Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ_መረጃ 📢🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ merja01 — ወቅታዊ_መረጃ 📢🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ merja01 — ወቅታዊ_መረጃ 📢🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @merja01
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.60K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel 👎
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-20 21:14:41
836 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 09:29:26
ብሪታኒያ ጠቅላይ ሚነስትር ለመሆን እየተፎካከረች ያለችው ትውልደ አፍሪካዊቷ እንስት

ከሚ ባደኖች ትባላለች፤ ተሰናባቹ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጀንሰንን ለመተካት እየተደረገ ባለው የሶስተኛ ዙር ፉክክር ሳትጠበቅ ከቀዳሚዎቹ አራት ሰዎች አንዷ ለመሆን የቻለች ጠንካራ እንስት ናት።

በናይጄሪያ እና ብሪታኒያ ያደገችው የ42 አመቷ ከሚ ባደኖች አሁን ላይ የእኩልነት ሚኒስትር በመሆን በማገልገል ላይ ትገኛለች።

በተለይም ከባድ የሆኑ ዘረኝነት ዝንባሌዎች በሚታዩባት ብሪታኒያ፤ ውጤታማ ስራ በመስራት በበርካቶች ዘንዳ የምትወደስም ናት ከሚ ባደኖቼ።

ጠንካራ ፉክክር እያስተናገደ ባለው የብሪታኒያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን የመተካት ፉክክር አራት እጩዎች ቀርተዋል።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01
https://t.me/Merja01
2.1K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 09:25:39
" እኛ የሙስሊም ሀገር ነን። ባህሎች እና ወጎች አሉን እናም እስልምና እነዚህን ድርጊቶች (የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን) ይከለክላል " - አል ሃማሚ

ኢራቅ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል እንዲሆንና ከፍተኛ የሆነ ቅጣት እንዲጣል እየሰራች መሆኗን አሳውቃለች።

የኢራቅ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚከለክል ህግ ለማፅደቅ ማቀዱን አስታውቋል።

ኢራቅ በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሶስት ብዙ አረቦች ከሚኖሩበት ሀገር መካከል አንዷና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን #በግልፅ ወንጀል እንደሆነ ካላወጁ ሀገራት የምትጠቀስ ናት፤ ሌሎቹ ጆርዳን እና ባህሬን ናቸው።

ምንም እንኳን በግልፅ ወንጀል ነው ተብሎ ባይገለፅም ድርጊቱ በማህበረሰቡ ዘንድ እጅግ በጣም የተወገዘ ነው።

አሁን ያለው ሁኔታ ያላማራት ኢራቅ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል እንደሆነ በህግ ለመደንገግ እየሰራች ሲሆን ህጉ ከወጣ ኢራቅ ሌሎች ድርጊቱን በህግ ወንጀል እንደሆነ ካፀደቁ ሀገራት ተርታ ትሆናለች።

አብዛኛዎቹ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በቀጥታ በግልፅ የሚከለክሉ እና ወንጀል ነው ያሉ ሲሆን ከገንዘብ ቅጣት እስከ እስራት ፤ ሳውዲ አረቢያ ደግሞ #የሞት_ቅጣት ትቀጣለች።

በኢራቅ ፓርላማ የህግ ኮሚቴ ውስጥ ያሉት የፓርላማ አባል አሬፍ አል ሃማሚ ለDW በሰጡት ቃላቸው ፥ " አዲሱ ህግ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ያላቸውን በወንጀል ተጠያቂ ያደርጋል ፤ በእነሱ ላይም ከባድ ቅጣት ይጥላል " ብለዋል።

ህጉ እስካሁን ድምጽ ያልተሰጠበት ሲሆን ድምፅ እንዲሰጥበት እየተሰራ ነው።

አል ሃማሚ ፤ ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትችት ቢሰነዘርም ህጉ ይፀድቃል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01
1.9K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 06:15:01 ህወሃት ከፌዴራል መንግሥት ጋር ለሚደረገው ድርድር ተደራዳሪዎችን መሰየሙን አስታወቀ

ሐምሌ 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተውን የእርስ በርስ ጦርነት በሰላም ለመፍታት ለሚደረገው ድርድር የሰላም ቡድን መቋቋሙን የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

የፌዴራል መንግሥት ለዚሁ ይደረጋል ለባለው ድርድር ተደራዳሪ ኮሚቴ በማቋቋም ሥራ መጀመሩን መግለፁ ይታወሳል።

ይህንም ተከትሎ የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ”ለድርድር የሚሆን ልዑክ ወደ ናይሮቢ ለመላክ ዝግጁ እንሆናለን” ሲሉ መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ቃላ አቀባዩ ተደራዳሪ ቡድኑ ውስጥ እነማን እንደተካተቱና ቁጥራቸውን በተመለከተ ያሉት ነገር ባይኖርም፤ በከፍተኛ ሥልጣን ደረጃ የሚገኙ አባላት ያሉት ኮሚቴም መቀቋቋሙን ግን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሃት ጋር የሚደረገው ምንም አይነት ድርድር ሊመራ የሚችለው በአፍሪካ ህብረት ብቻ መሆኑን አቋሙን ያስታወቀ አስታውቋል። ይህንንም ተከትሎ የህወሃት አመራሮች በህብረቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በማንሳት ድርድሩ በህብረቱ ጥላ ሥር ብቻ እንዲሆን እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።

