Get Mystery Box with random crypto!

የኔ ዕይታ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeneeyeta — የኔ ዕይታ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeneeyeta — የኔ ዕይታ
የሰርጥ አድራሻ: @yeneeyeta
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 301
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች እስኪ በቀናነት share አርጉ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-10 13:20:59 እምነት!

አንዳንዴ ፈጣሪ ላንተ ያደላ እስኪመስልህ ድረስ ያለፍካቸው ከባድ ጊዜያት አሉ፤ አንተም እንደዚህ ጠንካራ ነኝ እንዴ እስክትል ድረስ ያለፍካቸው ፈተናዎች አሉ፤ አየህ ትክክለኛው ማንነትህ እሱ ነው!

ገና ምኑን አይተህ አንተ አማኝ ከሆንክ የማትሻገረው ባህር፤ የማታሳካው ህልም አይኖርም! መሬትን ስትረግጣት የምታምናትን ያህል በፈጣሪህ ታምናለህ? ከዛስ በተሰጠህ አቅም ትተማመናለህ? በቃ ልዩነት የሚፈጥሩት ሁለቱ ጥያቄዎች ናቸው።

መልካም ዕለት ይሁንላቹ
#ashu (d/n)
https://t.me/yeneeyeta
31 views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 16:15:28 ለማን ብለህ?

ለእግርህ የተሰራ ጫማ ትፈልጋለህ እንጂ ለጫማው ስትል እግርህን አትሰራውም፤ ታዲያ ለማን ብለህ ነው የማታምንበትን የምታደርገው? አየህ አንድን ነገር ልብህ ካላመነበት እና አይምሮህ በቂ ምክንያት ካላገኘበት ያንን ነገር ማድረጉ ራስን አለማክበር ነው።

ህልምህን ማሳደድ አላማህን መኖር እየቻልክ፤ ልብህ የሚያምንበት ብዙ ነገር እያለ ለሰዎች ስትል ለምን ነገ የሚቆጭህን ዋጋ አሁን ትከፍላለህ? ባልጠፋ ጫማ እግርህን ለምን ታሰቃየዋለህ?

መልካም ምሽት
#ashu (diyakon)
46 viewsedited  13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 21:14:57 አንድ ፈረስ ብቻ የነበረው አንድ ገበሬ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን፥ ፈረሱ ለግሞ ከቤቱ ያመልጣል።

ጎረቤቶቹም እቤቱ መጥተው “ፈረስህ መጥፋቱንና ማዘንህን ሰማን። ልናፅናናህ መጥተን ነው።” አሉት።

ገበሬውም “ አላዘንኩም! ለበጎ ነው” አላቸው።

ከጥቂት ቀናት በኋላ ፈረሱ ከጠፋበት ቦታ ብዙ ወርቅና ማዕድናት፥ አስለምዶ ከጫነው ሰው አምልጦ ገበሬው ጋ ይመለሳል።

ጎረቤቶቹ ወደ ቤቱ መጥተው "እንኳን ደስ አለህ። ፈረስህ ብዙ ወርቅና ብር ይዛልህ በመምጣቱ እንደተደሰትክ ሰምተን መጣን። " አሉት።

እሱም "ብዙም አልተደሰትኩም። ለበጎ ነው!" አላቸው።

ከጥቂት ጊዜም በኋላም ፈረሱ የብቸኛ ወጣት ልጁ እግር በርግጫው ይሰብረዋል።

ጎረቤቶቹም አሁንም መጥተው " የልጅህ እግር መሰበር አይተህ እንዳዘንክ ሰምተን ልናፅናናህ መጣን። " አሉት።

እሱም በመቀጠል እንዲህ አላቸው "ብዙም አላዘንኩም። ለበጎ ነው!"

