁ ሕጎች
በዚህ ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 72 እና በአንቀጽ 70 ንዑስ አንቀጽ 1/ሐ መሠረት የሚወሰኑ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፥ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ. 285/1994 ከእነ ማሻሻያዎቹ በዚህ አዋጅ እንደሚሻሩ ይጠበቃል።
396 viewsedited  18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 23:08:37
President Biden signed an Executive Order to protect the reproductive rights of women in the aftermath of the Supreme Court's extreme decision to overturn Roe v. Wade.

It formalizes the actions I announced right after the decision and will add new measures to protect women's health.
616 viewsedited  20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