Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳውያን

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxian — ኦርቶዶክሳውያን
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxian — ኦርቶዶክሳውያን
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxian
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 411
የሰርጥ መግለጫ

የ ሀይማኖት መሠረት አበው አባቶቻችን ያወረሱን የ ማትነቃነቅ አምድ ሀይማኖታችን ኦርቶዶክስ ናት።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-11 00:02:32
#AddisAbaba

የመኖሪያ ቤት ሽልማት ዕጣ የማውጣት ስነስርዓት ወደ ሐምሌ 25 ተሻገረ።

የአማራ ባንክ የመኖርያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስነስርዓት ነገ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚካሄድ ገልጾ ነበር።

ነገር ግን የአማራ ባንክ በጠራው ስብሰባ ምክንያት የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ወደ ሃምሌ 25 ቀን 2014 የተዛወረ መሆኑን የባንክ አስተዳደሩ አሳውቋል።

ከሚደረገው እጣ በተጨማሪም የመኪና የቤት እቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ እጣዎች ተካተውበታል።

የአማራ ባንክ ፥ ለተፈጠረው የፕሮግራም ለውጥ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ታዛቢዎች፣ ባለዕድለኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የሚዲያ አካላት በተለዋጩ ፕሮግራም እንዲገኙ (ማለትም ሐምሌ 25) መልዕክት አስተላልፏል።

ከእናንተ ሚጠበቀው ቻናላችንን መቀላቀል እንዲሁም ደግሞ ለዘመድ አዝማድዎ ለወዳጅዎ ለግሩፖች እድላቸውን እንዲሞክሩ ቢያንስ ለ60 ሰዎች ሼር በማረግ እንዲቀላቀሉ መጋበዝ ብቻ ነው፡፡ ከ 60 ሰው በላይ መጋበዝ እድልዎን ያሰፋል፡፡

መልካም እድል ከአማራ ባንክ።

@Amharabankb
@Amharabankb
@Amharabankb
50 views21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:45:52
72 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:57:56 #የወጣቶች_ሕይወት /ሕይወተ ወራዙት
(በቀሲስ ህብት የሺጥላ)

#ክፍል_3

#ግብረ_አውናን (Masterbation) #ምንድነው ?

እግዚአብሔር ለምህረትና ለመቅሰፍት ያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ ግዳጆችን የሚፈፅሙ መላእክት እንዳሉት ሁሉ ሰይጣንም ሰውን በልዩ ልዩ መንገድ እንዲፈትኑ ድርሻ ሰጥቶ ያዘጋጃቸው አጋንንት አሉት ። ከእነርሱም ውስጥ አንዱ #ሰይጣነ_ዝሙት ነው ። ሰይጣነ ዝሙት የሰው ልጆችን የሚፈትንበት መንገድ የተለያየ ነው ። እንደውም አንዳንዶቹ ፈተናዎቹ የዝሙት አይመስሉም

#ፆር_የለመዱ (የሰይጣንን የፈተና ስልት በደንብ ለይተው ያወቁ ) አበው ቅዱሳን ግን ሽንገላ የሞላበትን የሰይጣንን ፈተና አሸንክላ ምን እንደሚመስል መጪ ትውልድ እንዲያውቀው በሕይወታቸው ያዪትንና መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን ፅፈው አስቀምጠዋል ። ለምሳሌ ሰይጣነ ዝሙት የሰውን ልጅ ወደ ዝሙት ተግባር ከሚስብባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ገሢሥ ነው ። #ገሢሥ ማለት ማሻሸት፣ መነካካት ፣ መዳበስ ማለት ነው ። ነብዩ ሕዝቅኤል "ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር " (ሕዝ 23:3) በማለት እንደተናገረው ለዘር የደረሱ ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲላፋና ሲዳሩ ሩካቤ ሳይፈፅሙ ዘራቸው የሚፈስበት ጊዜ አለ ። ይህን ድርጊት እንደ ተድላ በመቁጠር ብዙ ወጣቶች ሆን ብለው ያደርጉታል

