Get Mystery Box with random crypto!

ኪነጥበብ ዘሰንበት ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ sundayschoolstudents — ኪነጥበብ ዘሰንበት ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ sundayschoolstudents — ኪነጥበብ ዘሰንበት ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @sundayschoolstudents
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.13K
የሰርጥ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የሰንበት ት/ቤትና ግቢ ጉባኤያት መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ድራማዎችን፣ እንቆቅልሾችን፣ አጫጭር ጭውውቶችን፣ እንካሰላንቲያዎችንና መንፈሳዊ ማስታወቂያዎችን... የሚቀርቡበት የሰንበት ት/ቤቶች የኪነጥበብ ቻናል ነው።

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 21:15:06 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






74 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:15:44 ኪራኮስ፡- መስቀሉም የተቀበረበት ቦታ በእዉነት ጎለጎታ ነዉ፡፡ እንሆ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተቀረበት ቦታ እንዳይታወቅ አይሁድ በቅናት በተቀበረበት ቦታ ቆሻሻ እንዲጣልበት ስላዘዙ በሙሉ አይሁድ ትዕዛዙን ተቀብሎ ከቤቱም ሆነ ከደጃፉም የጠረገዉን ቆሻሻ መስቀሉ ከተቀበረበት ቦታ ላይ እስካሁን እየጣሉ ይገኛሉ፡፡ ቦታዉም ከቆሻሻዉ ብዛት የተነሳ በጣም ትልቅ ተራራና ገደል ሆኗል። ይህዉም ከ300 ዘመን በላይ ሆኖታል፡፡ መስቀሉም ከተቀበረበት ቦታ ከምድር 250 ሜትር ወደ ሰማይ ርቋል፡፡ ንግስት ሆይ አይሁድ ትልቅ መሬት ቆፍረዉ መስቀለ ክርስቶስን የቀበሩበት ቦታ ገቢታ ይባላል። ይህውም ጎሎጎታ ነው፡፡

ዕሌኒ፡-  (እልል ትላለች) አቤቱ ህያዉ የእግዚአብሔር አብ የባህሪ ልጅ ያለ ዘረዓብእሲ ለአዳም ብለህ ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ የተወለድክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የሀይማኖቴን ፅናት አይተህ እርዳኝ፡፡ በደመ መለኮትህ የተቀደሰዉን መስቀልህን ለመፈለግ ወደዚህ ስፍራ በእንግድነት መጥቻለዉና የተቀበረበትን ቦታ ትገልፅልኝ ዘንድ እለምንሀለሁ፡፡

ዕሌኒ ፡-  አባቶቼ ሆይ ለእኔ እዉነቱን ስለነገራችሁኝ ጥሩ አደረጋችሁ፡፡መድሃኒታችን  እስካሁንም ድረስ አይሁድን በመፍራት የምታዉቁትን ደብቃችሁ ኖራችኋል፡፡ ከእንግዲ ግን አትፍሩ፡፡ ዉሰዷቸዉ የሚጠጡትን ሰጥታችሁ  አሳርፏቸዉ፡፡ ነገ ወደ ቦታዉ እንጓዛለን ፡፡

#ትዕይንት_ሶስት (3)

ተራኪ 1፡- ከዚህ በኃላ  ንግስት ዕሌኒ ካለችበት ቦታ ነቢያት ፣ሐዋሪያት ፣ ፃድቃን ፣ሰማዕታት ባህታዊያን በጎለጎታ ተሰበሰቡ፡፡ ከእነርሱም ዉስጥ ግማሾቹ በአፀደ ነፍስ ከገነት የመጡ ነበሩ፡፡

ተራኪ 2፡- ንግስት ዕሌንም አንዳንድ ሸክም የወይራ እንጨት ያመጡ ዘንድ ህዝቡን አዘዘቻቸዉ፡፡ እነርሱም እንደታዘዙት የወይራ እንጨት አንዳንድ ሸክም አምጥተዉ ከአንድ ቦታ ላይ ከመሩ፡፡ ዕሌንም ደመራ አስደምራ  በመስከረም 16 ቀን  በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ ወታሮቿን አዘዘች፡፡ እነርሱም  እንደታዘዙት በእሳት አቃጠሉት፡፡ ንግስት ዕሌኒም አንድ ግመል የተጫነ ዕጣን በእሳት ላይ ጨመረች፡፡ በዚህ ጊዜ የዕጣኑ ጭስ ወደ ሰባቱ ሰማያት ወጥቶ ከመንበረ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እግር ስር ሰገደ፡፡ ወደ ታች ተመልሶ የዕጣኑ ጪስ እንደ ቀስተ ደመና ሆኖ መስቀሉ ከቀተበረበት ቦታ ላይ በጎለጎታ ተተከለ፡፡

ተራኪ 1፡- ኪራኮስና አሚሎስ እንደ ዕሌኒ በሀይማኖት ፀንተዉ ዕጣን አምጥተዉ በእሳቱ ላይ ጨመሩ፡፡

ተራኪ 2፡- በነፍስና በአካለ ስጋ የመጡ ነቢያትና ሐዋሪያት፣ ፃድቃንና ሰማዕታት  ባህታዊያንም እጣኑን በእሳቱ ላይ ጨመሩ፡፡ ‹‹ዘዕጣን አንፀረ ሰገደ ጢስ በጎለጎታ ዘደፈኑ አይሁድ ዮም ተረክበ እፀመስቀል ›› እንዳለ ኢትዮጲያዊዉ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ  ሦስት ጊዜም ጥሱ ወደ ላይ ወጥቶ ሲመለስ  መስቀሉ ወደተቀበረበት ቦታ  አመለከተ፡፡

ዕሌኒ፡- ነገር በሦስት ይፀናልና ይበቃል፡፡ መስቀለ ክርስቶስ ወዴት እንደተቀበረ በልዑል እግዚአብሔር መሪነት ተረድተናል፡፡ በሉ ህዝበ አይሁድ ይጥሉት የነበረዉን ቆሻሻ እንዲያነሱ አድርጉ፡፡ እናንተም  መስቀለ ክርስቶስ እስከሚገኝ ድረስ  ከነገ ጀምራችሁ ቆፍሩ፡፡

ተራኪ 1፡- ሰራዊቱም እንዳዘዘቻቸዉ የዕጣኑ ጢስ ያረፈበትን ቦታ መስከረም 17 ቀን በብዙ ድካም ይቆፍሩ ጀመር፡፡ ህዝቡም እንደታዘዙት የዕጣኑ ጢስያረፈበትን ቦታ ከመስከረም 17 ቀን አንስተው እስከ መጋቢት 10 ቀን ድረስ በጣም ወደታች አርቀው 90 ክንድ አበራ ቆፈሩ፡፡

ተራኪ 2፡- 90 ክንድም ወደ ታች አርቀው በቆፈሩ ጊዜ እንደ ነፀብራቅ ሆኖ የፀሃይ ብርሃን ከጉድጓዱ ውስጥ ወጥቶ ታያቸው፡፡ ብርሃኑም እስከ ሳሌም ድረስ ወጥቶ አበራ፡፡

