Get Mystery Box with random crypto!

ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕

የቴሌግራም ቻናል አርማ negerefej — ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕
የቴሌግራም ቻናል አርማ negerefej — ነገረ ፈጅ Negere Fej 📕
የሰርጥ አድራሻ: @negerefej
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.91K
የሰርጥ መግለጫ

ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2035(2)
Ignorance of the law is no excuse.
civil code article 2035(2)
ነገረ ፈጅ ከፈለጉ አለን @NegereFeji_Bot ወይም negerefej@gmail.com ይላኩልን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

3

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 19:39:36 ለተወሰነ ጊዜ (የኮንትራት ውል) የተደረገ የሥራ ውል በየጊዜዉ እየታደሰ መቆየቱ ምን ዓይነት ውጤት ያስከትላል
416 views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:39:29 ስለ ቼክ ይርጋ ጊዜ
።።።።።። ።።።።።።።
ቼክ የወጣበት ቀን ከግምት ሳይገባ በቼክ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በሚከተሉት 6 (ስድስት) ወራት ውስጥ እንዲከፈል ባንክ መቅረብ እንዳለበት በንግድ ሕግ ቁጥር 855 ሥር ተመልክቷል፡፡

በንግድ ሕግ ቁጥር ቁጥር 881(1) ሥር ደግሞ በቼክ የሚገደዱ ሰዎች ላይ ቼኩን የተቀበለው ሰው ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩን ለክፍያ ባንክ ለማቅረብ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ ጀምሮ እስከ (6) ስድስት ወር ድረስ ነው፡፡
በመሆኑም ቼክ የተቀበለ ሰው፣ ቼክ ሰጪው ላይ የፍትሀ-ብሄር ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በ 1 (አንድ) ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
500 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 13:57:02
የአዲስ አበባ የህግ ምሩቃንን ያገለለው የስልጠና እና ስራ ዕድል
የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት አዳዲስ የህግ ምሩቃንን በዳኝት እና በዐቃቤ ህግነት አሰልጥኖ የሚቀጥር ነው። የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በቀጥታ የፍትህ ስርዓቱን ከመቀላቀላቸው በፊት የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ ማስቻል ነው። 

የ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ተመራቂዎች  “በአዲስ አበባ የፍትህ አካላት የቅድመ ስራ ስልጠና ተቋም ባለመኖሩ ዓቃቤ ህግ ወይም ዳኛ ሆነው ለመሥራት መቸገራቸውን ይናገራሉ። ወደ ክልልሎች ሲሄዱም ስልጠና ለማግኘት የነዋሪነት መታወቂያና ቋንቋ እንደ ቅድመ ሁኔታ በመቀመጡ ስልጠናውን ማግኘት ሳይችሉ ይቀራሉ።
በተጨማሪም ከክልሉ ነዋሪ ውጪ እድሉን እንደማይሰጡና ቅድሚያ ለክልሎቹ ተመራቂዎች እንደሆነም ይነገራቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ "አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የፍትሕ አካላት ማሰልጠኛ ተቋም ባይኖራትም ከፌደራል የፍትህ እና የህግ ምርምር ተቋም በመቀናጀት ስልጠናው እየሰጠን መጥተናል፣ አሁንም እንሰጣለን። በመሆኑም ተቋም አለመኖሩ ችግር የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም” ባይ ናቸው። ከተማዋ የራሷ የሆነ የፍትህ አካላት የቅድመ ሥራ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲኖራት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ  የህግ ባለሙያ “አንድ የህግ ባለሙያ  ስልጠና ካልወሰደና በዓቃቤ ህግነት ወይም በዳኝነት ተቀጥሮ የመስራት አድሉ ጠባብ ነው ለዚህ ችግር መፍትሄው  አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የህግ የቅድመ ስልጠና ማዕከል ማቋቋም ወይም እንኳን አዲስ አበባ የፌደራል መንግስት መቀመጫ እስከሆነች ድረስ ነዋሪዎቿ በፌደራል የፍትህ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ገብተው ስልጠናውን እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው ይገባል" ብለዋል።
አዲስ ዘይቤ
via #tikvahethmagazine
571 viewsedited  10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:37:48 #ቅን_ልቦና በሰበር ችሎት ክፍል አንድ
ቅን ልቦና ከውክልና እና አላግባብ መበልጸግ ጋር በተያያዘ በሰበር ችሎት የተሰጡ ትርጉሞች
አብርሃም ዮሐንስ
ውክልና
ሰ_መ_ቁ. 14974 ቅጽ 1

