Get Mystery Box with random crypto!

MISSIONARIES OF CHRIST

የቴሌግራም ቻናል አርማ mojcn — MISSIONARIES OF CHRIST M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mojcn — MISSIONARIES OF CHRIST
የሰርጥ አድራሻ: @mojcn
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 212
የሰርጥ መግለጫ

ይህ channel ወንጌልን ምንሰብክበት እንድሁም ወንጌልን እንድንሰብክ የምያነቃቁ የተለያዩ ትምህርቶችንና ለወንጌል ተልዕኮ የሚያነሳሱ መዝሙሮችን ምናገኝበት ነው።
“ወንጌልን መስበኬ አያስመካኝም፤ የምሰብከው ግዴታዬ ስለ ሆነ ነው፤ ወንጌልን ባልሰብክ ግን ወዮልኝ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥16 (አዲሱ መ.ት)
አስተያየት ወይም ጥያቄ
እዝህ➡️ @moJcn2013feedback ያስቀምጡ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 07:00:22 (ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53)
----------
3፤ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።

4፤ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።

5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

6፤ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።

7፤ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

8፤ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

9፤ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገንበትም ነበር።

10፤ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈከደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።

11፤ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሰከማል።

12፤ ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
38 views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 13:14:27 ስጋ ለብሶ መጣ፣ቃል ወደ ምድር፤
እሱ ዝቅ ብሎ ፣
እኛን ግን ሊያከብር።
ተመታ ቆሰለ ፣ ተሰቀለ በግፍ፤
ህይወትን ሊሰጠን ፣ኀጥያቴን ሊያራግፍ።
ዛሬ ግን በዚያ የለም፣ ቤዛችን ተነስቷል፤
መክፈል ያቃተንን ፣እዳችን ከፍሏል ።
             HAPPY PASSOVER
1ኛ ቆሮንቶስ 15÷3-4
158 views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 10:53:32
154 views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 11:14:38 GOOD (HOLY) FRIDAY
መልካም(ቅዱስ) አርብ

የዛሬው አርብ መልካም አርብ፣ እንዲሁም 'ቅዱስ አርብ' በመባልም ይታወቃል፣ አርብ ወዲያውኑ ከፋሲካ እሁድ በፊት ነው። ኢየሱስ የተሰቀለበት ቀን ተብሎ በተለምዶ ይከበራል።
ኢየሱስ በዕለተ አርብ እንደተሰቀለና እንደሞተ በማሰብ ክርስቲያኖች መልካም አርብ በማክበር የኢየሱስን ሞት ማስታወስ ይገባቸዋልን?

መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች አንድን ቀን በማክበር የክርስቶስን ሞት እንዲያስታውሱ መመሪያ አይሰጥም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ነፃነት ይሰጠናል። ሮሜ 14፡5 እንዲህ ይለናል፡- “አንድ ሰው አንዱን ቀን ከሌላው ቀን ይልቅ የተቀደሰ ያስባል። ሌላ ሰው እያንዳንዱን ቀን በእኩል ይመለከታል። እያንዳንዱ ሰው በራሱ አእምሮ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስን ሞት በተወሰነ ቀን ማለትም በዓመት አንድ ጊዜ ከማስታወስ ይልቅ የጌታን እራት በማክበር የክርስቶስን ሞት እንድናስታውስ ይመክረናል። 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡24-26 እንዲህ ይላል "...ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት...ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።"

ለምን ጥሩ አርብ "ጥሩ" ተብሎ ይጠራል? (Why Good Friday)

የአይሁድ ባለ ሥልጣናት እና ሮማውያን በኢየሱስ ላይ ያደረጉት ነገር በእርግጠኝነት ጥሩ አልነበረም (ማቴዎስ ምዕራፍ 26-27 ተመልከት)። ይሁን እንጂ የክርስቶስ ሞት ውጤቶች በጣም ጥሩ ናቸው! ሮሜ 5፡8 "ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአል በዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።" 1ኛ ጴጥሮስ 3፡18 እንዲህ ይለናል፡- “ክርስቶስ እናንተን ወደ እግዚአብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ አንድ ጊዜ ስለ ኃጢአት ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች ሞቶአልና። በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ። ”

ብዙ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት መልካሙን አርብ በተለያዩ አገልግሎት ያከብራሉ፣ ብዙ ጊዜ ምሽት ላይ፣ የክርስቶስ ሞት በታላቅ መዝሙር፣ የምስጋና ጸሎቶች፣ ስለ እኛ ሲል ክርስቶስ መከራን ያማከለ መልእክት ...