ዕሌኒ፡- አይዟችሁ አትደንግጡ የመስቀሉ መገኛ ስለደረሰ የብርሃን ነፀብራቅ ታየ፡፡ ተነሱ አሁንም ቆፍሩ፡፡

ተራኪ 1፡- እነሆ መጋቢት 10 ቀን ሶስት መስቀሎችን አገኙ፡፡ ከመሬትም ውስጥ ሶስቱን  መስቀሎች አወጡ፡፡ ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት ፣አዴራ እና ሮዳስ የሚባሉ የኢየሱስ ክርስቶስ  እጁና እግሩን የተቸነከረባቸዉን አምስቱንም ችንካሮች  አነገስንህ በማለት እየተዘባበቱ በራሱ ላይ የደፉትን አክሊከ ሶክ መራራ ሀሞት ያጠጡበትን  ሰፍነግ የተገረፈበትን ጅራፍ ከለሜዳዉንም  ከመሬት ዉስጥ አግኝተዉ አወጡ፡፡

ተራኩ 2፡- ከሦስቱ መስቀሌች  ሁለቱ መስቀል በጌታ ግራና ቀኝ ሁለቱ ወንበዴዎች የተሰቀሉበት ነዉ፡፡ አንደኛዉ መስቀል ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ አለም የተሰቀለበት መስቀል ነው፡፡ በክርስቶስ መስቀልም ህመምተኞች ፈጥነው ዳኑ፣ አንካሶች ረቱ፣ እውሮች በሩ፣ ሙታን ተነሱ ድንቅም ተደረገ፡፡

ዕሌኒ፡- መስቀል ሐይላችን ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው፣ መስቀል መፅናኛችን ነው፣መስቀል ሕይወታችን ነዉ፣ መስቀል የነፍሳችን መድሃኒት ነዉ፣ መስቀል የጠላቶቻችን ድል መንሻ ነዉ፡፡

ተራኪ 1 እና 2፡- መስቀል ሐይላችን ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው፣ መስቀል መፅናኛችን ነው፣ መስቀል ሕይወታችን ነዉ፣ መስቀል የነፍሳችን መድሃኒት ነዉ፣ መስቀል የጠላቶቻችን ድል መንሻ ነዉ፡፡
                  
መዝ ፦ እሰይ የምስራች ተገኘ መስቀሉ
          ክርስቲያኖች ሁሉ እልል እልል በሉ
         (መስቀል አበራ መዝሙር ይዘመራል)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር      
ወለወላዲቱ ድንግል         
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !!!

ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም ያድርሰን !!

ሀሳብ አሰተያየት ፦ @harabirhanu21

የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ !
@sundayschoolstudents
የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
207 viewsብርሃኑ መለሠ, edited  16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:15:21 #ትዕይንት_ሁለት (2)

ተራኪ 1፡- ይህ ከሆነ ከ300 ዓመት በላይ አለፈ፡፡ ተርቢኖስ የተባለው ባሏ በሐሰት በሌላ ወንድ የጠረጠራት አንዲት ዕሌኒ ምትባል ቅድስት ሴት በቁመቷ ልክ በተሰራላት ሳጥን ውስጥ ሆና በባህር ተጥላ ስትሔድ መንፈስ ቅዱስ መጋቢ መልዐኩ ቀዛፊ ሆነው ሳጥኗ ብራንጥያ በተባለችው ወደብ ደረሰች።

ተራኪ 2፡- ያን ጊዜ ቁንስጣ የሚባል ንጉስ በባህሩ ዳር ነበር፡፡ ንጉስ ቁንስጣም ሳጥኑን ባየው ጊዜ ማዕበል ሞገድ ከነጋዲያን ነጥቆ ያመጣው ነው ብሎ አስመጥቶ ከፍቶ ቢያየው እንደ ፀሐይ  የምታበራ ሴት ወይዘሮ አገኘ፡፡ በሮሐም ትቀመጥ ዘንድ አደረገ፡፡

ተራኪ 1፡- ንጉስ ቁንስጣም በሮሐ ያሉትን ሕዝብ በሙሉ እንዲገዙላት አዘዛቸው፡፡ የሚያገለግሏት አሽከርና ገረድ አድርጎ በመልካም አጠባበቅ እንዲጠብቋት አዘዘ፡፡  ንጉስ ቁንስጣ ዕሌኒን ከእቁባቶቹ አንዷ አድርጎ አስቀመጣት፡፡ በደም ግባቷም ይህ ቀረሽ ማትባል በመሆኗም ወደዳት፡፡

ተራኪ 2፡- ንጉስ ቁንስጣም ከአሕዛብ ወገን ነበርና ንግስት ህሌኒ አውራ ጣቷን በምላጭ ሰንጥቃ ደሟን ቀድታ ውሃ ውስጥ ጨምራ ንጉሱን የእርሷ ደም በተቀላቀለበት ውሃ እንዲጠመቅ አደረገችው ይህም እንደ ጥምቀት ተቆጠረለት፡፡

ተራኪ 1፡-  ከዘጠኝ ወርም በኋላ ስም አጠራሩ ከሁሉም በላይ የሆነ ንጉስ ቆስጠንጢኖስን ወለደች ፡፡ ‹‹ እነሆ በደመ መለኮቴ ተቀድሶ የከበረው የተሰቀልኩበትመስቀል ክፉዎች አይሁድ ከቀበሩበት ጉድጓድ ውስጥ እሌኒ ባለችበት ዘመን ይገኛል፡፡ ››  በማለት የተስፋ ቃልን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልፆ ስለ ዕሌኒ ተናገረ፡፡

ተራኪ 2፡- ንጉስ ቁንስጣም በዘጠና ዘጠኝ አመቱ አረፈ፡፡ ንግስት ዕሌኒንም በእርሱ ፈንታ ተተክታ በንግስና ህዝቡን መምራት ጀመረች፡፡ ልጇን ቆስጠንጢኖስን የጌታችን የስጋዊውን  ሕማሙን፣ሞቱን፣ እርገቱን እየነገረችው በመልካም ክርስትና ኮትኩታ አሳደገችው፡፡ ሐሳቧ ክርስቶስን መስቀል ፈልጎ ማግኘት ነበርና ሮም መኳንንትን ክርስቶስን መስቀል ያለበትን ቦታ እንዲነግሯት ሰብስባ ጠይቃ በእየሩሳሌም እንደሚገኝ ስለነገሯት በእርሷ ፈንታ ልጇን በንግስናው ተክታ ወደ እየሩሳሌም ወታደሮቿን አስከትላ ገሰገሰች፡፡

(አዋጅ )

አዋጅ ነጋሪ፡-  አዋጅ አዋጅ አዋጅ የሰማህ ስማ ላልሰማ አሰማ ንግስት ዕሌኒ መንገድ ተጉዘው ባህር ተሸግረው ሰራዊታቸውን አስከትለው ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል የተደበቀበትን ቦታ ለማግኘት ገስገሰው ወደ እየሩሳሌም መጥተዋልና የመስቀሉን ዜና የምታወቁ ከህፃን እስከ አረጋዊ ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያላችሁ አይሁድ ሁሉ ንግስቲቱ ባሉበት እየተገኛችሁ እንድታሳውቁ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ለመላው አይሁድ ሁሉ ውርድ ከራሴ በሉ ማንኛውም ዜጋ ሁሉ ከራስ ፀጉሩ ዝቅ ብሎ ከእግር ጥፍሩ ከፍ ብሎ ይቆረጣል፡፡   አዋጅ አዋጅ አዋጅ ።