በቅዱስ መፅሐፍ "የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር " እንደተባለው ቦታ ሳይመርጡና ሰው ሳይለዩ የሴት ልጅን ገላ በመዳበስ "ግልሙትናን ማፍሰስ " ያሳፍራል ። ይህ መጥፎ ልማድ የተጠናወታቸው ሰዎች ግርግርና በሰው ብዛት የተጨናነቀ ስፍራ የሴቶችን ገላ እንደ ሐሳባቸው ለመነካካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሰው ስራቸውን አይቶ እንዳይነቅፋቸው የተለያዪ ዘዴዎችን ይፈጥራሉ። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ምንም ሳያውቁና በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ለማስመሰል እንደ ተኛ ሰው እየተገላበጡና እያንኮራፋ በልዩ አጋጣሚ አጠገባቸው የተኛችውን ሴት ገላ ሲዳብሱ ያድራሉ

ይህ ድርጊት ያለ ሩካቤ የወንድ ዘር ከሚፈስባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ነው ። ሌሎች ደግሞ በአድካሚ የጉዞ ወቅት ደጋፊ ፣ በሕመም ጊዜ ደግሞ አስታማሚ ... እየመሰሉ ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት ለመደባበስ የሚሞክሩ ናቸው ። አንዳንዶች ደሞ እነርሱ ፈፅሞ ለመንካት እንዳላሰቡ ነገር ግን የተፈጠረው ሁኔታ እንዲጋፋ ወይም እንዲነካኩ እንዳደረጋቸው ለማስመሰል ይሞክራሉ ። በብዛት እንደዚ የሚያደርጉት ሕዝባዊ ስብሰባዎች በሚደረግባቸው እለታትና መጨናነቅ በሚኖርባቸው ስፍራዎች ነው ። ለምሳሌ እንደ ጥምቀት ፣ መስቀል ፣ ኤግዚብሽኖች ፣ የሞሉ ሚኒባሶች ሀይገሮች ባሶችና ባቡሮች መጥቀስ ይቻላል

ሌሎች ደግሞ ውጫዊ ይዘታቸው ሲታይ በዚህ ዓይነት ዘርን በማፍሰስ የመርካት ተግባር የማይጠረጠሩ አይነት ናቸው ። ለምሳሌ እድሜያቸው በጣም የገፋ ፣ በአስተሳሰብ የበሰሉ ፣ በአለባበስና በምጣኔ ሀብት የተከበሩ የሚመስሉ ወይም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ አቋምና መልካም ስም የያዙ ናቸው ። እንደዚ ያሉት ሰዎች የሌሎችን ህዋሳት ለመነካካት የሚያደርጉት ጥረት "ይህን አስበው አይደለም " እየተባለ ብዙ ጊዜ በበጎ ይተረጎምላቸዋል

ሌላው ዝንባሌያቸው ደግሞ ታዳጊ ህፃናትን ማባለግ ነው ። በቅጡ ጡት ያላጎጠጎጡ ሕፃናትም እንኳን የእነዚህ ሰዎች የጥቃት ሰለባዎች ናቸው ። ህፃናቱ እነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ አያስተውሉም ፣ አያውቁም ፣ ቢያውቁም አይቃወሟቸውም አይከሷቸውም ። ወይም በትንሽ ነገር ሊባበሉና ሊታለሉ ይችላሉ ።ሕፃናቱን ያጫወቱና ያሳሳቁ በመምሰል ሲታገሉና ሲላፋ በፍትወት እየተቃጠሉ ልብሳቸውን በዘር ጭቃ የሚለውሱትን ወንዶች ቁጥር ቤት ይቁጠረው

... ይቀጥላል

@ortodoxian
@ortodoxian
158 views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:26:53 #የወጣቶች_ሕይወት /ሕይወተ ወራዙት

@kokuha_haymanot
@kokuha_haymanot
@kokuha_haymanot
73 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 20:36:30 ++ በሰንበት መፍረስ ++

የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡

ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡

ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡

እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!

ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
@ortodoxian
@ortodoxian
78 views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 21:21:20
102 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 21:20:36 ​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ሰኔ_20_እና_21

ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።

ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!
@ortodoxian
@ortodoxian
100 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 20:17:09 ወላዲተ አምላክ ስለመሆኗ

ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እናምናለን ። ይኸውም ወልደ አብ ኢየሱስ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ በሥጋ ወልዳዋለችና ። ለዚህ ማስረጃ የሚሆኑንን ጥቅሶች እንመልከት ምክንያቱም ድንግል ማርያምን እንደ ማህደር ተጠቀመባት እንጂ ወላዲተ አምላክ አትባልም ብለው የሚያምኑ ስላሉ ፦ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች " ትን ኢሳ 7:14 ይህ ቃል የሚወለደው ሕፃን አማኑኤል ተብሎ ይጠራል የወለደቺውም ድንግል ናት ካልን ከቃሉ ከፍ ብሎ እንዲህ ይለናል፦

"እርሱም አለ እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ ስሙ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን አምላኬ ደግሞ የምታደክሙ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣቹዋል " ኢሳ 7:13 ይህን ቃል ልናጤነው ይገባል የእስራኤል ቤት ብቻ ሳይሆን አለሙ ሁሉ ለመትረፍ በሰው ድካም አልሆነም ። አሁን ግን አምላክ ሊደክም የኛን መከራ ተሸክሞ ሊያድነን መጣ ። እርሱም #ምልክት ሰጠን #ምልክታችንም ድንግል ማርያም ነች አምላኬን የምታደክሙ ያለው ደግሞ ከድንግል የሚወለደው አምላክ መሆኑን ለማመልከት ነው

እናቱንም ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላ ጥቅስ እንይ ፦ "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል "ኢሳ 9:6 ሕፃን ተወልዶልናል እርሱ ደግሞ ኃያል አምላክ ነው ። ስለዚህ የወለደቺው ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ እንላታለን ። ይኸውም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በ#ተዋህዶ ከብሮ ተወልዷልና ። ሌላም ጥቅስ እንጨምር ፦ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል " ሉቃ 1:43 አስተውሉ ስራው የመንፈስ ቅዱስ ነው ኤልሳቤጥ አክስት መሆኗን እንጂ ድንግል ማርያም የጌታ እናት ትሁን አትሁን የምታውቀው ነገር የለም

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልታ ስለነበር የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል ስትል የጠየቀቺው ስለዚ ነው ። መንፈስ ቅዱስን የተሞላ ድንግልን ያውቃታል ፣ ያከብራታል ፣ ያመሰግናታል እርሱ ጌታ ነውና ወላዲተ እግዚዕ እርሷ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላም እንይ ፦ "ቃል ሥጋ ሆነ ፀጋንና ክብርን ተመልቶ በኛ አደረ " ዮሐ 1:14 ያ ቃል ይለናል መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐ 1:1 ላይ "ቃል እግዚአብሔር ነው " ስለዚህ የተወለደው የኛን ሥጋ የተዋሀደውን ክርስቶስ ኢየሱስን በሥጋ የወለደቺው ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ። ሌላ ፦ "ነገር ግን የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ " ገላ 4:4 ሴቲቱ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ነች

በአጭሩ ፦
እርሱ አምላክ ስለሆነ እርሷም የአምላክ እናት ትባላለች
እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር እናት ትባላለች
እርሱ ጌታ ስለሆነ እርሷም የጌታ እናት ትባላለች
እርሱ ብርሃን ስለሆነ እርሷም የብርሃን እናት /እመብርሃን/ ትባላለች። ጌታ አምላክ እናቱን ማደሪያው ስላደረጋት ከፈጣሪ በታች በሰማይና በምድር ከከበሩ ሁሉ የከበረች ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን ናት ስለዚህም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት እያሏት እያመሰገንዋት ይኖራሉ ስሟንም እየጠሩ በደስታ እየዘለሉ ይዘምራሉ ሉቃ 1:39-55 ልጇ አምላክ ነው እርሷ እናቱም ወላዲተ አምላክ ናት

@ortodoxian
@ortodoxian
102 views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 20:11:26 ክፍል 2
ስለ ንቅሳት

