Get Mystery Box with random crypto!

ነገረ ወንጌላውያን

የቴሌግራም ቻናል አርማ negere_evangelical — ነገረ ወንጌላውያን
የቴሌግራም ቻናል አርማ negere_evangelical — ነገረ ወንጌላውያን
የሰርጥ አድራሻ: @negere_evangelical
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.86K
የሰርጥ መግለጫ

በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ የሚፃፉ ፅሁፎች፣ ዘገባዎችና ዜናዎች ይቀርባሉ! ትምህርቶች፣ መረጃዎችና ምካቴ እምነቶች በዚህ ቻናል ይስተናገዳሉ! በተለያዮ ሶሻል ሚዲያዎች የሚገኙ ፀሐፊያን የሚፅፉቸው ፅሁፎችን እናጋራለን።

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 10:58:42
266 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:58:18 ላሁኑ እዚህ ደርሰናል!

የመንፈሳዊ አገልግሎት ጉዳይ መያዣ መጨበጫ ጠፍቶለት፤ ውሉ እንደጠፋ በግስጋሴ ላይ ይገኛል፡፡ እንኳ ይሆናል ይሰማል ብለን የማናስበው ነገር ሁሉ በመሐከላችን እየነገሠ ነው፡፡ መጠየቅን አነውረው የሚያዩ በተቀደደው ሁሉ የሚፈሱ ምእመናን እየበዙ፣ ስሕተት ቀንድ እና ጥፍር አብቅሏል፡፡

ወንጌላዊው ክርስትና ሐዲዱን ለቅቆ እየተንሸራተተ፣ የወንጌሉ ማእከላዊነት ጥጉን ይዞ፣ የግለሰቦች ገናናነት ሰማይ ደርሷል፡፡

የልክነት እና ስሕተት ሚዛኑ የማይለወጠው ቃለ እግዚአብሔር መሆኑ ቀርቶ ግለሰቦች በማይከሰሱበት እና በማይወቀሱበት ዙፋን ላይ ተሰይመዋል፡፡ መጠየቅ የተረገመ ሆኗል፤ ለምን? በሚሉ ላይ እልፍ የስድብ ምላሶች ይዘረጋሉ፤ ተቀባን ባዮች ስር እልፎች ተኮልኩለው በሆነው መንገድ ረድኤታቸውን ይጠባበቃሉ፡፡ እግዚአብሔርን በግል መማጠን ያለፈበት ፋሽን ሆኗል፡፡ የማይመረመሩት እና አይጠየቄዎቹ ቅቡዐን ያለ ከልካይ ይፋንናሉ፡፡

የዛሬ አመት እንዳሁኑ ወቅት የነሸጠው ቅቡዕ እግዚአብሔር እንደተናገረው እየማለ እየተገዘተ “2014 አንዳች ኮሽታ የሌለበት፣ ክፉ ሁሉ የሚያልፍበት፣ ለእናንተ እና ለኢትዮጵያ የመድረስ አመት ይሆናል፡፡” ብሎ ለፍፎ ነበር፡፡ አመቱ ግን እንዳያልፍ አለፈ፡፡ ለምን? ያለ ግን አልነበረም፤ አንዳንድ ደፋሮች እንደውም ትንቢቱን ቀባብተው እውነተኛ ለማስመሰል አይጥሩ ጥረት ጣሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እንቅጩን የመናገር ችግር የለበትም፤ ተናግሮም ከሆነ ዘወርዋራነት ጨርሶውኑ ሊኖረው አይችልም፡፡

በዘመነ ኤርሚያስ ሕዝቡ ተማርኮ መከራውን እንደሚበላ ነጩን ነበር የተናገረው፤ እርግጥ ይህ ያልተዋጠላቸው ሐሳውያን ነባያት ከገዛ ልባቸው እየወለዱ፣ በባዶ ተስፋ ሕዝቡን ሊያረጋጉ ይሞክሩ ነበር፡፡ በእስራኤል እና በይሁዳ የሆነው ግን እግዚአብሔር በኤርሚያስ የተናገረው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ከሌለበት ማባባበል፣ እግዚአብሔር ያለበት ቁጣ በስንት ጣዕሙ፡፡ የሆነው ሆኖ ግን ሕዝቡም ይህንን ወድዷል፤ ሐሰትን እየተጋተ ባዶነትን ያገሳል፡፡

