Get Mystery Box with random crypto!

TechnoStar IT Solutions PLC

የቴሌግራም ቻናል አርማ technostarplc — TechnoStar IT Solutions PLC T
የቴሌግራም ቻናል አርማ technostarplc — TechnoStar IT Solutions PLC
የሰርጥ አድራሻ: @technostarplc
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 404
የሰርጥ መግለጫ

ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ መረጃዎች እና ሶፍትዌር የሚያገኙበት ቻናል፡፡
🕳Desktop and Mobile App Devt.
☞ Computer Networking
☞Training &Support
☞Software gallary
☞Web Development
👉
📧 ለጥያቄ☞ @
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Contact Us
@TechnoStar_bot
➖➖➖➖

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-30 22:15:20 Good News for you

Hello Dears how are you doing ..?
I had an intersting Software product for cafes ,Resturants and Hotel including order and Stock Management system. So if there is any one who have Cafes ,Resturants and Hotels and intersted to automate his/her services please contact me through the following Addresses .

Mobile:-0922276688
Email:-sendtoyona@gmail.com
Telegram:-@TechnostarY


Thanks !
111 viewsedited  19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 19:48:57
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሠላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!
268 views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 22:31:57
298 views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-02 21:47:45 Research SPSS ሶፍትዌሮች ይፈልጋሉ?
ሊንኩን በመጫን ማውረድ ይችላሉ!
SPSS Software

https://t.me/researchRC/68
SPSD cracker

https://t.me/researchRC/69
549 views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-14 06:47:33 በብዙ የቻናላችን ተከታታዮች ጥያቄ መሰረት የተዘጋጀ።

ለአንድሮይድ ስልኮች በተደጋጋሚ ኢንተርኔት ገብተው ሲወጡ በዛ ያለ ገንዘብ እየወሰደባችሁ ለተቸገራችሁ በሙሉ የሚከተለውን ሁለት የተለታዩ መፍትሄዎችን ይዘን ቀርበንላችኋል።
የስልኮቻችንን Setting በማስተካከል
Software በመጠቀም

የሚከተሉትን የስልኮቻችንን Setting በመጠቀም ኢንተርኔት ስንጠቀም በዛ ያለ ገንዘብ እንዳይወስድብን ማደረግ እንችላለን።

Setting -> Connection ( Wireless
and networks) ከሚለው ስር Data usage የሚለው ውስጥ ስንገባ ኢንተርኔት በጣም የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን እንደወሰዱት መጠን ተዘርዝረው ያገኟቸዋል። ሁሉንም አፕ በየተራ ይክፈቷቸው። Foreground (ከፍተው የተጠቀሙት) እና Background (ያለፍቃድዎ እና ሳይታዩ አፑ በራሱ የተጠቀመው) ምን ያህል Mega Bytes እንደሆነ ያስቀምጠዋል።
እሱን ዝቅ አድርገው Limit background process ከሚለው ፊት ያለውን [ √ ] በማድረግ ይምረጡት። ይሄም ካለ እኛ ፈቃድ አፑ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም መከልከል ሲሆን ወደ ሗላ እየተመለስን ሁሉንም Data usage ውስጥ የተዘረዘሩ አፖች እየከፈትን መዝጋት (Limit) ማድረግ አለብን።

ሁሌም አዲስ አፕ በጫን ቁጥር እየገባን መዝጋት ይኖርብናል።

አንድሮይዳቸው ከ 4.0 በታች ለሆኑ (samsung 5830 አይነቶች) Data usage የላቸውም፣ በዚህ ምትክ Setting-> Accounts and Sync ገብተን Background data የሚለውን አለመምረጥ ።
በተጨማሪም Setting -> Privacy የሚለውን በመክፈት Back up my data የሚለውን እንዲሁ አለመምረጥ።
ይህ አንድሮይዳቸው ከ 4.0 በላይ ለሆኑትም ይሰራል።

ለ Huawei ስልኮች Data usage ለመግባት፣ Setting —> wireless & Networks -> more .. — > Data
Usage -> Restrict background data የሚለውን [ √ ] በማድረግ መምረጥ Setting -> personal ከሚለው ስር Location access የሚለው ውስጥ ገብተን እሱን መዝጋት።
ይሄም ስልካችን ያለንበትን ቦታ ለማወቅ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ያደርጋል።

