Get Mystery Box with random crypto!

Orthodox picture

የቴሌግራም ቻናል አርማ photoortodox — Orthodox picture O
የቴሌግራም ቻናል አርማ photoortodox — Orthodox picture
የሰርጥ አድራሻ: @photoortodox
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 165
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ውድ የተዋህዶ ልጆች ይህ ቻናል የተከፈተው
የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ምስሎችን እንዲተላለፉበት ነው።
✞በዚህ ቻናል ላይ የምንለቃቸው
🔸ቤተክርስቲያናዊ ምስሎች ፤
🔸የንግስ በአላት ጥሪዎች
🔸መዝሙሮች
🔸ስብከቶች

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-06 22:39:49 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"

ሰኔ ፴ (30) ቀን።

እንኳን ለነቢዩ ለሰማዕቱ ለካህኑ ለሐዋርያው ለመጥምቀ መለኮት ለተወለደበት (ለልደት) በዓልና በሕንደኬ ካሉ ደሴቶቸ በአንዲቱ ውስጥ ለሚኖር ለገድለኛ ለሆነ ለአባ ጌራን ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ማርያና፣ ከማርታ፣ ከመነኰስ ገብረ ክርስቶስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

+ + +
የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ሰምዑ አዝማዲሃ ወሰብአ ቤታ። እስመ አዕበየ እግዚአብሔር ሣህሎ ላዕሌሃ። ወተፈሥሁ ፍሥሃ ፈድፋደ። ወፈቀዱ ይስምይዎ በስመ አቡሁ ዘካርያስ። ወትቤ እሙ ዮሐንስሃ ይሰመይ"። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።

+ + +
ነቢይ፣ ሰማዕትና ሐዋርያ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ልደት፦ ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው።

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን "አይሆንም ዮሐንስ ይባል" አለች። "ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም" አሏት።

አባቱንም ጠቅሰው "ማን ሊባል ትወዳለህ" አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ "ዮሐንስ ይባል" ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።

ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።

ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና "ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት" አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።

"የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምጽ እነሆ" ብሎ ኢያሳያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለርሱ እንዲህ አለ "በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልአክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ"።

ራሱ መድኃኒታችንም ስርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።

ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛንም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

+ + +
ገድለኛው የሆነ አባ ጌራን፦ ይህም ቅዱስ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ነው። እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚወደው ጾምና ጸሎትንም የሚወድ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም የሚለምነውን ሁሉ ይሰማው ነበር። በጸሎቱም ከዚያች አገር ንዳድ፣ አባር፣ ድርቅ፣ በጠላት መማረክ፣ የደም መፍሰስና የመርከቦች መሥጠም ተወገደ የፈለገውንም ሁሉ በጸሎቱ ያገኝ ነበር።

ሰይጣንም ስለዚህ ስለ ተሰጠው ጸጋ ቀናበት በዕንቊ ያጌጠ ነገሥታትን ልብስ በለበሰች መልከ መልካም ሴት አምሳልም ታየው እርሷም ብቻዋን ትንጎራደድ ነበር። በአያትም ጊዜ ወደርሷ ሒዶ ሥራዋን ጠየቃት እርሷም እንዲህ አለችው "የንጉሥ ሰርስባን ልጅ ነኝ እኅቴ ከአባቷ ባሮች ጋራ በአመነዘረች ጊዜ ሁላችንንም ሊገድለን ፈለገ። ስለዚህ ፈርቼ በሌሊት ወጣሁ ወደዚች በረሀም መጣሁ ቅዱሱን ሰው አንተን በማግኘቴም እድለኛ ነኝ" አለችው። እርሱም "ወደ እኔ የሚመጡ ሰዎች እንዳያዩሽ ወደዚያች የዐለት ዋሻ ሒጂ" አላት።

በሌሊትም ከአራዊት የተነሣ እንደፈራ ሰው እየጮኸች መጥታ "የዱር አራዊት እንዳይበሉኝ ክፈትልኝ" አለችው። እርሱም ከፈተላትና ገባች በጎኑም ተኝታ ደረቱን አቀፈችው ልቡን ወደ ፍቅርዋ እስከ አዘነበለችው ድረስ ነገሯን አለሰለሰችለት። ያን ጊዜ ያደረበት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተለየው ከእርሷም ጋራ ተኝቶ ኃጢአት እደሚሠራ ሆነ። ከስህተት ስካርም በነቃ ጊዜ በጠላት ሰይጣን ተንኰል ተሸንፎ እንደ በደለ አወቀ።

ከዚህም በኋላ ከሰይጣን ተንኰል የተነሣ ያገኘውን ሁሉ በሥጋውም ኃጢአት እንደሠራ ጻፈ። ከዚህ በኋላም ከደሴቱ ተራራ ድንጊያ አንሥቶ እስከሚሞት ድረስ ራሱንና ደረቱን እየደበደበ ኖረ። ነፍሱም ድና ወደ ዘላለም ሕይወት በጌታ ቸርነት ገባች።

ከዚህም በኋላ እንደ ልማዳቸው ከእርሱ ቡራኬ ሊቀበሉ ሰዎች መጥተው አላገኙትም በፈለጉትም ጊዜ ተኝቶ አገኙትና ያንቀላፋ መስሏቸው ጀምሩ ግን ሞቶ አገኙት አለቀሱለት ተሳለሙት ገንዘውም ቀበሩት።

ከዚህም በኋላ ሞቱ በጠላት ሰይጣን ተንኮል ምክንያት ስለመሆኑ የጻፈውን አገኙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን።

የተባረ የሰኔ ወር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈጸመ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 30ስንክሳር።