ያልዘራችሁትን፣ ያለፋችሁበትን፣ ያልደከማችሁበትን ትበላላችሁ የሚልም ቅዠት ሰምተን ነበር፡፡ በየአካውንታቸው የራሳቸው ያልሆነን ብር የሚጠብቁ፣ የባንክ ደብረታቸውን በውሃ እና በዘይት ያረጠቡ፣ የኤቲኤም ካርድ የገዙ ተላላ “ምእመናንም” አይተናል፡፡

ከእግዜሩ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀናል፤ ክፍተኛ ግብግብ ላይ ነንም የሚለውን ጀግና አይተናል፡፡

በዚህ ሰሞን ደግሞ አዳፋ ላቤን የጠረኩበትን ስስ ወረቀት soft እያኘካችሁ በውሃ አወራርዱት ባይ ተከስቷል፡፡

እስከ አሁን እንግዲህ እዚህ ደረሰናል፡፡ ነገ የትም ልንደርስ እንችላለን፡፡ የክርስቶስ የሆነችው ቤተክርስቲያን ከድንዛዜዋ ወጥታ እንዲህ ያለውን ሸፍጥ እንቢኝ ልትል እና እውነትን በማስተማር ምእመኗን ልትጠብቅ ይገባታል፡፡ መሽኮርመሟን ወዲያ ጥላ፣ እውነት በሚጠይቀው ድፍረት ልትገለጥ ይገባታል፡፡ ቅዱሱን ወንጌል ከሚያረክስ እና ከሚያስወቅስ የትኛውም የሐሰት አሠራር ጋር ያላት ሰውር ይሁን ግልጥ ሕብረት ልታቆም ይገባታል፡፡ አጥሯን በማጠባበቅ የገዛ ዐደራዋን በአግባብ ልትወጣም ይገባታል፡፡

እግዚአብሔር ይርዳን!!!

መጋቢ ስንታየሁ በቀለ
249 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:18:25
281 views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:17:32 አንድ "ነብይ"ላቡን የጠረገበትን ሶፍት ፔፐር "ከፈለክ በውሃ ከፈለክ በምግብ ሶፍቱን ብላው" ብሎ ለአንድ ምዕመን ሲሰጥና ምዕመኑ "ላብህን የጠረክበትን ሶፍት በልቸ ከኩላሊት ህመም ተፈወስኩ" ሲል የመሰከረበትን ቪዲዮ ተመለከትኩ! አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ልክ አይደሉም ሲባሉ በቤታቸው ከሚፈፀመው ክብረ ነክ ወንጀል ይልቅ ገና ለገና እምነታችን ተነካ በሚል ስሌት "እግዚአብሔር አሰራሩ ልዩ ልዩ ነው" "በመንፈስ ካልሆኑ አሰራሩን መረዳት አይቻልም" ምናምን ይላሉ! ጥቅስ ያጠጋጋሉ! የማንንም የግል አረዳድ እምነት አከብራለሁ ... ግን እነዚህ "ነብያት" ዛሬ የፊታቸው ቆሻሻ በተጠረገበት ሶፍት በኩል እግዚአብሔር ተዓምር ሰራ ካሉ ፣ ነገ ሌላ ነገራቸውን የጠረጉበትን ሶፍት ለዚህ ምዕመን ቢያቀርቡለት እልል ብሎ እየከፈለ ይወስዳል ፣ለምስክርነትም ይቆማል!

ብቻ ይደክማል! ከማንም በፊት የቤቱ ሰዎች ይሄን ነገር አንድ በሉት! "እኔን ማን ፈራጅ አረገኝ" በሚል አጉል መንፈሳዊነት ስትሸበቡ ነገ በሌላው ዓለም ስንሰማው የኖርነው በእምነት ስም የሚፈፀም ዘግናኝ ግፍና ሰቆቃ በቤታችሁ እንዳይሆን ከእምነት ቤቱ አልፎ እንደአገር የሞራል ጥያቄ እንዳያስነሳ ሳይቃጠል በቅጠል

አሌክስ አብርሃም
297 views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:57:59
343 views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:57:50 የትኛውን ኢየሱስ ተቀበሉ?

ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያቱ ከስህተት ትምህርት ስለ መጠበቅ ብዙ ብለዋል። የአዲስ ኪዳን መልዕክቶችም እኩሌታ ስለዚሁ ጉዳይ የሚያወሳ ነው። ሌላ "ወንጌል" እና ሌላ "ኢየሱስ" የሚባልም ነገር አለ ብለውናል። በተለይ የሃሰትን ትምህርት ጉዳይ በቀላሉ ልንመለከተው እንደማይገባ በርካታ ማሳሰቢያዎች ተፅፈውልናል። ለምሳሌ እንኳ ብንወስድ ጴጥሮስም ሃሰት ስለሚያስከትለው አደጋ እንዲህ ነበር ያለው:-

“ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ.... አሹልከው ያገባሉ” (2ጴጥ 2:1)

ጳውሎስ ደግሞ የሚከተለውን ብሏል

“መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል” (1ኛ ጢሞ 4፥1-2)

ቢያንስ በእነኚህ ሁለት ጥቅሶች መሰረት ሃሰትን መማርም ሆነ ማስተማር ጌታን "መከተል" ሳይሆን "መካድ" ነው። "የህይወት" ሳይሆን "የጥፋት" በር ነው። ሃይማኖትን "መጠበቅ" ሳይሆን "መካድ" ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነውን "ኢየሱስ" ሳይሆን ሌላ "ኢየሱስ" ማምለክ ነው። የእግዚአብሔርን "ወንጌል" ሳይሆን ሌላ "ወንጌል" መቀበል ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያቱም ሆነ የቤተክርስቲያን አባቶች ሃሰትን በአደባባይ የሚገልጡትና ጉባኤ ጠርተው የሚቃወመት ብሎም የሚያወግዙት።

ወንድሜ ሆይ የሃሰት ትምህርት በነገሰበት ጉባኤ ወይም የሃሰት ትምህርት በነገሰበት አስተማሪ "አገልግሎት" ይህንን ያክል ሰው "ዳነ" ብሎ ማንቆለጳጰስ የጌታን ቁስል መውጋት ነው። ለንፁሁ ወንጌል ውድ ህይወታቸውን የከፈሉትን አባቶች መቀለጃ ማድረግ ነው። ስለዚህ "ጌታን ተቀበሉ" ሲባል ጠይቅ፤ የቱን ጌታ ሐዋርያቱ የሰበኩትን ወይስ እነ ኬነት ሃገን የሰበኩትን? የቱን ኢየሱስ መስቀል ላይ የሞተውን ወይስ ሲኦል የሞተውን? መንፈሰ የሆነውን ወይስ አምላክ ሰው የሆነውን? የቱን ከእኛ ጋር አኩያ የሆነውን ወይስ ከአብ ጋር እኩያ የሆነውን?.....የቱን ኢየሱስ ተቀበሉ ብለህ ጠይቅ?

"ዳነ" የተባለውን ሁሉ "በምስጋና" የምንቀበል ከሆነ ታዲያ ለምን ኦንሊ ጂሰሶች ሲያጠምቁ አብረን አንዘምርም? ለምን ታዲያ ጆሆቫ ዊተነሶች አዳዲስ አባላቶቻቸውን በጉባኤያቸው ሲያስተዋውቁ እልል አንልም? ሞርሞኖች "የወንጌል" ስርጭት መርሃ ግብራችን "የተሳካ ነበር" ሲሉ ለምን "በርቱልን" ብለን የምስጋና ደብዳቤ አንፅፍላቸውም? ኦርቶዶክሳዊያኑም እኮ አዳዲስ አባላት አጥምቀው ይቀበላሉ ለምን ታዲያ "አበጃችሁ ድንቅ የጌታ ስራ ነው" አንላቸውም?

