Get Mystery Box with random crypto!

ዝክረ ብሒለ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @behileabew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 345

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-19 05:16:44 የሕገ ወጡ ሲኖዶስ ቡድን አማካሪ የተናገረው...

"አንዴ በይቅርታ አንዴ በክህደት አድክሟቸው። ዕረፍት ንሧቸው። ሕዝቡን ተስፋ አስቆርጡት፤ ከዚያም ሕዝቡና አባቶች ይነጣጠላሉ። አንድነት ያጣሉ። ከዚያ በኋላ ሲኖዶሱም ፈውሱም ንጉሱም የእናንተ ይሆናል። በመጀመሪያ ሕዝቡንና አባቶችን ነጥሉ።

ከዚያም በመጨቃጨቅ፣ በመካሰስ፣ በየአደባባዩ በመፈራረጅ በሰው ሕሊና ውስጥ የጵጵስናን ዋጋ አሳንሡት። በስተመጨረሻም መምታት የምንፈልገው ቅኔ ቤት ይመታል። መፍረስ የሚፈለገው ቅኔም ይፈርሳል። ሁሉም ቀላል የሚሆነው ከዚያ በኋላ ነው"
35 viewsእሱበ ዐይናለም, 02:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 01:50:31 እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነወ።

ከፊት ይልቅ አሁን ልንተጋ ይገባል አባቶች አባት ሆነውን ከፊታችን ቆመው እግዚአብሔር ለፀሎታችን መልስ ሰቶናል።
እኛም በሁሉ ነገር ነቅተን እንኑር
24 viewsእሱበ ዐይናለም, 22:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 20:16:28
21 viewsbisrat, 17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 20:16:00 #የካቲት_2_ዕረፍቱ_ለርዕሰ_ባህታውያን_አባ_ጳውሊ

ይህም የበርሃው መልአክ፤ የባህታውያን ሁሉ አለቃቸው የሆነ አባ ጳውሊ ነው። ስርዓተ ብሕትውና በጳውሊ ስርዓተ ምንኩስና በእንጦኒ ተጀምሯል ይላል፤

ጳውሊ አባቱ ባለጸጋ ነበር ሲሞት ለታላቅ ወንድሙ በጴጥሮስ እጅ አድርጎ ኃላ አካለ መጠን ሲያደርስ ከፍለህ ስጠው ብሎት ተናዞ አረፈ፤ አባ ጳውሊ አካለ መጠን ሲደርስ “ ደረስሁ ልጅ ፈላሁ ጠጅ ” የአባቴን ገንዘብ ከፍለህ ስጠኝ አለው አይሆንም አልሰጥህም አለው ምነው ቢለው ልጅ ነህ ታጠፋዋለህ ብዬ ነው ይለዋል አላጠፋውም ስጠኝ ይለዋል ግድማ ካልኸኝ ብሎ ብዙውን አስቀርቶ ጥቂቱን፤ መልካሙን አስቀርቶ ተራ ተራውን ሰጠው አባ ጳውሊ በዚህ ተበሳጭቶ ዳኛ ጋር ሄደ በመንገድ ላይ አንድ ባለጸጋ ሞቶ ሊቀብሩት ሲወስዱት አየ አባቴ ባለጸጋ ነበር ሞተ ይሄም ባለጸጋ ነበር ሞተ እኔስ ነገ እሞት የለምን ብሎ ወደ ወንድሙ ተመልሶ ወንድሜ ገንዘቡ ላንተ ይሁን ትቼልሃለው ብሎ ከቤት ወጠ፤

መጀመሪያ ለ 3 ቀን ከመቃብር ቤት ገብቶ ጸለየ በ3ኛው ቀን ከሰማይ ግማሽ ህብስት ወረደለት፤ ገረመው፤ ፈጽሞ ሳይለዩ እንዲህ ከሆነማ ፈጽሞ ቢለዩማ እንደምን ያለ ተአምር በተደረገ ብሎ አናብስት አናምርት አካይስት አቃርብት ካሉበት ነቃዐ ማይ ልምላሜ ዕፅ ከሌለበት ድሩክ ለተአቅቦ ይለዋል ዘር ተክል ከማይገኝበት ከጽኑ በርሃ ገባ፤ የሰው ፊት ሳያይ ለ 80 ዓመት በተጋድሎ ኖሯል። ምግቡን ግማሽ ህብስት በየቀኑ የሚያመጣለት ቁራ ነበር።

