Get Mystery Box with random crypto!

(Hamid Al_ashariy

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamid_al_ashariy — (Hamid Al_ashariy H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamid_al_ashariy — (Hamid Al_ashariy
የሰርጥ አድራሻ: @hamid_al_ashariy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 853
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ
በዚህ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ
@Sodrudin

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-16 16:13:05 ድምጽን ከፍ በሚደረግባቸው (ጀህሪይ) ሶላቶች ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂም አብሮ ከፍ ይደረጋል ወይስ በዝግታ ነው ወይስ ከእነ ጭራሹ አይቀራም?

ሶላት አሰጋገድ ውስጥ በመቶዎች ኺላፎች (የሊቃውንት) ልዩነቶች አሉ:: ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በጀህሪይ ሶላቶች ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂም ድምጽን ጎላ ተደርጎ ይነበባል ወይ የሚለው ነው::
-> ከእነ ጭራሹ አይቀራም የሚሉ ውሱን ዑለሞች አሉ::
-> ሀንበሊዮች ድምጽን ዝቅ ተደርጎ ይነበባል የሚለውን ይዘዋል::

የሁለቱ መረጃ የአነስ ኢብን ማሊክ ሀዲስ ሲሆን ከነቢዩ ﷺ ከአቡበክር, ከዑመርና ከዑሥማን ጋር ሰግጃለሁ:: ሶላትን በአልሃምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን ነው የሰገዱት ይላል:: ሀዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል::

-> ሻፍዒዮቹ በአቡሁረይራ ሀዲስ ነው የሄዱት:: ከነቢዩ ﷺ ከአቡበክር, ከዑመርና ከዑሥማን ጋር ሰግጃለሁ:: ሁሉንም ሶላት በ ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂም ነው የሰገዱት ብለዋል:: ይህ ሀዲሱ የተረጋገጠ ሶሂህ ነው::

ሻፍዒዮቹ <<ካልሰማው አነስ ኢብኒማሊክ የሰማው አቡሁረይራ ሀዲስ ይጠነክራል:: ካልሰማማ አልሰማም:: ሰማሁኝ ያለ ታማኝ ከተገኘ በቂ ነው>> ይላሉ::

ከሊቃውንቱ ከፊሉ አነስ ኢብን ማሊክ ያልሰማው ምናልባት ከሗላ ይሰግድ ስለነበርና ነቢያችን ﷺ ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂምን ድምጻቸው ዝቅ አድርገው ቀርተውት ስላልሰማ ስለሚሆን ድምፃችንን ዝቅ እናድርግ እንጂ አንተወውም በሚለው የሄዱ አሉ::

በዘካ, ንግድ, ኒካህ, ሀጅ የሀነፊይ መዝሃብ ሲመረጥ ሶላት ላይ ደግሞ የሻፍዒይ ይመረጣል:: በመሆኑም ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂም በየቁርአኑ መግቢያ መደጋገሙ ልዩ ትኩረት ስላለው በግልጽ ማድረጉ ይወዳል በሚለው የሀበሻ ዑለሞቻችን ሄደዋል:: ወሏሁ አዕለም ወአህከም
https://t.me/hamid_al_ashariy
92 viewsedited  13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 18:36:03
እነዚህ ሁለት ልጆች ወንድምማቾች ናቸው።
ታላቁ ትንሹን ወንድሙን ፀሀይ እንዳይመታበት የራሱን ልብስ አውልቆ ለታናሹ እራሱ ላይ አልብሶታል። سبحان الله
https://t.me/hamid_al_ashariy
83 viewsedited  15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:50:32 መልዕክተኛው ከባልደረቦቻቸው መሀል ቁጭ ብለው ህግጋቶችን እያስተማሯቸው ነው።ባልደረቦቹም ከመሀከላቸው የተቀመጡትን ነቢይ በስስት እየተመለከቱ እያዳመጡ ነው።

ድንገት አንድ የአይሁድ ሊቅ ሲንደረደር ወደ ስብስቡ መሀል ገብቶ ትሁቱን መልዕክተኛ አነቃቸው። ኮሌታቸው ጨፍግጎ ከያዘም በኋላ፦‹‹ብድሬን መልስ! ድሮም በኑ ሀሺም ጎሳዎች ብድር ታዘገያላችሁ›› እያለ ያንገላታቸው ጀመር።

ይህ ሰው በርግጥ ለመልዕክተኛው ገንዘብ ያበደረ ቢሆንም የተዋዋሉበት የመክፈያ ግዜ ግን አልደረሰም ነበር።

ቀና ብሎ ለማየት የሚሳሳላቸው ዑመር ረዐ ይህንን እንግልት ሲመለከት ብድግ ብሎ ሰይፉን ከማንገቻው መዘዘ'ና፦‹‹እባክዎ አንቱ ነቢ ይፍቀዱልኝና ይህን ሰው አንገቱን ልቀንጥስ›› አላቸው።

አንገታቸው የታነቀው ነቢይ ወደ ዑመር ዙረው ፍፁም በተረጋጋ አንደበት፦‹‹ተው እንጂ ዑመር! እኔ ብድሬን እንድመልስ ምከረኝ፣ እሱም በስርዐት እንዲጠይቀኝ አድርግ እንጂ ሰይፍን ምን አመጣው?›› አሉት።

