Get Mystery Box with random crypto!

ነገረ ወንጌላውያን

የቴሌግራም ቻናል አርማ negere_evangelical — ነገረ ወንጌላውያን
የቴሌግራም ቻናል አርማ negere_evangelical — ነገረ ወንጌላውያን
የሰርጥ አድራሻ: @negere_evangelical
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.86K
የሰርጥ መግለጫ

በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ የሚፃፉ ፅሁፎች፣ ዘገባዎችና ዜናዎች ይቀርባሉ! ትምህርቶች፣ መረጃዎችና ምካቴ እምነቶች በዚህ ቻናል ይስተናገዳሉ! በተለያዮ ሶሻል ሚዲያዎች የሚገኙ ፀሐፊያን የሚፅፉቸው ፅሁፎችን እናጋራለን።

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-18 20:24:38 ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ

የኢዩኤል ዘመን ወይም ትንቢተ ኢዩኤል የተጻፈበት ዘመን የታወቀ አይደለም። በመጽሐፉ የትኛውም ንጉሥ በስም ስላልተጠቀሰ ወይም ምንም ፍንጭ ስላልተሰጠ፥ ወይም በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፈው በተከታታይ ዓመታት የተፈጸመ የአንበጣ ወረራ በሌሎች መጻሕፍት እና ታሪኮች ውስጥ ስላልተዘገበ፥ ኢዩኤል ስለኖረበት ወይም መጽሐፉ ስለተጻፈበት ዘመን የሚታወቅ ነገር የለም። ስለ ካህናት፥ ስለ እግዚአብሔር ቤት፥ ስለ መቅደስ አገልጋዮች፥ ስለ ይሁዳ፥ ስለ ጽዮን፥ ስለ ኢየሩሳሌም ስለሚናገር ኢዩኤል ያገለገለው በኢየሩሳሌም ወይም በይሁዳ ሆኖ ከኢየሩሳሌም መወረርና ከመቅደሱ መፍረስ በጣም ቀድሞ ሳይሆን አይቀርም። በትንቢቱ ውስጥ ከልመናዎቹ አንዱ ርስቱን ለማላገጫ አሳልፎ እንዳይሰጥ ነው።

አስፈሪው ነገር፥ ኋላ ግን ሰጠ። እግዚአብሔር ርስቱን በገዛ እጁ አሳልፎ ሰጠ። (ዳን. 1፥2)

ርስቱ ሕዝቡ ነው፤ ርስቱ ሕዝቡ ነን።

ኢዩ. 2፥12-17
12፥ አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። 13፥ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ። 14፥ የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? 15፥ በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥ 16፥ ሕዝቡንም አከማቹ፥ ማኅበሩንም ቀድሱ፥ ሽማግሌዎቹንም ሰብስቡ፥ ሕፃናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ ሙሽራው ከእልፍኙ፥ ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ። 17፥ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናት ከወለሉና ከመሠዊያው መካከል እያለቀሱ፦ አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብ መካከል፦ አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ? ይበሉ።

ይህ መዝሙር ብዙ ተንበርክኬ የሰማሁትና አብሬ የዘመርኩት ነው። አድምጡት፤ ዘምሩት፤ ጸልዩት።

በደልን ይቅር የሚል፥ ዓመጻን የሚያሳልፍ፥
ከጠላት ሊያድናቸው በሕዝቡ ላይ የሚሰፍፍ፥
እንዳንተ ያለ አምላክ ምሕረቱ የበዛ፥
ቅዱሳንንህ ሲሰደዱ መከራውም ሲበዛ።

ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤
የተቀደሰ መቅደስህን ለጠላት አታስረግጥ።

የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ተጽፏል ሕዝቡ ነው፤
ሊያመልከው ሊያገለግለው ከግብጽ አገር ያፈለሰው፥
አርነቱን በባርነት ሊተካ የሚከጅለው፥
ይገባኛል የሚል ማነው? ሕዝቡ የእግዚአብሔር ነው።

እስከዛሬ ከብረሃል በአሕዛብ ተፈርተሃል፤
የጠላትን እርግማን በረከት አድርገሃል፤
ያሳዳጁን ፈረሶች በባህር አስጥመሃል፤
በክንድህ ተከላክለህ ርስትህን ጠብቀሃል።

(መዝሙር በተስፋዬ ጋቢሶ)

ዘላለም መንግሥቱ
672 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 09:40:30
780 views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 09:40:26 ይህ ከሆነ እንደተቀበልነው በእርሱ መመላለስ አለብን። እርሱ ጌታችን ስለሆነ እኛ እንደ እርሱ ተከታዮች፥ ደቀ መዝሙሮች፥ እንደ ክርስቲያኖች ሆነን መመላለስ አለብን። እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ። ሰዎች ጌታን መቀበል የማይፈልጉት ስጦታውን ሳይፈልጉ ቀርተው ሳይሆን ስጦታው ጌታ ነውና ጌታ ስለሆነ የሚጠይቀው የፈቃድ ዋጋ ስላለ ነው። የመመላለስ ዋጋ። እርሱን የመምሰል ዋጋ። ግን ይህ ዋጋ ኋላ ከምንቀበለው ደመወዝ ጋር ሲነጻጸር ተመን የለውም።

የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው። ሮሜ 6፥23

ይህንን አጭር ትምህርት ስጨርስ ልጋብዛችሁ እወዳለሁ። እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጥቶናል፤ ስጦታ ነው። እኛስ ተቀብለነዋል? ይህ መቀበል ከላይ እንዳልኩት ሥርዓት መፈጸም አይደለም። ፈቃድን ለፈቃዱ ማስገዛት ነው። እርሱን የሕይወታችን ጌታ ማድረግ ነው።

ምናልባት ጌታን መቀበል ሳይገባችሁ ኖራችሁ አሁን የተከሰተላችሁና ጌታን ለመቀበል የምትፈልጉ ከኖራችሁ፤ ሁለት ነገሮች አድርጉ፤

1. ኃጢአተኛ መሆናችሁን አውቃችሁ ተጸጸቱና እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠይቁት። እኔ ኃጢአተኛ ነኝ ይቅር በለኝ። በሉት። የዚህ ይቅርታ መገኛ ደግሞ ከላይ ያልኩት ክርስቶስ አምላክ ሳለ ሰው ሆኖ ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ መውሰዱ ነው። ይቅር በለኝ ስንል ይህ የኃጢአታችን ደመወዝ በዚያ መስቀል ላይ መከፈሉን መገንዘባችን ነው።

2. ይቅርታ ከጠየቅን በኋላ ጌታ እርሱ ጌታችን እንዲሆን ወደ ልባችን እንዲገባ መጋበዝ ነው። ጌታ ሆይ ና ወደ ሕይወቴ፥ ወደ ልቤ፥ ወደ ኑሮዬ ግባ፤ መሪዬ ጌታዬ ሁን እንበለው።

ይህን ካደረግን እንደ ተስፋ ቃሉ ታማኝ ነውና ወደ ሕይወታችን ይገባል። አዲስ ፍጥረትም ሆነናል። ከዚህ አዲስነት በኋላ በቅርባችን የምትገኝ ወንጌልን የምትሰብክ፥ ቃሉን የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ፈልገን አብረን ማምለክ፥ ይህን ያገኘነውን አዲስ ሕይወት ለሌሎች ማካፈል እና በቆላ. 2፥6 እንደተጻፈው በእርሱ መመላለስ እንጀምር።

እኔ ጌታን ተቀብያለሁ። አንተስ፥ ጌታን ተቀብለሃል? አንቺስ፥ ጌታን ተቀብለሻል?

ዘላለም መንግሥቱ
711 views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 09:40:26 ጌታን ተቀብለሃል? ጌታን ተቀብለሻል? (ለሌሎች አካፍሉት)

ሰዎች ጌታን ተቀበይ ወይም ተቀበል ብለው ሲጋብዙን ወይም፥ ጌታን የግል አዳኝህ አድርገህ ተቀብለሃል? ተቀብለሻል? ሲሉ፥ ወይም እኔ ጌታን የተቀበልኩት በዚህ በዚህ ቀን ነው ሲሉ ሰምተን እናውቃለን? ለምሳሌ፥ እኔ ጌታን የተቀበልኩት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1975 ከፋሲካ ቀጥሎ በነበረው ማክሰኞ ግንቦት 2 ቀን ነው። [ወይም May 10, 1983 ነው።]

ግን ምንድርን ነው ይህ ጌታን መቀበል? ጌታን መቀበል የተወሳሰበ የስነ መለኮት ቃል አይደለም። ፍቺና ፈቺ የሚፈልግ ጥልቅ አስተምህሮም አይደለም። ይህንን ትልቅ እና ድንቅ እውነት እግዚአብሔር የተወሳሰበ አድርጎ አላቀረበም። በጣም ግልጽ፥ በጣም ቀላል ነው። ሁላችንም ሰጥተንም ተቀብለንም እናውቃለን። ይህ መስጠትና መቀበል ከሰው ፍጥረት ጀምሮ የኖረ ልምድ ነው። በመስጠትና በመቀበል ውስጥ ሰጪ አለ፤ ተቀባይ አለ፤ ስጦታ ደግሞ አለ።

ይህንን ጌታን መቀበል የሚለውን እውነት የሚያስረዱን ሁለት ጥቅሶች እንመልከት።
የመጀመሪያው፥ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው። የሚለው ነው፤ ዮሐ. 1፥11-12።

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ የመጣ አምላክ ነው። ሙሉ አምላክ ሆኖ ከአምላክነቱ ምንም ሳይቀነስ ፍጹም ሰው ሆኖ የመጣ ነው። በሥጋ መምጣት የኖረበት ምክንያት ሊቤዠን ወይም ቤዛ ለመሆን ነው። ቤዛ ማለት ምትክ ማለት ነው። በምትካችን ሊሞት፥ ኃጢአታችንን ሊወስድ ማለት ነው። ሳይሞት ኃጢአታችንን ሊወስድ ወይም ሊደመስስ አይችልም ነበር ወይ? ኃጢአት እንዲህ በቀላሉ ድምስስ የሚል ነገር አይደለም። ኃጢአት ደመወዝ አለው፤ ደመወዙም ሞት ነው፤ ሮሜ 6፥23። ኃጢአት የእግዚአብሔር ተቃራኒ ባህርይ ነውና ኃጢአት ሁሉ ሕይወትን ይጠይቃል።