የእረፍቱ ቀኑ ሲደርስ ከአባ እንጦንስ ጋር በእግዚያብሔር ፈቃድ ተገናኝተው ብዙ ነገር ተጨዋወቱ በተለይም በኃለኛው ዘመን ስለሚነሱት መነኮሳትና፤ ግብጽ በሙስሊሞች እንደምትወረር ብዙ ምስጢር አወሩ ብዙ ትንቢትም ተናገሩ።

ከዚህ በኃላ አባ ጳውሊ አስኬማ መልአክ አምጣልኝ ብሎ ይልከዋል፤ አባ እንጦስ ወደ ገዳሙ ሄደ የ 2 ቀን ጎዳና ነው ሲመለስ በርሃው ላይ ሰማያውያን መልአክ ሰፍረውበት ሲዘምሩ ሲያመሰግኑ አየ፤ ልብን የሚመስጥ የእጣን መዓዛም አሸተተ፤ ምንድር ነው ? ብሎ አንዱን መልአክ ይጠይቀዋል አባ ጳውሊ ሞቶ ነፍሱን እያሳረግን ነው ይለዋል ይሄን አስኬማ አምጣልኝ ብሎኝ ነበር ምን ላድርገው ? ይለዋል፤ ጸሎት አድርሰህ አድርግለት፤ ደግሞም መቃብሩን የሚቆፍሩ አንበሶች ይመጣሉ ቦታውን ለክተህ ስጣቸው አለው፤ ወደ ገዳሙ ሲገባ እጁን መስቀልያ እንደዘረጋ ሞቶ አገኘው የሚጸልይ እንጂ የሞተ አይመስልም ነበር አስኬማውን አድርጎለት ሲያበቃ ከራስጌው ቆሞ ኤልያስ ልበልህ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ልበልህ እያለ አለቀሰለት፤ ሁለት አንበሶች መቃብሩን ቆፈሩለት ገንዞ ቀበረው።

80 ዘመን ሙሉ ለብሶት የኖረው የሰሌን ልብስ ነበረችው ወስዶ ለሊቀ ጳጳሱ ለአባ አትናቴዎስ ሰጠው፤ በዚህች ልብስ አባ አትናቴዎስ ብዙ ተአምራትን ሰረቶበታል ይልቁንም ሙት አስነስቶበታል። በነገራችን ላይ የዚህ አባት ገድሉ በስፋት ከመጻፉ ባሻገር ግብጻውያን ፊልም ሰርተውለታል ይህን ፊልም ማህበረ ቅዱሳን ጥሩ አድርገው ወደ አማርኛ ተርጉመውታል። የበረታ ገድሉን ያንብብ የደከመው ፊልሙን ይመልከት።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ከአባ ጳውሊ በረከት ያሳትፈን። አሜን!!!
22 viewsbisrat, 17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 19:35:26
35 viewsbisrat, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 19:34:30 #በሦስት_ቀን_ጾም_ጸሎት_የሕዝበ_እስራኤላውያን_የሞት_አዋጅ_ተቀለበሰ።

ነገሩ እንዲህ ነው :-
በፋርስ ንጉሥ አርጤክስስ ዘመን እስራኤላውያን በምርኮኝነት በፋርስ ይኖሩ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን የፋርስ ንጉሥ አርጤክስስ በቤተመንግሥቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፡፡ በግብዣውም ላይ ባለሥልጣኖች፣ ባለሟሎች እና አገልጋዮች ተገኝተው እየበሉ እና እየጠጡ እጅግ በጣም ይደሰቱ ነበር፡፡ ነገር ግን በግብዣው ላይ የንጉሡ ሚስት ንግሥት እስጢን ስላልተገኘች ብዙ ሰዎች አለመኖሯን ይጠይቁ ስለነበር ንጉሡ ንግሥት እስጢን የንግሥት ዘውድ ደፍታ እንዲሁም በከበሩ ጌጣጌጦች አሸብርቃ በፍጥነት ወደ ግብዣው እንድትመጣ ታማኝ አገልጋዮቹን ላከ፡፡ ንግሥት እስጢን ግን በግብዣው ላይ እንደማትገኝ እንቢታዋን በመግለጿ ንጉሥ አርጤክስስ በጣም ተናደደ፡፡

