2020-10-15 16:46:48
ዳሰሳ መጽሐፍ (book review ) (ዲ/ን ዘአማኑኤል ገዛኸኝ)
የመጽሐፉ ርዕስ :- ትምህርተ ጽድቅ
የመጽሐፉ አዘጋጅ :- ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው
የገጽ ብዛት :- 351
መቼተ ኅትመት :- አዲስ አበባ ፡ 2013
የመጽሐፉ ዋጋ :- 200 ብር
መግቢያ
ይህ የዲያቆን ዮሐንስ መጽሐፍ ዕቅበተ እምነታዊ (APOLOGETIC) ይዘት ሲኖረው በዋናነትም በነገረ ማርያምና በነገረ ክርስቶስ ዙርያ ከቀደሙት ዘመናት አንስቶ አሁን ድረስ ሲያከራክሩ ሲያወያዩ የነበሩ ጉዳዮችን እያነሳ የብዙ ቀደምት አበውን (Early Church fathers) አስተምህሮና ምስክርነትን በመግለጥ ጥሬውን አብስሎ ፣ አንኳሩን አድቅቆ ፣ የተበተነውን ሰብስቦ፣ የረቀቀውን አጉልቶ ፣ የተቋጠረውን ፈትቶ የሚያብራራ "ማለፊያ ነው" የሚያሰኝ መጽሐፍ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ " ቅዱሳት መጽሕፍትን ስታነቡ ገጸ ንባቡን ማንበብ ሳይኾን የጽሑፉን ሐሳብመፈለግ ይገባችኋል። ማንኛውም ሰው ምሥጢሩን መሠረት ሳያደርግቃላቶችንና የተጻፉትን ጽሑፎች ብቻ የሚመለከት ከኾነ ብዙ ስሕተቶችን ይፈጽማል” እንዲል ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በጥሬው የሚበሉ እየመሰላቸው ግራ ለሚጋቡ ምዕመናን ንባባቸውን ከቤተክርስቲያን ጋር
( ecclesiastical reading) እንዲሆን በማድረግ ከስህተት
የሚጠብቅ መጽሐፍ ነው ።
ምክንያተ- ጽሒፍአጽራረ ሃይማኖት የሆኑ ትምህርቶች ዛሬ እንደ አሸን ቢፈሉም መነሻቸው ግን ከፍጥረተ መላእክት ጀምሮ ነበር ። በኋላም
በዘመነ አበው ፣ ዘመነ ነቢያት፣ በዘመነ ሐዋርያት፣ በሐዋርያነ
አበው ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያንን ሲፈትን የኖረ ነው ።
ምንም እንኳ አርዮስ በስጋ ቢሞት በመንፈስ የወለዳቸው ብዙ
አርዮሳውያን አሉ ፤ መቅዶንዮስ በአካል ባይኖርም በመንፈስ
ያደረባቸው ነፍስን የሚገድሉ ትምህርቶችን የሚነዙ ሐሳውያን
አሉና ዛሬም እነ ቅዱስ አትናቴዎስ ፣ ጎርጎርዮስ እነ ሳዊሮስ
በመምህራነ ቤ/ክ አድረው ያስተምራሉ ፤ መጽሐፍትን ያጽፋሉ
፤ ሕይወትን ይሰጣሉ ።
ይህም መጽሕፍ ትኩረት የሚያደርገው በተአምረ ማርያምና
በነገረ ክርስቶስትምህርት ላይ በሚነሡ ጥያቄዎች መልስ ላይ
ነው። የተአምረ ማርያምንሥራቸው አድርገው ምእመናንን
ስለሚያደናግሩበት ምእመናንን ለመጠበቅ በጉዳዩ ላይ
የጥብቅና ጽሑፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ስለ ነበር ጸሐፊው
እነዚህን ችግሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህን መጽሐፍ አዘጋጅቷል ።
ሐተታበዚህ "ትምህርተ ጽድቅ" በተሰኘው መጽሐፍ አዘጋጁን
ሊያስመሰግነው የሚችሉ ብዙ አዳዲስ ነገሮች ይዞ የመጣ
ቢሆንም በተለይ ግን ከምንጭ አንጻርም ሊሆን ይችላል
በብዙ የነገረ ማርያም መጻሕፍት ያልተዳሰሱ አንዳንድ የነገረ
ማርያም ትምህርቶችን ሰፊ ዳሰሳ (broad overview) በማድረግና ሀገርኛና የባሕር ማዶ ተጨባጭ ምንጮችን (concrete sources ) በመጠቀም " ይበል " የሚያስብል ማብራርያ ሰጥቷል ።
ባጠቃላይም መጽሐፉ ሁለት ክፍል ፣ አራት ምዕራፎች
ሲኖሩት በክፍል አንድ ተአምረ ማርያምን መነሻ በማድረግ
የተአምር ምንነት ፣ ጥቅምና መገለጫዎችን ከብዙ ነቅዐ
መጻሕፍት ትንታኔ ጋር ማብራርያ ይሰጣል ። በተለይም ነገረ
ማርያምን(mariology) በተመለከተ የዘመኑ አሳቾች
ለራሳቸው እንዲመቻቸው በማድረግ ተአምረ ማርያምን
በማጣመምና የዋሀንን በማሳት ያሉትን የሚረታና በእምነት ያሉትንም የሚያጸና ገለጻ የቀረበበት ክፍል ነው። አንዳንዶች በመንፈሰ ንስጥሮስ ሆነው የአውሬው አፍ ተሰጥቷቸው ስለምን ለድንግል ማርያም ይህን ያህል ክብር ሰጣችኋት? ከክርስቶስ አስበለጣችኋት ! እያሉ የስድብን ነገር ለሚያነሱት አፋቸውን የሚያዘጋና ማክሲሚልያን የተባለው ሊቅ እንደተናገረው" ቅድስት ድንግል ማርያምን መውደድ ከሚገባኝ መጠን በላይ አልፌ ወድጄያት ይሆን? ብለህ ሥጋት አይግባህ። ኢየሱስ ክርስቶስ ከወደዳት በላይ
ልትወዳት አትችልምና" እንዳለው ገና ከዚህ በላይ እንወዳት
ዘንድ ፍቅሯን የሚያሳድርብን የመጽሐፉ ክፍል ነው ።
በክፍል ሁለትም በነገረ ክርስቶስ(christology) ዙርያ
ለሚነሱ የነገረ ድኅነት (soteriology) ይዘት ያላቸውን
የመናፍቃን ጥያቄዎች የመጽሐፍ ቅዱሱን ነገረ መለኮታዊ
ዐውድ( biblical Theology) ጠብቆ " መንክር "
በሚያስብል በአበው ትምህርት ተቀምሞ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።
11.8K viewsedited 13:46