ሰው ሁሉ ደግሞ በአዳም በኩል እና በራሱም ሥራ ኃጢአተኛ ነው። ማንም ኃጢአት የለብኝም ወይም ኃጢአተኛ አይደለሁም ማለት አይችልም። ሮሜ 3፥23። ሁሉ ከኃጢአት በታች፥ ከፍርድ በታች ናቸው። የኃጢአት ደመወዙ ሞት ከሆነ ደግሞ ሁሉ ሟቾች ናቸው። አንድም በሕይወት የሚተርፍና የሚኖር የለም። ማንም ደግሞ የማንንም ሞት መውሰድ አይችልም። አዳኝ ወይም ቤዛ ለሰው ልጅ ኃጢአት መሞት ከኖረበት ያ ቤዛ ማሟላት ያለበት አራት ነገሮች አሉ። (ከአንድ ጓደኛዬ የትርጉም መጽሐፍ የወሰድኩት ነው።) እነዚያም

1ኛ፥ ሰው መሆን አለበት። ጌታ አምላክ እያለ ሰው የሆነው በዚህ ዋና ምክንያት ነው። ለመሞት ሥጋ መልበስ አለበት። ደሙን ለማፍሰስ ደም እንዲኖረው ያስፈልጋል፤ ደም እንዲኖረው ሰው መሆን አለበት።

2ኛ፥ ምንም ኃጢአት የሌለበት መሆን ይገባዋል። ያለዚያ ራሱም ኃጢአተኛ ነዋ! የራሱ ኃጢአት ምን አድርጎ ለሌላው ይሞታል? ለራሱ ኃጢአት ብቻ ነው የሚሞተው። ሌላውን ማዳን አይችልም።

3ኛ፥ አምላክ መሆን አለበት፤ ይኸውም በምትክነት የሚሰዋው ቁጥር ስፍር ለሌለው ኃጢአትና እጅግ ብዙ ኃጢአተኞች በመሆኑ ነው። ሰው ብቻ ከሆነ ከሰው ይህን ማድረግ የሚችል ንጹሕ ሰው የለም። ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና። ይህ ቤዛ ከተራ ሰው በላይ የሆነ ሰው መሆን አለበት።

4ኛ፥ እራሱን ለሌሎች ኃጢአት ሲል አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆን አለበት።

ጌታችን እነዚህን መስፈርት የሚያሟላ ቤዛ ነው። ይህንን ሆኖ ነው ወደ ወገኖቹ የመጣው። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ሰው ሆኖ መምጣት ከኖረበት ወደ አንድ ወገን መምጣት አለበት። ያ ወገን ማንም ሊሆን ይችላል። ያንን ወገን ከአብርሃም ወገን እንዲሆን እግዚአብሔር መረጠ። ተስፋ ሰጠ። በትንቢት ተናገረ፤ ሕጻን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል እያሉ ነቢያት ተናገሩ። ተሰጥቶናል ሲሉ ስጦታ መሆኑን መናገራቸው ነው።

ስጦታ ከሆነ ይህ ስጦታ የሚቀበሉት ስጦታ ነው። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው። የሚለው ነው። ስጦታ ዋጋ የተከፈለበት፥ ግን ተቀባዩ ያልከፈለበት፤ እንዲቀበሉት የተገባ ግን ግዴታ የሌለበት የፈቃድ ነገር ነው።

ይህ ነው መቀበል። መቀበል መውሰድና የራስ ማድረግ ነው። ስጦታው ዕቃ ከሆነ ወስዶ መጠቀሚያ ማድረግ ነው። ስጦታው ጌጥ ከሆነ ተቀብሎ ማጌጥ ነው። ስጦታው ጌታ ከሆነ ተቀብሎ ጌታ ማድረግ ነው። ክርስቶስን ጌታ አድርጎ መቀበል ማለት በራስ ላይ ጌታ እንዲሆን መፍቀድ ነው።

ይህ 'የግል አዳኝ' የተባለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ ነው። የግል ማለት የራስ ማለት ነው። የግል አዳኝ አድርጎ መቀበል ሲባል ተቀባዩ ራሱ በውሳኔው የሚቀበለው መሆኑን መናገሩ ነው። ወላጆቼ ስለ እኔ ጌታን አይቀበሉልኝም። ኦርቶዶክሳውያን ሃይማኖተኞች ስለነበሩ በ40 ቀኔ አስጠምቀውኛል፤ የክርስትና ስም ተሰጥቶኛል፤ ያንን ማድረጋቸው ለኔ ክርስቲያን መሆን አስበው ነው። መልካም ምኞት ነው፤ ያስመሰግናቸዋል። ግን ያ እነርሱ ለኔ ያደረጉት ነገር እኔን አያድነኝም። ፈቃዴ የለበትማ! ይልቅስ ከዚያ በኋላ ቃሉን በማስተማር፥ ክርስቶስን በማሳየት ተግተው ኖሮ ቢሆን መልካም ነበር። ያንንም እንኳ አድርገው እኔ በራሴ ውሳኔ፥ በራሴ ፈቃድ ጌታን ጌታዬ አድርጌ ካልተቀበልኩ አይሆንም።