ወገን "መመዘኛችን" በራሱ "መመዘኛ" ያስፈልገዋል። በጴንጤነት ጎራ (መደብ) ሳይሆን በቃለ እግዚአብሔር መርህ "መለካት" አለብን። በቃል እምነት (word of faith) ስሁት ትምህርቶች የተጠመቀ (ዮናታን የword of faith ሰው ካልመሰህ ኮሜንት መስጫ ላይ ሊንክ አስቀምጥልሃለሁ) እና በሃሰት ትንቢት የተገኘ ሰው "ይህንን ያክል ሰዎች ጌታን ተቀበሉ አመስግኑልኝ ሲል" ምን ሰበከላቸው? የትኛውንስ ጌታ ነው የተቀበሉት?....ወዘተ ብለህ ሳትጠይቅ ለጭብጨባ እጅህን የምታነሳ ከሆነ በርግጥ "በመጨረሻው ዘመን ይገለጣል" የተባለው ክፉ መንፈስ አግኝቶሃል። ወንጌሉም አልገባህም። "የትም ፍጪው..." በሚለውም ተረት ታምናለህ ማለት ነው። "ከፈሪሳዊያን እርሾ ተጠበቁ" ያለው ምን እንደሆነም ገና አልመረመርክም። "ለድነት" የአስተምህሮ ጤነኛ መሆን የግዴታ እንደሆነ ከቶ አላወቅህም። አባቶችም ዋጋ እየከፈሉ ከሃሰት ትምህርት ጋር ለምን እንደተጋደሉም ገና አልተገለጠልህም ማለት ነው። ታዲያ በዚህ አያያዝህ ነገ ሃሰተኛው ክርስቶስም ሲገለጥ ሳታጨበጭብ ትቀራለህ? ይርዳሃ!

አንዳንዶች "የዮኒ ስህተት እኮ ብዙም አይደለም" ብለው ለመሸፋፈን ይጥራሉ። ሲጀመር ተሳስተዋል እነርሱ እንዳሉት እንኳ ይሁን ብንል፤ የብርጭቆ ውሃ ጥቂት ብቻ መርዝ ቢገባበት ለመጠጥ ይሆናል? ጥቂት እርሾስ ሊጡን ሁሉ አያቦካውም? ለመሆኑ አንድ ትምህርት "የስህተት ትምህርት" ለመባል ምን ያህል መጠን "ስህተት" ሊገባበት ያስፈልገዋል? ወዘተ..ብለን እንጠይቃለን። ወዳጅ ሆይ መመዘኛችን ቃለ እግዚአብሔር እንጂ የሚዲያ "ፕሮፖጋንዳ" ወይም "አባቶች" የተባሉ ሰዎች "አጃቢነት" አይደሉም።

በመጨረሻም

“ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን”
(ገላ1፥8) ተብሎ እንደተፃፈ ማስታወስ "ለማሰብ" ይረዳል እላለሁ። ሌላው ደግሞ ሃሳዊያን ላይ ተቃውሞ በቀረበ ቁጥር ተሽቀዳድመው "ቀንታችሁ ነው" "እናንተ ምን ሰራችሁ!?" "አንድ ሰው አድነሃል!?" የሚሉ ደካሞች ወይም በገንዘብ የተገዙ አሉ። ለእነርሱ ያለኝ መልስ "አዎ ቀንቼ ነው!" ይህንን ሁሉ የምለው ለክርስቶስ ወንጌል "ቀንቼ ነው" ልክ ያልሆነውን የምናገረው ደግሞ ከእኔ "ስራ" ጋር ሳይሆን ከቃሉ ጋር አስተያይቼ ነው የሚል ነው። የዚህ ልጥፍ ዓላማም "የእንጠይቅ ጥሪ" እንጂ የሰውን ስራ የማጣጣል አለመሆኑ ይታወቅልኝ። ማስተዋሉን ያድለና!

ቴዎድሮስ ተጫን
339 views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 15:19:24
530 views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 15:15:20 ቤተክርስቲያን እና ቄሳር

ታሪክ እንደሚነግረን በአውግስጦስ ቄሳር ዘመነ መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረችው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በተለይ በቄሳር ኔሮ አገዛዝ ወቅት በብዙ ስደትና መከራ አልፋለች። በዘመነ ቆስጠንጢኖስ ደግሞ የሮም መንግስታዊ ሃይማኖት ለመሆን በቅታለች። ቀስ በቀስም የሮም አፄያዊ አገዛዝ እየተዳከመ ሲመጣም ከመንፈሳዊ ተቋምነቷ በፍጥነት ተለውጣ የፖለቲካ አመራሩን በእጅ አዙርም ቢሆን ወደ መምራት መጣች።