Setting -> Developer option
(About phone ከሚለው ከፍ ብሎ ያገኙታል) የሚለውን ከፍተን ወደ ታች ስንወርድ Background Process limit የሚለውን እንክፈት። ይሄ ሁሌም ስልኩ በራሱ Standard Limit የሚለውን ይመርጠዋል። እዚህ ላይ No background process የሚለውን እንምረጥ። ሁሌም ስልካችንን አጥፍተን ካበራነው በራሱ ወደ Standard limit ስለሚቀየር እየገባን መቀየር ይኖርብናል። Standard Limit ላይ ከሆነ ቢያንስ እስከ 10 አፕሊኬሽኖች ያለ እኛ ፈቃድ ኢንተርኔት ጋ ይገናኛሉ ማለት ነው። ይሄም ከፍተኛ ገንዘብ ይወስዳል።

☞ Developer option የሚለውን Setting ውስጥ ካጡት የሚከተለውን ያድርጉ። Setting ->About phone የሚለው ውስጥ እንግባና Build number የሚለውን 7 ጊዜ በፍጥነት እንካው። ከዚያ ሲመለሱ Setting ውስጥ About Phone ከሚለው ከፍ ብሎ Developer option ያገኙታል።

የስልካችን ሶፍትዌር ራሱን እንዳያድስ (update) መዝጋት።
ለዚህም Setting -> About phone (device) -> Software update ገብተን Auto update የሚለው የተመረጠ ከሆነ [ √ ] እሱን ማንሳት ወይንም አለመምረጥ።
GPS መዝጋት
.ኢንተርኔት ክፍት እንዳደረግን ኢንተርኔት የማይጠይቁ አፖችን (ጌም) አለመጠቀም። ይሄም አፖቹ ከአምራቻቸው ጋ በመገናኘት ፣ ማስታወቂያ እንዲመጣ በማድረግ ... የሚጠቀሙትን ኢንተርኔት ያስቀራል።
Play store በ Wi–fi ካልሆነ በስልካችን ኢንተርኔት አለመግባት።
ከዚህም በተጨማሪ ስልካችሁ #telegram ስትጠቀሙ ብዙ ብር እየወሰደባችሁ ከተቸገራችው አሁኑኑ የቴሌግራሞን setting ያስተካክሉ
•••••••ቴሌግራሞን ይክፈቱ••••••••••

° Setting
°
° data and storage
°
° automatic media downloaded
°
° #click when using Mobile data
°
° #Unmark all & #save it
☞ [_]....photos
☞ [_]....voice messages
☞ [_]....videos
☞ [_]....files
☞ [_]....music
☞ [_]....GIFS
ከላይ የጠቀስናቸውን መፍትሄዎች ካስተካከሉ እመኑን በእርግጠኝነት በትንሽ ብር ለረጅም Time መጠቀም ይችላሉ።
533 views03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-03 13:44:55 DV 2023 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?
በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2023 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ
›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ መስከረም 27,2014 በኢትዮጵያ ወይም በፈረንጆች ኦክቶበር ሀሙስ 07/2021 ጀምሮ ህዳር 09/2021 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።
DV-2023 Program: Online Registration
DV-2023 Program: The online registration period for the DV-2023 Program begins on Wednesday, October 7, 2021 at 12:00 noon, Eastern Daylight Time (EDT) (GMT-4), and concludes on Tuesday, November 09, 2021 at 12:00 noon, Eastern Standard Time (EST) (GMT-5). Individuals who submit more than one entry during the registration period will be disqualified.
DV-2023 Program Instructions