ምክንያቱም ይህ የጌታና የተከታይ ግንኙነት ነው። በግድ ከሆነ ፈቃድ የለበትም። ተገድጄ ነው የምከተለው። ፈቃድ ደግሞ እግዚአብሔር ማንንም ሳይለይ ለሰው ልጆች ሁሉ የሰጠው ድንቅ ስጦታ ነው። ለዚህ ነው የግል አዳኝ የተባለው። ውሳኔው ማንም ለማንም የማያደርገው የግልና የፈቃድ ውሳኔ ስለሆነ ነው።

አንዴ ከካናዳ ትምህርቴን ጨርሼ እንደተመለስኩ በዲላ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አንድ እሁድ አገለግል ሳለሁ ከካናዳ የገዛኋትን ቆንጆ ሰዓት አሳየሁና፥ ይህችን ሰዓት የሚወስድ ካለ መጥቶ መውሰድ ይችላል፤ የሚወስድ አለ? ብዬ ጠየቅሁ። ሰው አፍሮ ዝም። ፈልገዋል፤ ግን ምንተፍረት ያዛቸው። ኋላ ትንሽ ልጅ ወደ ፊት መጣና እጁን ዘረጋ፤ በገዛ እጄ አውጥቼ ሰጠሁት። ስጦታ ነው፤ የሚቀበል ካለ ብዬ ጋበዝኩ፤ አንድ መጣ፤ ተቀበለ። እንግዲህ መቀበል ይህ ነው። ተቀብሎ የራስ ማድረግ። የምንቀበለው ጌታ ከሆነ ተቀብሎ የራስ ጌታ ማድረግ ነው። ጌታን ተቀብለሃል? ጌታን ተቀብለሻል? አሁን ጥያቄው ግልጽ ነው።

ሁለተኛው፥ እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ። የሚል ቃል ነው፤ ቆላ. 2፥6። ጌታን ስንቀበል የተቀበልነው እንደ ጌጥ ወይም እንደ መብል ሳይሆን እንደ ጌታ ነው። ስለዚህ በኛ ላይ በፈቃዳችን የሆነ ጌትነቱን ነው የተቀበልነው። ባንቀበለውም እርሱ ጌታ ነው። አንድ ቀን ጉልበት ሁሉ ለእርሱ ይንበረከካል፤ መላስ ሁሉ ለአብ ክብር ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል። ይህ እውነት ነው። ግን ጌትነቱን መቀበል በኛ ላይ ጌታ፥ አለቃ፥ አዛዥ፥ ባለ ሙሉ ሥልጣን፥ ንጉሥ፥ አምላክ እንዲሆን ፈቅደን መቀበላችን ነው።
578 views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 16:53:02 እስቲ እያመነዠግን!

ያለንበት ዓለም እንዴት ያለ ዓለም ነው?

በየዕለቱ የምጥ ዜና የሚሰማበት ፣ ለቅሶ እና ዋይታ የነገሠበት ፣ አዳዲስ ወረርሽኝ የሚስተናገድበት በክፋቱ እየባስ የሚሄድ ዓለም ነው፡፡ አስተዋዩ ዘማሪ ገና ነገሮች አሁን የደረሱበት ክረት ላይ ሳይደርሱ ከአመታት በፊት “ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ፣

የሚሆነው በምድር ዙሪያ፣
እየከፋ ሲሄድ ጊዜው
መሸሸጊያው ኢየሱስ ነው፡፡ ብሎ ዘምሯል፡፡

ዓለሙ ስብራት የበዛበት ከዕለት ዕለትም እየገሸበ የሚሄድ ዓለም ነው።
በአጭሩ ለመናገር ምንም አጓጊ ነገር የሌለው የከሸፈ ዓለም ነው! የአመጹን ጡንቻ እያፈረጠመ፣ ምስኪኑን እየረመረመ፣ እያደከመ የሚሄድ ክፉ ዓለም ነው፡፡ ከቀን ወደ ቀን ደግሞ በውጭ ቀርቶ በእግዚአብሔር ቤት ሳይቀር አመፅ ጫፍ የረገጠበት ዘመንም ነው።

ይህን ዘመን አለመረዳት ዘመኑን የሚመጥን ዝግጅት እና ኑሮ እንዳይኖረን ያቅበናል፡፡ በስብከት፣ በመዝሙር እና በልዩ ልዩ ትንቢቶች የዓለምን እና የዘመኑን መልክ ሌላ አድርጎ መሳል ለጠላት ዱላ ማቀበል ነው፡፡