ክርስቲያኖች መልካም ዓርብን "ለማክበር" ቢመርጡም ባይመርጡም የዚያ ቀን ክስተቶች በአእምሮአችን ውስጥ መሆን አለባቸው ምክንያቱም ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞቱ የክርስትና እምነት ዋነኛ ክስተት ነው።

አሳ፦53 ለይ ያለው ቃል የተፈፀመበት ቀን ነበር ።

።።።።። GOOD FRIDAY።።።።።


ወንጌል ሕይወተን ይሰጣል
128 viewsedited  08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 23:11:09 ወንገል ይሰበካል ትውልድ አርነት ይወጣል!!!! ከታች ያሉት 'Username' ሞች ውስጥ አንዱን በመንካት ሙስሊም ወንድም እህቶች
በማግኘትና እውነተኛ መንገድ እና ሕይወት ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ልትገልጡላቸው ትችላላችሁ።

በደቂቃ ውስጥ ለመስበክ ከፈለጉ ደግሞ
1, ከላይ ያለውን ጽሁፍ copy ያርጉ
2, ከ username ሞቹ አንዱን ይንኩ
3,ከዛን ስምና ምስል ይመጣል ወደ ውስጥ በመግባት paste ማድረግ በመጨረሻ መላክ።

ይሄን ስለምታደርጉ እግዚአብሔር አምላክ የሕይወት ዘመናችሁን ይባርክ


username በመንካት ላኩ።



@Enatyemam
@ZMMKAN
@Alahumeselialamuhammed
@Kun_Ala_Besira
@Nuseyb @Almewtubilhak
@MMUUBBAA
@Fochinka
@Fuadf14
@aellhe
@Abityy85 @Hanutiiii18
107 viewsedited  20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 23:11:09 በኢየሱስ የምያምን ሁሉ ይድናል


“እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።”
ራእይ> 3፡20 (KJV)

“የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።”
ሮሜ>10፡13 ( KJV )
“ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።”
— ማርቆስ 16፥16
“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”
— ሐዋርያት 4፥12
ስለዝህ ውድ ወንድሜ/እህቴ የዘለዓለምን ህይወት እንድታገኝ በኢየሱስ ከርስቶስ እመን/ኝ
ኢየሱስ ይወድሃል/ሻል!! ለዛም ነው ህይወቱን አሳልፎ የሰጠው እንድሁም ይህ ፅሑፍ አንተ/ች ጋር እንዲደርስ ያረገው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል
ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝዎ ለመቀበል ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ ቃል በማውጣት ያውጁ

"እኔ አለምን ሰይጣንን ክጃለሁ። ኃጢአተኛ እንደሆንኩ ኢየሱስ ክርስቶስም ስለ ኃጢአቴ በመስቀል ላይ እንደሞተ እና ለጽድቄም እንደተነሣ በማመን አሁን ክርስቶስ የግል አዳኝ አድርጌ ተቀብያለሁ! ስለዝህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስሜን በሕይወት መዝገብ ፃፍ!
97 views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 23:06:56 : ሰላም ነሽ ቤቲ?

: አይደለሁም ባክህ ትንሽ ደብሮኛል

: ምነው ምን ሆንሽ?

: ቴሌግራም ተጠቅሜ ስወጣ ጥሩ ስሜት አይሰማኝም

: ለምንድ ነው?

:ጌዜዬን አላግባብ እንዳባከንኩ ይሰማኛል

:እንደዛማ ከሆነ መፍትሄ አለው

:ምንድነው በናትህ ንገረኝ?

:አሁን የምነግርሽን ቻናል ከተቀላቀልሽ አሁን ያልሺኝ ሁሉ ገደል ይገባሉ ከዚህ ቻናል እኔ ብዙ ነገር ተጠቅሚያለሁ ሁሌ ቴሌግራም ስጠቀም #ወንገል ሰብከ ተምሬ ደስ ብሎኝ ነው ምወጣው

:በጣም ነው join ለማድረግ የጓጓሁት ሊንኩን ንገረኝ?

:ከስር @MOJCN የምትለዋን ከነካሽ ወደ ቻናሉ ይወስድሻል

:ስለነገርከኝ በጣም አመሰግናለሁ በቃ ቻው

:አረ ተረጋጊ...


@MOJCN
212 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 23:01:40 ፈዋሹ ቁስለኛ

ሐምራዊ ደመና ለበሰ ሰማዩ
ቁልቁል ሲተረተር የግርዶሽ ኪዳኑ፤
ወደ ላይ ሲወጣ የሥቃይ ተማጽኖ
የደሙ እንፋሎት ጠፈር ላይ ደምኖ
ከብርሃን ዕልፍኝ አልፎ እስኪገባ
ጸባኦት እስኪደርስ ከራስ ቅሉ ካባ
እሪታ ጩኸቱ
ቅናቱ ብርታቱ
እስኪቆም ትንፋሹ ወጣ ገሠገሠ
አካሉ ካለበት ሰማየ ሰማያት አልፎ እየጣሰ፤
ማን ካህን ይቆማል በጌቴሴማኒ
ምን ትርጉም ሊያመጣ የኃያላን ወኔ
ማን ቀምሶ ይኖራል ከጽዋው ጠብታ
ትንፋሽ ትነሣለች ከሰውነት ገብታ።