ተራኪ 1 ፡- አዋጁን ሰምተው ሃይማኖታቸው የቀና ከክርስቲያን ወገን የሆኑት ወደ ዕሌኒ መጥተው እንዲህ አሏት፡፡

ተናጋሪ 1፡- እመቤታችን ሆይ እነሆ እኛ ክርስቶስን ከሰቀሉት ወገን አይደለንም፡፡ ነገር ግን ከጉባኤው መካከል የመስቀሉን ነገር የሚያውቁ ሰዎች ከመካከላችን አሉ፡፡

ተናጋሪ 2፡- እኛ ልጆች ስለሆንን መስቀሉ የተሰቀለበትን ቦታ አናውቅም፡፡ ነገር ግን ስለ ክርስቶስ ተሰቅሎ መሞትና ስለ መስቀሉ መቀበር ሁሉ ሁኔታውን የሚያውቁ ኪራኮስ እና አሚኖስ የሚባሉ ሁለት ሽማግሌዎች ከእ ዘንድ አሉ፤ እነሱም በዚያን ዘመን ስለነበሩ ይነግሩሽ ዘንድ አቅርበሽ ጠይቂቸው፡፡

ዕሌኒ፡- በሉ ፈጥናችሁ ካሉበት ቦታ እነዚህን ሽማግሌዎች ወደ እኔ አምጡልኝ፡፡ (ኪራኮስና አሚኖስም ወደ እርሷ ቀረቡ)

ዕሌኒ፡- አባቶቼ ሆይ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም ልጆች ብሎ በለበሰው ስጋ የተሰቀለበት መስቀል የት ቦታ እንደተቀበረ አሳዩኝ፡፡   ብትነግሩኝ ይሻላል፡፡ ትዕግስቴን እንደሆነ ህዝቡ አሳጥቶኛል ታዝንልኛለች ብላችሁ ተስፋ እንዳታደርጉ፡፡

አሚኖስ፡- እመቤታችን ሆይ ይህን ነገር ፈፅሞ አናውቅም፡፡ ክርስቶስ መሰቀሉንና መስቀሉም ከመሬት ውስጥ መቀበሩን አልሰማንም፡፡

ዕሌኒ፡-  እርስዎስ አባቴ እባክዎትን ይንገሩኝ ክፉ እንዳደርገባችሁ አታስገድዱኝ፡፡

ኪራኮስ ፡- እመቤቴ ሆይ የኛ አባቶቻችን ክርስቶስን አልሰቀሉም፤ መስቀሉንም ከመሬት ውስጥ አልቀበሩም፡፡ እኛም ስለ መስቀሉ ምንም ምናውቀው ነገር ለም አባቶቻችን እንኳን ክርስቶስን አንድንም ሰው በመስቀል  ላይ አልገደሉም፤ መስቀሉንም ከመሬት ውስት አልቀበሩም፡፡

ዕሌኒ፡- እነዚህን ሰዎች እጃቸውን በሰንሰለት እግራቸውን በብረት አስራችሁ እህል ውሃ ነስታችሁ ከባዶ ቤት ውጥ አስቀምጧቸው ውሰዱልኝ፡፡ (ይወስዷቸዋል)

ዕሌኒ ፡- (ፀሎት) አቤቱ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የእኔ ባሪህን ልመና ትሰማ ዘንድ ትጋትን በያዘ ልቦና እማልድሀለሁ፡፡ ቸልም አትበለኝ ፤ ከአይሁድ መጠራጠርና መተሳሰብ፤ ከክፉ ስራቸው ሁሉ ነፍሴን አድናት፤፡ ስለ እናትህ ስለ ድንግል ማርያም ስከ ባለሟሎችህ ስለ አብርሀምና ስለ ይስሃቅ ብለህ በደመ መለኮትህ የከበረውን መስቀልህን እኩን አቤቱ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የእኔ ባሪህን ልመና ትሰማ ዘንድ ትጋትን በያዘ ልቦና እማልድሀለሁ፡፡  ቸልም አትበለኝ ፤ ከአይሁድ መጠራጠርና መተሳሰብ፤ ከክፉ ስራቸው ሁሉ ነፍሴን አድናት ስለ እናትህ ስለ ድንግል ማርያም ስከ ባለሟሎችህ ስለ አብርሀምና ስለ ይስሃቅ ብለህ  በደመ መለኮትህ የከበረውን መስቀልህን እኩን አይሁድ ቀበሩበትን፣ አቤቱ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የእኔ ባሪህን ልመና ትሰማ ዘንድ ትጋትን በያዘ ልቦና እማልድሀለሁ፡፡  ቸልም አትበለኝ ፤ ከአይሁድ መጠራጠርና መተሳሰብ፤ ከክፉ ስራቸው ሁሉ ነፍሴን  አድናት፤፡ ስለ እናትህ ስለ ድንግል ማርያም ስከ ባለሟሎችህ ስለ አብርሀምና ስለ ይስሃቅ ብለህ በደመ መለኮትህ የከበረውን መስቀልህን እኩን አይሁድ ቀበሩበትን ቦታ ትገልጥልኝ ዘንድ እለምንሀለሁ፡፡

ተራኪ 1፡- (መልዓኩ ሚካኤልም ተገልፃላት እንዲህ ሲል ነገራት) ‹‹ አሚኖስና ኪራኮስ ያሰርሻቸው ሁለቱን ሰዎች በጣም አጥብቀሽ ጠይቂያቸው ፤ ይልቁንም ኪራኮስ የሚባለውን ወደ አንቺ አቅርበሽ መርምሪው እሱም ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ ታሪኩን ይነግርሻል ፤ መስቀሉንም የት ቦታ እንደ ቀበሩት ያሳይሻል፡፡

ዕሌኒ፡- ሽማግሌው አባቴ ሆይ እኔ ክርስቶስን መስቀል የተራብኩ ትጉህ ነኝ እናም ከዚህ የበለጠ መከራ ሳላመጣብህ አባቶችህ መስቀለ ክርስቶስን የት ቦታ እንደቀበሩት ንገረኝ፡፡

ኪራኮስ፡-  በረሃብና በጥም አስጨነክሽን ፤ ለመናገር አቅቶናል መጀመሪያ ትንሥ እህልና ውሃ አቅምሽን ታሳርፊን ዘንድ እንለምንሻለን፤ ነፍሳችን ከስጋችን ለመለየት ትንሽ ቀርቷታል እኛም እንነግርሻለን፡፡

ዕሌኒ ፡- በሉ የሚበሉትን ስጧቸው፤ ከመከራቸውም ያርፉ ዘንድ እጃቸውንና እግራቸውን ፍቱላቸው፡፡ (ከበሉ በኃላ)

ዕሌኒ ፡- (በልተዉ ከጨረሱ በኋላ ወደ እርሷ ታስመጣቸዋለች) የጠየቃችሁኝን ምግብ ሰጥቻችኅለሁ እንግዲያዉስ ንገሩኝ።

አሚኖስ፡ ንግስት ሆይ እንሆ በልጅነታችን ህፃን ሳለን ከአያቶቻችን ከአባቶቻችን እንዲ ሲባል ሰምተናል ጌታ ፤  ኢየሱስን ከቀራኒዮ መካን በመስቀል ላይ ሰቅለዉ አይሁዶች ገድለዉታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀልንም ሙታንን በማንሳትና ህሙማንን በመፈወሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ቦታ በጎለጎታ ቀብረዉታል፡፡
161 viewsብርሃኑ መለሠ, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:12:36 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






