Get Mystery Box with random crypto!

Mujib Amino Z islam

የቴሌግራም ቻናል አርማ mujibbinislam — Mujib Amino Z islam M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mujibbinislam — Mujib Amino Z islam
የሰርጥ አድራሻ: @mujibbinislam
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.61K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-08 20:49:23
6.8K viewsAllah Is Great, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 06:06:55
3.3K viewsAllah Is Great, 03:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 06:06:39 የነፍስ አድን ጥሪ
''ልጃችንን ታደጉልን''

ልጃችን አይሰል ጀማል አህመድ ትባላለች። ከተወለደች ገና የ4 ወር እድሜ አልሞላትም። ለቼክ አፕ ወደ ሆስፒታል ባቀናንበት ወቅት ዶክተሮቹ በድንገት አስደንጋጭ መርዶ አረዱን። ልጃችን አይሰል የልብ ችግር እንዳለባት እና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቼክ መደረግ እንዳለባት አሳወቁን።

ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብንወስዳትም የተሻለ ነገር አልገጠመንም። ይልቁንም ህክምናው በሀገር ውስጥ እንደማይገኝና በአስቸኳይ ወደ ውጭ ሂዳ መታከም እንዳለባት ነገሩን። ለህክምናውም እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል። ይህ በልጃችን ላይ የተከሰተው የልብ ቧንቧ ችግር በልጃችን ላይ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ የመጣ የክብደት መቀነስ ልጃችንን ለከፋ ህመም እየዳረገብን ስለሆነ እባካችሁ ሁላችሁም በምትችሉት አቅም እንድታግዙን በፈጣሪ ስም እንጠይቃችኋለን።

የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ
1000387141204
አባቷ ጀማል አህመድ
+251 98 504 6004
3.3K viewsAllah Is Great, 03:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 00:48:42 https://www.facebook.com/100045337022542/posts/pfbid02JNPVKkTf4m86me3vBMpoNZtcjSuhMBTD67sQ7a6WG4HZBxnuE6JevFj1RpiWJxCXl/?sfnsn=mo
3.3K viewsAllah Is Great, 21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 23:10:31
3.5K viewsAllah Is Great, 20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 23:10:24 አስተሳሰብ ሲጎለብት

አሁን በምገኝበት ቤልጂየም ሁለት ሀገራት የሚጋሩበት ድንበር ላይ ተገኝቼ ነበር:: ሁለቱ ሀገራት ቤልጂየም እና ኔዘርላንድ ናቸው:: በመካከላቸው ምንም ዐይነት የድንበር መከለያ፣ ጠባቂ ወታደር ወይንም ሌላ ሰው ሰራሽ ግርዶሽ አልተበጀለትም::

አንድ መኖሪያ ቤትም ግማሹ ክፍል በቤልጂየም ሀገር ውስጥ ሲገኝ ግማሹ ደግሞ በኔዘርላንድ ሀገር ግዛት ውስጥ ይገኛል::

የነዚህ ሀገራትን የድንበር ሁኔታ ተመልክተን ወደ እኛ ሀገር ስናስብ ግን የአንድ ሀገር ህዝቦች ሆነን እንኳን በቋንቋ እና በብሄር ድንበር ለይተን የኔ መሬት ነው ውጣልኝ እየተባባልን እንገዳደላለን::

የአረቡ አለምን ስንመለከትም አንድ ኡማ መሆን ሲገባው ተመሳሳይ እምነት ፣ተመሳሳይ ባህል፣ ቋንቋ እና የአኗኗር ዘይቤ ኖሯቸውም ድንበር አበጅተው፣ አጥረው እና ተከፋፍለው ይኖራሉ::

ኢስላም አለምን በመራበት ዘመን በጨለማ አስተሳሰብ ውስጥ የነበሩት አውሮፓውያን ዛሬ ላይ ከነበሩበት ኋላ ቀር አስተሳሰብ ተላቀው የሀገራት መለያየት የአስተዳደር ወሰን መለያ እንጂ የሰው ልጆች መለያያ አለመሆኑን ተረድተው በመካከላቸው ያለውን ሰው ደራሽ የድንበር ግርዶሽ አንስተው እርስ በእርስ በሰላም እየኖሩ ይገኛሉ::

ጌታችን አላህ(ሱወ) የሰው ልጆችን ጎሳ እና ነገድ አድርጎ መፍጠሩ እርስ በእርስ ለመተዋወቅ ብቻ እንጂ አንዱን ከአንዱ በማበላለጥ እንድንፎካከር፣ ድንበር አበጅተን እንድንጋደል እና እንድበታተን አይደለም::

አላህ(ሱ•ወ•) በቁርዓኑ እንዲህ ይለናል:-

"እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድ እና ከሴት ፈጠርናችሁ። ትተዋወቁም ዘንድ ጎሳና ነገድ አደረግናችሁ። ከናንተ ውስጥ በላጩ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ነው።"

ይህን የቤልጂየም እና የኔዘርላንድን ድንበር ስንመለከትም ብዙ ትምህርቶችን እናገኝበታለን::