የአይሁዱ ሊቅ ተረጋግቶ ቆመ። እንዲህም አለ፦‹‹በዕውነት በላከህ ጌታ እምላለሁ፤ ብድር ልጠይቅህ ሳይሆን የመጣሁት ትዕግስትህን ልፈትን ነው። በርግጥ ብድር መመለሻ ግዜህ አልደረሰም ነበር። ግና መገለጫዎችህን ሁሉ እኛ ዘንድ ባለው የኦሪት መፅሀፍ ስለተመለከትኩ አንድ ባህሪህን ብቻ ለማረጋገጥ ነው ዛሬ የመጣሁት።

ኦሪት ላይ እንዲህ ይላል" ያ ነብይ በቁጣ ግዜ ታጋሽ ነው፣ የመሀይማንም ጉንተላ ትሁትነትን እንጂ ሌላን አይጨምርለትም" አንቱ ነቢይ ሆይ! ዛሬ ይህን አረጋገጥኩ። ከአላህ ሌላ ጌታ እንደ ሌለ እመሰክራለሁ፤ አንቱም የአላህ ነቢይ መሆንዎን እመሰክራለሁ።

አንቱ ነቢ! ያ ያበደርኮት ገንዘብ ለድኾች ምፅዋት እንዲሆን ለግሻለሁ›› ብሎ እስልምናን ተቀበለ። ይህ ሰው ከትሁቱ ነቢይ የተወሰኑ አመታትን ካሳለፈ በኋላ በስተመጨረሻ በተቡክ ዘመቻ ከነቢ ሰዐወ ጎን እየተፋለመ መስዋዕት ሆነ።

ምንጭ፦
دلائل النبوة
https://t.me/hamid_al_ashariy
424 viewsedited  12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:35:32
የነብያችን ልጆች ስንት ናቸው???
Anonymous Quiz
3%
4
13%
6
75%
7
9%
8
32 voters147 views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 10:02:06 "ለኡድሂያ ምን አረድክ ያቢላል" አሉት ረሱሉላህ ﷺ
"ዶሮ" አላቸው
"ሙአዚን ሙአዚንን ያርዳል?" አሉት


የረሱልﷺ ቀልድ የገባው
152 views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:13:31 በከተማዋ ውስጥ በስስታምነቱ የሚታወቅ አንድ ኃብታም ነበር። ከብዙ ዓመታት ማንገራገር በኋላ አንድ ቀን ሐጅ ለማድረግ ሰምሮለት ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ አቀና። የሐጅ ሥነስርዓቱን አጠናቆ ወደ ትውልድ ቀዬው መመለሱን የሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰልፍ ወደ ቤቱ ጎረፉ። «ከሐጅ መልሥ ትልቅ ድግስ እንደምታዘጋጅ ከመሄድህ በፊት ቃል ገብተህልን ነበር። የገባኸውን ቃል ፈጽም እንጂ ?» በማለት ጠየቁት።

ምን ብሎ ቢመልስ ጥሩ ነው ??

«አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ከሐጅ በፊት ስለተናገርናቸው ነገሮች አዛኝ የሆነው አላህ በርግጥ ምህረት አድርጎልናል» አላቸው

መልዕክቱ «አሁን ወሬ ሳታበዛ የቤቴን ግቢ ለቀህ ተበተን » እንደማለት ነው

https://t.me/hamid_al_ashariy
163 viewsedited  15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 17:22:36 ሚስት ማግባት ከፈለግክ እልም ያለች አህባሽ መርጠህ አግባ። ወሀብያም ከሆንክ ጭልምልም ያለች ሰለፊስት አግባ።
እንደዛ ካልሆነ የማንነት ቀውስ ውስጥ ትገባለህ።
ምክሩ ለንቁ ትውልድ ነው!

https://t.me/hamid_al_ashariy
443 viewsedited  14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 17:46:24
211 views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 12:00:59 ጆሮዎቻችን የሞት ዜና መስማት የሚያቆሙበት፣ አንደበቶቻችን ክፉ ንግግር ከመናገር የሚቆጠቡበት፣ ልቡናዎቻችን ተንኮል ከመሸረብ የሚርቁበት ፣ እጆቻችን ለጥፋት ከመዘርጋት የሚታቀቡበት፣ እግሮቻችን ወደ ወንጀል ድግስ ለመታደም የሚያደርጉት ጉዞ የሚገታበት ፣ በአገራችን ሰማይ ስር ሰላም ሰፍኖ የፍቅር ሸማ ተከናነብን ከፍ የምንልበት ጊዜ አላህ እንዲያደርግልን እመኛለሁ።

እንኳን ለ1443ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢደል-አድሓ (ዐረፋ) በዓል አላህ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ

ዒዱኩም ሙባረክ
164 views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:34:38
ክቡራን አህባቦቼ፣ ወዳጆቼ፣ የቴሌግራም ጓደኞቼ እና መላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንኳን ለ1443ኛ ዓመተ ሂጅራ ለዒድ አል-አድሓ በዓል አላህ አደረሳችሁ!
ወንድማችሁ ሐሚድ
https://t.me/hamid_al_ashariy
182 viewsedited  18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