በቅርብ ሰሞናት አየሩን ይዞ የነበረው መዝሙር ይህ መንፈስ ያለው አዘናጊ ነው፡፡ መዝሙሩ “ማዘን እያለብህ ለምን ትስቃለህ?” ብሎ ይጀምርና “ያለሁበት ዓለም ለቅሦ አይታወቅም፤ በፈረቃ አልቅሼ በፈረቃ አልስቅም” ይላል፡፡ በርግጥ መዝሙሩ ውድም ያለ ክፉ ነው ማለት አይቻል ይሆናል፡፡ “ኢየሱስ ሳቄ ነዋ!” ብሎ መዘመርምር ችግር አይደለም:: ሳቅ የሚለው ከንፈርን ገለጥ አድርጎ ጥርስን ከማሳየት ባለፈ፣ በክርስቶስ ያገኘነውን ሁኔታ መር ያልሆነውን ደስታ ያሳይ ከሆነ፡፡ ባለሁበት ዓለም ለቅሦ አይታወቅም ማለት ግን፤ በየትኛው ዓለም እየኖሩ ነው? የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ያስገድደናል::

ከላይ ለመግለጥ እንደሞከርኩት ያለንበት ዓለም መልኩ ግልጥ ነው፡፡ በእርግጥ በዚህ ምጥ ጭንቅ በሞላበት ዓለም ሆነን፣ የዚህ ዓለም የትኛውም አስጨናቂ ነገር የማይስተናገድበትን መጪ ዓለም እንጠባበቃለን፡፡ እዚህ ግን በተስፋ ኾነን እንቃትታለን፡፡

የጠቀስኩትን መዝሙር ጨምሮ አንዳንድ መዝሙሮቻችን ዓለሙን ፍፁም በማስመስል የሚቀጥለው ዓለም ናፍቆታችንን የሚፃረሩ ናቸው፡፡ በዓለም ውስጥ ስንኖር በጌታ እየተፅናናን ቀጣዩን ዓለም እንናፍቃለን ::

ያለንበት ዓለም ግን የለቅሶም ዓለም ነው፡፡ ኧረ እንደውም “እዘኑ አልቅሱ!” የሚል መመሪያም ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡ ዓለሙ የለቆሦ ዓለም ነዋ! እኛ ምልቶልን ባናለቅስ እንኴ ከሚያስለቅሱ ጋር አልቅሱ የሚል የቅዱስ ቃሉ መመርያ አለን።

ዓይኖቻችንን ካልጨፈንን ጆሮቻችንን ካልደፈንን፤ አላይም አልስማም ካልልን በስተቀር ለቅሶማ የዓለሙ መታወቂያ ነው። በለቅሶ እና በሐዝን መካከልም ዝም ብሎ መሳቅ እኮ የአዕምሮ ጉድለት ነው። በጌታ ደስ ይለናል ማለት ሐዘን አልባ ነን ማለት ጨርሶ አይደለም፡፡ ምናልባት ይሄ ይሆን እንዴ፣ ከከበርቻቻ እና ከአስረሽ ምቺው እንዳንወጣ ያደረገን? የወገንን ሕመም እንዳንታመም፣ ለተራበው እንዳንቆርስ፣ የምልጃ እንባችንን ያደረቀው ይህ ይኾንን?

ነቢዩ ኤርሚያስ በዙሪያው ስለነበረ ምስቅልቅል ልባዊ ስሜቱን ለመግለጽ እንዲህ ብሏል “በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ ጠቍሬማለሁ፤ አድናቆትም ይዞኛል። ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!”

መጽሐፉ ለሁሉ ጊዜ አለው ይለናል፤ ለሳቅም ሆነ ለልቅሶ፤ በጌታ የሆነው ደስታችን እንዳለ ሆኖ ልናለቅስ ደግሞ እንችላለን፡፡ ይህም ደግሞ ጤና ነው፡፡

ግን ቀን አለ ታላቅ ቀን እንባ ሁሉ ከዓይኖች የሚታበሰበት ሓዘን ትካዜ የማይታወቀበት ሕመም፣ ሞት፣ እንግልት፣ ስደት እና መፈናቀል ሁሉ የማይታወቅበት ዐዲስ የብርሃን ዓለም አለ፡፡ በዚህ ሆነን ግን እንቃትታለን፣ እንናፍቃለንም።

አሁን ግን ምናልባት ሳቃችንን ገታ ማድረግ ሳይኖርብን አይቀርም፡፡ የዓለሙ ዝብርቅርቅ መልክ በምንፈልገው መንገድ እና መልክ ባይለወጥ እንኳ ደግሞ ልብን ሰብሮ፣ እንባን ስንቅ አድርጎ ማልቀስ መጮኽ የተገባ ነው፡፡ ያለንበት ዓለም ብዙዎችን ይዘን ደግሞ የምናምጥ፣ የምንቃትትበትም ነው፤ በየማኅበሮቻንም ቢሆን አንዳንዱን አስረሽ ምቺው ገታ አድርጎ ማጠሞን፤ ዙሪያን መቃኘት መንፈሳዊነት ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ አዝኖም፣ አልቅሶም ያውቃል፡፡ የቅርብ ተከታዮቹ የነበሩት ሐዋርያቱም እንባ ነበራቸው፡፡ እኛም ብንሆን ወደ ተለየ ዓለም አልመጣንም፡፡
ዘማሪ ታምራት ኃይሌ በአዝመራ ጊዜ መኝታ
በጥሞና ጊዜ ጫጫታ
የሰልፍ ነው የድል ይህ ሁሉ እልልታ
ጌታ ሆይ ማስተዋልን ስጠን
ጊዜ እንዳያመልጠን፡፡ እንዳለው ጊዜን መለየት ትልቅ የመንፈሳዊነት ጥበብ ነውና፤ ቅዠት ከሆነው መንፈሳዊ ዓለም ባንነን ዘመኑን ለሚመጥን መንፈሳዊ ሕይወት ራሳችንን እናማጥን!!