እናንተስ የሁለቱ ሀገራትን ድንበር ስትመለከቱ ምን ተማራችሁ??
3.4K viewsAllah Is Great, 20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 23:07:21
3.2K viewsAllah Is Great, 20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 23:06:55 የተከበሩ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ Ustaz Kamil Shamsu-offical የታክስ አምባሳደር ተደርገዉ ተሾሙ።
Mujib Amino
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ከየካቲት 2015 እስከ የካቲት 2016 «ግብር፥ለሀገር ክብር» በሚል መሪ ሃሳብ በሚያሂዱት ሀገራዊ የታክስና የጉምሩክ ሕግ ተገዥነት ንቅናቄ የተከበሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የታክስ አምባሳደር ሆነው በኃላፊነት እንዲሰሩ ከገቢዎች ሚኒስትር በዛሬዉ እለት ተሹመዋል።

ላለፉት አራት አመታት የታክስ አምባሳደር በመሆን ተቋሞቹን ሲያገለግሉ ለነበሩ የታክስ አምባሳደሮች እውቅና እና ምስጋና የተሰጠ ሲሆን ከተቋሞቹ ጋር በቀጣይ ለመስራት በታክስ አምባሳደርነት ለተሾሙት ትውውቅ ተደርጓል፡፡ የገቢዎች ሚኒስትር ከዚህ ቀደም የነበሩትን ሰዎች የሚተኩ የተከበሩ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱን ጨምሮ 9 ሰዎች በዛሬዉ እለት ሾሟል።

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ፣ የጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ፣ ሚኒስቴር ድኤታዎች፣ የታክስ አምባሳደሮች፣ ከዋናው መስሪያ ቤት፣ ከቅርንጫፍ እና ከክልሎች የተገኙ የገቢ ተቋም ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።
3.6K viewsAllah Is Great, 20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 21:26:10
5.6K viewsAllah Is Great, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 21:26:01 ዘመድኩን ና በኀይማኖት ተቋማት ስር የተሰገሰጉ ጽንፈኛ ሽብርተኞች!

የፀጥታ ግብረ ኅይሉ በተለይም ዘመድኩም በቀለን
ጨምሮ በኃይማኖት ተቋማት ስር የተሰገሰጉ ሽብርተኛና ጽንፈኛ ግብረ አበሮቹን በቁጥጥር ስር እንዲያዉል ስለመጠየቅ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
Mujib Amino

የሽብር ኃይሎቹ ከሚኖሩባቸው ሀገራት በአለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) እንዲሁም  እነሱ ከሚኖሩባቸው ሀገራት መንግሥት የፀጥታ እና የደኅንነት ተቋማት ጋር በተመሠረቱ የትብብር ማዕቀፎች አማካኝነት ወደ ሀገር ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ በህግም እንዲጠየቁ እየተሰራ ይገኛል።

እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የሀሰት ወሬዎችን በመፍጠር እና ከፍተኛ የሽብር ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ህዝቡን በብሄር እና በሀይማኖት በመከፋፈልና በማጋጨት የክልል እና የፌደራል መንግሥትን በኃይል ለመጣል እንዲሁም ሀገሪቱ ከጀመረችው የለውጥና የልማት መንገድ ወጥታ ወደ ለየለት ሁከትና ትርምስ እንድትገባ በህቡዕ ተደራጅተው እየሠሩ መሆናቸውን የገለፀው የጋራ ግብረ ኃይሉ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሆነው በሀሰት ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩ እነዚህን ጨምሮ ሌሎችም በህቡዕ አደረጃጀቱ ውስጥ ያሉ ግለሰቦችም  ጭምር በሽብርተኝነት ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።

የፀጥታ ግብረ ኅይሉ በተለይም ዘመድኩም በቀለን ጨምሮ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሁከት እንዲንሰራፋ፣ ብጥብጥ እንዲነሳ፣ ሽብርና ጥፋትን በማቀጣጠል ዜጎች በጥርጣሪ እንዲተያዩና ሃገሪቷ የደም መሬት እንድትሆን ጭካኔየዊ፣ ኢ ሰብዓዊ ፣ ኢ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የሚታወቅ ነዉ።

በመሆኑም ህግና ስርዓትን በተከተለ መንገድ የኃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ በስራቸዉ የሚገኙ መጋዘኖችና ሱቆች ላይ ትኩረት በማድረግ ፍተሻ እንዲያደርግ እንገልጻለን።

በተለይም በአዲስ አበባ ና አከባቢዋ ከዘመድኩን በቀለ ጋር ግንኙነት ያላቸዉ አካላት በግልጽ የሚታወቁ በመሆኑ መረጃና ማስረጃዎች ሳይሸሹ ኣፋጣኝ የምርመራ ሂደት እንዲዘረጋ እናሳስባለን።

በዚህ የምርመራ ሒደት ዉስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረገ ለሚገኘዉ የጸጥታና የደህንነት ግብረ ኀይል
በማህበረሰባችን፣ በሕዝባችን ስም የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
5.6K viewsAllah Is Great, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