“ኹሉንም የድርድር ሂደቶች ለአፍሪካ ኅብረት መስጠቱ ለእኛ በጣም ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” ያሉት ጌታቸው፣ ማንኛውም ድርድር በሰላም ጥረት ውስጥ ንቁ ሚና የተጫወቱትን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ማካተት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

ቃል አቀባዩ በተጨማሪም በአማራ ክልል ዘንድ የይገባኛል ጥያቄ ያለበትና፤ በአሁኑ ወቅት በአማራ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ያለው ምዕራብ ትግራይ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም በማለት መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘገባው አስነብቧል።

ከህወሃት ከምዕራብ ትግራይ በተጨማሪ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለድርድር አይቀርብም በሚል በተደጋጋሚ መናገሩ የሚታወስ ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ግን እስካሁን የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ የለም።

የፌዴራል መንግሥት ከህወሃት አመራሮች ጋር የሚያደርገው ውይይት መቼ እንደሚጀመርም ሆነ፣ የት እንደሚደረግ ከኹለቱም ተደራዳሪ ወገኖች በኩል እስካሁን የተገለጸ መረጃ ባይኖርም፤ በህወሃት በኩል የኬንያ መዲና ናይሮቢ ትሁን የሚል ሃሳብ ቀርቧል።

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01
https://t.me/Merja01
2.2K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 06:55:04
18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና

ለሜቻ ግርማ የወንዶች 3ዐዐዐሜትር መሠናክል ዉድድር በ8:26.11 በመግባት ለሃገሩ ብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።


ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01
https://t.me/Merja01
2.9K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 06:45:01
ጉዳፍ ፀጋዬ የሴቶች 15ዐዐሜትር 3:54.53 በመግባት ለሃገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች

እንኳን ደስ አለሽ ሃገራችን

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01
https://t.me/Merja01
2.9K views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 15:57:14
3.3K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 23:46:50
3.8K views20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:55:01
ሰራዊታችን ዛሬም እንደቀደመው ሁሉ የኢትዮጵያን ጠላቶች ድባቅ መምታት የሚያስችል ወታደራዊ ዝግጁነት እንዳለው የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ገለፁ፡፡

የውስጥ እና የውጭ ጠላቶቻችን ሊቃጡብን የሚችልን ማንኛውንም አይነት ትንኮሳ መክቶ ድባቅ መምታት የሚያስችል ሙሉ ዝግጅት እንዳለው የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜ/ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡

ጀኔራል መኮንኑ እንደተናገሩት ሰራዊታችን በስነ-ልቦና፣ በአካል ብቃት፣ በቴክኒክ ያለውን አቅም ከምንጊዜውም በላይ እያሳደገ የመጣ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ሽብርተኛውን ህወሃትን ሆነ ሌሎች ተላላኪ ሽብርተኞችን ድል አድርጎ የአገራችንን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ቁመና ገንብቶ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሰራዊታችን ከመንግስትና ከህዝባችን ሊሰጠው የሚችልን ማንኛውንም አይነት ተልዕኮ ተቀብሎ በማንኛውም የሀገራችንን አካባቢ ላይ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ከመላው ህዝባችን ጋር በመተባበር ድል አድርጎ ሀገር መከታ መሆኑን ለማስመስከር የሚያስችል ወታደራዊ፣ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ዝግጅቱን አጠናክሮ እንደሚገኝ ሜ/ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ ገልፀዋል፡፡

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01
https://t.me/Merja01
3.6K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 12:00:01 ከአመታዊ ብድሬ 15 ከመቶውን ለስራ ፈጣሪዎች ለማበደረው ያቀደው አሐዱ ባንክ   በይፋ ዛሬ ስራውን ጀመረ

በ17 አደራጅ ኮሚቴ አባላት የተጠነሰሰውና አስር ሺሕ ያህል ባለአክሲዮኖች ያሉት አሃዱ ባንክ በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራውን ጀምሯል።

ባንኩን በይፋ ሥራ ያስጀመሩት የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን አሳስበዋል።

አሃዱ ባንክም የተጠቀማቸውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች በመክፈቻው ቀን በመተግበሩ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ከፋይናንስ ተቋማት የብድር ተጠቃሚ ዜጎች ከ6 ሚሊየን አይበልጡም ያሉት የብሄራዊ ባንኩ ገዥ ባንኮች እና የቁጠባ ተቋማት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለሚኖረው ማኅበረሰብ የብድር አገልግሎት በማቅረብ ልማቱን መደገፍ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ባንኩ በ564 ሚሊየን ብር የተከፈለ እና በ702 ሚሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል ሥራውን እንደጀመረ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አንተነህ ሰብስቤ ተናግረዋል።

አሃዱ ባንክ በዓመቱ ከሚያቀርበው ብድር 15 ከመቶ ያህሉን ለሥራ ፈጣሪዎች እና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንደሚያመቻች ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01
https://t.me/Merja01
3.6K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