ንጉሡ ከአማካሪዎቹ ጋር በመሆን ብዙ ከመከረ በኋላ እስጢን ንግሥት መሆኗ እንዲቀር እና በምትኳ ንግሥት የምትሆን ሴት እንድትፈለግ ተሰማማ፡፡ በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት በፋርስ ይኖሩ የነበሩ መልከመልካም ሴቶች ከየሥፍራው ተሰብስበው ለምርጫ ቀረቡ፡፡ ከእነዚህ መልከመልካም እና ቆንጆ ሴቶች መካከል አስቴር አንዷ ነበረች፡፡ አስቴር በፋርስ በምርኮ ከሚኖሩ እስራኤላውያን መካከል አንዷ ስትሆን እናት እና አባት ስላልነበራት አጎቷ መርዶክዮስ ያሳድጋት ነበር፡፡ አጎቷ መርዶክዮስ የንጉሡን ዓዋጅ እንደሰማ አስቴር በጣም ቆንጆ ሴት ሰለነበረች በንጉሡ እንድትመረጥ አዘጋጃት፡፡ ከዐሥራ ሁለት ወራት ዝግጅት በኋላ ቆነጃጅቱ በንጉሥ አርጤክስስ ፊት ቀረቡ፡፡ ከቆነጃጅቱ መካከል አስቴር በንጉሡ እና በሚያዩአት ሰዎች ሁሉ ፊት ሞገስን በማግኘቷ አንደኛ ሆና ተመረጠች፡፡ ከዛን ዕለት ጀምሮ አስቴር የፋርስ ንግሥት ሆና የንግሥና ዘውድ ደፋች፡፡

ንጉሥ አርጤክስስ ቆንጆዋን እና ተወዳጅ የሆነችውን አስቴርን በማግኙቱ በጣም ተደስቶ ለአስቴር ክብር ታላቅ በዓል አድርጎ ሕዝቡን ጋበዘ፡፡ አስቴር በሰው ሀገር በምርኮ የምትኖር ሴት ስትሆን እግዚአብሔር ሞገስና ውበት ሆኗት የንጉሥ ሚስት ሆነች፡፡ በፋርስ መንግሥት ላይ እግዚአብሔር ንግሥት አድርጎ ሾማት፡፡

በንጉሥ አርጤክስስ ዘመን በፋርስ መንግሥት ላይ የተሾመ ሐማ የሚባል ባለሥልጣን ነበር፡፡ ሐማ ከፍተኛ ባለሥልጣንና የንጉሥ አርጤክስስ የቅርብ ሰው ሰለነበረ ወደ ቤተመንግሥት ሲገባ እና ሲወጣ ብዙ ሕዝብ ይሰግድለት ነበር፡፡ ነገር ግን የንግሥት አስቴር አጎት መርደክዮስ ለሐማ እንደማይሰግድ እና እይሁዳዊ እንደሆነ የሐማ የቅርብ ሰዎች ክፉ ነገር ስለተናገሩበት ሐማ በጣም ተቆጣ፡፡ ሐማ ንጉሥ አርጤክስስን በውሸት አሳስቶ በፋርስ መንግሥት ግዛት ውስጥ ያሉ አይሁዳውያን ሁሉ እንዲገደሉ በንጉሡ ማኅተም ዓዋጅ እንዲወጣ አደረገ፡፡

ብዙ አይሁዳውያን በሐማ ተንኮልና በዓዋጁ በጣም አዘኑ፡፡ ነገር ግን መርዶክዮስ እግዚብሔር አስቴርን ንግሥት ያደረጋት ለዚህ ቀን እንደሆነ በማመን እና በአስቴር ምክንያት የሞት ዓዋጅ እንደሚቀየር ተስፋ በማድረግ ወደ አስቴር መልእክት ላከ፡፡ ንግሥት አስቴር እና ሕዝቡ ሦስት ቀን እና ሦስት ለሊት በጾም እና በጸሎት እግዚአብሔርን ከጠየቁ በኋላ አስቴር ወደ ንጉሥ አርጤክስስ ገብታ ሁኔታውን አስረዳችው፡፡ ንጉሡም አስቴር ሰለ ሕዝቧ ያቀረበችውን ልመና እና ምልጃ ተቀብሎ የሐማን ዓዋጅ ሻረ፡፡