መጋቢ ስንታየሁ በቀለ
599 views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 13:00:26
594 views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 11:54:35 "ጉራማይሌው ሰልፍ"

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ዋናው ጽ/ቤት በ2009 ዓ.ም. በጊዜው የነበረውን የቤተ-ክርስቲያንን የአስተምህሮ፣ የልምምድና የሥነ ምግባር ተግዳሮቶችን አብራርቶ፥13 ሐሰተኛ መምህራንና ነቢያት በስም ጠርቶ ማውገዙ ይታወቃል። ይህ ቁርጠኛና ታሪካዊ ውሳኔ የተላለፈበት ደብዳቤ ላይ አራተኛው ነጥብ እንዲህ ይላል፡-

"የአጥቢያዎቻችን መድረኮች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና ከመሠረተ ክርስቶስ አስተምህሮ ጋር የማይስማሙ አስተምህሮ የሚያስተምሩ ማናቸውም ሰዎች ማለትም የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት አባል እንኳ የትምህርትና ስብከት እድል እንዳይሰጣቸው ማድረግ።"

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በዚህ ውሳኔ መሰረት ከታች የተለጠፈው ማስታወቂያ የፈጠረብኝን ጥያቄዎች መጠየቅና ቅሬታዬን መግለጥ ነው።

በማስታወቂያው ላይ በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ የሚነሱ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶችና ልምምዶችን የሚያስተምሩ፣ የሚደግፉና የሚቃወሙ አካላት አንድ ላይ ተሰልፈው ይታያሉ። ጉራማይሌ ሰልፍ!! እንደዚህ አይነት ግልጽ አቋም የሌለው ኮንፍረንስ ታዳሚውንና ተመልካቹን ያወዛግባል። እንደዚህ ለማለት ያስደፈረኝን በአዘጋጁ፣ በአገልጋዮች፥ በተባባሪ አዘጋጁና በመድረክ አመቻቹ ላይ ያለኝን ቅሬታዎች ጥቂቱን በማስረጃ አብራራለሁ።

•መጋቢ በቀለ ወ/ኪዳን (ጋሽ በቄ)

በዕድሜያቸው፣ በድሮ አገልግሎታቸውና "ጣልቃ እየገባ" በሚለው መጽሐፋቸው ምክንያት አከብራቸዋለሁ። ነገር ግን ብዙዎች እንደሚስማሙት፥ ጋሽ በቄን ጤና-ቢስ የ"ሪቫይቫል" ናፋቂነታቸው መስመር ካሳታቸው ሰንበትበት ብሏል። የወንጌላውያንን ክርስትና ማንነትና ስም ለሚያጠለሹና የእውነትን መንገድ ለሚያሰድቡ ሐሰተኛ መምህራንና ነቢያት ድጋፍና ሽፋን በመስጠትም ይታወቃሉ። በወንጌላውያን ዘንድ ያላቸውን አንጋፋነትና ተደማጭነት ለስህተት እንቅስቃሴዎች ፈቃድ ለመስጠት ተጠቅመውበታል። ብዙዎችን አስተዋል፥ እያሳቱም ነው። ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቊም፥ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ይመስላል አንድም ቀን ተሳስቺያለሁ ሲሉ አልተደመጡም። ስለዚህ ጋሽ በቄን እንደማንኛውም ሐሰተኛ አስተማሪ በጥርጣሬ አያቸዋለሁ።

•"ሐዋርያ" ዮሐንስ ግርማ (ጆዬ)

የዝማሬ አገልግሎቱን አከብራለሁ። ሌላውን ለጊዜው ትተን፥ ሰሞኑን በኤሊያና ሆቴል የተዘጋጀውን ዓመታዊውን "ሰባቱ ተራራዎች" [7 Spheres] የተሰኘ "የአዲሱ ሐዋርያዊ እንቅስቃሴ" - New Apostolic Reformation [NAR] ስሁት ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች ውስጥ አሾልኮ በማስገባት ረገድ ቀዳሚ ሚና ተጫውቷል ፥ እየተጫወተም ነው። ቤተ ክርስቲያን የዚህ እንቅስቃሴ ገፈት እየቀመሰች ቢሆንም ምንነቱንና አደገኛነቱን በተመለከተ ብዙ ሥራ አልተሠራም። መሰል ኮንፍራንስም በየአመቱ ሲደረግ ከአብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ጀምሮ አንድም ሃይ ባይ አልነበረም። ይኼም ፕሮግራም የ7 Spheres ኮንፍራንስ ማጠቃለያ መሆኑን ልብ ይሏል።

