Get Mystery Box with random crypto!

የዉጪ ባንኮች ወደ ሀገርዉስጥ መግባታቸዉ ስለማይቀር ባንኮች ራሳቸዉን ማጠናከር እንደሚገባቸዉ ዶ/ር | ወቅታዊ_መረጃ 📢🇪🇹

የዉጪ ባንኮች ወደ ሀገርዉስጥ መግባታቸዉ ስለማይቀር ባንኮች ራሳቸዉን ማጠናከር እንደሚገባቸዉ ዶ/ር ይናገር ደሴ አሳሰቡ

በዛሬዉ እለት ስራዉን በይፋ በጀመረዉ አሐዱ ባንክ የስራ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ፤ ባንኮች ራሳቸዉን በማጠናከር ከዉጪ ባንኮች ጋር ለሚኖረዉ ዉድድር ማዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ የባንኮች ተደራሽነት ፣ ከሚያቀርቡት የብድር ስርጭት አናሳነት ፣ ከሚጠቀሟቸዉ የቴክኖሎጂ መሻሻሎች ዉስንነት አንጻር እና ሌሎች ምክኒያቶች የዉጪ ባንኮች ወደ ሀገርዉስጥ መግባታቸዉ ስለማይቀር የሀገርዉስጥ ባንኮች ራሳቸዉን ማጠናከር እንደሚገባቸዉ ተናግረዋል።

አያይዘዉም የሀገርዉስጥ ባንኮች ተደምረዉ አንድ መካከለኛ ደረጃ ካላቸዉ የዉጪ ባንኮች ጋር ሊወዳደሩ የማይችሉ መሆናቸዉንም አንስተዋል።
የዉጪ ባንኮች ወደ ሀገርዉስጥ የመግባታቸዉም ነገር እርግጥ ነዉ ብለዋል የብሔራዊ ባንክ ገዢዉ ዶ/ር ይናገር ደሴ።

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Merja01