እሱማ እሱ ግን ይሄን ሁሉ ችሎ
ዕርጉም እስከሚባል ዕርግማን ላይ ሆኖ
ያሰማል ሰቆቃ ከሰው ዝቅ ብሎ።
___
እንኳን አደረሳችሁ
201 views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 23:01:08 "የምትሰብከውን ወንጌል ታምናለህ?" አለኝ
# እውነተኛ_ገጠመኝ_የማንቂያ_ደወል
የዛሬ 19 ዓመት አከባቢ ነው። አቤት ጊዜው እንዴት ይሮጣል?!
ጎዳና ላይ ቆመን የአዋጅ ነጋሪ አገልጋዮች በጀማአ ወንጌል
እያወጅን ነበር በጎዳና ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆመው
አገልግሎታችንን ይሰሙ ነበር።
ሙሉ ፕሮግራሙን ( ሰብከን፣ ዘምረን እና ለሁሉም ጸልየን ) ከጨረስን በኋላ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ ጥያቄ አለኝ አለ እኔም እሺ ወንድሜ ይቻላል አልኩት!

ፈጠን ብሎ #የምትሰብከውን_ወንጌል ታምናለህ? አለኝ በልቤ ምን ይጠየቃል ይህማ ግልፅ ነገር አይደለ እንዴ እያልኩ፤ ለመልስ ጊዜ ሳይሰጠኝ ከአንተ ጋር ያሉትስ በወንጌል ያምናሉ? ሁሉም
ጴንጤዎች ያምናሉ ትላለህ? እያለ ተመሳሳይ ጥያቄዉን አከታተለ
የሚገርመው አፉ ውስጥ ጫት እንደሞላ ነበር በጥያቄ
የሚያጣድፈኝ።
እኔም በወንጌል በደንብ አምናለሁ ቤተክርስቲያንም በሚገባ
ታምናለች አልኩት።
አንዳንድ ሰዎች ወሬያችንን ለመስማት ሰብሰብ ማለት ጀመሩ
እርሱም እዉነት ቅድም አንተ እንደምትሰብከው ሲኦል እንደነገርከን መጥፎ ስፍራ ከሆነና መንግስተ ሰማይ የከበረ ስፍራ ከሆነ፤ ኃጢአተኞችም ሁሉ በኢየሱሱ ክርስቶስ ስራ አምነው መዳን የሚችሉ ከሆነና የማያምኑ ሁሉ ደግሞ ሲኦል የሚገቡ ከሆነ ዛሬ ምድርን የሞሉ በኢየሱስ የማያምኑ ሰዎች ወደ ሲኦል ሲሄዱ እያያችሁ እንዴት አስችሎአችሁ ዝም ብላችሁ ቤተክርስቲያን ብቻ ተሰብስባችሁ ትለያያላችሁ?
እኔ ግን የምታምኑ አይመስለኝ?! ታዲያ እንዴት ጴንጤ ሁሉ
በየመንገዱ ወጥቶ ከሲኦል አምልጡ እያለ አይጮኽም?
እስቲ አስብ አንድ ህፃን እሳት ውሰጥ እየገባ እያየ ዝም ብሎ
የሚያይ ሰው ይኖራል? ሁሉም ሰው ህፃኑን ከእሳት ለማዳን
አይሮጥም? አለ።
እኔም እውነት ነው ለማዳን ይሮጣል አልኩት።
እርሱም እኔ ግን ትናገራላችሁ እንጂ ሲኦል እንዳለ የምታምኑ
አይመስለኝም አለኝ።

እውነቱን ለመናገር ደነገጥኩ የዚህ ሰው ጥያቄ ሳላስበው የእኔም
ጥያቄ ሆነ እውነት ትክክል ነን? የዘላለም ሞትና ሕይወት እንዳለ
ከተረዳን ለምን ሁሉም ሰው ወጥቶ አይጮህም? አልኩ።
ውስጤ በአማኞች (በእኛ ሁኔታ) በጥያቄ እንደተሞላሁ ብቻ ግን
ይህ ሰው ወደ ጌታ እንዲመጣ በማሰብ ለራሴም ጥያቄ
እንደፈጠረብኝ ስለዚህ እኮ ነው ይኸው እንደምታየኝ ጎሮሮዬ
እስኪዘጋ ስጮህ የነበረው ቅድም አላየኽኝም? አልኩት።
ብዙም አልተዋጠለትም እርሱ አማኝ ቢሆን ኖሮ ወንጌል ለመስበክ ያለ ዕረፍት እንደ እብድ እንደምጮህ እየታየው መሰለኝ እናንተ እንደምታምኑ እኔ ባምን... ብሎ ዝም አለ።

ይህ ሰው እንዴት አይነት እንቅልፍ ውስጥ (አግባብ ባልሆነ ዝምታ
ውስጥ) እንዳለን አሳይቶኝ ተለየኝ።
ወገኖቼ እኔም የሰውዬውን ጥያቄ እደግማለሁ በወንጌል
እናምናለን? የማያምኑ ሰዎች እንደማይድኑ የምናምን ከሆነ ለሰው ዘር ሁሉ ወጥተን በጌታ በኢየሱስ እመኑ ከዘላለም ሞት ዳኑ ብለን ለምን አንጮህም?


ወንጌል ለሁሉም ሁሉም ለወንጌል እንወጣለን እንወርሳለን
164 views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