183 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 06:35:18     #ትዕይንት_አንድ (1)

 (ህዝበ አይሁድ ስብሰባ ያደረጉ)

አይሁድ፡- እነሆ እኛ በበደሉና በጥፋቱ ኢየሱስ ሚባለውን ሰው በላዩ ላይ ሰቅለን በገደልነው በክርስቶስ መስቀል ስምና ሃይል ብዙ ተአምራት ሲደርግ እናያለን፡፡ ኢየሱስ የተባለውን ሰው በሃይላችንና በጉልበታችን በመስቀል ሰቅለን እንደገደልነው አሁንም እሱ በተሰቀለበት መስቀል ሃይል ተአምራት ሲደረግ ማየት የለብንም  (አይገባንም)፡፡

ፈሪሳዊ፡-  ጆሮአችን መስማት የለበትም፡፡ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን እንነሳና የመስቀለ ክርስቶስን ስም አጠራር ከገፀ ምድር እናጥፋ፡፡ የመስቀሉ ገቢረ ተአምራት እንዳይታወቅ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረን ከመሬት ውስጥ እንቅበረው፡፡ ፍለጋውም እንዳይገኝ፤ የስም አጠራሩ ዝና እንዳይታወቅ እናድርግ፡፡

ጸሐፍት፡- ስለዚህ በእዚህ ጉዳይ ላይ ማንኛውንም አይሁድ ህዝብ ጠርተን ማነጋገር አለብን፡፡

አይሁድ፡-  ስለዚህ ጥሪው ለህዝቡ ጆሮ ይድረስ እኛም በቀጠሯችን ቀድመን እንገናኝ።

      ( አዋጅ )

አዋጅ ነጋሪ ፡-  አዋጅ አዋጅ አዋጅ ለምድረ ይሁዳ ነዋሪዎች በሙሉ ካህናቱ በጥብቅ ጉዳይ ህዝቡን ሁሉ ሊያወያዩ ስለሚፈልጉ ሁሉም ህዝብ ካለበት ወጥቶ በጉዳይ ላይ እንዲወያይ ታዟል፡፡ ይህን የማያደርግ የአይሁድ ነዋሪ ቢኖር ግን ውርድ ከራሴ ይበል፡፡ (ህዝቡ እና አይሁድ ስብሰባ እያደረጉ)

#ተራኪ 1፡- ህዝበ አይሁድም አዋጁን በሰሙ ጊዜ እውሩ እተመራ ደካማው እተደገፈ በሽተኛው በአልጋ ተሸክመው ትልቁም ትንሹም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያለው ሁሉ ከአንድ ቦታ ተሰበሰቡ፡፡

#ተራኪ 2፡- ከዚህ በኋላ ለስጋቸውም ጥፋት ለነፍሳቸውም ሞትና መከራ የሚሆናቸውን ምክር በአንድነት መከሩ፡፡ መስቀለ ክርስቶስን ከመሬት ቀብረን የስም አጠራሩ ዝና እንዳይታወቅ እናድርግ አሉ፡፡ ህዝቡም ሙሉ በሙሉ እውነት በእውነት የመስቀሉ ስም  እንዳይታወቅ ከመሬት ውስጥ እንቀብራለን እያሉ ተናገሩ፡፡

#ተራኪ 1፡- ይህን ከተባባሉ በኋላ ወደ ታች ርቀቱ ዘጠና(90) ክንድ ጉድጓድ ቆፈሩ፤ ጠማማ ድንጋዮችንም በውስጡ አነጠፉ፤ በደመ መለኮት የከበረውን መስቀለ ክርስቶስን በተነጠፈው ድንጋይ ላይ አኖሩት፡፡ እጅና እግሩ የተቸነከረበትን አምስቱን ችንካሮች፣ የተገረፈበትንም ጅራፍ ፣መራራ ሀሞት የጠጣበትን ሰፍነግ ፣በራሱ ላይ የደፉትን አክሊል ሶክ ፣ ጎኑን የተወጋበት ጦር ፣ራሱን የመቱበትን ዘንግ ፣ ሁሉ ከመስቀሉ ጋር ከመሬት ላይ አስቀመጡት፡፡

#ተራኪ 2፡- ሁለቱ ወንበዴዎች የተሰቀሉበትን መስቀሎች ከበላይ አስቀመጡት ፡፡ ከላይ ደግሞ ጠማማ ድንጋዮችን አስቀመጡ፡፡ ከዚህ በኋላ የቦታው ፍለጋ እንዳይታወቅ ጉድጓዱን በአፈር አስተካክለው ደፈኑት፡፡ በደመ መለኮት የከበረ መስቀል በተቀበረ ጊዜ በእለተ አርብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ የተደረገ ተአምራት ተደረገ፡፡ ክፉዎች አይሁድ መስቀሉን ከመሬት ውስጥ በቀበሩት ጊዜ በአለሙ ሁሉ ንውፅውፅጻና ነጎድጓድ ሆነ፡፡ (የነጎድጓድ ድምፅ ይሰማል)

( ትዕይንቱ ይቀጥላል ... )
374 viewsብርሃኑ መለሠ, 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 06:02:04 ++ ኪነጥበብ - የመስቀል ድራማ !

      (ርዕስ - ዕሌኒ ንግስት)

#ተራኪ 1፡-  ሐዋርያት ወንጌልን እየሰበኩ የመስቀሉን ሀይል ለሰው ሁሉ አስተምሩ ነበር፤፡ ህዝቡም ትምህርታቸውን ከተቀበሉ በኋላ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ያጠምቋቸው ነበር፡፡ መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የሚደርስባቸውን መከራ ሁሉ እንዲታገሱ በመዓልትም በለሊትም ከእነሱ አይለያቸውም ፡፡ ያስተማሩትንም ትምህርት ከእናታቸው  ማህፀን ለተመረጡ ሰዎች ሁሉ በልቦናቸው ያሳድርላቸው ነበር፡፡ በአምልኮተ ጣኦትና በገቢረ ሐጢያት ጨለማ የነበረው አለም አባቶቻችን ሀዋርያት በመስቀሉ ሃይልና ረድኤተ ወንጌልን እየሰበኩ ህዝቡን እያሳመኑ በክርስቶስ እምነት ዓለምን ብርት ፅድት አደረጓት ፡፡

#ተራኪ 2፡- የሐዋርያትም ትምህርት ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ ሁሉ ተሰማ ፡፡  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የተሰቀለበት መስቀል ብዙ ተዓምራት ያደርግ ነበር፡፡ በመስቀሉ ሃይል ሙታን ተነሱ፡፡ አጋንንቶችም ከሰዎች ላይ ወጥተው ሄዱ፡፡ ለምጣሞች ነፁ፤ አንካሶችም ረቱ፤ ዲዳዎችም ተናገሩ፤ እውራን አይናቸው በራላቸው፤ ጎባጣዎች ቀና ብለው ሄዱ፡፡  በደመ መለኮት በከበረው ክርሰቶስ በተሰቀለበት መስቀል ስም ብዙ ተአምራት ተደረገ፡፡ በመለኮት ደም የከበረ መስቀለ ክርስቶስ ያደረገውን ተአምራት በአዩና በተመለከቱ ጊዜ በእኩያን አይሁድ ልቡና ምቀኝነት አደረባቸው፡፡ በጣምም ተናደዱ ሀፍረትም ተጎናፀፉ ፤ ምቀኝነት የተሞሉና ተጠራጣሪዎች አይሁድም በአንድነት ተሰብስበው እንዲህ በማለት ምክር አደረጉ እርስ በእርሳቸው እንዲህ አሉ፡፡

(ትዕይንቱ ይቀጥላል .....)