ሐማ ንጉሥ አርጤክስስን በሐሰት በማሳሳቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ አይሁድ በንግሥት አስቴር ምክንያት እግዚአብሔር የሞቱን ዓዋጅ በሕይወት እንደየቀረው፣ ሐማም እንደ ተፈረደበት ዜናውን ሲሰሙ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡

በምርኮ ይኖሩ ለነበሩ አይሁዳውያን ንግሥት አስቴርን ከሞት እንዲያመልጡ እግዚአብሔር ምክንያት አድርጓታል በዚህ ትምህርት አውቃችኋል፡፡ ሕዝቡ በፍጹም ልባቸው በመታመን እግዚአብሔርን በጾም እና ጸሎት ተስፋ በማድረጋቸው በአስቴር ልመና እንዲሁም ምልጃ የሞት ዓዋጅ ሊየቀር ችሏል፡፡

ጾም ጸሎታችንን በቸርነቱ ተቀብሎ
የእኛንም የሞት አዋጅ ያርቅልን!!!
32 viewsbisrat, 16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 08:44:15
37 viewsbisrat, 05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 08:43:52 #ጥር_30_ቅድስት_ሶፍያና_ሦስት_ልጆቿ_በሰማዕትነት_ዐረፉ ።

ይኽችም ቅድስት ሶፍያ ከአንጾኪያ ከከበሩ ወገኖች የተገኘች ናት፡፡
የልጆቿ ስም ጲስጢስ፣ አላጲስና አጋጲስ ነው፡፡ የስማቸውም ትርጓሜ በቅደም ተከተላቸው መሠረት ‹‹ሃይማኖት፣ ተስፋ፣ ፍቅር›› የሚል ነው፡፡ ዕድሜአቸውም 12፣ 10 እና 9 ነው፡፡ የራሷ የሶፍያ የስሟ ትርጓሜ ደግሞ ጥበብ ማለት ነው፡፡

ልጆቿንም ወደ ሮሜ ከተማ ወስዳ እግዚአብሔርን መፍራትንና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማረቻቸው፡፡ የልጆቹም ምግባር ሃይማኖታቸው በከሃዲው የሮም ንጉሥ በአርያኖስ ዘንድ ስለተሰማ ንጉሡ ጭፍሮቹን ልኮ አስመጣቸው፡፡

እናታቸውም ‹‹ልጆቼ ተጠበቁ የዚህን የኃላፊውን ዓለም ክብር በማየት ልባችሁ እንዳይደክምና ከዘላለማዊ ክብር እንዳትርቁ፣ ከሙሽራው ከክርስቶስ ጋር ሆናችሁ ወደ ሰማያዊው ሠርግ እንዲትገቡ ጠንክሩ…›› እያለች ትመክራቸውና ታጽናናቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ እናታቸው ይዛ ወደ ንጉሡ አቀረበቻቸው፡፡

ንጉሡም ታላቂቱን የ12 ዓመቷን ጲስጢስን ‹‹ስታድጊ ከመንግሥቴ ታላላቅ ባለሥልጣናት ውስጥ ከአንዱ ጋር አጋባሻለሁ፣ ብዙ ስጦታንም እሰጥሻለሁ፡፡ አሁን ግን ለጣዖቴ ለአጵሎን ስገጂ›› እያለ ሊደልላት ሞከረ፡፡ እርሷም ንጉሡንና የረከሱ አማልክቶቹን ረገመቻቸው፡፡ ንጉሡም አማልክቶቹንና እርሱን ስለረገመች ቅድስት ጲስጢስን እጅግ በጽኑ ሥቃዮች አሠቃያት፡፡ በብረት ዘንግ አስደበደባት፤ ጡቶቿን አስቆረጣቸው፤ በብረት ምጣድ አድርጎ ከሥር እሳት አስነደደባት ነገር ግን በእሳቱ ውስጥ ሆና ስትጸልይ እሳቱ እንደጠዋት ጤዛ ቀዝቃዛ ሆነ፡፡ በዙሪያዋ ያሉና ይህንን ተአምር ያዩ ሰዎች ሁሉ ‹‹በዚህች ብላቴና አምላክ እናምናለን›› ብለው ጮኹ፡፡ ወዲያውም ራሶቻቸውን ቆረጧቸውና በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡

ከዚህም በኋላ የቅድስት ጲስጢስ አንገት ይቆርጡት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፡፡ እንዳዘዘውም አንገቷን ሰየፏትና ሰማዕትነቷን በድል ፈጽማ የክብር አክሊልን ተቀዳጀች፡፡ እናቷም ሥጋዋን አንሥታ ወሰደች፡፡

አሁንም ንጉሡ በሁለተኛይቱ ልጅ በቅድስት አላጲስ ላይም እንዲሁ ተመሳሳይ ሥቃይ አደረሰባትና አንገቷን አስቆረጠው፡፡ አሁንም እናቷ ቅድስት ሶፍያ ሥጋዋን አንሥታ ከወሰደች በኋላ እንዳትፈራ በማሰብ ስለ 9 ዓመቷ ታናሽ ልጇ ስለ አጋጲስ ጸለየች፤ አጽናናቻትም፡፡
ወዲያውም አጋጲስን አንስተው በመንኰራኩር ውስጥ ጨመሯት፡፡ የታዘዘ መልአክም መንኰራኩሩን ሰበረውና በሰላም ወጣች፡፡

ዳግመኛም ነበልባሉ እስከ ሰማይ የሚደርስ እሳትንም አንድደው በዚያ ይጨምሯት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፡፡ ቅድስት አጋጲስም በመስቀል ምልክት አማትባ ወደ እሳቱ ተወርውራ ገባች፡፡ ጌታችንም መልአኩን ልኮ እሳቱ እንደ ውርጭ አቀዘቀዘላት፡፡ በዚያ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎችም ሁለት ነጫጭ ልብሶችን የለበሱ ሰዎች በልብሳቸው ሲጋርዷት አይተው እጅግ አደነቁ፡፡ በጌታችንም ስም አምነው ምስክንርነታቸውን ሲሰጡ ራሶቻውን በሰይፍ ቆርጠዋቸው በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡

በመጨረሻም የቅድስት አጋጲስንም አንገቷን በሰይፍ ቆርጠው ሰማዕትነቷን በድል ፈጽማ አክሊልን እንድትቀዳጅ አደረጓት፡፡ የከበረች ሶፍያም የሦስት ልጆቿን ሥጋቸውን ወስዳ ገነዘቻቸውና ከከተማው ውጭ ወስዳ ቀበረቻቸው፡፡

በ3ኛውም ቀን መቃብራቸው ላይ ሄዳ በማልቀስ ነፍሷን ይወስድ ዘንድ ጌታችንን ለመነችው፡፡ ጌታችንም ልመናዋን ሰምቶ ጥር 30 ቀን ነፍሷን ወሰዳት፡፡ ምእመናንም መጥተው ገንዘው ከልጆቿ ጋር ቀበሯት፡፡ ከሃዲው ንጉሡ ግን በተአምራት ወዲያው ዐይኖቹ ጠፍተው ሥጋው ሁሉ ተሰነጣጠቀ፡፡ እጆቹም ተቆራርጠው፣ ሰውነቱ ተልቶና ሸቶ ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በሰማዕታቱም ጸሎት ይማረን!!!
318 viewsbisrat, 05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 20:29:04
71 viewsbisrat, 17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 20:26:56 40 ያውን የመጀመሪያውን አስር መዝሙር ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡ይህን ሁሉ ማድረስ ያልተቻለው ግን የተወሰኑ መዝሙራትን መርጦ በየእለቱ ያደርሳል፡፡