2. ንቅሳትን የሚነቀሱ ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? በዓለም ባሉ ሴቶች መካከል ከወገባቸው በታች በዳሌአቸው ላይ፣ ቁርጭምጪሚቶቻቸው ላይ፣ ከእንብርታቸው በታች፣ በአጠቃላይ የወንድን ዕይታ ለዝሙት ፈቃድ በሚማርክ ስፍራ ላይ ሲነቀሱ ይታያል፡፡ በዝሙት ሥራ ላይ የተሠማሩ፣ ግብረ ሰዶማውያን፣ ጠንቋዮች፣ በወንጀል ውስጥ ያሉ የውንብድና ቡድኖች፣ አስገድደው የሚደፍሩ ንቅሳትን መለያቸው ያደርጋሉ፡፡ በእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ከሚመሩ ክርስቲያኖች መካከል የሚነቀስ አይገኝም፣ ቀድሞ በዓለም ሳሉና ወደ ጌታ ኢየሱስ ሳይመጡ ተነቅሰው የነበሩ እንኳን ቢሆኑ ወደ ወንጌል ከመምጣታቸው በፊት በንቅሳቱ የተነሳ ሰይጣን ምን ያህል ተቆጣጥሯቸው እንደነበር ሊመሰክሩልን ይችላሉ፡፡

3. በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቃቸው ክርስቲያኖች አንዳቸውም ንቅሳት አልነበራቸውም፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ሲል ከተቀበለው መከራ፤ በእጆቹ፣ በእግሮቹ፣ በጎኑ ካለው የቁስል ምልክት በስተቀር ንቅሳት የለበትም፡፡ ሐዋርያትም ከእነርሱ በኋላ የመጡት ሐዋርያነ አበውም ንቅሳት አልነበራቸውም፡፡

4. ንቅሳትን የበለጠ ታዋቂና ተፈላጊ ያደረገው የሮክና ሮል ሙዚቃ አቀንቃኞች ስለሚጠቀሙበት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ካለማስተዋል የተነሣ በእነርሱ ዕይታ ‹‹ታላላቅ፣ ታዋቂ›› ያሏቸውን ሰዎች ሁኔታ መከተል፣ መገልበጥ
ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለምን እንደሚያደርጓቸው ሳያውቁ አድናቂ ነኝ በማለት እነርሱን መከተል አደጋ አለው፡፡ እነርሱ ዝናንና ገንዘብን ለማግኘት ከሰይጣን ጋር በገቡት ኪዳን መሠረት ራሳቸውን ለገሃነም ሰጥተው ሌላውን ለዲያቢሎስ የሚያጠምዱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የሰይጣን ቀንድ የሚባለውን የአውራና የትንሿ ጣትን ምልክት፣ አንድ ዓይንን የፒራሚድ ቅርጽ እንዲመስል በተስተካከለ እጅ ውስጥ አድርጎ ማሳየት፣ የተገለበጠ ወይም የተለየ ቅርጽ ያለው “መስቀል” አድርገው የሚታዩት ዓለም “ታላቅ” አድርጋ ያስቀመጠቻቸው ነገር ግን የመልካም ሥነ ምግባርና የሕይወት ምስክርነት የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በመጠጥና አደንዛዥ ዕጽ የተጠመዱ፣ ደስታ የራቃቸውና ፍጻሜአቸው በአብዛኛው አሳዛኝ የሆነ፤ ራሳቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ የማጥፋት ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡

ንቅሳት ማድረግ የሚገባን ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔርን አስቀድሞ ከዚህ ጋር በፈጠረን ነበር፡፡ አንድ ሰው፡- “እግዚአብሔር ሰዎች ሲጋራ እንዲያጨሱ ቢፈቅድ ኖሮ ከራሳችን ላይ፣ በአናታችን በኩል አብሮ የጭስ መውጫን ይፈጥርልን ነበር” ብሏል፡፡ ሰው ፈልጎ ንቅሳትን ሲያደርግ ሰይጣን ሆይ ና እደርብኝ ብሎ በራስ ፈቃድ የመጋበዝ ያህል መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

ይቀጥላል......
@ortodoxian
69 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