የተወደዳችሁ የኪነጥበብ ተከታታዮች ይኸ በሦስት ትዕይንቶች የተሰናዳ ድንቅ የመስቀል በዓል ድራማ ነው ። ሸር እያደረጋችሁ !

ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም ያድርሰን !!

ሀሳብ አሰተያየት ፦ @harabirhanu21

የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ !
@sundayschoolstudents
የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
374 viewsብርሃኑ መለሠ, 03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:31:21 ንግስት እሌኒ ፦ ማነህ ….(ከሌሎዎቹ አንዱ ትጠራለች)
አሽከር ፪ ፦ አቤት ንግስት ሆይ ሺህ አመት ንገሺ ፤ እነሆ ምንን ትሻለሽ ምንስ ልታዘዝ ?
ንግስት እሌኒ ፦ ሂድና ደመራ ይደመር ዘንድ አዘጋጅ እነሆም ቆፋሪ የሚሆኑ ሌሎዎችንም አዘጋጅ። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ዛሬ መስከረም ፲፯ ቀን ቁፋሮውን እንጀምራለን ።
አሽከር ፪  ፦ እሺ ንግስት ሆይ ታዛዥ ነኝ !
(መዝሙር :- ይረድአነ አምላክነ…..)

      #ትዕይንት_ሁለት

(ደመራው ይደመራል ጢሱ ይጤሳል ሲሰግድ ይታያል)

ኪራኮስ  ፦ እንግዲህ ጢሱ ከዚህ መሬት ላይ ነው ያረፈው (መስቀሉ ወደ አለበት ቦታ እየተመለከተ)። ስለዚህ ቁፋሮው ይጀመር (ይጀመራል)
አሽከር ፫  ፦ (ከሌሎች ወታደሮች ጋር ይገባል) ንግስት ሆይ ሺህ ዓመት ንገሺ፤ እነሆ ከቁስጥንጥኒያ ንጉስ ልከውኝ መጣሁ
ንግስት እሌኒ ፦ እንደው ሀገሩ ሰላም ነውን? ልጄስ እንዴት ነው?
አሽከር ፫  ፦ ሁሉም ሰላም ነው ! ንጉስም በርቱ አይዟችሁ እኔም ከጎናችሁ ነኝ ተጨማሪ ወርቅና ብር ልኬያለሁ ብለዎታል። (ያመጣውን እቃ እያስረከበ)
ንግስት እሌኒ ፦ በል እንግዲህ ሰላም እንደሆንን ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ስራችንን እያከናወንን እንደሆነ ንገራቸው። ሰላምታም አድርስልን በሉ ሰላም ግቡ።
(እጅ ነስቶ ይወጣል። የአውደምህረቱ መብራት ቢጠፋ ደስ ይላል)

#ትረካ ፦ ንግስት እሌኒ ቁፋሮውን አፋጥና ለቁፋሬዎቹ ገንዘብ እያሳደገች ቁፋሮውን አፋጥና ሴኮንዳትን ደቂቃዎችን ሰዓታቶችን ቀናትን ወራትን አሳልፎ ልክ መጋቢት ፲ ቀን አንድ ፍንጭ አገኘች (መብራቱ ይበራል)

ንግስት እሌኒ  ፦ (በደስታ) እንዴት ደስ ይላል። ዛሬ ከብዙ ድካም በኋላ …..
ኪራኮስ  ፦ (እሱም ደስ እያለው) እጅግ ደስ ይላል እንጂ።
ንግስት እሌኒ ፦ ግን እውነተኛ የክርስቶስ መስቀል መሆኑን ለምን ማረጋገጥ ይቻላል ? (አሰብ አድርጋ) እህ…. ያኔ የክርስቶስ መስቀል ሙታንን ያስነሳ እውራንን ያበራ ነበር ዛ…ዛሬስ …
ኪራኮስ ፦ ልክ ብለሻል። እንግዲያማ ሙታንን ፅሙማንን ልበ ብርሃናትን እናምጣ (አሽከሮችን ታዛለች ያመጧቸው መስቀል ይደረግባቸዋል መልሱ ምንም ይሆናል)

ንግስት እሌኒ  ፦ ለነገሩ በቀኙ ወይም በግራው ካሉት ያንዱ ይሆናል፤ ይልቅ ቁፈራችንን እንቀጥል። እግዚአብሔር አምላክ ይረዳናል።
ኪራኮስ ፦ አዎ እውነትሽን ነው እንደዛ ነው የሚሆነው (ይህንን እያወሩ ቆፋሪዎች እየቆፈሩ ነበር ከዛ ሌላ መስቀል ይገኛል)
ንግስት እሌኒ ፦ (አሁንም ደስታ እየተሰማ) ምስጋናውን ከአፌ ሳጨጨርስ እነሆ መስቀል … ዕውራን ላይ ታደርጋለች አይሳካም)
ኪራኮስ ፦ አሁን እንግዲህ አባቶቻችን ነገር በሶስት ይፀናል እንዲሉ እስቲ ለሦስተኛ ጊዜ እንጀምር ተባባሉ።
ንግስት እሌኒ ፦ እውነት ብለዋል። (ይቆፍራሉ ፤ጥቂት ቆየት ይልና ) እንግዲህ ለእግዚአብሔር ምን ይከፈለዋል። ኃጢያተኛ ሳለን ለሚያከብረን።

ኪራኮስ  ፦ እንደው ግን መስቀሉን ለመፈለግ ምን አነሳሳሽ ?
ንግስት እሌኒ ፦ አይ አባቴ ብፅዓት ገብቼ ነበር።  ልጄ እንደአላውያን ነገስታት ካልሆነ የተዘጉ ቤቶቹን አስከፍታለሁ የፈረሱ ቤቶችህንም አስተካክላለሁ እንዲሁም መስቀልህን እፈልጋለሁ ብዬ ስለነበር ነው። ልጄም ብፅዓት እንደገባሁት ሆኖ ሳገኘው ይኸው ስራዬን ጀመርኩ።
ኪራኮስ  ፦  ግሩም ነው ….(እያሉ ብርሃን ከወደ ቆፋሮዎቹ ይወጣል ፤ ይደነግጣሉ ፤ መስቀሉን አሁን ፅሙማንን ላይ ልበ ብርሃናት ላይ ሙታን ላይ ታደርጋለች ይነሳሉ)
ንግስት እሌኒ ፦ ተመስገን አምላኬ !(ሁሉም ፈጣሪን ያመሰግናሉ የዳኑትም )
(መዝሙር :- ርዕዩ ዕበዩ ለቅዱስ ዕፀ መስቀል)

