Get Mystery Box with random crypto!

እንደምን ቆያችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች? በቴሌግራም የሚተላለፉ አንዳንድ ቻነሎች ላይ በቅዱስ ሲ | ምን እንጠይቅሎ?

እንደምን ቆያችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች?

በቴሌግራም የሚተላለፉ አንዳንድ ቻነሎች ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩ ግለሰቦችን ዲያቆን መሪጌታ መጋቤ ሐዲስ በሚል ስም ትምህርታቸውን እየለቀቁ ይገኛሉ። እንዲህ የሚያደርጉ ቻነሎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በየዋሕነት ሊሆን ይችላልና ከዚህ እንድትጠበቁ ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ዲ/ን አሸናፊ መኮንን በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዞ የተለየ እንደነበር ይታወቃል። የርሱን ስብከት ኦርቶዶክሳዊ አድርገው (አስመስለው) የሚያቀርቡ ቻነሎችን ታዝበናል። ከነዚህም መካከል "መልካም እረኛ" ፤ "ፍኖተ ቅዱሳን" የተሰኘና ሌሎች የቴሌግራም ቻነሎች ይገኙበታል። እናም ቤተ ክርስቲያን ከማታውቃቸው አስተማሪዎች እንድትጠበቁ አደራ እንላለን። "አእመረ አሸብር" የተባለ ግለሰብም ራሱን መጋቤ ብሉይ ብሎ የሚጠራ ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የተለየ ትምህርት የሚያስተምርና የተለየ ሆኖ ሳለ ለማደናገር በቤተ ክርስቲያን ስም ሲጠቀም ነበር። ምንም እንኳ ክፉውን ዛፍ ከፍሬው ማወቅ ቢቻልም አንዳንዴ ግን በረቀቀ መንገድ ምንፍቅናቸውን እውትን ከሐሰት ቀላቅለው ያማረ አስመስለው ስለሚያስተምሩ መጠንቀቅ ያሻል!

ከዚህ በፊት ቤተ ክርስቲያን አውግዛ ለይታቸው የነበሩት ሰዎች በፎቶ ከታች ተያይዟል። ለሌሎችም ሼር በማድረግ ከስሕተት አካሄድ ሌሎችን ይጠብቁ!