Get Mystery Box with random crypto!

ከአመታዊ ብድሬ 15 ከመቶውን ለስራ ፈጣሪዎች ለማበደረው ያቀደው አሐዱ ባንክ   በይፋ ዛሬ ስራውን | ወቅታዊ_መረጃ 📢🇪🇹

ከአመታዊ ብድሬ 15 ከመቶውን ለስራ ፈጣሪዎች ለማበደረው ያቀደው አሐዱ ባንክ   በይፋ ዛሬ ስራውን ጀመረ

በ17 አደራጅ ኮሚቴ አባላት የተጠነሰሰውና አስር ሺሕ ያህል ባለአክሲዮኖች ያሉት አሃዱ ባንክ በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራውን ጀምሯል።

ባንኩን በይፋ ሥራ ያስጀመሩት የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን አሳስበዋል።

አሃዱ ባንክም የተጠቀማቸውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች በመክፈቻው ቀን በመተግበሩ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ከፋይናንስ ተቋማት የብድር ተጠቃሚ ዜጎች ከ6 ሚሊየን አይበልጡም ያሉት የብሄራዊ ባንኩ ገዥ ባንኮች እና የቁጠባ ተቋማት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለሚኖረው ማኅበረሰብ የብድር አገልግሎት በማቅረብ ልማቱን መደገፍ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ባንኩ በ564 ሚሊየን ብር የተከፈለ እና በ702 ሚሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል ሥራውን እንደጀመረ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አንተነህ ሰብስቤ ተናግረዋል።

አሃዱ ባንክ በዓመቱ ከሚያቀርበው ብድር 15 ከመቶ ያህሉን ለሥራ ፈጣሪዎች እና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንደሚያመቻች ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01
https://t.me/Merja01