›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦
እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት
ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም-
• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት
በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም
• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
•ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ
ፎርም መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም
የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።
2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።
3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year
( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.
4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.
5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር
6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር
ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ
7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል
* በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።
8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት
9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ
10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል
11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት
12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ
13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ
14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች
በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ
ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።
»በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2023 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2023 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ ፔጃችንም
መልካም እድል ይመኝላቹሀል
ይሄን መረጃ ለወዳጆ ሼር በማድረግ ማስተላለፍ ትችላላችሁ
https://t.me/yonatanComputer
625 viewsedited  10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-02 09:26:02 የትኛውን የስልጠና ሶፍትዌር ቪዲዮ ይፈልጋሉ?
1,AUTOCAD
2,CIVIL 3D
3,MS PROJECT
4,WATER CAD
5,EPANET
6,ARC GIS
7,SAP
8,STAD PRO
9,ETABS
10,PRIMAVERA
11,REVIT
12,MX ROAD
13, SMARTA
14,ARCHICAD
15, TEKLA STRUCTURE
16,PHOTOSHOP
17,SAFE
18,IN ROAD
19,EAGLE POINT
20, MS EXCEL
21,SWAT
22,SPSS
23,CIS BRIDGE
24,CONMIS
25,ELECTRICAL INSTALLATION
26,ILISTRATOR
27,VIDEO EDITING
28,INTERIOR DESIGN
29,C++
30, JAVA
31,QUANTITY SURVEYING
430 viewsedited  06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-23 22:07:49 የኮምፒዉተራችን storage space ሲሞላብን እንዴት ማስለቀቅ እንችላለን
የኮምፒዉተርዎ storage space ሞልቶበት ተቸግረዋል፡፡ እንግዲያዉስ የሚከተሉትን ምክሮች ይከተሉ
1. ለብዙዎች እፎይታን የሰጠ መፍትሔ ሲሆን የኮምፒዉተራችንን ስቶሬጅ የሞሉብንን የተለያዩ ፋይሎች በማጥፋት ብዙ ትርፍ storage space እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ ኮምፒዉተራችን ላይ የማንጠቀምባቸዉ እና የማይጠቅሙን ጊዜያዊ ፋይሎችን (temporary files) በማጥፋት ኮምፒዉተራችን ላይ ብዙ ቦታ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡
Delete unnecessary temporary file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።
2. የማንጠቀምባቸዉን ፕሮግራሞች Uninstall ማድረግ
አብዛኞቹ ኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች የኮምፒዉተራቸዉን ቦታ የሚያጣብባቸዉ የጫኗቸዉ ሶፍትዌሮች እና ጌሞች ናቸዉ፡፡ የማንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮች Uninstall በማድረግ ቦታ መቆጠብ እንችላለን፡፡ ከኮምፒዉተሮ ላይ የማይፈልጉትን ሶፍትዌር ለማጥፋት የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-
1. Start -> Control Panel -> Uninstall a program
2. ብዙ ቦታ የያዘዉን ሶፍትዌር ለማወቅ በ size ቅደም ተከተል ይደርድሯቸዉ፡፡
3. ማጥፋት የፈለጉትን ሶፍትዌር መርጠዉ Uninstall የሚለዉን ይጫኑ፡፡
3. የተደጋገሙ ፋይሎችን ያጥፉ
ዊንዶዉስ በራሱ የተደገሙ ፋይሎችን ለይቶ የሚያጠፋ ሲስተም የለዉም ስለዚህ ይህንን ስራ የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን መጫን ይኖርብናል፡፡ ይህንን የሚያደርጉ የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ Duplicate Sweeper አንዱ ነዉ፡፡ Duplicate Sweeper ኮምፒዉተራችን ላይ ያሉ የተደጋገሙ ፋይሎችን scan አድርጎ ያቀርብልናል፡፡ እኛም ከዘ ዉስጥ የተደገሙ መሆናቸዉን እያረጋገጥን ማጥፋት እንችላለን፡፡
4. ጊዜያዊ ፋይሎች (Temporary Files)
በ Windows Disk Cleanup አማካኝነት ጊዜያዊ ፋይሎችን እንዴት ማጥፋት እንደምንችል አይተናል፡፡ ነገርግን Windows Disk Cleanup ሊያገኛቸዉ የማይችሉ እንደ browser ያሉ የጫንናቸዉ ሶፍትዌሮች የፈጠሩትን ጊዜያዊ ፋይሎች ለማጥፋት የሚያስችለን ሌላ መንገድ Google Chrome ን እንደ ምሳሌ በመዉሰድ እናያለን፡፡
1. Google Chrome ን ይክፈቱ
2. settings menu ይክፈቱ
3. More tools የሚለዉን ይምረጡ
4.Clear Browsing data የሚለዉ ዉስጥ በመግባት ማጥፋት የሚፈልጉትን ጊዜያዊ ፋይል
መርጠዉ ያጥፉ
5. Recycle Bin ዉስጥ ያሉ ፋይሎችን ያጥፉ
ከኮምፒዉተራችን ላይ ያጠፋናቸዉ ፋይሎች permanently delete ካላደረግናቸዉ መልሰን ብንፈልጋቸዉ ማግኘት እንድንችል Recycle Bin ዉስጥ ይቀመጣሉ፡፡ ከላይ ባሉት መንገዶች ያጠፋናቸዉ ፋይሎችም Recycle Bin ዉስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ Recycle Bin ያሉ ፋይሎች ግን ከኮምፒዉተራችን ላይ የያዙትን storage space እንደያዙ ነዉ የሚቆዩት፡፡ ስለዚህ storage space ለማስለቀቅ እነዚህን የማንፈልጋቸዉ ፋይሎች ከRecycle Bin ዉስጥ ማጥፋት ይኖርብናል፡፡
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
ይህ መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ!
አመሰግናለሁ!
➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤➤
463 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