ተወካዩ የራሱን ጥቅም የሚመለከት ጉዳይ ሲያጋጥመው ሁኔታውን ለወካዩ ሳያሳውቅና ወካዩ ሳይስማማ ስራውን እንዳይፈጽም ይከላከላል፡፡ ስለወኪልነት የተደነገጉትን የፍ/ብሔር ድንጋጌዎች ስንመለከትም ተወካዩ ከወካዩ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እንደሚገባ እና የውክልና ስልጣኑን የሚያስቀሩ ምክንያቶች እንዳለበት (የፍ/ብ/ህ/ቁ 2208)፣ ተወካዩ ስራውን የሚፈጽመው በተለይ ለወካዩ ጥቅም ሊሰጥ የሚችል መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት (ፍ/ብ/ህ/ቁ 2209(1))፣ እንዲሁም ተወካዩ በራሱ ስም ከወካዩ ጋር የሚያደርገው ውል ወካዩ ካላጸደቀው በቀር ሊፈርስ እንደሚችል (የፍ/ህ/ቁ 2188) መደንገጋቸው ተወካዩ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ መሆን እንዳለበት እና ለወካዩ ጥቅም ብቻ መስራት እንዳለበት፣ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ሁሉ ሁኔታውን ለወካዩ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት የሚያስገነዝቡ ናቸው፡፡ በመሆኑም Aንድ ተወካይ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ለወካዩ ሳያሳውቅ የሚየከናውነውን ስራ ወካዩ ሊቃወመው የሚችል መሆኑን እና በዚህ ሁኔታ የተከናወነው ስራም ወካዩ ካላፀደቀው በቀር ወካዩ ራሱ እንደፈጸመው ሊቆጠር እንደማይገባ ከውክልና ግንኙነት አጠቃላይ ዓላማ እና ከፍ/ብ/ህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡

ሰ_መ_ቁ. 26399 ቅጽ 5

ሿሚው በግልጽም ይሁን በዝምታ እንደራሴው ሥልጣኑ ቀሪ ከሆነ በኋላ የሠራውን ሥራ ያልተቀበለው መሆኑ ከተረጋገጠ የዚሁ ያለመቀበል ውጤት በቁጥር 2193 ተደንግጓል፡፡ የዚህን ድንጋጌ ይዘት ስንመለከት ሿሚው ይህንኑ የእንደራሴውን ሥራ ካልተቀበለው ምን ጊዜም ይኸው ውል ፈራሽ ነው የሚል አይደለም፡፡
ይልቁንም ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1808 እስከ 1818 ድረስ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ተከትሎ የውሉ መፍረስ ወይም መሰረዝ ሊወሰን የሚችል መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም እነዚህኑ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች በመከተል ውሉ ሊፈርስ የማይችልበት አጋጣሚ ያለ መሆኑን የሚያሳይና ነገር ግን ውሉ የሚፈርስ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ውሉ በመፍረሱ ምክንያት በቅን ልቦና ከእንደራሴው ጋር በተዋዋሉት 3ኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ካሣ የሚጠየቅበት መንገድ የሚያመቻች ድንጋጌ ነው፡፡

ሰ_መ_ቁ. 77983 ቅጽ 15

ተወካዩ ከወካዩ ጋር የሚያሰተሳስረው ግንኙነት ውስጥ ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እንደሚገባ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2208(1) ስር ተደንግጓል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተወካዩ የተወካይነት ሥራውን የሚፈጽመው በተለይ የወካዩን ጥቅም ሊሰጥ በሚችልበት መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2209 (1) ድንጋጌ ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተወካዩ በውክልና ሥራው ላይ በሚገኝባቸው ጊዜዎች ሁሉ በውክልና በተሰጠው አደራ አንድ መልካም የቤተሰብ አባት ቤተሰቡን ለመጠበቅ እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መጠበቅ ያለበት መሆኑን በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2211(1) ስር በግልጽ ተደንግጓል፡፡