•የወንጌላውን አብያተ ክርቲያናት ኅብረት

በተነጻጻሪ መልኩ "ደህና" የሚባል ተቋሟችን ነው። እስከነተግዳሮቱ የወንጌላውያን ማንነትና አስተምኅሮ ግድ የሚላቸው መሪዎች ያሉበት ይመስለኛል። ነገር ግን ከ"ካውንስሉ" መቋቋም ጋር ተያይዞ የተከፈቱበትን ስልታዊ ጥቃቶችን ለመከላከልና ኅልውናውን ለማረጋገጥ የሚኼድበት ርቀት እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። ከቤተ እምነቶች የአባልነት ምልመላ ጀምሮ የኅብረቱ መሪዎች የሚገኙባቸውን መድረኮች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሥፈርት አንጻር መዝኖ በመምረጥ ረገድ በውስጡ ላቀፋቸው ቤተ እምነቶች ምሳሌ መሆን አልቻለም። ይኼ ማመቻመች ገደብ ካልተበጀለት አሁን ያለው ቅይጥነት የበለጠ እንዳይስፋፋና ተቋሙ የቆመበትን መሰረት እንዳይነቀንቀው ያስፈራል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ አቋምና ጥራት ከሌለው፥ ኅብረቱ ከግራጫው "ካውንስል" በምን ይሻላል?

•ምሥራቅ መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን

ቤተ ክርስቲያንኗ የስህተት አስተምህሮና ልምምዶች ላይ ጠንካራ አቋም እንዳላት አውቃለሁ። ምዕመኗን ለመጠበቅ ሌተ'ቀን የሚደክሙ አገልጋዮችም አሏት። በመግቢያው ላይ በተጠቀሰው በዋናው ፅ/ቤት ውሳኔ የተወገዙ ሐሰተኞች ጋር ወዳጅ ለሆነና "ቀጥሉበት" እያለ ለሚያበረታታ ደፋር ሰው መድረኳን መፍቀዷ በምን አግባብ ልክ ሊሆን ይችላል? ከጥቂት አመታት በፊት በቤተ ክርስቲያኗ የትምህርት ክፍል በኩል ስለNAR [7ቱ ተራራዎች/5ቱ ቢሮዎች/የግዛት ስነ መለኮት] አስተምህሮ ስሁትነትና አደገኛነት ላይ ያተኮረ ቪድዮ መዘጋጀቱንና በሚዲያ መተላለፉን አስታውሳለሁ። ዛሬ ላይ ምን ተፈጥሮ ነው የ"7 Spheres" ኮንፍራንስ ማሳረጊያ ለተባለ ፕሮግራም መድረኩ ክፍት የሆነው?

ይኼን መጻፍ ለምን አስፈለገ?

ለስህተት እርሾ ትንሽ ቀዳዳ መክፈት ብዙ ዋጋ ያስከፍላልና የሚመለከታቸው መሪዎች እንዲያስቡበትና ይኼን ፕሮግራም የሚካፈሉ ሰዎች (ተማሪዎች) ስለ "የአዲሱ ሐዋርያዊ እንቅስቃሴ"
NAR አደገኛነት መንቃት እንዳለባቸው ለማሳሰብ ከጠቀመ በሚል ነው!

መልካም ቅዳሜ!

ፍጹማን ግርማ
627 views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 09:26:00

825 views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 12:12:14 የሁለት መዝሙሮች ወግ

ለመዝሙር አገልግሎት ያለኝን አፍቅሮት በተለያዩ ጊዜያት ገልጫለሁ። ይኼም አገልግሎት ሲበደል እንደሚጎረብጠኝ ፣ ውስጤም እንደሚቆጣ ብዙ ጊዜ ጠቁሚያለሁ። በርግጥ ብዙዎች ይኼን ስሜት ሚጋሩትም ይመስለኛል።

በኔ ግላዊ አተያይ የቀደሙት ዘማሪያን በጥቅሉ ለዝማሬ አገልግሎት ጥሪ ተገቢውን ምላሽ ሰጥተዋል ብዬ አስባለሁ። አገልግሎታቸው እንዳይነቀፍ፣ ሰንኩል መስዋእትም ሆኖ እንዳይቀርብ ደግሞም ዘመናትን እንዲሻገር ራሳቸውን በቃሉ ብርሃን ፊት አቅርበዋል። ኑረታቸውንም በበረታ ጸሎት መርምረዋል። ልኡል አምላክም በህዝቡ ፊት ለነዚህ ታማኝ ሎሌዎቹ ሞገስን በመስጠት መስዋታቸውን እንደተቀበለው ገልጧል ብዬም አምናለሁ።እሱ ያከበሩትን ያከብራልና!

ዳሩ ግን ዝማሬ ድሮ የቀረ የጥንት ዘመን ትውስታ ብቻ ግን አይደለም። ራሱን ያለ ምስክር ማይተው ህያው አምላክ ዘንድሮም ቅሬታዎችን አላጣም! በብዙ መሰጠት አገልግሎታቸውን ሚከውኑ ወጣትና ታዳጊ ዘማሪያንን ለቤቱ እያስነሳ አለ። ስሙ ይክበር!