#2_ውዳሴ_ማርያም
ውዳሴ ማርያም ከተቻለ የሰባቱን ዕለታት ካልተቻለ የእለቱን ማድረስ ተገቢ ነው።የዘወትር ጸሎት ካደረስን በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም አድርሰን ይዌድስዋ መላዕክትን ደግመን ከእመቤታችን በረከት ተሳታፊ መሆን ተገቢ ነው፡፡ በዋልድባ የሚኖሩ መነኮሳት ውዳሴ ማርያም ከቅዳሴ ማርያም ሳያደርሱ ውለው አያድሩም፡፡ በየአብነት ትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና ተማሪዎች እና በየገዳማት ያሉ መነኮሳት ሁሉ ውዳሴ ማርያምን በየዕለቱ ያደርሳሉ፡፡እኛም ከአበው ተምረን ማታ ከመኝታ በፊት ወይም ጠዋት ስንነሳ ይህን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው፡፡

#3_ወንጌል_ዘዮሐንስ
የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ ከፋፍለን በየእለቱ ማንበብ ሌላው ጸሎት ነው፡፡አባቶች ይህንን ጸሎት በየእለቱ እያደረሱ ብዙ ተጠቅመውበታል።

4.ሌሎች_ጸሎታት:-
ውዳሴ አምላክ፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም ፣ በመዝገበ ጸሎት እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍት ላይ ያሉትን ሌሎች ጸሎታት፣እንዲሁም ገድላት፣ተአምራትን፣እንደ ችሎታችን በየዕለቱ እናደርሳለን፡፡ቢያንስ ግን ይህ ሁሉ ባይሆንልን ከላይ የጠቀስነውን የመዝሙረ ዳዊትና ፣ውዳሴ ማርያምን ጸሎት ማድረስ ይገባናል፡፡

አጭር ጸሎት በተቻኮልን እና መጻሕፍትን ለማንበብ ጨርሶውን ጊዜ በማይኖረን ሰዓት ይህንን እንድንጸልይ አንዳንድ አባቶች ይመክሩናል።አቡነ ዘበሰማያት፣ጸሎተ ሃይማኖት፣ሰላም ለኪ /ስለ ውዳሴ ማርያም ፈንታ/፣አቡነ ዘመሰማያት፣አንድ ከመዝሙረ ዳዊት/ መዝሙር 150/ በመዝሙረ ዳዊት ፈንታ/በመጨረሻም አቡነ ዘበሰማያት ማድረስ ብንችል መልካም ነው ።ጸሎተ ሃይማኖት የህይማንት መግለጫ በምህኑ እንጸልየዋለን። በመካከል ሰላም ለኪ በመድገማችንም የውዳሴ ማርያም በረከት ይደርሰናል። መዝሙረ ዳዊት 150 ስናደርስ ደግሞ ሁሉንም መዝሙራት የደገምን ያህል ይሆንልንና የዳዊቱን በረከት እናገኛለን፡፡ይህንን ሁሉ ማድረስ ካልተቻለን ግን ቢያንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን አቡነ ዘበሰማያት ብለን ከቤታችን ልንወጣ ይገባናል።

አጭር ጸሎት ከሥፍራ ሥፍራ ሊለያይ ይችላል፡;ዘጠኝ ሰላም ለኪ፣አስራ ሁለት አቡነ ዘበሰማያት በገዳማት ያሉ አበው ያደርሳሉ። አጭር ጸሎትን እነደ መደበኛ ማድረግ ለፈተና ያጋልጣል አጭር ጸሎት የምንጸልየው በጣም በተቸገርንበት፣ጊዜ ባጣንበት ሰዓት ነው።ይህንን ጸሎት እንደመደበኛ ይዞ በየእለቱ አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብቻ መድገም ግን ስንፍና እንዳይሆን ያስፈራል።ይልቁንም በክርስትና ሕይወት ጅማሬ ላይ ያሉ ምእመናን/ወጣንያን/ክርስትናውን እስኪላመዱ ጸሎታቸው አጭር ሊሆን ይችላል።እየቆዩ ሲሄዱ ግን በጸሎት እየበረቱ ወደ መደበኛው ጸሎት መድረስ አለባቸው።ሁል ግዜ ወተት መመኘት ሁል ግዜ አልበረታውም እያሉ አጭር ጸሎት እያደረሱ መተኛት ተገቢ አይደለም።ይህ አይነቱ አካሄድ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለስንፍና ምክንያት አድርጎ መጠቀምም ነው።