አላግባብ መበልጸግ

ሰ_መ_ቁ. 81081 ቅጽ 14

የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2168 ድንጋጌ ይዘት ሲታይም አንድ ሰው ለተወሰነ ጊዜ በእጁ ያቆየውን እቃ እንዲመለስ የተገደደ እንደሆነ ለሕግ ወይም ለውል ተቃራኒ የሚሆን ድንጋጌ ከሌለ በቀር የተባለውን እቃ ከመለዋወጥ የተነሳ ያሉት መብቶችና ግዴታዎች ከድንጋጌው ቀጥለው ባሉት ደንቦች መሰረት የሚወሰን መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን በዚሁ ድንጋጌ ስር ከሰፈሩት ደንቦች መካከል አንዱ የሆነው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2169 ስር የተቀመጠው ደግሞ የያዘውን እቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው በእቃው ላይ ያደረገው ወጪ ሊመለስለት የሚገባው ወጪው የግድ አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ስለመሆኑና ወጪው አስፈላጊ ሳይሆን ከቀረ ወይም ወጪው እቃውን እንዲመለስ በተገደደው ሰው ወይም ተገዳጁ ኃላፊ በሚሆንበት ሰው ጥፋት ምክንያት ከሆነ ወጪው ሊመለስ የማይችል መሆኑን ያሳያል፡፡
ሕጉ በአንቀጽ 2171(1) ስርም ለእቃው የተደረገው ወጪ የእቃውን ዋጋ ግምት ከፍ አድርጎት እንደሆነም እቃውን ለመመለስ የተገደደው ሰው ስለዚሁ ጉዳይ ያወጣው ገንዘብ ሊመልስለት እንደሚገባ የደነገገ ሲሆን ይህ ወጪ በክፉ ልቦና ስለመደረጉ የተረጋገጠ ወይም ርትዕም የሚያስገድድ ከሆነ ደግሞ ዳኞች ወጪውን ለመቀነስ ወይም ጭራሹን ለማስቀረት የሚችሉበት አግባብ መኖሩንን የተጠቃሹ ድንጋጌ ቀጣይ የሆነው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2172((1) ይዘት ያሳያል፡፡
ይህ ድንጋጌ አንድን ወጪ በክፉ ልቦና የተደረገ ነው ለማለት የሚቻልበት አግባብም ወጪው በተደረገበት ጊዜ ወጪውን የሚጠይቅ ሰው እቃውን ለመመለስ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያውቅ እንደነበረ ወይም ማወቅ ይገባው የነበረና ርትዕም ሲያስገድድ መሆኑን በመለኪያነት አስቀምጧል፡፡
ስለሆነም እነዚህ ድንጋጌዎች ሲታዩ አንድ ሰው የሌላ ሰው ንብረት ይዞ ሲጠቀም ከቆየና ንብረቱን በሚጠቀምበት ጊዜ ንብረቱን ከጥፋት ወይም ከብልሽት ለማዳን ሲል ተገቢውን ወጪ ቢያወጣ ይኼው ወጪ በሕጋዊ ባለሃብቱ እንዲተካለት መጠየቅ የሚችልበት አግባብ የሚኖረው ወጪው የግድ አስፈላጊ ከሆነና በቅን ልቦና የተደረገ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የሚያስገነዝቡ ሲሆን በክፉ ልቦና የተደረገ ስለመሆኑ የተረጋገጠውን ወጪ ግን እቃውን እንዲመለስ የተደረገ ሰው ሊቀነስበት ወይም ጭራሹንም ዳኞች ሊያስቀሩት የሚችሉ ስለመሆኑ ሕግ ስልጣን የሰጣቸው መሆኑን ድንጋጌዎች ያስረዳሉ፡፡
559 views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 06:03:14 ጋብቻ መኖሩ ስለሚረጋገጥበት መንገድ ሰ/መ/ቁ 206403

ጋብቻ የሚፈጸመው በሦስት መንገድ ማለት በክብር መዝገብ ሹም ፊት፣ በሃይማኖት ሥርዓት ወይም በባህሌ ሥርዓት ሲሆን ከእነዚህ ከሦስቱ በአንዱ መንገድ መፈጸሙን በማስረጃ በማስረዳት የጋብቻ መኖርን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ እነዚህ ጋብቻ የሚፈፀምባቸው መንገዶች የራሳቸው አፈፃፀም ሥርዓት ያላቸው በመሆኑ ከተጋቢ ጥንዶች ውጭ ሥርዓቱን በማስፈፀም፣ በምስክርነት፣ በታዳሚነት ወዘተ ደረጃዎች ሰዎች የሚሳተፉበት ነው፡፡ በተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 94 መሰረት ጋብቻ መኖሩን ለማስረዳት የሚቀርበው ቀዳሚ ማስረጃ የጋብቻ የምስክር ወረቀት ነው፡፡
ጋብቻቸውን አስመዝግበው የምስክር ወረቀት ያልያዙ ተጋቢዎች ወይም መዝገቡ በመጥፋቱ ምክንያት የጋብቻ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ያልቻሉ ተጋቢዎች ጋብቻ መፈፀሙን በትዳር ሁኔታ መኖር ማስረዳት እንደሚችሉ በአዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 95 ተመልክቷል፡፡ አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት የትዳር ሁኔታ አላቸው ለማለት እራሳቸውን እንደባልና ሚስት የሚቆጥሩና የሚኖሩ ከመሆናቸው በላይ ቤተሰቦቻቸውና ማህብረሰቡ በባልና ሚስትነት የሚቀበሏቸው ሆነው ሲገኙ መሆኑን አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 96 ያስረዳል፡፡
የትዳር ሁኔታ መኖር ሌላ አራተኛ ጋብቻ የሚፈፀምበት ሥርዓት ሳይሆን ከሦስቱ የጋብቻ አፈፃፀም መንገዶች በአንዱ ጋብቻ መፈፀሙን የሚያስረዳ ማስረጃ ነው፡፡ የትዳር ሁኔታ መኖሩን ለማስረዳት የሰው ምስክር፣ የሰነድ ማስረጃን እና ሌላ ማስረጃ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን፣ ማስረጃውን የማቅረቡ ዓላማ ጋብቻ መኖሩን ለማስረዳት በመሆኑ፤ ማስረጃው ማስረዳት ያለበት ጭብጥ ጋብቻ መፈፀሙን ማወቅን የሚያመለክት እንጂ በባልና ሚስትነት መኖራቸው ላይ ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ ምስክርነቱ እራሳቸውን እንደ ባልና ሚስት መቁጠር ወይንም እንደ ባልና ሚስት ማወቅ ላይ ብቻ የሚንጠለጠል ከሆነ የጋብቻ መኖርን በትዳር ሁኔታ ለማስረዳት በሚል ምክንያት ጋብቻንና ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት መኖር መካከል ልዩነት የሌለ ያስመስላል፡፡
ጋብቻ ተፈጽሟል ሊባል የሚችለው ጋብቻ ከሚፈጸምባቸው ሶስቱ መንገዶች በአንዱ መንገድ ተፈጽሞ ሲገኝ በመሆኑ ጋብቻን በትዳር ሁኔታ ለማስረዳት የሚቀርብ ማስረጃ ጋብቻው መኖሩን እንዲሁም የተፈፀመበት ሥርዓት (types of celebration) ማስረዳት ይጠበቅበታል (የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ቁ 213/1992 አንቀጽ 95) ይመልከቱ።
660 views03:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:03:37
Exemption of stamp duty for investor on loans for investment purpose
752 views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 18:13:47 National Insurance