ሁለት የጊዜያችንን ዝማሬዎች እንደ Trend ጠቋሚ በመውሰድ ንጽጽር ለመስራት ነው ሙከራ ማደርገው። የተመረጡት ዝማሬዎች ብቸኛ ማሳያ ናቸው እያልኩ ግን አይደለም። ይልቅ ሁለት ረድፍ ላይ የተሰለፉ ትይዩ መስመሮችን እነዚህ ዝማሬዎች ይወክሉልኛል።

ፍጹም ምንም አይነት የቅዱሳት መጻሕፍትን እውቀት ማይጠይቁ፣ መደዴ የቃላት አጠቃቀም ያላቸው፤ ከስነ ግጥም ሆነ ነገረ መለኮት አንጻር የቀነጨሩ ዝማሬዎች ዘመናችንን እንደሞሉት ሀገር ያወቀው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው። የጊዜ ማዘንበል ካገዘፋቸው መድረክ አድምቄዎች መሃል አንዱ ዘማሪ ይትባረክ አለሙ ነው። የዚህን ግለሰብ አንድ ዝማሬ ልዋስ።

መጣ ቤቴን አንኳኳ
ገብቶ ጩኸቴን ሰማ
ተለወጠ ሃዘን በደስታ
ሲጠጋጋኝ ወደኔ ጌታ።
እንኳን ቤቴ ገባ እንኳን ቤቴን አየው
ባለቀው ነገሬ በሱ ክብር አየሁ።

ይኼን አንጓ ለመጻፍ ሁለቴ ማሰብም ሆነ አንድ የመጽሃፍ ቅዱስ ምንባብ ማጥናት ያስፈልጋል ብዬ አላምንም። በጽኑ ጸሎት መሃል ሚቀበሉት አይነት መዝሙር ነው ብዬም አላስብም።

ሩቅ ሳልሄድ አንድ ሌላ ዝማሬ ላንሳ። ኤባ ዳንኤል፤ አቤኔዘር ደጀኔ፣ ብሩክ አሰፋና አብርሃም ሃለኬ በጋራ ሆነው የዘመሩት መዝሙር ነው። መልከጸዴቅ ይሰኛል የዝማሬው ርእስ።

በሞሪያም የታየው ታስሮ በዕፀ ሳቤቅ
የሳሌም ንጉስ ነው እርሱ መልከጸዴቅ
የአዲስ ኪዳን በግ የደህንነት መባ
መንገድ የሆነልን በስጋው ወደ አብ መንግስት መግቢያ!!!

ይኼን ጥልቅ ዝማሬ ለመዘመር በትንሹ ዘፍጥረት 14ን እና እብራዊያን 7ን ማጥናት ግድ ይላል። ማጥናት ብቻ ሳይሆን ጤናማ ተዛምዶ መስራትን ይጠይቃል። በአብርሃም ዘመን የነበረውን ንጉስና ካህን የሆነውን መልከጸዴቅን የክርስቶስ ኢየሱስ pattern/type አድርጎ ማቅረብ ቀላል የቤት ስራ ነው ብዬ አላስብም። የአዲስ ኪዳን በግ የሚለውም ሃሳብ የአለምን ሁሉ ሃጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ከሚለው የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 1 ትርክት የተቀዳ ይመስላል። በስጋው ወደ አብ መንግስት መግባት የሚለውም ሃይለ ቃል ከኤፌሶን ምእራፍ 2 የተወሰደ ይመስለኛል። እንግዲህ ዝማሬ እንዲህ በቃሉ እውነት ሲታጨቅ ለነፍስ የቀረበ መብል ይኾናል!!! ዝማሬው ይቀጥላል እንዲህ እያለ።

ሊቀ ካህናችን ወደ ቅድስት ገባ የገዛ ደሙን ይዞ
የእዳ ጽህፈታችን በሞቱ ተሽሯል በእርሱ ተሰርዞ
ዋስትና የሰጠን ለተሻለው ኪዳን የቆመ መካከለኛ
ከዘላለም ጥፋት በደሙ ዋጅቶናል ሆኖልናል መዳኛ!!!

እያንዳንዱ ገለጻ በቃሉ የተደገፈ ነው። ስለሆነም ዘልቆ ይነካል። ምንም እንኳ እልፍ ተመልካቾች ባይኖሩትም ለቃሉ የወገን የዘመኔ ዝማሬ ነው።

እንግዲህ የቤቴልሔም ተዘራ "ቃልህ ይሁን ትዝታዬ" እና የኤፍሬም አለሙ "ይረበሽ መንደሩ" ፣ የሃና ተክሌ "ይኽ ነው የኔ እረኛ" እና የይሳኮር ንጉሴ "ደስ ደስ እያለኝ ነው" ሁለቱም ዝማሬ ተብለው የተጠሩ ዳሩ ግን በብርሃን አመት ያህል የተራራቁ የዘመናችን ሁለት ጽንፎች ናቸው። አንደኛው ለስሜት ሲወግን ሌላኛው ለቃሉ ይወግናል። እንግዲያውስ መርጣቹ ፈትናቹ አድምጡ!!!

ኢብሳ ቡርቃ
861 viewsedited  09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 13:30:16
712 views10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