#ትረካ ፦ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በርካታ ተዓምራትን እየፈፀሙ አይሁድ እንዲያፍሩ የክርስቲያንም ልጆች እንዲደሰቱ አደረገ …. ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህንን በማሰብ ስርዓቱ ሳይበረዝና ሳይከለስ ቅድመ ታሪኩን መሰረት በማድረግ በየዓመቱ መስከረም ፲፮ ቀን ደመራ ደምራ መስከረም ፲፯ ቀን ቁፋሮ የተጀመረበትን ዕለት እንዲሁም መጋቢት ፲ የመስቀሉ መገኘትን በማሰብ በደማቅ አከባበር ታከብረዋለች። የምህረት ባለቤት ከምንመካበት ፤ሰይጣን ጠላታችን ድል ከተነሳበት አዳም ከነ ልጆቹ ነፃ ከወጣበት ከመስቀሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን ።
                                                  
(መዝሙር :- ደስ ይበለን እልል በሉ...)

ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም ያድርሰን !!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር      
ወለወላዲቱ ድንግል         
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !!!

የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ !
@sundayschoolstudents
የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
928 viewsብርሃኑ መለሠ, 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:31:21 ++ ኪነጥበብ - የመስቀል በዓል ድራማ !

     ( ርዕስ - መስቀሉን ፍለጋ )

            #ትዕይንት_አንድ

(ትዕይንቱ ሲጀምር ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ከአሽከሮቹ ጋር ይታያል)

ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ፦ (ከመቀመጫው ተነስቶ) ተመስገን አምላኬ ተመስገን ያኔ በቤዛንቲን ነግሼ ሳለ የመክስምያኖስንና የዲዮቅልጢያኖስ አረመኔነትና ጭካኔ ስሰማ እጅግ አዝን ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር እርዳታ እነሱን ድል ገዝቼ እነሆ በቆስጠንጥኒያ ነገስኩ ተመስገን ተመስገን አምላኬ፤ አንተ ማነህ አሽከር.... !

አሽከር ፩ ፦ አቤት ንጉስ ሆይ ሺህ አመት ይንገሱ ! ጠሩኝ ?
ንጉስ ፦ ከእንግዲህ የክርስቲያኖች ደም መፍሰስ ይቅር ፤ የተፋለሰው ስርዓትም ወደነበረበት መልኩን ሳይቀይር ይስተካከል። አብያተ ጣኦታት ተደምስሰው አብያተ ክርስቲያናት ተስፋፍተው የክርስትና እምነት ወደነበረበት ይመለስ። አሁኑኑ አዋጁን ንገር ስራውም ይፋጠን።
አሽከር ፩ ፦ እሺ ንጉስ ሆይ ! አሁኑኑ እንደቃልዎ አደርጋለሁ ስራውም እጀምራለሁ (እጅ ነስቶ ይወጣል)

ንጉስ ፦  አዎ የክርስቲያን መናኞች ደም ልበቀልና ነፃነታቸውን ላውጅ የምችለው አሁን ነው። (ንግስት እሌኒ ትገባለች)
ንግስት እሌኒ ፦ ደህና ዋልክ ልጄ ? (እጅ ትነሳለች)
ንጉስ ፦ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ቸርነቱ የበዛ አምላክ ጠብቆኝ እነሆ እዚህ አድርሶኛል። ቁጭ በያ እናቴ
ንግስት እሌኒ ፦ አይ ልጄ ቁጭ በይ አልከኝ… ምን የሚያስቀምጥ ነገር አለ ብለህ ነው ?
ንጉስ ፦ እናቴ ምነው ምን ገጠመሽ ? (ደንገጥ በማለት) እንዲህ ከልክ በላይ የሚያስጨንቅ ነገር ?
ንግስት እሌኒ ፦ ልጄ ነገሩስ ቀላል ነው ፤ እንደው ፈቃድህን ለማግኘት ብዬ እንጂ።
ንጉስ ፦ እኮ ብትነግሪኝ ነገሩን…

ንግስት እሌኒ ፦ ብፅዐትን ለእግዚአብሔር ገብቼ ነበር ፤ ይኸውም አንተ ኃይማኖትህን ጠብቀህ እንደ አላውያን ነገስታት አረመኔነት ሳያጠቃህ ከስጋ ይልቅ ለመንፈሳዊ ህይወትህ እንድታደላ ካደረገልኝ…. የፈረሱ ቤቶችህን አስተካክላለሁ የተዘጉትንም አስከፍታለሁ መስቀሉንም እፈልጋለሁ የሚል ነበር ።
ንጉስ  ፦ እና እናቴ ያስጨነቀሽ ይህ ነው? ይሔማ እጅግ የተቀደሰ ሀሳብ ነው።  ታዲያ እኔ ምንን እንዳአደርግልሽ ትሻለሽ?
ንግስት እሌኒ ፦ ምንም አታደርግልኝም ብቻ መልካም ፈቃድህንና በቆይታዬ የሚያገለግሉኝ ሎሌዎችህን ትሰጠኝ ዘንድ እሻለሁ።

ንጉስ ፦ እንግዲያማ በሰላም ሂጂ እናቴ፤ ዓለም ሁሉ የዳነበትን መስቀል ፈልጊ እነሆም እኔ በስራሽ ሁሉ ከጎንሽ ነኝ። እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ይሁን። (አሽከር ይጠራል የሆነ ነገር ያመጣል እንደ አገልግል ምናምን /ሰላምታ ተሰጣተንው ትወጣለች)

#ትረካ ፦ ንጉሱም ብዙ ጊዜ ሳይወስድ የሚከተሏትን ሰራዊትና በኢየሩሳሌም ስንቆይ ለተለያየ ነገር የሚሆናትን አያሌ ብርና ወርቅ አሲዟት በሰላም ሸኛት። የሀገሩ መሳፍንትና መኳንንትም ከእርሷ ጋር አብረው ጉዟቸውን አደረጉ።
(መዝሙር ፦እሌኒ ንግስት ሀሠሠት መስቀሉ)

#ትረካ ፦ ንግስት እሌኒ ኢየሩሳሌም እንደደረሰች ፈጣሪዋ የልቧን መሸት ይፈፅምላት ዘንድ ሱባኤ ገባች። ሱባኤውን እንደፈፀመችም መስቀሉን ፍለጋ አንድ ብላ ጀመረች ።
(በመሀል ፦ እሌኒ ንግስት ድጋሚ ይዘመራል)

        #ትዕይንት_ሁለት

(ንግስት እሌኒ ትመጣለች፤ ሁለት ሰዎችን መንገድ ላይ ታገኛለች)
ንግስት እሌኒ ፦ ሠላም እንደምን ዋላችሁ ?
ሁለቱም ሰዎች ፦ ደህና
ንግስት እሌኒ ፦ ይቅርታ እንደው የክርስቶስ መስቀል ያለበትን ቦታ ታሳዩኝ ?
ሰውዬው ፩  ፦ ኸረ እኛ አናውቅም፤ የሰማነው ነገርም የለ (እየተኮፈሰ)
ንግስት እሌኒ  ፦ እሺ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
(እነሱም ዞር እያሉ እያላገጡ ይሄዳሉ ሁለቱ ቀዎች ፤ ንግስት እሌኒ እጅግ ሰው የመፈለግ ስራ ትሰራለች ከውስጥ መዝሙር ይዘመራል።       
መዝሙር :- አቤቱ አንተን እጠራለሁ
               ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለሁ
           ዝም አትበለኝ እጮኻለሁ /፪/