ከዚህ ጋር በቤተክርስቲያን አገልገሎት ላይ ያለንም ዳዊት መድገም ውዳሴ ማርያም ማድረስ ይጠበቅብናል።የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ዲያቆናት፣ቀሳውስት፣ሰባክያነ ወንጌል፣መዘምራን……እነዚህን ጸሎታት መጸለይ ይጠበቅባቸዋል።አልያ ግን እያወቅን ጸሎት ማድረስ እንዳለብን ብዙ ጊዜ ተምረን እንዳልተምርን ቸል ብንል ለፈተና መጋለጥ ይመጣል።ከእግዚአብሔርም ቸርነት እንድንርቅ ያደርገናል።

አቡነ ዘበሰማያት የጸሎታችን መነሻና መድረሻ ጸሎት ስናደርስ የጸሎታችን መነሻ (መጀመሪያ) አቡነ ዘበሰማያት ነው፡፡በመካከል ጸሎት አቋርጠን ከሰው የምንነጋገርበት ጉዳይ ቢገጥመን በአቡነ ዘበሰማያት ማሰር ተገቢ ነው፡፡በአቡነ ዘበሰማያት አስረን የገጠመንን ጉዳይ ፈፅመን እንመለሳለን፡፡ ከዚያም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ካቆምንበት እንቀጥላለን።ጸሎታችንን በአቡነ ዘበሰማያት ሳናስር በመሃል እንዳሻን እንዳናቋርጥ አበው ያስተምሩናል፡፡ የማህበር ጸሎት በቤታችን ከምንጸልየው ጸሎት በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ተገኝተን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው።

ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት እንደመሆና በእርሱአ የሚጸለይ ጸሎት ከጸሎታት ሁሉ የላቀ ነው።በካህናት እየተመራ ፣በሕብረት ሆነን የምናደርሰው በመሆኑ ታላቅ ኃይል አለው።እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ የምንጸልየውን ጸሎት እንደሚሰማ ሲያመለክተን እንዲህ በማለት ነግሮናል።”አሁንም በዚህ ሥፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ ፣ጆሮቼም ያደምጣሉ።ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም ዓይኖቼ እና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።”/2 ዜና መዋ 7-15/ ከዚህ አንጻር በቤተ መቅደስ እየተገኘን መጸለይ ተገቢ ነው።

በሰንበት ቀን ኪዳን ማድረስ ፣ ቅዳሴ ማስቀደስ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ተግባራችን መሆን አለበት።በሰንበት ያለ በቂ ምክንያት ቅዳሴ የሚያስታጉል በቀደሙ አባቶች /አባ ሚካኤል ወአባ ገብረኤል/ቃል መወገዙን የተአምረ ማርያም መቅድም ይነግረናል።ከዚህ ጋር በሰዓታት ፣በማኅሌት ጸሎታት ላይ በመገኘት ቤተ ክርስቲያናችን ካዘጋጀችልን የማይጠገብ ማእድ ልንሳተፍም ይገባናል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሃይማኖታችን ፍጹም ፍቅር የሚኖረን ከእነዚህ ጸሎታት ጋር ስንተዋወቅ ነው።አልያ የእንጀራ ልጅ መሆን ይመጣል።የመናፍቃንን አዳራሽ መናፈቅ ይመጣል። ከላይ በተመለከተው የጸሎት ጊዜ እየተጠቀምን፣የጸሎት ዓይነቶችንም በምትችለው መልኩ እያደረስን፣በቤተ መቅደስ እየተገኘን ኪዳን እያደረስን፣ቅዳሴ እያስቀደስን ከፈጣሪ ጋራ እለት እለት ተነጋገሩ::

ጸሎት ከሌለ መንፈሳዊነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ከጄነሬተሩ ተቋርጦ ገመዱ ተበጥሶ ብቻውን እንደተንጠለጠለ አምፖል መሆን ይመጣል፡፡ስለዚህ በርቱና ጸልዩ።

ፈጣሪ ለሁላችንም ብርታቱን ያድለን፡፡አሜን
136 viewsbisrat, 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