በመጀመሪያዎቹ ሶስት መቶ አመታት የነበራት ወንጌል የመስበክና ደቀ መዛሙርትን የማፍራት ትጋት በቄሳር ዘንድ ባገኘችው ተቀባይነት ምክንያትና "በቤተመንግስት ያለው ንጉስ የኛ ሰው ነው" በማለት ወንጌል የማስፋቱን ስራ "በመስዋዕትነት" ሳይሆን በቄሳር ቆስጠንጢኖስ ቤተመንግስት ትዕዛዝ ወደ ማከናወን ቀየረችው። ሺዎችም በቄሳር ትዕዛዝ "ጌታን" እንዲቀበሉ አደረገች ትልልቅ መሰብሰቢያ አዳራሾችን መግንባቱንም በሰፊው ገነባችበት።

ደቀ መዝሙር ማድረግ የሚባለው ጉዳይ እየተዘነጋ አገልጋዮቹም ስልጣን ማደላደልና በቤተመንግስት ማለፊያ ማዕድ ዙሪያ መታደም ላይ ብቻ አተኮሩ። ቤተክርስቲያንም የወንጌል ስራዋን በሶስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ እርግፍ አድርጋ ትታ ከቄሳር ጋር አሼሼ ገዳሜ ማለቱን እንደ ዋና ስልት ወሰደችው። ኋላም በስድስተኛው ክፍለ ዘመን የተወለደው እስልምና ጡንቻ አውጥቶ በአስረኛው ክፍለ ዘመን ላይ ኢየሩሳሌምን ልቆጣጠርና ዓለምንም ልሸፍን አንድ ምዕራፍ ነው የቀረኝ እያለ ሲፎክርባት ምርጫ ስላልነበራት "የመስቀል ጦርነትን" አወጀች። ጠብ መንጃ "ባርካ" በዚህ ጦርነት የተሳተፈ "የእርሱና የቤተሰቡ ሃጥያት ይሰረይለታል" ብላ ልጆቿን አሰለፈች። መስቀልና ሰይፍንም በአንድነት አነገበች። ያሳዝናል!

ቀድማ በጀመረችበት ሩጫ ልክ ፈጥና ቢሆን ኖሮ! "ኖሮ" ነው። የቆስጠንጢኖስ ግብዣ ባያደናቅፋት ኖሮ ቤተመንግስቱም "እንደገፋት" ቢቀር ወይም እርሷ "አንቢ ለግብዣህ" ብላው ቢሆን ኖሮ። "በቤተመንግስት እኮ ያለው የእኛ ሰው ነው" ማለት ባትጀምር ኖሮ። ዓለምን በሸፈነች! የክርስትና ተቃራኒ የሆኑትም ሆነ ሌሎች ሃይማኖቶችም ባልተስፋፉ ነበር።

ዛሬም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከተሰጣት ወንጌልን የመስበክና ደቀ መዝሙር የማፍራት ተልዕኮ ፈቀቅ ብላ "በቤተመንግስት እኮ ያለው የእኛ ሰው ነው" ብላ መንግስትን ወደ ማጀብ አልፋም የመንግስትን ስልጣን መከጀል ከጀመረች ሰንበት ብላ እንደ ጥንቱ ዘመን ታሪኳ ወንጌልን ለማስፋፋት ሆነ ለመጠበቅ የመንግስት ጡንቻ (ክላሽ) መበደሯ አይቀርም።

ስለዚህ የቀደመውን አጭር ልጥፍ እዚህም እደግመዋለሁ.... መንግስትን "መደገፍም" ሆነ "መቃወም" የቤተክርስቲያን ተልዕኮ አይደለም። የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ወንጌል መስበክና ደቀ መዛሙርትን ማፍራት ብቻ ነው።

ቆም ብሎ ለማሰብ ጊዜው ነው!

ቴዎድሮስ ተጫን

ዙሪያዬን አጅቦኝ ወታደር
በቄሳር ሰገነት ከማደር
ደም እምባ እያፈሰስኩ ለጌታ
ይሻለኛል ለእኔስ ጎልጎታ

ዘማሪ ታምራት ሃይሌ
627 views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:30:10
774 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