+ + +
"ሰላም ለዮሐንስ ግፋዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ ወስቡሕ ላእክ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ"። ትርጉም፦ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፤ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን ድንግል ሰማዕት፣ ነቢይና አገልጋይ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።


+ + +
የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አሜሃ ይቤሉ አሕዛብ። አዕበየ ገቢረ ሎሙ እግዚአብሔር። ወኮነ ፍሡሓነ። መዝ 125፥2፥3። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥76-ፍ.ም።
61 views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 08:08:11
214 views05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 23:14:59 የእግዚአብሔር መላዕክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል !(በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
224 views20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 01:01:29 ​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን

@ortodoxslijoch

Comment @Kokuhahaymanotbot

@Kokuha_haymanot
@kokuha_haymanot
@kokuha_haymanot
212 views22:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 13:16:11 ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል
"ሰኔ ፲፪"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።

ዚቅ
ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ።

ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ።

ወረብ
ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/
ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/

ዚቅ
አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ።

ዚቅ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ።

ወረብ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/
ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ።

ዚቅ
ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ።

ወረብ
"ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/
ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ።

ዚቅ
ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ።

ወረብ
ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/
ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።

ዚቅ
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ።

ወረብ
መልአከ ሰላምነ/፬/
ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/

ምልጣን
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ።

አመላለስ
ወሪዶ እመስቀሉ/፪/
እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/

ወረብ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/

እስመ ለዓለም
እምድኅረ ተንሥአ እሙታን ዓርገ ውስተ ሰማያት በስብሐት አምላከ ምሕረት: ወተቀብልዎ አዕላፋ አዕላፋት: ወሚካኤል ሊቀ መላእክት በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር: ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር።

ዓዲ (ወይም)
እስመ ለዓለም
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ: አዓርግ ሰማየ አቡየ ወአቡክሙ: ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ: ዘንተ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት: ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት: ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት: መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላእክት ኖላዊሆሙ።

አመላለስ
በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር/፪/
ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር/፪/
ኦ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ዕቀብ ሕይወተነ ወሥረይ ኀጢአተነ፤
አድኀነነ ወባልሐነ ከመ ኢይርከብ ኃይለ ላዕሌነ ዝንቱ ደዌ ዘኮነ በመዋዕሊነ፡፡
ክፍለነ እምበረከትከ ቅድስት፡ በጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለ አሥመሩከ እምፍጥረተ ዓለም፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
28 views10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 21:35:20 “እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ” /ማቴ.10፡16/

እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን! አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)
190 views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 21:38:49 #ጾመ_ሐዋርያት (ሰኔ 6 - ሐምሌ 5)
(የ2014 ዓ.ም)
ሰኔ
‹ይህ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል..››

በየዓመቱ በዕለተ ሰኑይ የሚጀምሩ ሶስት አጽዋማት ብቻ አሉ ፡፡ ከእነርሱ መካከል አንዱ ጾመ ሐዋርያት ነው ፡፡ ቅበላው በዕለተ እሑድ ይሆንና ጾሙ ሰኞ ይውላል ፡፡ የ2014 ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 6 ይገባል ፡፡

ይህ ጾም እራሱ ጌታቸን ኢየሱስ ክርቶስ ትንቢት የተናገረለት ጾም ነው፡፡
ይህ ታላቅ ጾም የዛሬ 1901 ዓመት በፊት በራሳቸው በቅዱሳን ሐዋርያት የተጀመረ ጾም ነው ፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት መካከልም አንዱ ነው ፡፡
ፈሪሳውያ ጌታችንን ደቀ መዛሙርትህ አይጾሙም ብለው በጠየቁት ጊዜ እርሱም ‹‹ ሚዜዎች ሙሽራ ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን መሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ፤ በዚያ ጊዜም ይጾማሉ ፡፡ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም ፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና ፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል ፡፡ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል የወይን ጠጁም ይፈሳል ፡፡አቁማዳው ይጠፋል ፡፡ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ ፡፡›› ማቴ 9 ፥ 14-17 አላቸው ፡፡ይህ ቃለ እራሱ ጌታችን መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ስለ ጾመ ሐዋርየት የተናገረው ትንቢት ነው ፡፡

‹‹#መሽራው_ከተወሰደ በኃላ›› ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኃላ ማለት ሲሆን ይህን ጾም ከዕረገት በኃላ የምንጀምረው ፤ ይህን ምሳሌ በማድረግ ነው ፡፡ አስር ቀን ዘግይቶ መጀመሩም የሐዋርያት ሰውነት ለጾሙ መዘጋጀት ነበረበትና ነው ፡፡
@zemariian
የዚህን ማብራርያ በቀጣይ ጽሁፋችን እንመለስበታልን፡፡
ይህ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል ልናውቅ የሚገባው ነገር ግን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ከማስተማራቸው በፊት ይህን ጾም ጾመዋል ፡፡ በዚህም ጌታችን የተናረው ተንቢት ተፈጽሟል፡፡ ከሰባቱ አጽዋማትን አንዱ ነው ፡፡ በዚህ ምክንያት ይህን ጾም ታላቅ እና ልዩ ያስብለዋል ፡፡ ይህንን አውቀን ሁላችንም ልንጾመው ይገባል ፡፡


#share
ምንጭ፦
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
241 views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:15:30 ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡ በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ጾመ ሐዋርያት (ሰኔ ጸም) ሰኔ 6/2014 ዓ.ም
(JUNE 13/2022 G.C) ይገባል፡፡

@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
214 views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 22:28:03 #ዕርገት
#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@zemariian
የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡

ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡

እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡

ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡

ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡

ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡

(ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
ዘወትር ምክረ አበውለማግኘት ሰማያዊውን ነክታችሁ ተቀላቀሉ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@zemariian
265 views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 07:15:43
21/09/14
58 views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