ንግስት እሌኒ ፦ በቃ እንግዲህ ተስፋዬ ተሟጧል አንድ ሰው እንኳን ስለመስቀሉ የሚነግረኝ አጣሁ።  እንግዲህ ምን አደርጋለሁ ወደ ሀገሬ ልመለስ (አሽከሮቹን ደሞ በሉ እናንተ ጓዛችንን ሁሉ ሰብስቡ እና ወደ ሀገራችን እንመለስ /እንግዲህ እያለች ኪራኮስ ይመጣል / እህ ….. ያ ….. እኛ አዛውንት ተመለከታችሁ። ተመስገን አምላኬ ምን አለ እውነቱን ቢነግሩኝ) 

ንግስት እሌኒ ፦ (ጠጋ ብላ) ደህና ዋሉ አባቴ ?
ኪራኮስ ፦ እግዚአብሔር ይመስገን
ንግስት እሌኒ ፦ እንደው የክርስቶስ መስቀል ያለበት ቦታ ቢያሳዩኝ ?
ኪራኮስ ፦ እግዚአብሔር ይመስገን
ንግስት እሌኒ  ፦ እንደው የክርስቶስ መስቀል ያለበትን ቦታ ቢያሳዩኝ ?
ኪራኮስ  ፦ (ትንሽ እንደማሰብ ይልና) በመሰረቱ እርግጠኛ ልሆን አልችልም ነገር ግን ከዛሬ ፪፺፪ ዓመት በፊት ይህ ጌታችን የተሰቀለበት መስቀል ብዙ ህሙማንን ይፈውስ ሙታንን ያስነሳና ሌሎች ታላላቅ ተአምራትን ያደርግ ስለነበረ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሊሆን ቢመጣ የሰውን ልጅ ከዲያቢሎስ አስራት ነፃ ሊያወጣው ሞትን በሞቱ ሊሽር ከሰማየ ሠማያት ቢወርድ ይቃወሙት የነበሩትና በኋላም ወንጅለው አሰቃይተው ለሞት ያበቁት አይሁድ መስቀሉ ያደረጋቸውን ታምራት ማየት ውርደት ስለመሰላቸው ደበቁት።

ንግስት እሌኒ ፦ (ፈጠን በማለት) ወደየት ደበቁት ?
ኪራኮስ ፦ ያ……. ያ……. ያ ይታይሻል ? (ወደ ሩቅ እያሳያት)
ንግስት እሌኒ ፦ (በአዎንታ እራሷን ትነቀንቃለች) አዎ !
ኪራኮስ ፦ ጎላጎል ይባላል ፤ የራስ ቅል ማለት ነው በዚህ ውሉ በማይታወቅ ሰፊ ቦታ እንደተቀበረና ህዝቡም ሁሉ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እንደሆነ አያቴ በታሪክ አጫውተውኛል (ይሉና በለሆሳስ ያወራሉ)           
(መዝሙር ፦ ትቤሎ እሌኒ ለኪራኮስ)

ንግስት እሌኒ ፦ ተመስገን አምላኬ ይህንን ነገር ያመለከትከኝ ፤ አሁን አንተ ከእኔ ጋር ሁሉ፤ እረዳትም ሁነኝ። እንደው ባላስቸግሮት መልካም ፈቃድህ ከሆነ መስቀሉን አብረን ብንፈልግ ?
ኪራኮስ ፦ እ…… (ጥቂት አሰብ ያደርግና) በጄ እንዳልሽ ነገር ግን ከስራችን አስቀድመን በቶሎ እንዲሳካልንና ፈጣሪያችን እንዲያመለክተን ሱባኤ መግባት አለብን ።
ንግስት እሌኒ ፦ እርሱንማ እኔም አስቀድሜ አስቤው ነበር።
ኪራኮስ ፦ እንዲያማ እንሂድ ፤ ዛሬ ነገ ሳንል ስራችንን መጀመር አለብን።
ንግስት እሌኒ ፦ (ፈጣሪን የማመስገን ነገር እያሳየች ወደ ውስጥ ይገባሉ፤ መስቀሉ ያለበት መሬት መሰል ነገር ይገባል፤ እየተስተካከለ ከውስጥ የእግዚአብሔር ድምፅ ይሰማል)
እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ /፪/
በእንተ ማርያም መሀረነ ክርስቶስ /፪/
በእንተ መስቀልከ ርድአነ ክርስቶስ /፪/

#ትረካ ፦ ንግስት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር እንደእሳት ያቃጠላት መሆኑን የተረዳለት ሁሉን የሚያውቅ የሁሉ ገዢ የሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል መሪነት በአረጋዊ ኪራኮስ አማካኝነት ደመራ ደመራ እጣን እንድትጨምርበትና እጣኑም ወደ ሰማይ ደርሶ ሲመለስ የሚያፍርበትን ስፍራ አስቆፍራ መስቀሉን እንድታወጣ አመልክቷት ሱባኤዋንም በሰላም ፈፀመች። ንግስቲቱም መልአኩ የነገራትን መሰረት አድርጋ ደመራ ይደመር ዘንድ ትዕዛዝ አስተላለፈች።
775 viewsብርሃኑ መለሠ, 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 09:37:00 የአዲስ ዓመት ሥነጽሑፍ !

( ርዕስ - አዲስ ዓመት )
.
.
ኧረ ! ይከበር ዓመት በዓሉ
ሰዎች ሁሉ ዕልል በሉ
ተሰብሰቡ ይሰማ ቃሉ።
አፍሩ ፍሬ መክሊት ይብዛ
እንዳንጠፋ እንደጤዛ
ጨዋታችን አይጎምዝዛ  ።
ይሁን አንደበት የማር ወለላ
ለሁሉም ይሰጥ ደስታ ተድላ
መቅረዛችን እየሞላ ።
ብርሃናችን በሰው ፊት ይብራ
ሐሰት ትሙት ትውረድ ከስራ
እውነት ትቁም ከእኛ ጋራ
የአዲስ ዓመት ይህ ነው ክብሯ ።
የዓመት በዓል ጣዕሙ
ማጣፈጫው ቅመሙ
የዕለት የቀን ትርጉሙ
መተሳሰብ ነው ማኅተሙ ።
.
.
የግጥሙን ሙሉ ጹሁፍ በPdf ነው አውርዳችሁ ተጠቀሙ !

የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ !
@sundayschoolstudents
የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
806 viewsብርሃኑ መለሠ, 06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 19:16:53 ++ ሥነጽሑፍ - ግጥም !