ከጥቂት ቀናት በኋላ በሀገሪቱ ከፍተኛ ጦርነት ተከፍቶ፤ ሁሉም ጤነኛ ወጣት በግዴታ እንዲዘምት አዋጅ ተላለፈ። የጎረቤቶቹም ልጆች ሲዘምቱ፤ የእርሱ ልጅ እግሩ ስለተሰበረ ከዘመቻው ይቀራል።

ከጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነቱ አለቀ። ከጦርነቱ የተረፈ አንድም ወጣት አልነበረም። ጎረቤቶቹም ልጆቻቸው መሞታቸው ተነገራቸው።

ገበሬውም ወደ ሰማይ አንጋጦ "የልጄ እግር መሠበር ለበጎ ሆነለት። ተመስገን!" አለ።

ወዳጄ በነገር ሁሉ 'ሁሉም ለበጎ ነው!' በል
https://t.me/yeneeyeta
#ashu
72 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 16:07:36 መከፋትህን ነግረኸው በአንተ መከፋት የሚከፋው የሚያዝንልህ ሰው ካለህ በጣም እድለኛ ነህ

መከፋትህን ሳትነግረው በፊት አይቶህ ወይም ከድምፅህ ወይ ከፅሁፍህ የሚረዳ ሰው ካለህ ደግም እጅግ በጣም እድለኛ ነህ

በአንተ ላይ የሆነ ችግር ሲመጣብህ እኔ አለሁልህ የሚል የልብ ወዳጅ ካለህ ከአንተ በላይ እድለኛ የለምና እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሀለሁ ማለትን አትርሳ ያንን ሰው"ም አጥብቀህ ያዥ/ያዝ ሳታመነታ ሁለቴ ሳታስብ ሙትለት


~መልካም~ምሽት

#ashu
112 viewsedited  13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 15:40:21 ስስቅ ብታዩኝ ደስ ብሎኝ አደለም

ሳቄ ውስጥ በኔ ተስፋ መቁረጥ የሚሞቱ የሚከፉ ብዙ ነፍሶች አሉ

አለመኖር ፈልጌ በሰው በመወደዴ ብቻ መትረፌ ሳቄ ውስጥ አለ

ሳቄ ውስጥ ከሐኪም ቤት ለ4ተኛ ጊዜ ሲወጣ ብርድ ልብሱ እዚህ ይቅር ብሎ ነርሶችን ያሳቀ ጥቁር ቀልድ አለ

በኔ ሳቅ ውስጥ ከፍቅሬ ተጣልቼ ቤቴ ጨንቆኝ ምን ላድርግ እያልኩ መስታወት ድንገት አይቶ የሚያፍር ጅል ነፍስ አለ

በኔ ሳቅ ውስጥ የምሰርዘው ብዙ ጥቁር ትዝታ አለ

ግን ከልቤ ጥሩ እንድሆን የሰው መከፋት ሰበብ መሆንን እንድጠየፍ ያደረገኝ ማንነትን ወላጆቼ እና ጎረቤቶቼ ሰጥተውኛል "ያልፋል ብዘይገድስ ሂንደርባ" አቦ ብለው በአቦአቸው አስቀውኛል

የምስቀው እነሱን እና እናንተን ለማሳቅ ነው

እንጂማ ከፊኡኒሎ
190 views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 07:10:59 ሲከፋህ መኖርህ ትርጉም ያጣ ይመስልሀል እንጂ ያንተ መኖር የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ ባዶነት ሁሉም ሰው ይሰማዋል ወሳኙ ነገር በዛው ቅፅበት ያንተ ወደዚህ አለም መምጣት ህይወታቸው ላይ እንድ ሀይል የሚጨምርላቸው ሰዎች እንዳሉም እትዘንጋ። በፍፁም አላስፈልግም እንዳትል! ወዳጄ
_ ታስፈልገናለህ!
257 views04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 21:13:54 + ልጅሽ ደጅ ላይ ቆሟል +

ከመስከረም 26-እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደየካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው . . . መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ። ‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡ ‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤ ‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ፣ ‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት . . .

ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡ ‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ

ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው . . . በሲጋራና በመጠጥ ሽታ የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤

‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ። መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት

‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት . . . ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን . . . ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት . . . ለረጅም ዓመታት . . . አክሊለ ጽጌ ብዬ . . . ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ

‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ . . . በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ. . . አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ . . . ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ. . . ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል

‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም . . . ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ. . . መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣ . . . የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ . . . ማልቀስ እጀምራለሁ . . . ፍቅሯን አስባለሁ . . . የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው. . . ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል . . . በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ››

አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤
‹‹ወደውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ ‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤
‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣

‹‹ማን . . . እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ . . . እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ
ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ። ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ››አልኩ አምላኬን፣
በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት
339 views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 18:07:13 #ይህን_ያውቁ_ኖሯል?
ሼር አድርጉት
አሐዱ ተብሎ ቅዳሴ ከተገባ በኃላ (በቅዳሴ ሰአት)፡-
- ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር፣
- ቅዳሴ አቋርጦ መውጣት
- የግል ፀሎት ማድረግ፣
- የጸሎት መጽሐፍትን ማንበብ፣
- ሳቅ፣ ወሬ፣
- ሞባይል ማስጮህና ማነጋገር
- ምግብ ይዞ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት
- ወደ አውደ ምህረት አካባቢ መጠጋት
- እህቶች ሱሪ አድርገው መምጣት እንዲሁም ፀጉርን በሚገባ ሳይከናነቡ ለቅዳሴ ጸሎት መቆም
- ልጆችን ያለ ነጠላ ማቁረብ
- ቅዱስ ቁርባን በሚሰጥበት ግዜ ስነ-ስርአቱን በቪዲዮ፣ ፎቶ ካሜራ እና በሞባይል መቅረጽና ማንሳት ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን
- በተጨማሪ ህፃናትን ማቁረብ ሲያስቡ በተቻለ መጠን ካህናት ቅዳሴ ከመግባታቸው በፊት ይዘዋቸው ወደ ቤተ-መቅደስ ቢደርሱ መልካም ነውና ዘወትር ይህንን ተግባራዊ ያድርጉ።

#ለሰው_ሳይሆን_ለጌታ_እንደምታደርጉ፤
#የምታደርጉትን_ሁሉ_በትጋት_አድርጉ።

@ortodoxmeme1
594 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 18:21:50 አሁን የደረሰን መረጃ

ለመስቀሉ እሮጣለሁ በሚል መሪ ቃል በነገው እለት (7/9/2014 ዓ.ም) ሊካሄድ የነበረው መርሐ ግብር በመንግስት እምቢተኝነት መከልከሉን ምንተ ንግበር ለማወቅ የቻለች ሲሆን የመርሐ ግብሩ አዘጋጅ ኮሚቴዎች
ጉዳዩን በሕግ ከመያዝ በተጨማሪ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደወሰዱት ታውቋል።
583 views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 10:41:07 " ኢሀሎ ዝየ ተንስአ በከመ ይቤ "
እንደተናገረው ተነስቷል በዚህ የለም
ማቴ 28÷6

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ "ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
ሞገሶሙ ለጻድቃን ብርሃኖሙ ለፍጹማን
መርዐዊሃ ለቤተ ክርስቲያን"


(የጻድቃን ሞገሳቸው የፍጹማን ብርሃናቸው የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ክርስቶስ በገናና ኃይልና ሥልጣን ከሞት ተነሣ"
እንዲል የፃድቃን ሞገሳቸው የሰማዕታት አክሊለ ክብራቸው የቤተክርስቲያንም መሰረቷና ጉልላቷ ለሆነው ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሳኤው በጠብቆቱ ጠብቆ በመግቦቱ መግቦ አስፈሪ ነበር ካልነው ብዙ አስከፊ ነገር በቸርነቱ አሳልፎ ስላደረሰን እናመሰግነዋለን ።


ቅዱስ ሉቃስ "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ? "ሉቃ24÷5 ይለናል እኛስ ዘላለማዊ እና ሕያው የሆነውን የጌታን ትንሳኤ የት ልናከብረው አስበናል በመጠጥ ቤት ፣ በኮንሰርት ፣ አብዝቶ በመብላት እና መጠጣት ወንድሜ አንተ ትንሳኤውን እንደዚህ ካከበር "ሕያውን ጌታ ከሙታን መካከል እየፈለከው ነው እዛ ከሙታን ጋር ደሞ አታገኘውም ።

ትንሳኤውን "ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት "(ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ ሞቶ ሞትን አጠፋው ) እያለች አዋጅን በምትናገረዋ ቤተክርስቲያን አሳልፍ ።
ጌታ ሆይ በአንተ የትንሳኤ ቀን እኔ በኃጢያት ሞት ከመሞት አድነኝ

በድጋሚ በመላው አለም ለምትገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ። መልካም በዓል

ዲያቆን አሸናፊ መስፍን
ሚያዝያ 15/2014
#ቀዳም_ሥዑር
646 viewsedited  07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