ለህግ ባለሙያዎች የወጣ ክፍት የስራ ማስታወቂያ

Position:-
1. Junior Legal Officer 1
2. Legal Officer I
3. Branch Manager 3
4. Branch Manager 2

የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:
.

የስራቦታ:-Addis Ababa

የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ  ጳጉሜ
4/2014 ዓ.ም   

ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት  እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ

https://jobs.amazonethiopia.com/job/national-insurance-s-c/

903 viewsedited  15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 17:40:19 መኖሪያ ቤት ግዥ ሲፈፀም ትኩረት መደረግ ያለባችሁ ጉዳዮች
====================
ማንኛውም መኖሪያ ቤት ግዥ ሲፈፅሙ ትኩረት ማድረግ ያለባችሁ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
o በመጀመሪያ ይዞታው ህጋዊ ካርታ (የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት)ና ህጋዊ ፕላን ያለው መሆን አለበት፡፡
o በሻጭ እጅ ያሉ ሰነዶችና በክ/ከተማው በመዝገብ ቤት በሻጭ ስም ያለ የይዞታ ማህደር ጋር ሰነዶች በትዩዩ አንድ አይነት መሆናቸውን ማረጋገጥ፡፡ በተለይም በካርታው ላይ ያለው የካርታ ቁጥርና በክ/ከተማ መዝገብ ቤት ያለው ቀሪ ካርታ ቁጥር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
o የይዞታ ማህደሩ ከእዳ፣እገዳና ሌሎች ክልከላዎች ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ የሊዝ እዳ ገዥው እስከ እዳው መግዛት የሚፈልግ ከሆነ እዳውን ማስተላለፍ ይቻላል፡፡
o ትዳር ያለው ከሆነ ከወሳኝ ኩነት የትዳር ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት፡፡ ትዳር የሌለው ከሆነ ይህንን የሚያረጋግጥ መረጃ ያስፈልጋል፡፡
o ህጋዊ የሽያጭ ውል ከፍትህ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
o በውክልና የሚሻሻጡ ከሆነ ውክልናው ህጋዊ መሆኑን ውክልና ከሰጠው የፍትህ ተቋም ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
o በተጨማሪም በአካል ወደ ሚሸጠው ቤት ሂዶ ቤቱን በአካል ማየትና ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
o ከመሬት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ማለትም ይዞታው ወደ ፊት ለመኖሪያ ወይስ ወደ ንግድ መቀየር ይቻላል የሚለውን ሀሳብና ከግንባታ ከፍታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን ማማከርና ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
via ቢቡኝ
782 views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 17:11:23 #DMC Construction PLC#

1 -  Liaison Officer
2 - Secretary
3 - Junior Lawyer
4 - Senior Accountant
5 - Mechanical Engineer
6 - Senior HR Officer
7 - Office Engineer II
8 - Logistics Head
Find More Details here

https://bit.ly/3AjKrKL

Deadline - August 26/22
731 views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