( ርዕስ - ምን አሉ )

ምን ነበር ያሉት አበው ሲናገሩ
የታሪክ አደራ የቅርሳቸው ክብሩ
ለምን ነበር ይጨነቁ የነበሩ
ስለምን ነበር ያስቡ የነበሩ
ስጋቸውን ለማስደሰት
ያመረና የጣመ ለመብላት
በእስፕሪንግ አልጋ ላይ ለመተኛት
ቢሮ ተቀምጦ ዳቦ ለመብላት
ባለስልጣን ሆነው ለመታየት
ስለምን ነበር ሲያስቡ የነበሩት
ስለምን ነበር ሲናገሩ የነበሩት
ምን ተብሎ ተጽፎ ስለ እነርሡ ክብር
ምን ተብሎ ታወሰ የእነርሡ ዝክር
ብርሀናው ይውጣ ይነገር ሥራቸው
ዳግም ይነገር ይታይ ውጤታቸው
ብርሀናው ከወጣ ከተፈለገ ሥራቸው።

አስታዋሽ ካገኛ ከታየ ሥራቸው
እንዲህ ነበር አበው የታሪክ ገድላቸው
ገና ጉዞውን ሲጀምር የክርስትናውን
ከሰባት ወንድሞች ጋር በአበው የተሾመው
ያ ታለቅ አባት የወንጌል አርበኛው
በአንድ ስብከት 12ሺህ ያተመቀው
ምን አለ እስጢፋኖስ በድንጋይ ሲወግሩት
ስጋውን ቆራርጠው ደሙን ሲያፈሱት
እንደ ስንዴ ክምር ድንገይ ሲጭኑበት
ስለምን ተናገረ ምና ብሎ መሰከረ
ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍስን ተቀበል
ጌታ ሆይ ይህን ኃጢያት አትቁጠርባቸው።

ያ አረጋዊ ታላቅ አባት
ጌታን የሚወደው ከሁሉ በፊት
ሲናገር ቀደም ቀደም ብሎ የሚመሠክረው
ከጌታ ስብከት ለአፍታ ያልተለየው
አንተ ከምትሞት እኔ ልሙት ያለው
የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ አደራ የተሰጠው
በጎቹን እንዲያሰማራ ቃል የገባው
ለመሆኑ ምን አለ ጴጥሮስ ያ ታላቁ አባት።

ጌታ ሆይ ወዴት ትሄዳለህ ደግመኛ
በሮም አደባበባይ ልሰቀል ሲለው
ጌታ ሆይ አንተ ከምትሰቀል እኔ እሰቀላለሁ
ስለመንግስተ ሠማያት ሲከራከሩ ሀዋሪያት
ጌታችን በምሳሌ የነበረው አቅርቦት
ያ ታናሽ ብላቴና ያልተለየው ከዮሐንስ
የሠማውን ለማስተላለፍ የተሯሯጠው በእግር በፈረስ
ምን አለ አግናጢዎስ ለባሴ እግዚአብሔር ምጥው ለአንበሳ
በትርኢት ቀርቦ በሮም አደባባይ ሲሰዋ
ዛሬ ተረኛ ነኝ በአምላክ እንደንጹህ መገበሪያ ስንዴ ልቀርብ ይገባኛል አለ
በ451 በጉባኤ ኬልቄዶን
እንዲቀበል ተገደደ ሁለት ባህሪይን
በበክርሊያና መለቂያ በሀይል የታዘዘው
ወልድ ዋህድ አንድ ባህርይ ብሎ የመሰከረው
የበርክሊያንና የመርቂልያን ዱላ የጠገበው
በግዞት የተሰደደው
ጥርሱ በግፍ የወለቀው
ፅህሙ በግፍ የተነጨው
ምን አለ ዲዮስቆሮስ ያ ታላቅ ባለሙያ
ምን ብሎ መሰከረ ስለምንስ ተናገረ
ጥርሱንና ጽህሙን በመሀረብ አስሮ ለክርስቲያኖች
ይህ የሀይማኖት ፍሬ ነው በርቱ አይዟችሁ።

ምን አለች ያቺ ታላቅ እናት
በስጋ ስትኖር ዓለምን የናቀች
ምን ያደርግልኛል ብላ በልጅነቷ የመነነች
የሰውን ልጅ ከአምላክ ለማስታረቅ የበቃች
ደግሞም ሰይጣንን ለማስታረቅ የለመነች
የዓለምን አምልኮት ታግላ ያሸነፈች
ለስጋዋ ሳይሆን ለነፍሷ የቆመች
ለብልጭልጭና ለጌጥ እጇን ያልሰጠች
በአጓጉል ፋሽን ያልተንበረከከች
በስጋዊ ምኞት በሀይሏ የገደለች
ለመሆኑ ምን አለች ክርስቶስ ሰምራ
ዘብሄረ ቡልጋ የኢትዮጲያ የቅርስ አደራ
ሳጥናኤል ሆይ ሳጥናኤል ሆይ ና ውጣ
ከአምላክህ ጋር ላስታርቅህ
ማነው በክብር ስሜ የጠራኝ ብሎ ሲናገር
ሚካኤል ደርሶ በሰይፍ መታው
ይህ ነበረ የአበው ገድላቸው
የቅድስና ስራ የክብር ጌጣቸው
ይሄን ነበር ያሉት አበው በቃላቸው
ለትውልድ እንዲተላለፍ የፃፉት በደማቸው
ስጋቸውን ቆርሰው አጥንታቸውን የሰበሰቡት
ህይወታቸውን ለክርስቶስ እንደስንዴ መገበሪያ የሰጡት ።

ኸረ ዛሬስ ምን አለን እኛ
የአበው ልጆች የተቀበልን አደራ
በእነርሱ እግር ለመተካት የጀመርን ስራ
ምን ነበር ስራችን ጌጥ ክብራችን
ስለምን ነበር ሀሳብ ጭንቀታችን
የእኛ ጭንቀትማ እንደው ከተነሳ
ስጋን ለማስደሰት የምናየው አበሳ
ድንቅና ውብ አድርጎ በፈጠረው አካላችን
ይበልጥ ለማሳመር ስናደርግ አዲስ ፋሽን
ግድግዳ ይመስል ቀለም ስንቀባው
የጠቆረውን ለማቅላት ብራውን እያልን ስንከልሰው
በዓለም ፋሽን ይበልጥ ስናጌጠው
እንደልኳንዳ ቤት ስጋ በመቶ ሻማ ስናሳየው
ይሄ ነው ጭንቀታችን ሀሳብ ክብራችን።

ለመሆኑ ምን አላችሁ መናፍቅ ቤታችሁ ሲገባ
ወንጌል ተሰበኩ ብሎ ሊላችሁ አላስወጣ አላስገባ
ምን ብላችሁ መለሳችሁ ስለምንስ አወራችሁ
ጀርመናዊ በንዴ ወንጌልን ለመስበክ ሲመጣ
ከተማራችሁት ውጭ አዲስ ቃል ሲያመጣ
ምን ብላችሁ መለሳችሁት ይህን መናፍቅ
ዘመቻ ተብሎ በአንድ ቃል ሲታወጅባችሁ
መዳን አለባችሁ ተብሎ ሲሰብክላችሁ
ቃሉን አልሰማችሁም ስሙ ስትባሉ
ለመሆኑ ምን አላችሁ
ከአበው አባቶች የተቀበልነውን አደራ
እንድንወጣ አምላክ ይሁን ከኛ ጋራ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !!!

የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ !
@sundayschoolstudents
የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !
1.6K viewsብርሃኑ መለሠ, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